ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ሰው የማይታወቅበት አመራርና አስተዳደር በኢትዮጵያ

"ሰው ሳትሆን ሰው አትምራ፣ ተመሪዎችን በልክህ ትከረክማቸዋለህ" የሚል ብሂል ላስተዋውቅ መሰለኝ?

በሕይወት ከምመለክተው የእኛ ሀገር ዋና የችግር መንጭ
(1) ሰውን የማያውቁ የሰው መሪዎች እና
(2) ሃይማኖት የሌላቸው የሃይማኖት መሪዎች ድምር ነፍስንም ሥጋንም እየጎዱ ነው።

እነዚህን ለመታገል የሚነሳ ማንኛውም ግለሰብእ ታጋይ ወይንም መሪ እራሱ ከእነዚህ መቅሰፍቶች ለመቃረን፦
"ሰው" መሆኑን፣ ፈሪሃ እግዚአብሔር እንዳለው፣ ለራሱ የግል ፍተወት መርኪያነትና የባዕዳን ማኅደርነት የሚያገለግል አለመሆኑን ማረጋገጥ ይኖርበታል።

ከአጥፊ እንታደጋችኋለን፣ ለህልውናችሁ እንድትታገሉ እንመራችኋለን እያሉ "ሰውን" የማያውቁ፦
--› ስው ሳይሆን ብሔረ-ስብእ፣
--› አማኝ ሳይሆን ካህንና ጳጳስ፣
--› በእውነት ላይ ቆመው ሐርነት ሳይኖራቸው "ነጻ አውጭ ፣ የህለውና ታዳጊ፣ መሪ ወዘተ" ባዮች የአዳዲስ መከራ ፈልፋዮች እንጂ መፍትሔዎች ሊሆኑ አይችሉም።

----- የሥልጣንና የዝና ጥማት ያደነቆራቸውና "ሥጋ ብቻዎችን" (ክብር-ነፍስን የማያውቁ የሆድ ሎሌዎች) መሪ ከማድርግና ሥጋ ብቻ ከመሆን ራስን መጠበቅ፣ ማሰብ፣ ማሰላሰል፣ በእምነት መጽናትን እንለማመድ። ለበለጠ ዐሳብ --› ይህን ይመልከቱ፣ ይሟገቱ፣ አዳዲስ "ሰውነትን" ያገናዘበ ዐሳብ ያመንጩ።

ሰውን የማያውቁቱ የጎጥ ባሮች በሰጡኝ ስሜ "ጃል" ዋቄ. ነኝ
============

ሰው የማይታወቅበት አመራርና አስተዳደር በኢትዮጵያ 

ሰውነትን ያላወቁ ሰው ነን ባዮች ከመክራችን ሊገላግሉን አይችሉም! ጭፍን መንጎች እየተከተላችሁ መከራችሁን አታራዝሙት!

ለሰው ያለን ትርጉ እንኳ አላግባባ ይበለን?  ለብልጽግና ወንጌል እና ለዘረኞች፣ ለብዚኃኑ ኢትዮጵያዊ ግን ትርጉሙ ለሺ ዘመናት ታውቆ የኖረና የተኖረለት ግልጽ ማኅበራዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ፖልቲካዊ፣ ሳይንሳዊ ትርጉም አለው።

ዛሬ ሰው  የብሔረ ሰብ ነጻ አውጭዎች ፖልቲካዊ ርዮት ትርጉም ያንሳል፤ ለብልጽግና ወንጌል መንግሥት መሪዎች ሰው ከችግኝ፣ ከአስፋልት ማስፋት ሥራ፣ ከመናፍሻ፣ ከፎቅ ርዝመት፣ ከባልሥልጣን ምቾትና ቤተ መንግሥት ሁሉ ያነሰ የባልሥልጣን መጠቀሚያ መሣሪያ ነው።

የሰው ትርጉም በመዛባቱ ምክንያት ሙሉ ሰብእና  (ህሊና እና ፈሪሃ እግዚአብሔር፣ ክብር-ሰበ) ያላቸው ሰዎች ከሚርዱት ተርጉም ሁሉ በተለየ “ሰውነትን” ዝቅ ባደረጉ የኑዑስ-ማንነትን በፖልቲካ ብያኔ ከሚተረጉሙ የዘመናችን የሀገር መቅሰፍቶች የፖለቲካ መንጋዎች ጋር በሚከተሉት ወሳኝ መግባቢያና የእሤት መሠረት ከሚመሩት ቃላት ትርጉም ላይ ተቃራኒ ጎራ ይዘናል፦

መዳን፣ ሰላም፣ መብት፣ ብሔረ-ስብእ፣ እኩልነት፣ “የራስ ዕድል” በራስ መወሰን፣ ሀገር፣ ሕዝብ፣ ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግራዋይነት፣ ህልውና፣ ተግል፣ ሃይማኖት፣ ሰው፣ ሴት፣ --- ወዘተ ሁሉ ላይ አዲሱ የአዲሲቷ ኢትዮጵያና እኛ በሰውነታችን ጸንተን ከምንገኘው ጋር አንግባባም።   

ስለዚህ ሕዝብን ከእንዚህ የቁም ሙታን መሪዎች ጥፋት ለመገላገል ትግል ውስጥ የገቡትን እንምራ የምትሉ ወገኖቻችን ከብልጣብልጥነት ውጡ፤ የትዛባውን የመግባቢያዎቻችንን ቃላት፣ ከሁሉም በላይ “ሰውን” ተርጉማችሁ ንገሩን!! ከስሑታኑ መቅሰፍቶቻችን የምትለዩበትን እምነታችሁን፣ ርእያችሁን፣ ርእያችሁን ለማሳካት የምትከተሉትን መርህ፣ የምትመሩበትን ፖልቲካዊ ርእዮት ግልጽ አድርጉት።  “የእገሌ ብሔርተኝነት” የሚለውን የድንቆሮዎች ጡሩምባ መንፋት አቁሙ። በእምነት ቤት የምትምሩም እግዚአብሔርን አክብራችሁ አክባሪ በማፍራት ሰውን ማዳን ሲገባችሁ እግዚአብሔርን ክዳችሁ፣ ሆዳችሁን አምልካችሁ ሰውነትን አታጥፉት።
 

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

  ኦ ርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩ . ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡ በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያ...