ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

አባቶችህን አክብር! ወደ መዳን መንገድ ያሳዩሃል።

ክብር ለማን ይገባል?

ጌትችን፣ አምላካችን፣ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ወንጌል ፲፪፣ ፵፫  
 "ከእግዚአብሔር ክብር ይልቅ የሰውን ክብር ወደዋልና።" ብሎ ፈሪሳውንን ሲወቅሳቸው  ለተከተሉት እና የዚህን ክፉ ዓለም ቅጣት ሳይሰቀቁ  መኖር ለተገባቸው  ደግሞ  በዚሁ መጽሐፍ ውስጥ ፲፯: ፳፪-፳፫  በተዋሐደው ሥጋ ለሚመለከቱትና ግራ ለተጋቡት ምሥጢር ሱገልጥ ወደ ሲጸልይ  "እኛም አንድ እንደ ሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ፤ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፥ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤ እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል።" ብሎ ክብር የሚገባቸው  እግዚአብሔር አብ ፣ እግዚአብሔር ወልድን በወደደበት የባህርይ ተዋህዶ አንጻር በጸጋ የፍቅር ተዋህዶን ከእግዚአብሔር ለማግኘት የሚጋደሉትን ወገኖቹን፣ በዚህ ተጋድሎ ፍቅረ እግዚአብሔርን ቀምሰው በፍቅረ ቢፅ የሰጠሙትን፣ እነርሱ የቀመሱትን ደግሞ ሌሎችም አማኞች  ሁሉም እንዲቀምሱላቸው፣ በክርስቶስ ሁሉም የጥምቀት ልጆች እንዲዋሀዱላቸው ሕይወታቸውን የሰጡትን  ሐርያትንና የሚመስሏቸውን  "አባቶች" ልንል፣ ከእግዚአብሔር በነሱት ክብር ልናከብራቸው  ይገባል። ይህን የምናደርገው ስለታዘዝን ብቻ ሳሆን ክርስትናን ለመኖር የምግብ ጀመሪያ መግቢያ በርና ግዴታችን ስለሆነም ነው፤ ከባህርይ መድኀኒት ከክርስቶስ የሚያገናኙ  ሰዎች የጸጋ መድኀኒት ናቸው እና መዳኛውን የማያከብር ኢአማኒ ብቻ ነው። 

በዚህ መልክ ለአባቶች ክብር ይገባቸዋል።  

 ነገር ግን እውነተኛ አባቶች የወሰዱትን የክህነት ደረጃ ማዕረገ ስም ወስደው፣ ምልክቶቻቸውን ተጎናጽፈው፣ ትምህርታቸውን በእምነት ያይደለ ለሙያ ያክል አጥንተው! በተግባር ግን!
* የክብር መቀባበያ፣ የካባ መሸላለሚያ፣
*  የድሎት ኑሮ ማደያደያ፣
* የዘመድ እዝማድ መጠቃቀሚያ
* የቤተ ምንግሥት ለዚያውም የአላዊ ሥርዓት ተላላኪነት ሚና መወጫ
* የክብር መሸመቻ ወዘተ የሚያደርጉ፣
* የክርስቴስን የአካል ብልቶች ቅድስቷን ጉባኤ የሕወሃትና የኦነግ፣ የብአዴንና የአገው ሸንጎ፣ የቅማንትና የብሔር ብሔረሰቦች ጉባኤ፤ የጎጥ መቧደኛ ያደረጉት ሁሉ ቅጣት እንጂ ---- የአባትነት  ክብር አይገባቸዉም።  ለንስሐ የሚያበቃ ተግሣጽና ወቀሳ እንጂ ጭብጨባና እልልታ፣ ግርግርታና አጀባ ማቅረብ እነርሱንም መግደል እና  ተከትሏቸው መሜት ነው። 

ጳጳሳት እና ሲኖዶሳተ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የሚታወቁት  ለክርስቶስ በመታዘዛቸው  እና ለእማኞች በሕይወታቸው አርአያ በመሆናቸው ነው።

እባት የተሰኙት ለክርስቶስ የመታዘዛቸው  ምልክት  ከቀዳማዊቷ ከአንዲት ቅድስት ቤተክርስትያን ህብረት ላለመለየታቸው  ምስክርነት ሲኖራቸው ነው።  ይህን የምናውቅበት ጉሉህ ማስመስከርያቸው ቅዱሳን ሐርያት ያስቀመጡትን ቀኖ በተለይ ክህነትን በሚመለከት አክብረውና አስከብረው እስከ ሰማዕትነት ሲጸኑ ብቻ ነው።

ከዚህ የወጣ የሌላ ሁሉ የሌላ ነው።  እግዚአብሔር በክህነት አይታገድም፣ ዳታንና አቤሜሮን፣ የኤሊ ልጆች መቀሰፍ፥ የእግዙአብሔር ወዳጅ የአባ ለትጹንን ምልጃ እምቢኝ በማለት አሳይቷል። 

በክህነትና በቤተክርስያን ጉዳይ የሚታገስ፣ የሚያስመስልና የሚቅለሰለስ ክርስቲያን ከእግዚአብሔር አይደለም። የክርስቲያን ቤተሰብ ማያው  የአበው ትምህርትና የምድራዊው  የአቅሌሲያ  ቀኖናዊ ጎዳና ወደ ሰማውያኑ ጉዞና ህብረት የሚያደርስ መሄኑን ማረጋገጥ ነው።

ቅዱስ፣ ክቡር፣ ንዑድ፣ ብፁዕ፣ ሌላም ማዕረጋት ቢደርቡ በተጠሩበት ቅፅል ትርጉም አንጻር ሆነው ለመገኘትም ይሁን ለመባል በትንሹ  ለአላዊ ምንግሥት እየታዘዙ ክርስትናን በሚቃረን ተግባር መገኘትን መጸየፍ ይገባል። አሁን ያጋጠመን የሚሻረውና አባት በግብሩ ሊገለጽ ከፈለገ ፦
፩) ጸረ ኦርቶዶስ ጠ/ሚ በአብይ አህመድ  ደብዳቤ የሻሩትን የሐዋርያት ቀኖና ወደ ቦታው መመለስ፤

፪)  በሕወሃት/ኢሕአዴግ እና ኦነግ/ብልጽግና ምርጫና ፈቃድ ተግበስብሰው ከደብር አለቃ እስከ ቁምስና የደረሱትን ፈትሾ እና ከእውነተኞቹ እረኞች ለይቶ ወደሚገባቸው ማዕረግ መመለስ፣

፫) አንድን ሲኖዶሱን ቅዱስ የሚያሰኘውን  ክብር  ለማስመለስ  አባላቱን ከዘር ፖለቲካ ኮታና እጅ መንሻ ካጰጰጰሳቸው ማጽዳት ፣ 

፬) በሻሸመኔ፣ በወለቴ፣ በእዱስ አበባ ወዘተ የጽምቀት ልጄችን  ደም ያድፈሰሱትን፣ የብሔር ብሔረሰብ 'ምክር ቤትን" ቅዱስ ሲኖዶስ ለማሰኘት ግድያ እስከማስፈጸም በጥምቀት ወገን ላይ ጦርነት ያስፈጸሙትን  ግለሰቦች በመሻርና "ብፁዐን"  ሊሰኙ የሚገባቸውን በቀኖናው ሚዛን ብቻ "አባት" የሲኖዶስ አባል በማድረግና፣ ከጎሣ ፖለቲካ አገልጋይነት መለይት የግድ ነው።

የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ማንነትና ምንነት፣ ቅድስትነትዋ፣ ኲላዊነቷ፣ አሐቲነቷ አሁን በተንሰራፉባት ምንደኛና የጎሣ ፖለቲካ ባሮች የግል ድካም እና የወል  ውንብድና፣  መገልገያ ሰብልሹ መዋቅራዊ ሙስና  አይመዘንም፤ አይናወጥም፤ አይረክስም። 
በነገራችን ላይ በበዛው ተናገርን እንጂ እግዚአብሔር ባስቻላቸውና መሸከም በቻሉት ልክ ለቅድስና የሚደክሙ፣ በዕንባና ሀዘን ልጆቻቸውን የሚራዱ፣ ይህ ክፉ ጠባያችን እንዲወገድልን የሚያማልዱን ጽቂቶች አባቶምአሉን። ግና ዘመኑ እንደሚፈልገው በግልጽ ወጥተው በዓለማዊውም ሆነ በቤተክርስቲያን መድረክ ስላልተዋጉልን አይታዩም።

 አጥፊዎቹ ግን ደምቀውናን ከፍ ብለው በዓለሙ የአሸዋ ጉብታ ላይ ቆመው ይገኛሉ፣ በትሁታኑና  በዐለት ላይ በቆሙት ላይ ስለሚብለጠለጡ እንደ እኔ አይነቱ ትዕግሥት ያጣ ምእመን አያያቸውም። 

በሌላ በኩል ምእመኑ ቤተክርስቲያን (ቅድስት አቅሌስያ) ማክበር ማለት እርሷን መጠበቅና በትምህርቷና  በቀኖናዋ መኖር መሆኑን ደብቆ በተቃራኒው  አጥፊዎቿን  የሚያገለግሉ የሐሰት እረኞችን በደፈናው  "አባት አክብሩ"  በሚል ደላላ ሰባኪዎችን እየተከተለ    ግራንይጋባል፣ በየአጥቢያው የክርስትና ሥራ እንዳይሠራ፣ ቤቱ እንዳይጸዳና መወቃቀስ እንዳይኖር እንቅፋት ይሆናል። እነዚህ እውርቶ አደሮች እንኳንስ በሃይማኖት የሕይወት ሕግ ተመዝነው  ክርስቲያን በተባሉት ልዕልና ሊገኙ ቀርቶ በማኅበራዊ የሞራል ለከታቸው ከአሕዛብ የከፉ የግራኝ አህመድና የአብይ አህመድ ቀዳሾች   ናቸው። የአድርባይነት  ስብከት በማዝነም  ለሆዳቸው መሙላት እና ለደረታቸው መቅላት ነፍሳትን ከማሳሳት አልፈው የቤተ ክርስቲያን. መልኳ ለትውልድ እንዳይተላለፍ እንቅፋት ሲሆኑ እሽ በጀ ብሎ መቀበል ክርስቶስን ከእነቤተሰቦች እንደመካድ ይቆጠራል።   ጌታችን በማቴዎስ ወንጌል እንደተጻፈልን " በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።" (ማቴ፲፥፴፫) ብሏል። 

ለብዙ ምእመናን የቸገራቸው ክህነትን አስከብሮ፣ አክብሮ በመገልገል እና ካህን ሳይሆን በስሙ  በቤተክርስቲያን ውስጥ መሽጎ ቤተክርስቲያንን የሚያፈርስ  አጥፊ ምንደኛን በመከላከል ቅዱስ ምግባር  እና አባቴችን በማክበር መካከል  ያለውን ልዩነት እያምታቱ ግራ መጋባት ይመስለኛል። 
 
ሾላ በድፍን "አባት አክብሩ" የሚለውን ስብከት ዘርዘር አድርጎ ማስታማር በአድርባይነት የጋን ውስጥ መብራት ያልሆኑ የመምህራን ድርሻ ነው።  መምህራን፦
፩) የሚከበር ኦርቶዶክሳዊ አባት ማነው?
፪)  መስሎ የሚያጠፋው እንዴት ይታወቃል? 
፫) ቀኖናተ አበው ቅዱሳን  ስለ እርኛ ምን ይላሉ?
፭) የሲመት ሥርዓትና የተሿሚዎች የምርጫ መለያ መሥፈርት ምንድ ነው?  
፮) እረኞች እረኝነታቸውን ትተዉት ከጠላት ጋር ሲተባበሩ የምእመናን ድርሻ ምንድነው?  ወዘተ ጥያቄዎችን በሚመልስ ደርጃ  የጠራ፣  ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ጸንታ ፪ሺ ዘመን የሄደችበትን  መንገድ ማሳየት ይገባል።

እንዲያው በድፍኑ አባት "አክብር፣ ተገዛ፣ ስገድ፣ እልል በል፣ አጨብጭብ" በማለት ምእመናን ወደ መለያየት፣ ክፉ ኢክርስቱያናዊ ልምምድና ባህል የሚመሩትን  መከላከል የዘመናችን ተጋድሎ መሆን አለበት።  ይህን የማደርግ ምእመንናንክህን ሁሉ ሰዎች ስህተትን እንዲከተሉ በመገፋፋት  የጥፋቱ አካል ብቻ ሳይሆን በመምህርነት ስም አደንቋሪና የነፍስ እንቅፋት መሆኑ ነው።

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳን እቃዎቹ የነገረን "ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን፥ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።" (ሮሜ ፲፫፥፯) እና " በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥  ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ፣  ስለዚህ ውሸትን አስወግዳችሁ፥ እርስ በርሳችን ብልቶች ሆነናልና እያንዳንዳችሁ ከባልንጀሮቻችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ።  ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ፤  በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት።" (ኤፌ ፬፥፳፫-፳፯) አለን እንጂ እየተሸነጋላችሁ ሙቱ  አላለንም።

የሚከበረውን ከማይከበር ለይቶ ማወቅ   እውነትና ሐሰትን፣ መልአክና ሰይጣንን የመለየት ያክል ትንሹ የክርስቲያናዊ ሕይወት መንሻ ነው።  ካልሆነማ መንገዱን በስህተተት ጀምረን በሞት እንጨርሰዋለን።

አድርባይነትና ጭፍን መንጋነት ውጤቱ እውነት ክርስቶስን ሰቅለው በምትኩ ወንጀል በርባንን እስከማስፈታት የደረሱ የአይሁድ የዘመኑ መሪዎችን፣  በእኛ ዘመን ደግሞ ደም እያፈሰሱ እንደ ጲላጦስ በውሃ እጆቻቸውን  ታጥበው ብፁዕ ለመባል ፖለቲካ መሥራትን  ብልህነት አድርገው የሚያምሱንን ክፉዎች ዐዝሎ አብሮ መቀበር ይሆናል።

https://www.youtube.com/live/0rJcAOUXMg8?feature=shared 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

የሐሰት ትርክት ኦነጋውያንና የሕወሃታውያ የጋራ ስልት ከነግሥታት ወደ ተራ ግለሰቦች

✏️ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።  እርሱ ይመስገን። ምድራችንን #በደም #ያጨቀየው $ህሊና #የነሳን ፣ #ልቦናችንን #ያጨለመን ፣ #ሰብእናችንን ያዋረደው:- 👉 የሕወሐታውያንናንየኦነጋውያን የንዑስ ማንነት የጎሣ ፖለቲካ የደንቆሮ ርእዮትና፣ 👉 መርዛማን ጥላቻን ለ፶ ዘመናት ያከፋፈሉት የሐሰት ትርክት ናቸው። ✏️እንደ ዳግማዊ #ምንልክ ያሉ   ከዋክብት መሪዎች፣ እንደራሴቻቸው፣ ደጃዝማቾችና ቀኝና ግራ አዝማቾቻቸው  ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ብዙ ውለታ ውለውልናል:- 👉 በዘመነ ኦቶማንና አውሮፓ፣ በዘመነ መሳፍንት የተበታተነውን እና የተቆነጻጸለውን፣ ጎሠኛ የአርብቶ አደሮች  መሬት ፍለጋ  የደመሰሱትን ክርስቲያናዊ የግዕዝ/የነፃነት ሥልጣኔ አሻራ እንዲያገግም ደክመውልናል፤ 👉 የጥንት አገርን እና ሕዝቦችን   በከፊልም ቢሆን በመሰብሰብ  ጠንካራና ብቸኛ የነጭ ቅኝነትንና ባርነትን በመከላከል፣ ከኦቶማን ቱርክ ወር ትናንት ውስጥ ጥረኛ  አህመድ ግራኝ በመጋደል  ልዩ የነጻነት ማንነት ያላትን አገር ብበቸኝነት በዓለም ካርታንላይ አቆይተዋል፤ 👉 የሬማ ግዛት በጎሣ ተብልቶ ፲ ትንንሽ ሲሆን ከበበባውን ተቋቁማ በዝኃነታችን በተመጋጋቢ አንድነት ከ፹ በላይብቋንቋ፣ ከዓለም ትልልቅ እምነቶች ክትስትናን ፣ ይሁዲን፣ እስልምናን፣ የእረማውያንን ቅሪት የሆኑ የባህል እምነቶችን ሁሉን ይዛ በአውሮፓ በአርብ አምሳል ሳትሠራ ለእኛ አቀብዋል፤ 👉 ወያኔና ኦነግ፣ ገንጣዩ ሻዕብያ፣ ከሃዲው የማርክሲስት የአእምሮ  ባሪያን ስብስብ  እስኪፈትናት ድረስ ራሷን የቻለች አገር እንድንፈጥር ያስተባበሩን ነገስታት የተመሰገኑ ናቸው። አገር ሲያረጅ ጃርት ያብቅላል እንዱሉ: መል...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩. ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡  በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡  ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በቋንቋ መ...

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...