ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ለሁኔታችን የሚመጥን መሪ እንዴት እንወቅ?

ለሁኔታችን የሚመጥን መሪ እንዴት እንወቅ?

#በአብይ እና ከርእዮት ወላጆቹ ከአመጡብን መከራ ተነስተን ስለ መሪዎች ሰብእና ምን እንማራለን?
==========

#አብይ አህመድ እርሱን ከፈጠሩት ቀዳሚ ዘረኛ መሪዎች በመርከብ በሀገራችን ላይ ያደረሰውና እያደረሰው የሚገኘው ጉዳት ካሣ የማይገኝለት ቢሆንም አንድ ትልቅ ውለታ ለትውልዱ ውሏል።

እርሱም የፖለቲካ መሪዎችን በምላሳቸውና በብልጣብልጥ ንግግሮቻቸው እና በአዲስነትና ለውጥ ሽፋን ምን ያህል ሕዝብን አደንዝዘው በማስከተል ወደ አጠቃላይ ውድቀት ሊወስዷቸው እንደሚችሉ ማሳየቱ ----

እንደ እኔ ግምት ከአሁን በኋላ ትውልድ ሁሉ  የፖለቲከኞችን የመጨርሻ ደረጃ ህሊና ቢስነትና የማታለል አቅማቸው ተገንዝቦ መሪዎችን ለመምረጥና ለመታዘዝ ከስሜትና ንግግር ባሻገር በግልጽ መሥፈርት ብቻ እንዲመዝን ትምህርት አግኝቷል እላለሁ።
ስለዚህ -----
መሪ ስንመርጥ ስንከተልና ስን ታዘዝ አስቀድመን  በሚከተሉት ነባር ሰብአዊ እናቶች  መመዘኛ መሆን ይኖርበታል ብለን የምንግባባ ይመስለኛል:-

፩) ፈሪሃ እግዚአብሔር እንዳለው በአጠቃላይ ሕይወቱ ያስመሰከረ

፪) ለራሱ ሳይሆን ለሚመራቸው ወገኖቹ ለመሰዋት ዝግጁነቱን በተግባራዊ ሕይወቱ ያረጋገጠ፤

፫) ተክለ ሰውነቱን መንጋ አጫፋሪዎችን በጎጥ፣ በጥቅም፣ በተስፋ እያጓጓ  በማሰማራት የማይገነባ ትሁትና እውነተኛ፣ በተግባር ብቻ ከፍ የሚል፣#

፬) ወገንተኝነቱን ከጎጥና ከጎሣ ነጻ አውጥቶና እርሱም  ወጥቶ ለክብር-ሰብእ፣ ለፍትህ፣ ለእውነት ፣  ለአሁንና ለመጭው  ትውልድ ሁለንተናዊ ደኅነት ማድረጉን በተግባር ያስመሰከረ፤

፭) በግል ሕይወቱ ከስግብግብነት፣ ፍቅር ንዋይ፣ ዝሙት፣ ትዳርን ከማርከስ፣ ከሤራ፣ ከከፋፋይነት፣ ከነፍሰ ገዳይነት፣ ፍርድ ከማጣመም እጅግ የራቀና  የንጽሕና እና ፍትሐዊነት አርአያ ለመሆን የሚጣጣር፤

፮) በወገኖቹ በኢትዮጵያውያን የጋራ ጥቅሞች ላይ ከጀርባ ከባእዳን ጋር  በመደራደር ለግል ሥልጣን የመሥራትን ከሻዕብያ፣ ሕወሃት፣ ኤነግ ውፕዘተ ወደ ትውልዱ የገባውን ክህደት የሙጸየፍ፤

፯) አሁን ለአለውና ለመጭው ትውልድ በሚጠቅም ስሌት ለሀገሩ ወዳጅ የሚያበዛ፣ ጠላት የሚቀንስ ግኑኝነት ላይ በማተኮር የሚታወቅ

፰) በብልሆች ብሔራውያን ሊቃውንት በባህሎችና እምነቶች ሊቃውንት ምክር የደረጀና አስተዋይነቱ ከትህትናና አድማጭነት ጋር የተስማሙለት፤

፱) ራሱን ከፍ ከፍ የማያደርግ፣ ሌሎች የእርሱን ጉድለት የሚሞሉለት መሪዎችን አክብሮ የሚተባበር፣ ከእኔ ወንድም እኅቶቼ ይሻላሉ በሚል እውነት፣ ትህትና ሥልጣኑን ለማስረከብ ዘወትር የሚጋብዝ፤

፲) ሐሰትን፣ ሤረኝነትን፣ የክፋት ቡድነኝነትን፣ የትንኮል መረብን ሳይሆን በፍትህ እውነትን በሰብአዊነትና በሀገር/ሕዝብ ትስስር መተማመንና ህብረት ላይ አተኩሮ የሚሠራ ለመሆኑ ያለፈ ታሪክ ያለው፤

፲፩) ከኢትዮጵያ ሀገራዊ፣ እምነታዊና ባህላዊ የቀኑ እሤቶችና ሁለንተናዊ ሀብታት አንጻር ተጻራሪነት ካላቸው የኮሚኒስት፣ የቅኝ ገዥ ወራሪዎች፣ ከክፋፋይ የጎሣና ውጭ-ገብ አሉታዊ አስተሳሰቤች ጋር ህብረት ፈጥሮ እንደማያውቅ ምስክርነት ያለው

፲፪) በግል የሥልጣንና ሀብት ፍተወት ያልተለከፈ
---- ሰው ብቻ መሪ እንዲሆን ያለ ፍርሃት ይሉኝታና ማስመሰል ትውልዱ እንዱሠራ፣ ከመንጋናንጎጥ ፖለቲካ ጋር በጠላትነት እንዲቆም #የአብይ አህመድ እና ጓዶቹ ነውርና ግፍ ትውልዱን ያስተምረዋል የሚል ተስፋ አለኝ።

ከ#አብይ እና ተመሳሳዮቹ ይእርሱ የርእዮት ወላጆቹ ከአመጡብን የህልውና አደጋ ለመገላገል ሌሎች #አብይ (አብይ-ዎችን)  በጭፍን መከተል ከረመጥ ወደ ፋመ እሣት መሸጋገር ይሆናል።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

  ኦ ርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩ . ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡ በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያ...