ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

የሚያድን እና የሚገድል ፍርሃት

ራሳችንን እንጠይቅ⁉️  ምን ነካን⁉️ የማያድን ፍርሃት ለምን እንፈራለን ⁉️

ሃምሳ ዓመት ሙሉ እንዲገድሉን ለምን ፈቀድን?⁉️

የሚያስገድሉንና ከገዳዮቻችን ጋር የሚተባበሩትን ምንደኞች እንዴት እረኛ ባለን ተቀበልን⁉️

እግዚአብሔር ሲፈጥረን ከሰጠን የመዳን ጸጋዎች መካከል አንደኛው ወደ ፍጹም ፍቅር እስክንደርስ ድረስ እርሱን በመፍራት ከጥፋት መጠበቅን ነው።

#ቅዱስ #ዳዊትና ሰሎሞን "የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው" አሉን፤ ለፍጹማን መነኮሳት የሚመክረው ሶሪያዊው ቅዱስ ይስሃቅ (ማር ይስሃቅ) "የጥበብ ሁሉ መጀምሪያ እግዚአብሔርን ማፍቀር ነው" ሲል "ፍርሃት" ወደ ፍቅር ማድረሻ መሆኗን ይጠቁመናል።

ጌታችን "ሥጋን የሚገድሉትን አትፍሩ፣ ይልቁንም ስጋና ነፍስን አዋህዶ በሲዖል ሊቀጣ የሚችለውን እግዚአብሔርን ብቻ ፍሩ" ብሎናል።
ከእነዚህ መልእክቶች የሚያድን ፍርሃትና የሚገድል ፍርሃት መኖሩን  እንረዳለን።

እኛ በዚህ ዘመን ያለን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና ተከታዮች ፍርሃንታችን የሚገድልና የሚያስገድለው አይነት ፍርሃት  ነው።

የሚያድነው ፍርሃት እግዚአብሔርን ብቻና ብቻ በመፍራት የእውነት ምስክርነት (ሰማእትነት) ሕይወት መኖር ነበር። ይህ አይነቱ አኗኗር በሥጋም፣ በንፍስም ነጻነት እንድናገኝ አባቶቻችን ኑረዉት ባስረከቡን ነጻ ሀገርና ብርሃን በሆኑ ቅዱሳን ታሪኬቻችን ይታወቃል።

ዛሬ ያለነው ሀገር ተነጥቀን፣ ቤተ ክርስቱያናችን የምንደኛ መንጋ ተንሰራፍቶባት፣ ታሪካችን ባእዳን አሠልጥነው ምሁራን ባሰኟቸውና ለሀገራቸው ዕንቁ ምሥጢር በማወቅ ዘርፍ ደንቆሮ የሆኑ፣ መዋስ እንጂ ማሰብን እርም ያደረጉ ሰዎች ጠልሽቶ፣ ፖለቲካችን እኛን በማጥፋት ፕሮጀክት ላይ ተዋቅሮ፣ እንደ ወያኔና ኦነግ፣ እንዲሁም እነርሱ ተዳቅለው ባስገኙት የጭንጋፎች መሰብሰቢያ በሆነው የብልጽግና ወንጌል መንጋ  ጥቃት ሥር ስንኖር የምንፈራ እግዚአብሔርን ሳይሆን ጠላቶቻችን እነርሱን ነው።

በዚህ ምክንያት እውነት መናገር፣ ፍትህን መሥራት፣ ግፍን መቃወም፣ ሐሰትን መሞገት፣ ራስን መከላከል፣ አንድ ሆኖ ለሰብአዊብክብር መረጋገጥ መነሳት ሁሉ ተሰውሮናል።

የተለማመድነውና በተለይ ከማኅበራዊ ሚዲያ ጋር ተጣምሮ የወረስነው  ጎጅ ዐመል:-

፩) እውነት የሚናገሩትን በአሉታዊ መንገድ ማዳከም፤
፪) ሰይጣንም ቢሆን ሥልጣንና የቁስ ሀብት ያለውን ሁሉ የትክክለኝነትና የእውነት  ሚዛን ማድረግና ማጎብደድ፣
፫) ያለ አመክንዮአዊ ተጠየቅ  ሩቅ ቆሞ በጭፍን መቃወም ወይንም መደገፍ
፬) በሌሎች መስዋእትነት ነጻነትና ሰላም እንዲገኝ መጠበቅ
፭) ሀገርን ለጠላት ሰጥቶ መሰደድ
፮) ከእውነት፣ ከሰብአዊነት፣ ከፍትህና ከፈሪሃ እግዚአብሔር አስበልጠን ለጎጥና ቋንቋ ቡድን ጥብቅና መቆም
፯) የሰይጣን ድግስም ቢሆን በደመቀበት ሁሉ ማጨብጨብ፣ የእህዚአብሔርን የምስጋናን ዜማና ቅኔ ሁሉ ለሆድ መሙያ ለጠላት ሳይቀር ማወደሻ ማድረግ ፣ ወዘተ በእግዚአብሔርና ህሊና ባላቸው የሰው ልጆች ዘንድ ሁሉ የተጸይፉ ጠባዮቻችን ናቸው።

እልቂት እጣ ፈንታዬ ነው ያለው ኦርቶዶክሳዊን ዜጋና በአባትነት ስም በዓላት እያደመቁ፣ እርስ በርሳቸው እየተመሰጋገኑ፣ ከአድርባዮችና አስመሳዮች የቅኔ ሙገሳ እየተቀባበሉ መኖር የማይሰለቻቸው የሐሰት እረኞች፣

እና
መንግሥት ሆኖ የመንግሥትነት ወግ ለአንድ ዕለት ስንኳ ማሳየት የተሳናቸው ከሰውነት ዝቅ ያሉ ድውያን የሚጫወቱበት ሕዝብ አንድ ሆኖ ይህ ግፍ ይቁም ለማለት ምን አገደው?

እየገደለ የሚገዛ መንግሥትን መንህሥቴ፣ እያስገደለ የሚጠብቅ እረኛን እረኛዬ፣ ሁለቱንም የቤተ መንግሥትና የቤተ እምነት ሸክሞችን አዝሎ ለምንንቀጠለ?
ሕዝብ የራሱን ሞትና ስደት ለመከላከል ዝግጁ መሆን አቅቶት፣ ጸሎተ ፍትሀትና የሰማእትነት ክብር ተነፍጎት ለምን በመከራው  ይቀጥላል?

መልሱ የቱ ነው?⁉️

፩) እፕሁንም ነጻ አውጭ እየጠበቀ?

፪) መንግሥት ልብ ገዝቶ እንደ ሰው ሊመለከተኝና ሊከላከልልኝ ይጀምራል ብሎ?

፫) ሲኖዶሱ በክርስትና አባትነቱ ድምጽ ይሆነኛል ብሎ?

፬) ፋኖ ይደርስልኛል ብሎ?

፭) ከመሞት ሌላ ምርጫ የለኝም ብሎ ተስፋ ቆርጦ ለሞት ወድዶ ተሰልፎ?

፮) ሀገርህ በሰማይ ነው በዙህ ምድር መጨፍጨፍ ያጸድቀኛል ብሎ አምኖ?

፯) የታወጅበት ጦርነት ከምድረ ገጽ ሊያጠፉት የተማማሉት በብልጽግና አስተባባሪነት የሚመሩ፣ በዘረኝነት፣ በዉሀቢ ጽንፈኛ፣ በሰይጣን አምናኪዎች፣ በቁስና መሬት አምላኪዎች ((ለፌ ፊ ለፋ (አጥንትና መሬት) Blood & Soil)) በሚሉ በሽተኞች ጥምረት መሆኑን፣ ካልተሸነፈ በስተቀር መግደል የማያቆም የአራዊቶች ፕሮጄክት መሆኑን መረዳት ተስኖት?
ለምን ሽባ ሆንን⁉️
ብቻ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአጠቃላይ ሰውነቱን ያዋረደው ለምንንይሆን? ግማሹ የወያኔ፣ ሌላው የኦነግ ኦሮሙማ፣ ትግራዋይነት ወዘተ (ከሂትለር Germenness ተቀድቶ. በOromoness የተውሶ ምሁርነት የተቀመረ መሆኑ ነው) አምላኪ ሆኖ ሃምሳ ዓመት ሙሉ በተጋተው ሀሰተኛ ትርክት፣ በቃዠው በሌላው መቃብር ላይ የሚጨብጠው ታላቅነት እየተመራ ለምን ከትልቅና ሰፊ ሀገሩ፣ ከረዥሙና አኩሩ ታሪኩ ወርዶ  በቋንቋና በቦታ ጠብቦ በማሰቡ ቀጠለ?
በመላውብሀገሪቱንስለሚጨፈጨፉ፣ ስለሚፈናቀሉ፣ ከእምነት ስለሚፈልሱ፣ ተሰድደው ሀገርዐልባ ባዛንኝ ስለሚሆኑ ልጆቹ የማይገደውን ሲኖዶስ ተብዬ የጎሣ ፖለቲካ ባሮችን ስብስብ  እንዴት "ቅዱስ" ጉባኤንእያለ መጃጃሉን ቀጠለ?
እንዳው በአጠቃላይ ምን ነካን?⁉️


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

የሐሰት ትርክት ኦነጋውያንና የሕወሃታውያ የጋራ ስልት ከነግሥታት ወደ ተራ ግለሰቦች

✏️ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።  እርሱ ይመስገን። ምድራችንን #በደም #ያጨቀየው $ህሊና #የነሳን ፣ #ልቦናችንን #ያጨለመን ፣ #ሰብእናችንን ያዋረደው:- 👉 የሕወሐታውያንናንየኦነጋውያን የንዑስ ማንነት የጎሣ ፖለቲካ የደንቆሮ ርእዮትና፣ 👉 መርዛማን ጥላቻን ለ፶ ዘመናት ያከፋፈሉት የሐሰት ትርክት ናቸው። ✏️እንደ ዳግማዊ #ምንልክ ያሉ   ከዋክብት መሪዎች፣ እንደራሴቻቸው፣ ደጃዝማቾችና ቀኝና ግራ አዝማቾቻቸው  ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ብዙ ውለታ ውለውልናል:- 👉 በዘመነ ኦቶማንና አውሮፓ፣ በዘመነ መሳፍንት የተበታተነውን እና የተቆነጻጸለውን፣ ጎሠኛ የአርብቶ አደሮች  መሬት ፍለጋ  የደመሰሱትን ክርስቲያናዊ የግዕዝ/የነፃነት ሥልጣኔ አሻራ እንዲያገግም ደክመውልናል፤ 👉 የጥንት አገርን እና ሕዝቦችን   በከፊልም ቢሆን በመሰብሰብ  ጠንካራና ብቸኛ የነጭ ቅኝነትንና ባርነትን በመከላከል፣ ከኦቶማን ቱርክ ወር ትናንት ውስጥ ጥረኛ  አህመድ ግራኝ በመጋደል  ልዩ የነጻነት ማንነት ያላትን አገር ብበቸኝነት በዓለም ካርታንላይ አቆይተዋል፤ 👉 የሬማ ግዛት በጎሣ ተብልቶ ፲ ትንንሽ ሲሆን ከበበባውን ተቋቁማ በዝኃነታችን በተመጋጋቢ አንድነት ከ፹ በላይብቋንቋ፣ ከዓለም ትልልቅ እምነቶች ክትስትናን ፣ ይሁዲን፣ እስልምናን፣ የእረማውያንን ቅሪት የሆኑ የባህል እምነቶችን ሁሉን ይዛ በአውሮፓ በአርብ አምሳል ሳትሠራ ለእኛ አቀብዋል፤ 👉 ወያኔና ኦነግ፣ ገንጣዩ ሻዕብያ፣ ከሃዲው የማርክሲስት የአእምሮ  ባሪያን ስብስብ  እስኪፈትናት ድረስ ራሷን የቻለች አገር እንድንፈጥር ያስተባበሩን ነገስታት የተመሰገኑ ናቸው። አገር ሲያረጅ ጃርት ያብቅላል እንዱሉ: መል...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩. ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡  በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡  ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በቋንቋ መ...

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...