ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ክ,ርስቲያን ወደ ጠላቶችህ ለምህረት አታልቅስ፣ አይምርህምና

ኤዲያ! ራስህን ተከላከል! 
ምን የማይለቅ ጽኑ አዚም ነው ኦርቶዶክስ ክርስቲያኑን የተፀናወተው?
አታልቅስ!  ሰሚ ወገን የለህም! ካለቀስክ ውድ እግዚአብሔር  ብቻ!
እንዴት የሚገድልህ መንግሥት ሊታደግህ  ይደርስልሃል?  ነው መንግሥት ይድረስልኝ  እያልክ ፯ ዓመት ሙሉ ምን ሆንክ አላየኸውም? 

 ራስህን ተከላከል! ነፃ አውጭም መፍትሄ ሰጭም የለም። በቤተመንህሥትም ሆነ ብቤተ ክህነት የተካድክ፣ እረኞች ግድ ይህን እያወደሱና ካባ እያለበሱ "በርታልን፣ እኛን ብቻ ከድሎታችን አታፈናቅለን ብለው አላግጠውብሃል።

መፍትሄው አንድ ሆኖ መነሳት ብቻ  ነው።

ለነገሩ  የጎሣ ፖለቲካ ጭፍን መንጋ ለ፶ ዓመታት ያጠቃውን የሃይማኖትና የቋንቋ መለያ የለጠለፈለትን ክፍለ-ሕዝብ በግልፅ እና በመደበኛ ሠራዊት እየጨፈጨፈው  እንደተለመደው  "መንግሥት ይድረስልን" የምትል ድምጽ ከወደ ወለጋ ዛሬም ቀጥሏል።  
አዚሙ ምንድነው? አጥፉውን ድረስልን የሚል እንደ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን የደነዘዘ ዜጋንየለም!!!

የባእዳኑ ተላላኪዎች ገብቷቸዋል፣ በጎሣ መንጋነት ከከፋፈልናቸው እንኳን ምእመኑ መነኩሴውና. ጳጳሱም ዳግም ተመልሶ የክርስቶስ አንድ መንጋ መሆን አይችሉም ብለው ሠርተዉበት አሁን የምናየውን ጎጠኛ፣ በደም ውስጥ ቆሞ የግል ፍተወቱን የሚያርካ፣ የአንድ እምነትና ቋንቋ ባለቤትና ተጠቂ የሆነውን አማራን ሕዝብ እንኳ የሚከፋፍል ሆኖ አገኙት። ፈነጩበት።

ከዘረኛ ፖለቲካ የበለጠ የአማራ ጠላቱ ጎጠኛና ናርሲሱስት ባህርይ ያላቸው የፋኖና የዲያስፖራ ደጋፊያቸው ነው።  እነዚህ ቅርብ አዳሪ ጎጠኞች  ከህዝብ ሞይ፣ ስደት፣ መራብ፣ የሕፃናት ትምህርት ማጣት፣ የወጣት በጤርነት መጠበስ፣ የማኅበረንሰብ መፍረስ በሁለተኛ ደረጃንየሚመለከቱት ነው። አምልኮአቸውን የሚፈጽሙት በሤራና ጎጠኝነት   በየሥርቻው ፈጥረው ከሙከተሉት የቡድን ጣዖታቸው ነው።

ከእነዚህ መፍትሄ አትጠብቅ! አምላክህን እግዚአብሔርን ይዘክ፣ ትዳር ማርክስ፣ ማመንዘር፣ በደም-መላሽነት ንጹህ ደም ለማፍሰስ ማቄሙን አቁመህ፣ በሥጋ ወደሙ ታትመህ፣ ባንዳና ጎጠኛን ከመካከልህ መንጥረህ ዝመት ትድናለህ!
አታልቅስ!  ሰሚ ወገን የለህም! ካለቀስክ እይቀር ወደ  እግዚአብሔር  ብቻ!!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

የሐሰት ትርክት ኦነጋውያንና የሕወሃታውያ የጋራ ስልት ከነግሥታት ወደ ተራ ግለሰቦች

✏️ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።  እርሱ ይመስገን። ምድራችንን #በደም #ያጨቀየው $ህሊና #የነሳን ፣ #ልቦናችንን #ያጨለመን ፣ #ሰብእናችንን ያዋረደው:- 👉 የሕወሐታውያንናንየኦነጋውያን የንዑስ ማንነት የጎሣ ፖለቲካ የደንቆሮ ርእዮትና፣ 👉 መርዛማን ጥላቻን ለ፶ ዘመናት ያከፋፈሉት የሐሰት ትርክት ናቸው። ✏️እንደ ዳግማዊ #ምንልክ ያሉ   ከዋክብት መሪዎች፣ እንደራሴቻቸው፣ ደጃዝማቾችና ቀኝና ግራ አዝማቾቻቸው  ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ብዙ ውለታ ውለውልናል:- 👉 በዘመነ ኦቶማንና አውሮፓ፣ በዘመነ መሳፍንት የተበታተነውን እና የተቆነጻጸለውን፣ ጎሠኛ የአርብቶ አደሮች  መሬት ፍለጋ  የደመሰሱትን ክርስቲያናዊ የግዕዝ/የነፃነት ሥልጣኔ አሻራ እንዲያገግም ደክመውልናል፤ 👉 የጥንት አገርን እና ሕዝቦችን   በከፊልም ቢሆን በመሰብሰብ  ጠንካራና ብቸኛ የነጭ ቅኝነትንና ባርነትን በመከላከል፣ ከኦቶማን ቱርክ ወር ትናንት ውስጥ ጥረኛ  አህመድ ግራኝ በመጋደል  ልዩ የነጻነት ማንነት ያላትን አገር ብበቸኝነት በዓለም ካርታንላይ አቆይተዋል፤ 👉 የሬማ ግዛት በጎሣ ተብልቶ ፲ ትንንሽ ሲሆን ከበበባውን ተቋቁማ በዝኃነታችን በተመጋጋቢ አንድነት ከ፹ በላይብቋንቋ፣ ከዓለም ትልልቅ እምነቶች ክትስትናን ፣ ይሁዲን፣ እስልምናን፣ የእረማውያንን ቅሪት የሆኑ የባህል እምነቶችን ሁሉን ይዛ በአውሮፓ በአርብ አምሳል ሳትሠራ ለእኛ አቀብዋል፤ 👉 ወያኔና ኦነግ፣ ገንጣዩ ሻዕብያ፣ ከሃዲው የማርክሲስት የአእምሮ  ባሪያን ስብስብ  እስኪፈትናት ድረስ ራሷን የቻለች አገር እንድንፈጥር ያስተባበሩን ነገስታት የተመሰገኑ ናቸው። አገር ሲያረጅ ጃርት ያብቅላል እንዱሉ: መል...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩. ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡  በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡  ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በቋንቋ መ...

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...