እሽ አትበሉኝ የሹም ዶሮ!!
--- እንትን ያለበት ዝላይ አይችልም እንደሚባለው ትንሿ የእኔ የግል ትችት በጓዳ ሲቦካን የከረመውን ቡኮ ወደ አደባባይ አውጥቶ ልብ ያለው ሁሉ የሽታውን መርዛማነት እንዲያውቀው በማድረጉ እግዚአብሔርን አመስግነዋለሁ።
======================
ይህ አገር እንደተቀሰፈ የጅዝቡን መከራ በማየት እናውቃለን። የበለጸ ግን እርግማኑ ጽኑ መሆኑን የሚያሳየው ከመከራ ልታደጋችሁ፣ ከሃውና አደጋ ልከላከላችሁ ዘመትኩ ከሚሉት ወይንም ከፕሮፓጋንዳ ክንፋቸው አንዳንዶች ወደ አደጋ ተለውጠው መከሰታቸው ነው።
አማራንና ኦርቶዶክስን አደጋ ላይ የጣለውን ትርክት በብታቸው ይዘው ተገኙ፤ እንዲህም ገለጡት!
፩) አሮጌ ትርክት አንሻም፣
፪) ሰለሞናዊ ትርክት ጠላታችን ነው፣
፫) እንደ ደርግ ኢሕአፓ፣ መኢሶን፣ ሕወሃት፣ ኦነግ ወዘተ "አዱሱቷ ኢትዮጵያ" ነባር እምነትም አይሻም፣
፬) ትግላችን እግዚአብሔርን እንደ አምላክ ታሳቢ የማያደርግ ሴኩላር፣ በተለይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጽጥስን የሚጸየፍ ነው፣
፭) ትግላችን ለዐስብና እሴት ይበልጥ የደም ጥራት ላይ የተመሠረተ ነው፣
፮) የኦርቶዶክሳዊ ክርስቱያንን መብት ይሚጠይቅ ንቅናቄንየአማራንትግል ጠላይ ነው፣
፯) ከጽምቀት የክርስቶስ ልጅነት ፖለቲካዊ አማራነት (ነባር ማነቱን የጣለ በልሂቃን ዕሳቤ ልክ ለተፈለገ ግብ መሳካትንየሚተረጎም፣ ለሕወሃቱንትግራዋይነትና ለኦነጉ ኦሮሞነት አቻ የሆነ አማራነትን ብቻንየሚቀበል)
--- በማለት ተገለጡ።
ይህ መገለጥንሳይዘገይ በመሆኑ እግዚአብሔር ይመስገን። ፕህን ልፉ ሤራንያነገቡ ሰዎች ወራት ኪሎ ደርሶ አዲሱ "የአማራው 'አብይ አህመድ' " ተገልጦ ቡሆን ኖሮ የአማራ መስዋእትነት ከንቱ በሆነ መከራችን በቀጠለ ነበር።
ከተጠቅመበት አሁን ለፋኖ ፍኖተካርታውን፣ የትግል መርሁን፣ እሤቶቹን፣ ርውዩን፣ መሪና አመራሩን በግልጽ በይኖ የሚቆጣጠርበት ጊዜ አለው።
==============
እስቲ ራሳችንን እንታዘብ፦
ንጉሥ ገድለን፣ ፓትሪያርክ አንቀን፣ በሀሰት ትርክት የተፈጠረ ዘር ቆጥረንና ሕዝቡን ተካፍለን የልሂቃን ቅዥት ማሳኪያ መሣሪያ ካደረግንበት ከ፷ዎቹ መጨረሻ ጀምሮ ኦርቶዶክሳዊት ክርስትና ፣ ብሎም አማራ የተስኘ ክፍለ ሕዝብ የንቅናቄዎች ሁሉ ማእከላዊ የጥፋት ዒላማ ከመሆን አላረፈም።
በሕወሃትና ኦነግ/ ብልጽግና ወደ ግልጽ ሥርዓታዊና መዋቅራዊ ዘር የማጥፋት ደረጃ አድጎ ሕገ መንግስትና ከዚያም የተግባር ፕሮጀክት ሆኖ ኑሯል። ከህልውና አደጋም አድርሶናል።
የህልውና አደጋ ለመቀልበስ የአማራ ሕዝብ ራሱንም ልጆቹንም ለመስዋእትነት አቀረበ። ይህ መስዋእትነት እንደ ቀደምት የዘረኞች ንቅናቄ ጥቂቶችን ወደሥልጣን አምጥቶ ብዙኃኑን መነገጃ በማድረግ ሕወሃት በትግራይ ኦነግ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ያደረስውን አይነት ቀጣይነት ያለው መከራ የሚያመጣ መሆን እንደሌለበት የትግሉንአነሳስንየህልውና መሆን ነው። ሌሎቹ ልሂቃን በፈጠሩት ዐስተሳሰብ የተመራ ኢስሰብአዊ፣ ኡሀገራዊ እና ኢፍትሐዊ የደም ጉዞ ነው። የህልውና ትግሉ እጅጉኑ ከዚህብየተለየ በመሆኑ ቀዳሚዎችን መስስሎ እንዳያርፈው ጥበቃ ሊደረግለት፣ ሊፈተሽ፣ ሊተችና ገንቢ ሂስ ሊቀርብበት ይገባል።
አሁን ቢያንስ በማኅበራዊ ሚዲያው እንደሚናፈሰው ከሆነ መጥፎ ምልክት ይታያል፣ በእርግጥ እሳት በሌለበት ጢስ አፕጤስም እንዲሉ ምልክቱን ሳይረፍድ ገላልጦ።ማከምንይጠቅማል።
አሁን አሁን በሕዝቡ ቁስል ሥር ተሸሽጎ "እሽ አትበሉኝ የሹም ዶሮ" አይነት ለምክረ ሀሳብና ለግብረ መልስ የማይመች፣ የጎጥ የሶሻል ሚዲያ በማሰማራት ስህተትን መከላከል ከትግሉ ዓላማ በተቃራኒ ቡድንናንግን ማእከል ያደረገ የሚመሰል ድምጵን ፕሰማል። ይህ ደግሞ የትግሉን ዓላማ ይቃረናል።
ኢትዮጵያውያን ይሉኝታ ያጠቃናል፣ "ከእኔ የተሻሉ እያሉ እኔ አልናገርም" በሚል የሞተ አይጥን በምጣፍ ሥር ደብቆ ቤቱን ሁሉ እንደማከርፋት ያለ ልማድ ለመከራ ዳርጎናል። የራሳችንን ጠማማ ሳናቃና ቅን ነህ ብለን ዙፋን እናስታቅፈውና ላይ ከወጣ በኋላ ግን "ሁላችሁም እኔን ምሰሉ" ብሎ።ሊያጣምመን ቀጥ ያልነውን ሁሉ ሲያጥፈን ይሰብረናል። የአማራ ፋኖ።ውስጥብያሉ ጠማሞዥ ብዙኃኑን ሳይበክሉ ቢመከሩ ጽቅሙንለአማራም፣ ለኢትዮጵያም ነው።
የተጣመመ እይታን እሽሩሩ ማለት ውጤቱ ጎጅ ነውና ሳይሳሱና ለብልጣብልጥ የባእድ ተልእኮ ተሸካሚዎች ሳያጎበድዱ ከጥፋት መንገድ እንዲመለሱ ማበረታታት፣ ከልተመለሱ መንጋ አበጅተው ጉዳት እንዳያደርሱ መመካከር ግን ለሁሉም ጠቃሚ ነው።
አሁን አሁን የሕዝብን ልጅ ደም የግል ሀብታቸውና እንደ ወደዱ በመጠቀም ለዐለሙት የግል ግብ ሁሉ ለመጠቀም ሰማያዊ መብት የተጎናጸፉ የሚመስላቸው ሰዎች ይታያሉ።
ይህ አካሄድ እንደ ስብሐት ነጋና ሌንጮ ለታ ፶ ዓመት የሚያታግሉ፣ ሺዎች ሲቆስሉና ሲጎሳቆሉ ከላካቸው ባእድ ወገን ድጋፍ እየተቀበሉ ከጠላት ጋር ሆነው ባስጀመሩት የእልቂት አዙሪት ዙሪያ ዶክትሬት የሚሠሩ፣ ሀብት ዘርፈው የሚያሸሹ፣ በሌላው ክንድ የዘንዶ ጉድጓድ የሚለኩ መሪዎች በፋኖ ትግል ውስጥ ለዚያውም ጸረ ኦርቶዶክስ አጀንዳ ያዘሉ ሰዎች ሲታዩ "ያለፈው ይበቃናልና እንተራረም" ማለት እጅግ አስፈላጊ ነው።
እነዚህ የስነልቡና ስብራት ያገኛቸው፣ ራሳቸውን ልዩም የሚያደርጉ ሰዎች የሀሳብ ሙግት ሱገጥማቸው የሚደበቁት "ከእኔ ሜዳ ላይ በአካል ከምታገለው የበለጠ አንተን ማን ተቆርቋሪና ዐሳቢ አደረገህ?" የሚልንነው። ያልገባቸው ወይንም እንዲገባቸው የማይፈልጉትብ እውነታ "ጠመንጃ የያዘ ሁሉ ቅዱስ ጠመንጃ ይል ያዘ ሁሉ እርኩስ" የሚል አምክንዮአዊ ተጠየቅ ሊኖር እንደማዥል ነው።
ሆስፑታልንእልጋ ላይብያለ ብልህ አረጋዊ፣ በስደት ይሚገኝ ቅን ዐሳቢ፣ ቤተ መቅደስ የሚፓገለግል ቄስ፣ ገዳም የሚጸልይ መነኩሴ፣ ልጅ የምታጠባ አመጫት የሚተኩሰውንና የሚመራውን እጅግ በሚያስከነዳ ደርጃ የትግሉን ፍኖተካርታ በጽራት ሊመለከት፣ አካሄዱን ሊቀይስ ይችላል። ይህን በመካድ አስተያየትና ሙግት የሚያቀርበውን ሁሉ በምክንያታዊ ተጠየቅና በትግሉ ግብ መዝኖ ለበለጠ የሀሳብ ጥራት በፍቅር መግጠም ተገቢ መሆኑን በመካድ የጎጥ ጓዳ በየቦታው መሥርቶ በስህተት ወይንም ሆን ተብሎ ለተቀመረ ክፉንግብ፤ ወይንም በባእድንተልእኮ ተመርቶ የትግሉን ዓላማ ለመጥለፍ የዐሳብ መንጋ ለመፍጠር መሞከር ከኦነግና ከሕወሃት የ፶ ዓመታት የጥፋት መንገድ የተለየ አይሆንም።
"አብይ አህመድ እንዳይገድላችሁ እናንተ እየሞታችሁ እኔ አንግሡኝ፣ ካልሆነ እኔ ልግደላችሁ እንደማለት ያለ አዲስ አብይ(ነት) ከማቆጥቆጡ አስቀድሞ።መመካከር ያስፈልጋል። ገና በጫካ ውስጥ አምባገነነት እንዲያቆጠቆጥ የሚሠራ መንጋ መፍጠር ከተጀመረ በትረ መንግሥት ከያዙ በኋላ አብይ እህመድንና መንግሥቱ ኃይለማርን የሚያስናፍቁ ላለመሆናቸው ከወዲሁ ዋስትና ማንበር ያሻል። ለዚህ መነሻው በቅንነት መተቻቸት ነው።
=================
እንደሚታወቀው የአማራ ሕዝብ ተገድዶ የጀመረው ትግል ዓላማው ለሃምሳ ዓመት አማራን ዒላማ አድርጎ የበላውን የዘረኝነት አውሬ በመዋጋት የሕዝቡን ህልውና ማስቀጠል፣ ብሎም ዋስትና የሚሰጥ ሥርዓት ማቆም ነው።
ልብ በሉልኝማ ፣ "ሥርዓት እንጂ ቡድኖችና ግለሰቦችን ማቆም አይደለም"።
በእርግጥ ግለሰቦችና ቡድኖች ለትግሉ ዓላማና ግብ መሳካት እንደየጸጋቸው አስፈላጊዎችና ልዩ ክብካቤ የሚገባቸው ይሆናሉ። ክብካቤው የሚዘልቀው ግን የግል ፍተወታቸው የትግሉን ማእከላዊ ዓላማና ግብ እስካልተገዳደረ ብቻ ነው። አሁን በአንዳንድ ሚዱያ እንደሚታየው ከሆነ ከፊት ከፊት ለይስሙላ የዋናውን ትግል ዓላማንእያወጁ በተግባር ወደ ግል ጠባብ ፍተወት ማርኪያነት ትግሉን እስማዘቀጥ የሚያደርስ ፕሮፓጋንዳና ተስፈንጣሪነት ይታያል።
በዚህ ሁኔታ ውስጥ ፋኖዎች "ምንም ቢያደርጉ እደግፋቸዋለሁ" የሚል ሰው ከተገኘ የትግሉን መነሻና መድረሻ ሸጦ እንዳው የሚደግፈውን ቡድንና ግለሰብ፣ ወይንም ጎጥና ትርክት እንደ ጣዖት የሚከተል ከንቱ ሰው እንጂ በዓለአእምሮ አይሆንም። የዚህ የጣዖት አገልግሎት የሚሰጡ ግለሰቦዥ በማኅበራዊ ሚዱያ በርክተዋል።
ቁምነገሩ ከመበርከታቸውም በላይ ለጥፋታቸው መደራጀታቸው ነው። እናም ዝምታ መሰበር አለበት።
በዚህ ላይ ብዥታ ከሌለን ህልውና ምንድ ነው የሚለውን ማጥራት እንጀምር ።
ጉዳዩአጭር ነው:-
ማንም ጤናማ ሰው እንደሚረዳው ህልው መሆን በሥጋ ብቻ መኖር ማለት አይደለም። በእርግጥ ሌሎቹ የህልውና ምሶሶዎች ትእጉም የሚያገኙት በአካል ተገኝቶ መኖር ላይ ይቆማሉ፣ ሌሎቹ የህልውና መሠረቶች ፩) ባለርስትነት፣ ፪)/፫) ክብረ-ሰብእ ሥጋዊ፣ ፬) ክብረ-ነፍስ መንፈሳዊ፣ ፭) የትውልድ ትውፉታዊና ታሪካዊ የተቀደሰ ቅብብሎሽ፣ ፮) በእኩልነት ላይ የተመሠረተ ተመጋጋቢ ህብረት ከጎረቤትና ከዓለም ጋር መመሥረትና ማስጠበቅን ይመለከታል። ሁሉም የህልውና የማይነጣጠሉ ዘርፎች ናቸው።
በዚህ የህልውና ብያኔ ከተግባባን፣ ቀጥሎ የህልውና ተጋድሎ አመራርና አፈጻጸም፣ የድል ውጤቶች አንጓዎችና መሥፈርቶቻቸው ላይ እና ትግሉን ወደ ግቡ ለማድረስ የሂደትና የመርህ ጉዳይ ላይ መግባባትን ይመለከታል። እዚህ ላይ ለስሜትና ለወቅታዊ ገበያ የሚቀርቡ ጉዳዮችን መጥቀስ አያሻም።
ሂደትና መርህ ለሁሉም ግልጽና ቅቡል መሆን አለበት። ቅቡልነት የሚመነጨው ከብልጣብልጥ ወይንም ከአንድ ጥልቅ ዐሳቢ ግለሰብ ወይንም ቡድን አይደለም። ምንጩ ራሱ የሚጋደለው ሕዝብ ከወሳኝ የማህበረሰቡ ጥልቅ እሤቶች (ሃይማኖት፣ የቀና ባህል የሚያመነጨው ነጽሮተ ዓለም ወይንም የዓለም ማያ ) የሚያፈልቃቸው መሆን አለባቸው።
የጤናማና ትክክለኛ መሪዎች ሚና ርእዮት፣ መርህና ፍልስፍናን ከባእድ መቅዳት ወይንም በሤራ ክበብ ውስጥ በማመንጨት ሕዝቡን ለጠባብ ግባቸው መጠቀም ሳይሆን የሕዝቡን ነባርና ጠቃሚ እሤቶች ተረድቶ መግለጽ ብቻ ነው።
የትግል ሂደትና እሤት ምርጫችን የሕዝቡ ከሆነ በሕዝብ ላይ መደራደር አይኖርም። ለሕዝብ እሰዋለሁ ብለውንእየተናገሩ በሕዝብ ላይ ካልነገሥኩ የትግሉን ባለቤቶች ዋጋ ለማስከፈል ማሤር ክህደት ይሆናል።
የአንድ ማኅበረሰብ፣ ሀገር፣ ቤተሰብ የህልውና አደጋ ላይ ሲወድቅ ምላሹ ከትንሽ ወደ ርልቅ፣ ከቀላል ወደ ውስብስብ ያድጋል። ለምሳሌ የሙጀመረው በያለህበት፣
(፩) መወራጨት፣ ውና
(፪) መንፈራገጥ፣
(፫) አደጋውን ለመከላከል ለውጊያ መሰለፍ/መደራጀት (የአስተሳሰብ ጥራትና የአመራር አይነትን ይጨምራል)
(፬) በአንድ ዓላማ እና ፍኖት ላይ መቆም (ግልጽ ፍኖተ ካርታ:- ከየት ወዴት? ለምን እንዴት? ከማን ጋር? ከዚያስ? የሚሉትን ጥያቄዎች በግልጽ መመለስን ያካትታል) ፣
(፭) እደደሚገባ ጠላትን በአቻነት መከላከል፣
(፮) በጠላት ላይ ብልጫ ወስዶ ማጥቃት፣
(፯) ጠላትን ሰብሮ ማሸነፍ ብሎም፣
(፰) ድሉን ዘለቄታዊ ዋስትና የሚሰጥ ሥርዓታዊና መዋቅራዊ ደርጃንላይ ማቆምና ሁኔታዎችን ከአካባቢ ጀምሮ።በሀገርና በቀጠና፣ በእህጉርና በዓለም ዐቀፍ ደርጃ መፍጠር ይሆናል።
ከዚህ አንጻር ስንመዝነው፦
የአማራ የህልውና ትግል ደረጃ ፬ን ሳያሟላ ዘልሎ ፭ኛና ፮ኛ ደረጃዎች መካከል ደርሷል።
በዚህ ደረጃዎች መካከል የቆመውንትግል አንድነት እንዳይኖረው፣ የጠራ ጎዳና እንዳያሠምር በማድረግ ወደፈቀዱት ለመምራት የሚሹ አካላትብከሩቅም ከቅርብም፣ ከውስጥም ከውጭም የሚመኙ አካላት ቢወርሩት አያስገርምም። የሚያስደነግጠው ግን ራሱ ታጋዩን እንምራ የሚሉ ሰዎች የጎጥና የግለሰብ ጉዳይን ከፍ አድርገው በሤራ መረብ ድንክ አጀንዳን አየር ላይ በማንሳፈፍ ለትግሉ ዓላማ መጠለፍ በ የበለጠ በሩን ወለል አድርገው ሱከፍቱት ነው።
በሀሉም የጥፋት ንቅናቄዎች ውስጥ ሤረኝነትና መጠፋፋትንየተለመደ ነው። ነገር ግን ለህልውና በእውነትና በሰብአዉነት መርህንለሚመራንየአማራ ትግል የውስጥ ሤረኝነት ትግሉን መግደል ስለሚሆን በዚህ ውስጥ የሚገኝ ሁሉ የአማራንየህልውና ጠላቱ ሆኖ ቢፈርጅ ትክክል ይሆናል።
የውስጥ ሤረኞቹ ሤራቸው እንዳይታወቅባቸው "አማራ፣ ህልውና፣ ኢትዮያኒስት የሆነና ያልሆነ ወዘተ" የሚሉትን ቃላት ያለ ቦታው ሁሉ በማጮህ ነገርንግንንበተቃራኒው ለእነዚህ ቃላት ተስማሚ የጋራ ትርጓሜ ላይ እንዳደረስ በሀሜትና ስም ማጥፋት ተከታዮቻቸውን ይጠምዳሉ።
ከሀሳብ ይልቅ በግለሰቦች የደም ጥራት፣ የግል ተክለሰውነት ጉዳይ ላይ የሚንጠለጠሉ፣ አንድ የውጭ ዲፕሎማት ስልክና ተስፋ ሲሰጣቸው በአንድነት የሚገኘውን ዘለቄታዊ ፋይዳ እንደንእምንት ቄጥረው በራሳቸው ግላዊና አካባቢያዊ ምውሐር መሽከርከር ይጀምራሉ። ይልቁ ዓላማ ይደበዝዝባቸዋል፣ የራሳቸውንጠባብ ፍላጎት ያስምጣቸውና "እልሰማ ስሙኝ፣ አላይ እዩኝ፣ አልመራም ተከተሉኝ፣ አላውቃችሁም እወቁኝ" ወደሚል በእንድ ጊዜ ደንቆሮ፣ ዲዳ፣ እውር እና የማይዳስስ ግን ግዙፍና የሚወራጭ አስቸጋሪንየቤተሰብ አባል ሆነው ይጎለታሉ። ከቤቱ ውስጥ የአእምሮ ብስለት የሌላቸው ደግሞ በማያዩትና በማይሰሙት ጭብጨባና እልልታ በሽተኝነታቸው ውምዳይታወቅ፣ ያወቀውም ደፍሮ እንዳይናገር፣ ተናግሮም ለታወከው ቤተሰብ መፍትሔ እንዳይሰጥ እንቅፋት ይሆናሉ። ይህንን ሁኔታ ተስፋ በተጣለበት የፋኖ ተጋድሎ ውስጥ ሲፈጠር እያዩ በዝምታ ወይንም በድጋፍ የሚያባብሱ አእምሮዎች ይኖራሉ። ምክንያታቸው ብዙ ሊሆን ይችላል ነገርን ግን ከአስተውሎአችን የተለመዱት፦ በጭፍን መንጎች ላለመዋረድ መፍራት፣ የገዳዩን አደገኝነት ለመመዘን አቅም ማጣት፣ የተሻለ ማድረግና መሆን እንደሚቻል አለማሰብ፣ ይሉኝታ፣ ፍርሃት፣ ጥገኝነት፣ ከሌላ መልካም የራስ ክፉን የመምረጥ ባህል፣ የቡድን እሳቤ ባሪያ በመሆን በራስ አለመቆም፣ ጭፍን ተከታይነት እና ከጊዜአዊ መከራን ለመገላገል ብቻ መጨነቅና ዘለቄታዊውን አለማሰብ ናቸው።
ፋኖን በሚመለከት አደገኛው ወጥመድ ጎጠኝነት እየገነነ ዋናውንንየትግሉን ዓላማ ሲያጠላበትና አምክንዮን የሚያቀጭጭ ናርሲሲስቲክ ባሕርይያላቸው መሪዎች ከተፈጠሩ ነው። በእርግጥ ይህ ምልክት ምቆም አለ።
እንግዲህ ፋኖ በ፭ኛና ፮ኛ የትግል እድገት ደረጃዎች መካከል ቆሞ ራሱን ካላጠራ እና ደረጃ ፬ን ግልጽ ካላደረገ ትልቅ የመጠለፍ ሂደት ውስጥ ይወድቃል። በግል ግምገማዬ አሁንም የመጠልፍ እድሉን የሚያሰፉ የውስጥ አስጠላፊዎች ለመኖራቸው በማኅበራዊ ሚዲያ ከትግሉ የበለጠንራሳቸውን የሚያሻሽጡ፣ ከአንድነት የበለጠንጎጣቸውን የሚያደምቁ እየታየ ነው።
የአማራ ሕዝብ በመስዋእትነቱ ድሉን አበላሽተው ደጋግመው የሚሰዉት የሤራ ቡድኖች እንዳይጠቀሙበት ዋስትና ብገና አላበጀም። ይህን የምለው ሰሞኑን ኦርቶዶክስን ዒላማ ያደረገ የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ በማየቴና ዘመቻው ከአንድ ጎጠኛ የሤራ ስብስብን ማእከል አድርጎ በትግሉ ስም የሚሠራጭ ለመሆኑ ፍንጭ ስለሚሰጥን ነው።
በትልቅ ክፍለ-ህዝብና ክቡር ዓላማ የተሰለፈን የዋህ ወገን አዋርዶ ለድንክ ጠባብ ግቦች የመጠቀምም ጥረት ለመኖሩ የተለያዩ ሚዲያዎችንብበማድመጥ መገመትብይቻላል።
አንዳንዶች ወደ ፋሽዝም እያመሩንያሉ ይመስላሉ። ንግግሮቻቸው ውስጥ "አማራ ሀሳቡም፣ ደሙም፣ ሀብቱም የእኔ ግብ መገልገያ ስለሆነ ሃይማኖትም፣ ባህልም፣ ታሪክም፣ ኦርቶዶክስም፣ ሰለሞናዊነትም፣ ፍትህም፣ እውነትም አይድረሱብኝ" የሚል ድምጸት
ይህ ምልክት ደግሞ የትግሬ ሀገሩ፣ ፍላጎቱ፣ ርእዩ፣ ምኞቱ ሁሉ የሚወሰነው በእኛ ነው በሚሉት ጥቂት የሕወሃት ሤረኞች እንዲሁም ኦሮሞ ሁለንተናው የሚበየነው በእኛ አስተሳሰብ ብቻ ነው፣ ሕዝቡ እኛን ከመከተል ውጭ አማራጭ የለዉም ከሚሉት ኦነጎች ጋራ የሚያመሳስል ነው።
ሁለቱ ነፃ አውጭ ነን ባዮቹ የየብሔራቸው ባሪያ አሳዳሪዎች ለግማሽ ምዕተ ዓመት የተከተላቸውንና ጠላት ያሉትን ኤርቶዶክሳዊ ክርስትናና አማራን በመከራ ያሳቀፉ እና "ነፃ አውጭዎች ነን" ብለው ሁላችንንም በተለይ ነፃ እናውጣህ ብለው ያሳሳቱትንና ያስከተሉትን ክፍለ ሕዝብ በገዛ ሀገሩና ታሪኩ ላይ እንዳሳመስጹት ፣ ትውልዱን በሥጋም በነፍስም እንደጎዱት ሁሉ የአማራን ትግል አጥብቦ የጥቂት ቡድንና ወገን ፍላጎት መሣሪያ ማድረግ ከህልውናንትግል ወደ ዘርና ጎጥ ትግል ከመቀየር እንዴት ይለያል?
የጎጥና መንጋነት ባህል ለጅወሃትና ኦነግ አይነት እርግማን የተመቸ ማሳ በመሆኑ ሁሉንም ሀሳብ ዋጋ አሳጥቶ ሰብአዊነትን ያረክሳል። ከዚህ ርኩሰት መሸሽ የህልውና ታጋይ ሁሉ ኃላፊነት ነው።
ትግሉ የሀሳብ፣ የመርህ፣ የእሴት፣ የግብ፣ የአመራር ጥራት ይፈልጋል። ከመወራጭት ደረጃ አልፎ መጓዝ የጀመረን ታላቅ ተጋድሎ በግል ፍተውትና ጎጣዊ ጭቃ ውስጥ መድፈቅ ወንጀልም ኃጢአትም ነው።
ድርጊቱ በሕዝብ ላይ ክህደት መፈጸም ነውና ወንጀል ነው፣ የወጣቱን መስዋትነት ከዋናው ዓላማ በተቃራኒ ተጠቅሞ ሕይወት መቅጠፍ ነውና ኃጢአት ነው።
ይህን እውነት በሚከተሉት የተለመዱ ጠባብና ናርሲሲስቶች በሚጠቀሙት የማጭበርበሪያ ምላሾች መሸፋፈን አይቻልም፦
* "አንተ ምን አገባህ?" አማራ የግል ንብረታችን እና መገልገያ እቃችን ነው እንደማለት፤
* "ደምህና አጥንትህ በስምህና በቋንቋህ ይለካል" እናም ከእኛ ወገን አትመስልምና ስህተታችንን መጠቆም አይገባህም"፣ እውነትህ ዋጋ የሚያገኘው እኛ የምንተረጉመውና የምንስለው አይነት አማራ ስትሆን ብቻ ነው፣ አምራነትን የምናድለው እኛ ነን እንደማለት፤
* "የአማራን ትግል ለመጥለፍ ተደራጅተው ከሚሠሩት መካከል አንዱ አንተ ነህ" --- "ሞዓ ተውሕዶ ግብረ ኃይል ወደ አምራ ትግል ጠላትነት ተቀይሯል" በቃ ብያለሁ ብያለሁ፣ ማስረጃ ባላቀርብም ጥርጣሬ ፈጥሬ እኔ የማልፈልገውን ሀሳብ መንጎቼ እንዳይሰሙ እከላከላለሁ እንደማለት፤
* "የእኛ አዲስ ትውልድ ባረጀ ባፈጀ ተረት እይታለልም" --- ከኦነግ፣ ከሕወሃት፣ ከአንዳንድ ምእራባውያን የክብረ ነገሥት፣ የኦርቶዶክስና ነባር ትውልዳዊ ቅብብሎሽ ጋር ጠላትነት ያላቸውን አካላት በመከተል፣ ከሰለሞን ሥረወ መንግሥት፣ ከእግዚአብሔር ቅብዐ መንግሥት ጋር ጠላትነት አለን እንደማለት፤ ወዘተርፈ ናቸው።
እነዚህ ደግሞ በማስረጃ፣ በአመክንዮአዊ ተጠየቅ፣ በነባሩ የሞራል ልኬት፣ በፍትህና በስብአዊነት፣ በእውነትና በታሪክ ሚዛን ላይ ለማስቀመጥ የማይመቹ ሆነው ሳይሆን ስሜትን ብቻ ለመኮርኮር፣ የባእዳን ድጋፍ አግኝቶ አማራን ሳይሆን ራስን ለማንገስ የሚደርግ መርዛማ ሩጫ ነው። ንግግሮቹ የአጭበርባሪዎች ተወርዋሪ የጆሮ ቀለቦች እና የየዋሀን ማደናገሪያዎች ናቸው።
የአማራን ሕዝብ የትግል ዓላማ ያላገናዘቡ የጎጥ ሤረኞች ማኅበር የአስተሳሰብ ድውይነትን የሚያሳብቁም በመሆናቸው ለጥንቃቄ ብዙኃኑን ታጋይ የሚያነቁ ሊሆኑ ይችላሉ።
ናርሲሲስቶች፦
"ደምህን ፈልጋለሁ ነገር ግን እምነትህን፣ ታሪክህን፣ ነባርነትህን አልፈልገውም፣ እንደ እቃ 'በእኔ ትውልድ' የአስተሳሰብና የምኞቴ ልክ እገለግልብሃለሁ፣ ይህን ሳደርግብህ የሚመለከት ሁሉ ምንም እውነቱን፣ የሚጠቅምህንም ቢሆን ቢናገር እኔ እስከምፈቅድልህ አትስማው" የማለትን ያህል ከፍተኛ ትዕቢት ያጸባርቃሉ። ይህም ባሕርይ በአንዳንድ የጎጠኛ የፋኖ የሚዲያ ሰራዊት ይንጸባረቃል።
ለዚህ ወደገኛ አካሄድ መፍትሔ እንዲገኝ፣ ትግሉ ዓላማውን እንዳይስትና በሚከፈልለት መስዋዕትነት ልክ ፍሬያማ እንዲሆን ትፈልጋላችሁ?
ለዚህ ጥያቄ መልሳችሁ አዎ ከሆነ የታናሽ ወንድማችሁ ምክር እነሆ፦
፩) በወገን መካከል በጎጥ ማሤርን፣ ለአንድነት እንቅፋት ማንበርን ያለንይሉኝታ ተዋጉትና አቁሙይ፣
፪) ሰውና ሰው፣ ታጋይና ታጋይ መካከል መበላለጥና መቀዳደም እንደአለ፣ ልዩ ክብር የሚገባውና የማይገባው እንዳለ የሚያስመስል ግንጥል አደረጃጀትና መርዛማ ፕሮፓጋንዳ አጥፊ ነውና ያለ ይሉኝታንተጋፈጡትናንአቃኑት፣
፫) አንድን የአማራ ቤተስብ በልዩንልዩንየጎጥ ሕዋስ እስከ ውጭ ሀገር አደራጅቶ ሕዝብን መከፋፈል መከራን ማስቀጠል፣ የትግሉን ዓላማን ግብ ማጥፍ ነውናንታገሉት፣
፬) አምላክ የለሽ ፣ ታሪክ ከላሽ፣ ጭፍን ተዋሽ የባእድ ተላላኪ ከሚያስመስል "ነባር ጠልነትን" በደፈናው ትርጉሙ ባልተገለጸ "አዲስነት" የመተካትንንየእውር ድንብር ፍልስፍና አአጥሩት፣ አሮጌውንየቱ ነው? ተተኪው አዲስ።ምንድነው?/ለማንና ለምን ይጠቅማል? ሃይማኖታችንን፣ ነባር እሴታችንንህብረታችንን፣ ርስታችንን፣ የተነፈገ ፍትሀችንን እንዴት ያስመልሳል? ብላችሁንጠይቁ፣ መልሱ፣ አጥሩና አጋሩ፣
፭) ከጎሣ ነፃ አውጭ የተዋሳችሁትን ሀሰተኛ ትርክት አምርቶ ከማከፋፈል ልማድ ተቆጠቡ፣ ለሄዱበትም አልጠቀማቸውም፤ ነጻንእናወጣሃለን የሚሉት ተከታይ የግል ቁሳዊንጥቅም።ማሳኪያናንየሥልጣንንመወጣጫ አድርጎ ሚሊዮን ሙት አስታቅፏቸዋልና እምዳይደገም ዋስትናንያለው የትግል ፍኖትና መርህ ትከሉ፣ በአፈቀላጤ አትመሩ፣
፯) የአማራን ሕዝብ በነፍሱ ሳይቀር ለማገልገል የተሰለፈውን ታጋይና ፣ ትግሉን በላቡ ጠብታ ካገኘው ጥሪት ላይ የሚረዳውን ስደተኛ ወገን ሁሉ እንደ ግል መገልገያና መሣሪያ የመቁጠሩን ነውረኛ ብልጣብልጥነት እርም አድርጉት፣ ተጠያቂነትናንግልጸኝነትን በሚገባውንልክ አረጋግጡ፣
፰) እንደ ሂትለሩ ጎብል ሀስትን በመደጋገም "እውነት" ለማስመሰል መጣሩን ተዉት፣ አማራነት መሠረቱ እውነት፣ ፍትህ፣ ሰብአዊነት፣ ታሪክ እክባሪነትና ቅብብሎሽ፣ መስዋእትነትና የሀገር ባለቤትነት፣ ነጻነት እንጂንእንደ ጠላቶቹ ሐሰተኝነት፣ ኢሰብአዊነት፣ ኢፍትሐዊነት፣ ዘራፊነት፣ ርስት ነቀልነት አይደለምና ይህን ክፋት ከመዋስ ሽሹ።
---- የአማራን ትግል በእውነት፣ በፍትህ፣ በክብረ-ሰብእ መአከላዊነት፣ በእውነተኛ መስዋእትነት ቅድስናውን ጠብቃችሁ ለሁሉም ወደሚጠቅም ድል አድርሱት።
ግላዊ ርካሽ ፍተወታችሁን እንቢኝ ብላችሁ ግቱት። ታገሉት። ራስን ሳያሸንፉ ጠላትን ማሸነፍ ድል ሳይሆን ገደል ነው!
አበቃሁ።
ከዛሬ ጀምሮ ለሤረኞች በቀጥታ በአደባባይ ለመከራከርንዝግጁ መሆኔን እያሳወቅሁ ለዝግብየጎጠኞች ሀሜት ምላሽ አልሰጥም። ነገር ግን ቤተክርስቲያንን በሚመለከት ስንኳንስ ጎጠኛ ትጋይ ለምንደኛ ጳጳስም አልመለስምና እግዚአብሔር እንደፈቀደልኝ መጠን ዝም አልልም።
አስተያየቶች