L እንደግዲህ ጎጠኞች ምን አገባህ እንዳትሉኝ እንጂ እኔ ለአማራ ምሁራን ምክረ-ሀሳብ አለኝ፦ የአማራ ምሁራን ሚና በአማራ በህልውና ትግል ውስጥ ማንኛዉም የህልውና ትግል ውጤታማነቱን ማረጋገጥ የሚችለው ዘርፈ ብዙ የህልውና መሠረቶችን ታሳቢ ያደረገ ጉዳዮች ተንትኖና በሁሉም አቅጣጣ ተመጋጋቢ ድሎችን ማስመዝገብ ሲችል ነው። የአማራ የህለውና ተጋድሎም እንደዚሁ አሁን በፋኖ ከሚካሄደው የጥትጥቅ እኩልና ጎን ለጎን፥ ብሎም ከትጥቅ ትግሉ መጠናቀቅ መኃላ በአጭር፥ በመካከለኛ ግዜ (ከአሁን እስከሚቀጥሉት ፭ ዓመታት፥ ከ፮-፲፭ ዐመታት፥ ከ፲፮ እስከ ቢያን ፴ እና ከዚያ በላይ ዓመታት የሚመዘገቡ ድሎች፥ በየድል ምዕራፉ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአጠቃላይ ምን የተሻለ ሕይወትና የትውልድ ሰላማዊና ሁለገብ የሰብአዊ ክብር ሁኔታ እንዲሚያረጋግጥ የሚያመለክት የድል ጉዞ ፍኖተ-ካርታን ከወዲፉ በጭናጭልም ቢሆን ማሳየት አለበት/ ይህ ተግባር በአብዛኛው በሜዳ ላይ ውድ ሕይወቱን አስይዞ ለመጀመሪያው ድል፥ ማለትም የአመራን ሕዝብ ከጥፋት የመታደግ ተጋድሎ ላይ ከተሰለፈው ተዋጎ ኃይል የሚጠበቅ አይደለም። ይህ ፍኖተ-ካርታ፥ ፍኖቱ ላይ ለመሄድ የሚያስፈልገው መርህ፥ አቅምና አደረጃጀት፤ አደረጃጀቱ የሚመራበት ፖለቲካዊ፥ አስተዳደራዊና ማኅበራዊ አመራር ምን መሆን እንደሚገባው፥ በወዳጅነትና በጠላትነት የተሰለፉ አካላት በፍኖቱ ላይ በሚደረግ ጉዞ ውስጥ የሚኖራቸው ሚና እንዴት መስተናገድ እንደሚገባው፥ የትጥቅ ትገሉ መጠናቀቂያ መሥፈርቶችና ቀጣይ ተጋድሎዎች አይነትና አመራር ወዘተ ሁሉ በምሁራን ሊታሰብባቸውና ግልጽነት እያገኑ መሄድ የሚገባቸው ናቸው። በአመራ ሕዝብ የህልውና ትግልም ይሁን የትግሉው ውጤቶች ዘለቄታዊ ዋስትና ለማስገኝ በሚደረጉ ተያያዥና ተከታታይ ከትጥቅ ው...
This is a spot where I post and share part of my daily reality. I would love to hear from others too to learn how differently we interpret daily encounters including our imaginations. ይህ ሥፍራ የየዕለት ገጠመኞቼን፣ እንዴት በዕለቱ እንተረደሁትና የማስበውን ለሌሎች ያማጋራበት ነው፡፡ የሌሎችን በመስማትና ምን ያህል ዓለማችንን በተለያየ መንገድ እንደምንመለከታት ለመማር እጓጓለሁ፡፡