ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

በግላችሁ ጎልሙቱ! ሕዝብ ይዛችሁ አትሙቱ!!

በግላችሁ ጎልሙቱ! ሕዝብ ይዛችሁ አትሙቱ!! 

https://ethiopiaorthodoxchristian.blogspot.com/2025/06/blog-post_62.html

ነገር ግን  እንደ ሕወሃትና ኦነግ   የየሠፈራችሁን  የዋህ አታልላችሁ ሕዝብ ይዛችሁ አትሙቱ! ብሎ መናገር ሳይረፍድ መነገር አለበት።

ከ፶ ዓመቱ የናርሲስቶች እና የዘረኞች የሤራ ፕሮፓጋንዳ ተማሩ! ለተከተላቸው ምን እንዳተረፉላቸሁ አስቡ!
==================
እንደ እኔ ----
ግለ-ሰብእን ለማረቅ  የግለሰቡን ሰንእና የጎዳውን መሠረታዊ ዐስተሳሰብን ማቃናት  ለነፍስ ዋጋ ብዙ ያለው ይመስለኛል።  ጥመት ከጠማማ አእምሮ መንጭታ አድጋና ተንሰራፍታ  ትውልድን እንዳትበክል በዐሳብ ላይ መነጋገር   ለሀገር ይተርፋልና ከአንድ ጉልምት ድውይ ግለሰብ ተነስቼ  ትውልዱን እናገራለሁ። 

የእኔ የሕይወት መርህ ምንጩ ቤተክርስቲያን ናት።

እውነትን በፍቅር ስንናገር ሁላችንም ለታመሙ ወገኖቻችን ሐኪሞች እንሆናለን። ሌሎችም እኛ ስንታመም ያክሙናል። በጎጥና በሌላም የመሰባሰቢያ ምክንያት መነሻነት የቡድን ዕሳቤ ባርነት ተይዘን ጭፍን መንጎች ስንሆን  ግን ሁላችንም እንታመማለን። ሐኪም አይገኝም፣ ከተገኘም ክፉና ደጉን፣ ጤናና በሽታን መለየት እንዳይችል የቡድን አምላክ አይፈቅድለትም። ሞቶም  እያለ እኔን ምደሉ. ተከተሉኝ እያለ ጥፋቱን ያጋባል።

የታረማችሁ  ወገኖቼ አርሙኝ። 

=========
 የጎጥና የድብቅ ዓላማ ወዳጆቹ የምትሆኑ ሁሉ ለመናገርና ሀሳብን ለማካፈል ምክንያት ለሆነኝ ወንድሜን ምስግኑት። እኔ ላነጋግረው ብደውልለት  ለዚህ  የሕፃን ፕሮፓጋንዳ አገልግሎት የላኩት ተቆጡተውት ይመስለኛል " ደውላለሁ" ብሎኝ የውሃ ሽታ ሆኗል።  
==========
በእርግጥ ንቄ እንዳልተወዉ ተደራጅተው ያሰማሩትን የጎጠኞች ጫፍ ጥላ ሲውለበለብ እመለከታለሁና በእርሱ አንጻር ለአእምሮ ጌቶቹም መልእክቷ ደርሳ ከትእቢታቸው ተመልሰው የቆሸሸ የሤራ አመላቸውን በንስሐ እንዲያቃኑ ምክንያት ለመሆን ተመኝቼ ነው። 

በግሉ የሚጎለምት ሰው የጥፋቱ አድማስ አብሮት ከሚያመነዝር ልብ-ዐልቦ ሁለተኛ ግለስብእ አያልፍም።

ነገር ግን የአንድን ታላቅ ክፍለ-ሕዝብ የህልውና ትግል ጠልፎ የሚጎለምት ወሽካታ ከተፈቀደለት ትውልድን የማጥፋት አቅም ያገኛል።  ይህን በሕወሃትና በኤነግ አይተነው ዋጋ እየከፈልንበት ነው። 

ባሮ ቱምሳና ስብሐት ነጋ በልጅነታቸው በትምህርት ስም የተሸከሙትን የባእዳን ጸረ-ኢትዮጵያ ዕሳቤ በብሔር ነጻነት ካባ ቅመው ሲያስቅሙ በዐሳብ ሙጉት ያስቆማቸው አልነበረም። 

ባገኙት እድል ተጠቅመው  የሀስት ትርክት ሲተፉና የትውልድ ፖለቲካዊ ርእዮትን በጥራዝ ነጠቅነት ከባእዳን ጠልፈው በትውልድ ላይ ስሲደፉ አዋቂዎች በንቀት ስለተዉአቸው የዛሬዎቹን የመቅሰፍት መሪዎችና መዋቅር አፍርተዋል። 

ዛሬ ለአብይብእህመድ፣ ለሽመልስ አብዲሳ፣ ለአሻድሊ ሀሰን፣ ለሲዳማ ኤጄቶ፣ ለሱማሌ የዩጎ፣ ለኦሮ-ዉሀቢስቱ ቡድን፣ ለህወሃት መሪዎች  በጭፍን መንጋነት ተስልፈው የሚገድሉና የሚሞቱ፤  የሀገርን፣ የአማራን፣ የኦርቶዶክስ ክርስትናን፣ እንዲሁም ለሀሰቱና ለስህተቱ  የማይታዘዙትን የነቁ የትግራይ እና የኦሮሞን ልጆች የህልውና  አደጋ ላይ የጣሉ ትውልዶች  ማፍራት ችለዋል።

ታዲያ የዚህ ሂደት ሰለባ የሆነው የአማራ ሕዝብ ይህን መርዝ ላጽዳ ብሎ የጀመረውን የአማራ ትውልድ በግል  ጠልፎ  በግልና ቡድን ፍተወት ልክ ለመከርከም ፍላጎት ያላችሁ ሰዎች መንገዳችሁ ሕዝቡ ከሚሰዋለት ዓላማ የተቃረነ ነውና ተዉ፣ ታረሙ ማለት አይገባም?

ተጋድሎውን ከአማራ የፍትሐዊነትና የስብአዊነት ግቡ ውጭ  በሌላ የከፋ መርዝ የሚለውሱ የሀሳብ መካኖች እና ጭፍን መንጎችን ጊዜ መስጠት ተላላነት ነው። ካለፈው አለመማር ነው። 
እዚሁ ላይ እውነቱ ሊነገራቸው እንደሚገባ አጥብቄ አምናለሁ።

 እውነትም የምትገለጠው "አይተነው ጊዜው ወደሚያደላው" የሚለውን የህሊና ቢሶች ብሂል አሳድገው "ሁሉን በጎጥ መሪዎች ፍላጎት እንመዝን" የሚሉትን ድሁራን በይሉኝታ መታገስ ሳይሆን ሥር ሰዶ የራሱ ስሁት ጭፍን መንጋ ሳያበጅ ለማስቆም መሥራት  ሰብአዊ ልዕልና ነው።  አማራነትም ነው።

==============
"ሰው እስኪሞት መማር አያቆምም" የሚለው አባባል ባውቅም  ዛሬ ግን የዚህን ይጎጠኞች የአእምሮ ባሪያ ወንድሜን ጽሑፍ ስመለከት የበለጠ ጎልቶንታየኝ።

የተማርኩት፦
ለካስ እኔ የምከሳቸው ሕወሃትና ኦነግ/ብልጽግናዎችን በጣዖትነት ደርጃ ለ፶ ዘመናት በመከተል መከራ ካስታቀፉን የባሱ አረሞች በአማራ ስምና ጥላ ውስጥ ተፈልፍለውና ተንሰራፍተው ይገኛሉ የሚለውን ነው።  

ይህ አዲሱ ትምህርት ያስገኘልኝ ግንዛቤዬ  ትክክል ነው  ብዬ በማመን እንዚህ አረሞች የአማራን ባህል የበለጠ ሳያበሸቅጡትና ለህልውናው አደጋ ከደቀኑበት ስብኩል አካላት እኩል ድንክ ሳያደርጉት የንቃ ደወል ማሰማት አለብኝ አልኩ!

ስንፍናዬንም አየሁበት።
ለነገሩ ግብዝና የማላስተውል ሆኜ እንጂ "ወርቅ የሚወዱ ይነቀሉ" ብሎ ቀድሶ ለሙስና የሚደራጅ፣ "ንኅበር በዘዚአከ መንፈስ ቅዱስ/ ያንተ በሚሆን መንፈስ ቅዱስ አንድ አድርገን" ብሎ ቆርቦ ሲያበቃ በዚያው ቦታናንክርስቲያን ማህበረሰብ መካከል ሳያፍርና አምላኩን ሳይፈራ  የጎሣ መንበረ ጵጵስና የሚመሠርት እያየሁ ከአማራ ትግል መካከል በዚህ ደረጃ የተደራጁ ህልም ዐልቦ የርኩሰትና የሀሰት ምንጮች፣ የዓላ ድውያን አይኖሩም ብዬ መገመቴ ነው የሚገርመው።

ኢትዮጵያችን ዐቅፋ የያዘቻቸው የልጆቿን የስነ ልቦናና የሰብእና ብልሽት ጥልቀትና ስፋት በሥራ ልምድም፣ በምርምርም፣ በማገናዘብና በመገመትም የተወሰነ የማውቅ ይመስለኛል። 

ይሁን እንጂ አሁን አሁን  ሕወሃትና ኦነግ በተከሉት የሤራ፣ የቁማር፣ የሐተኛ ትርክት፣ የኢፍትሐዊነት፣ የኢሰብአዊነት፣ የክህደትና የአጭበርባሪነት ፍልስፍና ተጽንሶና አድጎ ደም የሚያስጎርፈውን የብልጽግና ሥርዓት  "እየተዋጋን ነው" ብለው የአማራን ወጣት መስዋእትነት በሌላ በኩል የሚዋጉትን ጠላት እሤት በማውረስ እና ጭፍን  መንጋዎች በማፍራት  ሕወሃት የትግራይን ሕዝብ ለማይረካው የቡድኑ ፍተወት ለመክራ እንደዳረገው ሁሉ አማራንም ለህልውናው የሚከፍለውን ዋጋ ገልብጠው ለበሽታቸው መታከሚያ የያደቡ  እንዲህ መፈልፈላቸውን አላውቅም ነበር። 

የገባኝ ነገር ቢኖር ባንዳ ምኒሻ፣ አድማ በታኝ፣ የብአዴን ትርፍራፊ ሰላይ ወዘተ የህልውና ትግሉ እንቅፋቶች መሆናቸው ብቻ ነበር። አሁን የተመለከትኩት  የሚኖረው  "አማራ ማለት በኪሳችን የያዝነው የሥልጣንና የፍተወታችን ማርኪያ እቃ ነውና አትጋሩኝ" የሚሉ ሤረኞች በሚያሠራጩት መልእክት ነው።   በሰብእናቸው  ልኬት ከሕወሃት፣ ከኦነግ እና የሁለቱ ድቅል ልጅ የብልጽግና ወንጌል መሪ የሚያስተባብራቸው የክፋት ምንጮች የማይለዩ   ግለሰቦችና ቡድኖች  በብዛት ትግሉን እያቆሸሹት ለመሆኑ በማኅበራዊ ሚዲያ ተቧድነው ለዋናው የህልውና ትግል እንቅፋት የሆኑ ዕሳቤዎችን ብቻንሳይሆን ቡድናዊ የጣዖት አምልኮዎችን ሲያራምዱ አያለሁ ። 

 በቀደሙት ዘመናት የምላስን መውለብለብ፣ የለውጦችን አጓጊ ምናባዊ ተስፋውዎችን፣ የብልጦችን ትጋትና ጉልበት በአዎንታዊነት በምውስድ የተጀመሩ የለውጥ  ሂደቶችን ሁሉ በእምነትና ዝምታ መደገፍ የተለመደ ነበር። ያ ልማድ  ሞትን፣ ስደትን፣ መለያየትን፣ ፍርሃትን፣ ተስፋቢስነትን ያፈራልን። እንደ ልምዳችን የመጣውን ብክለት በትዝብት በማለፍ ዳር ቆመን በመኖራችን ሀገራችንን በድውያነ አእምሮ ናርሲሲስቶች፣ ቤተክርስቲያናችንን በሆድ ሎሌዎችና መናፍቃን አስርከብን እንድንሰቃይብአደረገን።  

እኔ  በበኩሌ ይበቃል ማለት አለብኝ ብያለሁ። ማንም ሀገሩንና እምነቱን፣ ክብረ-ሰብእና ፍትህ ይገባኛል የሚል ሁሉ እንደየጸጋው ሤረኞችን፣ ህሊና ቢሶችን፣ ጎጠኞችን፣ ልብ-ዐልቦ ሆዳሞችን ዐዝዬ አልቀጥልም ማለት ይኖርበታል ብዬ አምባለሁ።  

ክርስቲያኖች ክርስቲያኖች "እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ" መባላችንን በግብር የምንገልጸው እነዚህን አእምሮአቸው ብቻ ሳይሆን የመንፈስ ቅዱስ ማደሩያ ሆኖ እግዚአብሔርን የሚያመለክት ልባቸውን "የሀሰት አባት" የተባለው የዲያብሎስ መገልገያ ባፈረጉት ወንድም እኅቶቻችን ላይ በመመስከር ራሳችንን  ከንፍስ ሀፍረት፣ እነርሱንም በክህደት ከመጽናት እንገላግላቸው።

ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ እና ለሀገራችን ውድቀት አስተዋጽኦ አድረገው ይሆናል የምላቸው፣ ከአገራችን ተጠራርገው እንዲጠፉ የመኛቸው እሤቶች፣ የሰብእና መገለጫዎች እና የስነልቦና ህመሞች መካከል፦

፩) ሐስተኝነት፤

፪) ጭፍን መንጋነት፤

፫) ባንዳነት፤

፬) የራስ ነባር-ጠልነትና የባእዳን ምንነት  ናፋቂነት ፤

፭) በድንቁርና የሚቀበሉትና የሚያሰራጩት ኑፋቄ፣ ፍልስፍና ፖለቲካዊ ርእዮት፤

፮) ታሪክን ባዛሬ ሚዛን ለክቶ ማጠልሸትና በዚያ ብያኔ ዛሬን በበቀል መርዝ መበከል፤

፯) በጎጠኝነትና ጎሣ የጣዖት አምልኮ ከማሰብና ማመዛዘን ውጭ ሆኖ አረፋን፣ አሬራን፣ አተላንና ገለባን ከዋናው ከፍሬው በላይ አድርጎ ፕሮፓጋንዳ ማንሰራፋት፤

፰)  በቅዠት በሚስሉት ምናባዊ ግብ ተመስጦ ምክንያት ፈሪሃ እግዚአብሔርን፣ መልካምነትንና እውነትን ሁሉ መደፍጠጥ ፤

፱) ሃይማኖታዊ አስተምህሮን ሳይቀር ገልብጦ ለጠባብ የቡድን መሪዎች ፍላጎት መሳካት መሸቀጥ፤

፲) ግለ-ፍተወትን የሚያሳካ ማንኛውም ፈጠራና ሐሰት  ያለ ፍርሃት "እውነት  ነው" በሚል ክህደት "እውነት ክርስቶስን"  ከራሳቸው ፍላጎት ማሳነስ ላይ መሰማራት  ---- ናቸው።

እነዚህ የሀገር መቅሰፍት መንስኤዎች የሆኑ የተዋረደ ሰብእና መገለጫዎች የሚሸነፉት በርቱዕ ክርስቶስን የአበው ቀደምት እምነት ጽንተው በሚቆሙ አማኞች እና ለህልውናው ተስፈንጥሮ ከተነሳው የአማራነት እሤት  መገለጫ ፋኖ ጋር በመቆም  ነው። 

 ጤናማ ሰብእና ያለው ሁሉ  እምነቱን ከኑፋቄ በትጋት እንደሚከላከለው ሀሉ ፋኖነትንም ከጎጠኞች፣ ከሥልጣን ፍተወት ምርኮኞችና ከላይ ከዘረዘርኳቸው ፲ሩ የመቅሰፍታችን መንስኤዎች  ለመጠበቅ ቁርጠኛ ሲሆን  ነው።

እውነትን በፍቅር ስንናገር ሁላችንም ለታመሙ ወገኖቻችን ሐኪሞች እንሆናለን። ሌሎችም እኛ ስንታመም ያክሙናል። በጎጥና በሌላም የቡድን ዕሳቤ ባርነት ተይዘን ጭፍን መንጎች ስንሆን  ግን ሁላችንም እንታመማለን

የታረማችሁ አርሙኝ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

  ኦ ርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩ . ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡ በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያ...