ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

በድለናል፣ እንመለስ!

ከ፫ ዓመት በፊት የተለጠፈ ነው። አሁንም እዚያው የውድቀት ደረጃን ላይ ስለምንገኝ እንድናስታውስ ደግሜ አጋራሁት።
=========
እንመለስ!!!

💠#ክርስቲያን መሆን ቢሳነን #ተፈጥሮአዊ
ሰው ብቻ ለመሆን እንሞክር እንጂ።

መምህራኑም ከማስጨብጨብና ከእልልታው ያለፈ ትምህርት አስተምሩንማ!

#ክርስቲያን መሆን ቢሳነን #ተፈጥሮአዊ ሰው ብቻ ለመሆን እንሞክር:- በውርጃ ሕጻናትን ከመፍጀት ንስሐ መግባት፣ ወጣቶች ዝሙትን ማቆም፣ ከሰዶምነት መውጣት፣ ዘረኝነትን መጸየፍ፣ ሐሰትና ጥላቻን መጥላት፣ ትዳርን ከማፍረስና ከማርከስ ራሳችንን በክርስትና መጠበቅ   እንዴት ይሰወረናል? 

አሁን የምንገኝበት በገዛ አገራችን መሰደድና መገድል፣ መዋረድና መሰደብ፣ ለምን ይመስላችኋል? እግዚብሔርን ስለማስቀየማችን የመጣ ቅጣት እይደለምን?

💠እኛ ክርስቲያን ነን ባዮች በዚህች በቅድስት አገር እየኖርን፣ በዚህ ክርስቲያን በተሰኘ ታላቅ ስም እየተጠራን  በእግዚአብሔር ፊት  ምን እየሰራን እንደሆነ በትክክል አውቀን ንስሐ እንግባ!
ከዚያም የአጋንንት ማኅበርና መሣሪያ ሆነው ክርስቲያኖችን በሁለገብ ጥቃት ሥር እያጠፉ ያሉትን ፊትለፊት በአንድነት፣ በአንድ ልብና በእምነት ሆነን እንግጠማቸው!!!

በክርስትና እየተጠራ ክፋትን የሚሠራ ሁሉ የአንድ አካለ-ክርስቶስ ብልት ነውና ያልበደለውን ሁሉ ያስቀጣናል!!!  ለሀጥአን የመጣ ለጻታድቃን አንዲሉ።
============
በጥፋታችን እንደንቀጣ  ሰውን ከሰውነት  ባዋረደ፣ ከዜግነትም ውጭ በሚያደርግ፣ ከሁሉም በላይ በጥምቀት የተገኘችዋን የክርስቶስ ልጅነት  ሁሉ አርክሶ፣ዘ ንግቶ በሌላ አይነት የማንነት መሥፈርት  በመሰብሰብ፤ ሌሎችን ለይቶ ለማዋረድና ብሎም ለመፍጀት ተደራጅተን በግፍ መሠማራታችን ትልቅ  የውድቀታችን ምልክት ነው።  

አንድ ሰው በዚህ መንገድ ለጥፋት  ከተደራጀ "ያ ግለሰብ ሰውም” ይሁን በዚያ አይነት ሰዎች የተፈጠረ ድርጅት እና አባል፣ መሪዎች፤ አወዳሽም የሆኑ "ሰዎች" ሁሉ ከሰውነት ጎድለዋል!

ሰው  ሰውን ሊጠብቀው እንጂ ሊያጠፋው አልተፈጠርምና ወደ አጥፊነት የተለወጠ ሁሉ  በገዛ ፈቃዱ መርጦ ከዲያብሎስ ከዲያብሎስ  ወገን የሆነ ነው።  የዚያ ሰው ውድቀት ከክርስትናም ብቻ ሳይሆን ባለሙሉ ሰብእና ከሚባል ሰውነትም ወድቋል!!!
=====================
እንደ አንድ የክርስቲያን ቤተሰብ አባል ራሳችንን እንፈትሽ ፡-

ቅጣት የጠራነው በሚከተሉት ግልጽና እንኳንስ በሌሎችና በአግዚአብሔር እኛው ራሳችን በየከተማውና በየገጠሩ  ሲፈጸም በዓይናችን በምናየው የክርስቲያኖች ርኵሰት ነው፡-

(1) የክርስቲያን ሴቶች ነፍሰ ገዳይነት፡- በዓመት ወደ 1,000,000 ሕፃናት በክርስቲያን ሴቶች ይገደላሉ (ውርጃ) (https://pubmed.ncbi.nlm.nih.gov/28825902/)። ይህ ቁጥር በኦሮሚያና በቡኒሻንጉል፣ በወያኔ ምከኒያት በአፋርና በአማራ፣ በትግራይ ሕዝብ በጦርነት ከሚያልቀው ነፍስ ይበልጣል።

(2)  ትዳርን ማፍረስ፡- በኢትዮጵያ ውስጥ በሴቶች ከሚፈጸሙ ትዳርን የማፍረስ አጠቃላይ ብዛት 70 በመቶ በኦርቶዶክሶች ይፈጸማል (https://core.ac.uk/reader/234691210). ትዳርን ማርከስ፦ በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ፌደራል  መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአንድ ችሎት ብቻ ከመስከረም 7 ቀን 2012- እስከ ሰኔ 8 ቀን  2014 (እ.አ.አ)    16,035 ጥንዶች ትዳራቸውን አፍርሰዋል (  https://www.facebook.com/265784033571676/posts/divorce-in-the-capital-ethiopia-staggeringly-high-some-are-still-with-an-opinion/512951702188240/) \

(3) የወጣት አመንዝራነት፡- በ2014 ዓ.ም. ዕድሜቸው ከ15-24  የተማሪ ወጣቶች  አመንዝራነት (የወዲፊቶቹ አገር ተረካቢዎች) ፡-በ2014 ለጥናት በናሙና (ሎተሪ) ተመልምለው መጠይቅ ከተደረገላቸው ወጣቶች  መላከል 41.4%  አመንዝራ ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ 37.1% ከሁለትና ከዚያ በላይ ሰው ጋር ያመነዝራሉ፤     (https://bmcpublichealth.biomedcentral.com/articles/10.1186/1471-2458-14-301)

(4)የወጣት ሱሰኝነት፡-  የዩኒቭረሲቴ ተማሪዎች  by 67%, 67%, እና 33%  በቅደም ተከተል የጫት፣ የሲጋራ፣ የአልኮል ሱሰኞች ናቸው  (https://www.researchgate.net/publication/353241458_Substance_Abuse_and_Legal_Consideration_in_Ethiopia )

(5)  ሰዶማዊነት፡- ቱሪሰት ከሚርመሰመስባቸው ከላሊበላ፣ ጎንደር፣ ባህር ዳር፣ ሐዋሳ፣ አርባ፣ ምንጭ፣ አዳማ፣ ወዘተ ያለውን የሰዶማዊያን መረጃ ሳንጨምር በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ  በ2021 (እ.አ.አ)  ራሳቸውን በግልጽ ሰዶማዊ ነን የሚሉና የገለጡ ሰዎች 60,000 ናቸው (https://africlaw.com/2021/10/01/time-to-consider-decriminalising-homosexuality-in-ethiopia/)

የኃጢአታችንና የርኵሰታችን ውጤቱ፡-
በመጽሐፍት እንደተነገረ  ለዘረኛ፣ አመንዝራ፣ ርኵስ፣ ነፍሰገዳይ፣ ሰዶማዊ ትውልድ የሚገባው  ቅጣት  ነው (ዘሌ 18፣22፤ ሕዝ 11፣21፤ ኢሳ 1፣20፤ ዘኁል 5፣27)። በፍቅሩ ጽናት ሙሉ በሙሉ በዘንጋኤ አንዳንጠፋና ስሙም ከምድር አንዳይደመሰስ በቅጣቱ በኩል የእግዚአብሑር ይጠራናል።  ጥሪው ይህ የሚካሄደው ጥፋት አንዲያበቃ ንስሐ ግቡ ነው።  በትንቢተ አሞጽ 4፥11 "ሰዶምንና ገሞራን እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፥ እንዲሁ ገለበጥኋችሁ፥ እናንተም ከእሳት ውስጥ እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤ ነገር ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡"  እንዳለው አግዚአብሔር እኛም ከላይ በጥቂቱ ያነሳናቸው እጅግ አጸያፊና በእግዚአብሔር የተጠላ፣ ክርስቲያኖች ነን በሚሉ ሰዎች የሚፈጸም ርኵሰትና ኃጢአት ውጤት ፍሬው፡- 👇🏿

(1) ዘርኝነት፡- የንዑስ ማንነት ፖለቲካ ያሳወረው መንግሥትና የፖለቲካ ንቅንቃዎች ክርስቲያኖችን በቡድን መካፈል (ከክርስቶስ የወይን ግንድነት ላይ የነበራቸውን ቅርንጫፍነት ቆርጦ መጣል (የነፍስ ሞት)) (1ዮሐ 2፣11፤ ዮሐ ቀ5፣5)

(2)  የእርስበርስ ጦርነትና ሥርዓታዊ ፍጅት፡-  በዘረኝነት ፖለቲካ የሚፈጸም ጦርነት መተላለቅ፣ እንድ ክርስቲያን ሕዝብ በጅምላ መገደልና መሳደድ፣ በመዋቅራዊ እቅድ ለድኽነት መጋለጥ

(3) መበታተንና ድንዛዜ፡-  አለመግባባትና አለመዋስተዋል፣ በከንቱ ንግርት፣ በባዶ ተስፋ ራስን ከጥፋት አለመከላከል፣ ድንዛዜ

(4) በጎችን በተኩላ የሚያስጠብቅ እረኛ መብዛት፡- ከክርስትና አስተምህሮ ውጭ በሆነ መንፈስ በዘር መከፋፈል፣ እርኛውና በጉ አለመግባባት፣ የግልና የሠፈር ጀግና አበጅቶ ንጉሥ አንደሌለው ንብ መበታተን፣ በድሎትና ምቾት ፍተወት ኃላፊነትን መዘንጋት፣ ወንጌልን ለሆድ አገልግሎት መዋል

💠መፍትሑው፡-
1- ንስሐ መግባት፣ ጾም፣ ጸሎት፣ ምጽዋት፣ ይርታን የሕይወታችን መገለጫ ማድረግ፤

2- ትዳርን መልሶ መቀደስ፤

3- አመንዝራና ሰዶማዊውን ከአጠገባችን ማስወገድ (ንስሐ እንዲገባ የሚገባውን ትምህርትና ጠቃሚ ቅጣት መስጠት)፤

4- ከሱሰኝነት ሁሉ ራስን ነፃ በመዋጣት አካላችንን ለእግዚአብሔር በቅዱስ ቁርባን መቀደስ፤

5- ዘረኝነትና ዘረኞችን መቃወምና ራስን ከማንኛውም እግዚአብሔር ከማይቀደስበት ኢክርስቲያናዊ የቡድን አደረጃጀት መለየትና በክርስትና እና ከመልካሞች ጋር በሰብእና መሥፈርት ብቻ መደራጀት፣ መተባበር፣ ኃይል መሆን፤  

6- ሐሰትን፣ ኢክርስቲያናዊ፣ ኢሰብአዊና ኢ-ሀገራዊ ርእዮቶች፣ ትርክቶችና የአስተዳደር ሥርዓትን ያለ ይሉኝታ መቃወም፣ በምንም መንግድ  አለመተባበር፤

7- ከዘረኞችና አራዊታዊ መንፈስ ካደረባቸው መሪዎችና ስብስቦች ተለይቶ ሰውን በሰውነቱ ብቻ ከሚቀበሉ ጤናማዎች ጋር በመደራጀት የጥፋትን ሠራዊት ፊት ለፊት መግጠም

—- ድል ከእግዚአብሔር ወገኖች ጋር ናውና ክፋትና ክፉዎች ይሸነፋሉ!!! 
—-ኦሪት ዘሌዋውያን 26፣6-7   በምድራችሁም ላይ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ማንም ሳያስፈራችሁ ትተኛላችሁ፤ ክፉዎችንም አራዊት ከምድራችሁ አጠፋለሁ፥ ሰይፍም በምድራችሁ ላይ አያልፍም። ጠላቶቻችሁንም ታሳድዳላችሁ፥ በፊታችሁም በሰይፍ ይወድቃሉ።
ከከንቱ ልፋት ራስን መጠበቅ፡-
ዘረኝነትን ሳይተዉ፤ ማመንዝረን ሳያቆሙ፤ ውርጃና ሰዶምን እየፈጸሙ፤ ትዳርን እያረከሱ፤ በሱስ እየናወዙ፤ ጾምና ጸሎት፣ ምጽዋትንና ይቅርታን ሳይታጠቁ  የአጋንንትን ሠራዊት ማሸነፍ አይቻልም!!!  ለቅሶና ጫጫታው ሁሉ ከንቱ ነው።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

  ኦ ርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩ . ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡ በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያ...