መከራ ለጸናበት የትግራይ ሕዝብ ትድረስ የትግራይ ሕዝብ ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ነው። ይህን የማያውቅ፣ አብሮ የማይታመም አራት አካል ነው፦ (1) የሕወሃት እና የኦነግ ዕሳቤዎች ተጠቂና በሰው ልጆች መከራ ታሪካዊ አገር አፍርሰው አዳዲስ ሪፐብሊክ በመፈጠር የስስት‹ የበተአችነት፣ የተላላኪነት ስነ ልቦናቸውን ለማከም የሚጣጣሩ ጨካኞች፤ (2) ኢትዮጵያ እንድትፈርስላቸውና ስም አጠርሯ ከዓለም ካርታ እንዲፋቅ ለብዙ ዘመናት ለፍተው በእኛው የእርስብርስ መጠፋፋት ሂደት እንድናጥፋት ሻዕብአን፣ ሕወሃትንና ኦነግን ፈጥረውን ደግፈው የጫኑብን የአድዋ ቁስለኞችና የግራኝ አህመድ መሸንፍ የሚያንገበግባቸው የውጭ አካላት፣ (3) በኢትዮጵያ መደምሰስና ቤተ ክርስቲያን መዳከም ታሪኳን ደምሰሰው በሊቢያ፣ በሶርያ፣ በየመን፣ በአልጄርያ፣ በቁስጥንጥንያ የክርስትናና አሻራ አጭልመው በደም ላይ አዲስ የክህደት መልክ ለማቆም በድማችን መፈሰስና በስቃያችን ግባቸውን ለማአስካት አጋጣሚዎችን የሚጠቀሙ ጽንፈኞች ናቸው፤ (4) ኦርቶቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንና ክርስቲያኖችን በማዳከም በቅኝ ገዥዎቹ የማደንዘዣ እምነት ለመተካት በዙ ዘመናት የልፉቱ ቀሳጢዎች። የትግራይን ሕዝብ ለመከራ አጋልጦ 50 ዓመት ደም ያፈሰሰው፣ የስደትና የመከራ በር የክፈተው ሕወሃትና የእርሱ ፍልፍሎች ለሁሉም ኢትዮጵያን ለሚሉ የአማራ፣ የጉራጌ፣ የኦሮሞ፣ የቤኒሻንጉል ሕዝብም ሁሉ የሰቃይ ፋብሪካ የሆነውን የዘር ፖለቲካ፣ ትርክት፣ ክልል፣ ሠራዊት፣ ኢኮኖሚ፣ ጥላቻ አከፋፍለዉለታል። ከዚህ አንፃር ሁሉ ስቃይ ውስጥ ነው። የትግራይ ሕዝብ መከራ ግን ልዩ ነው። ልዩነቱ ያለው የሌላው ማኅበረሰብ የሚሰቃየው ሕወሃት በዘረጋው የዘር ፖለቲካ ነው። ችግሩን ምንጭ ከራሱ ጉያ አርቆ ይመለከተዋል፣ እናም ሐውሃትንና ፍጡራኑን ማስወገድ መፍ...
This is a spot where I post and share part of my daily reality. I would love to hear from others too to learn how differently we interpret daily encounters including our imaginations. ይህ ሥፍራ የየዕለት ገጠመኞቼን፣ እንዴት በዕለቱ እንደተረደሁትና የማስበውን ለሌሎች ያማጋራበት ነው፡፡ የሌሎችን በመስማትና ምን ያህል ዓለማችንን በተለያየ መንገድ እንደምንመለከታት ለመማር እጓጓለሁ፡፡