ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ሃይማኖት የለሽ ትግል ጸረ ኦርቶዶስ ለመሆኑ በሃምሳ ዓመታት ተምረናል

ይበቃል! ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ እንዲሉ የበሽታው ምልክት ታይቷልና ሕክምና ያስፈልጋል!!! 

አምላክ የለሾች፣ ሀሰትኞች፣ የባእዳን ዕሳቤ ባሮች የድፕቅኑትን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ የተሰለፈውን ክቡር የሰው ልጅ ሕይወት እየከፈሉ፣ በተቃራኒው ሕይወቱን የሚሰጠውን ማኅበረ-ሰብእ ሃይማኖት፣ እሤት፣ ነባር ትርክት   ከጀርባ ለማጥቃት መሞከር  ከባድብክህደትም ኃጢአትም ነው። 

" ጸረ-ኦርቶዶክስ ካልሆንን ትግል አይሳካም" የሚል  መዝሙር የማነው? መልስ ይፈልጋል። ፶ እና ከዚያም እጥፍ የሆነውን ሕዝብ የእሤትና የማነት ምንጭ የሄነችዋን ኦርቶዶክሳዊት ክርስትና እንደሌለች ቆጥሮ ፖለቲካና ትግል ለማካሄድ ማሤርን ከደርግ፣ ከኦነግ፣ ከወያናና ከድቅል ልጃቸው ከብልጽግና ወንጌሉ ፖለቲካዊ ኦሮሙማ ውጤቱን አጭደናል።  ተምረናል። የአማራንም ተጋድሎ ጠልፎ በጸረ-ኦርቶዶክስ አጀንዳ መበከል ተቀባይነት አይኖረዉም። 

 ይህንን  በአቃፊነት ስም ያልተጻፈውን፣ በተክባር አግልሎ የማያውቀውን አማራነትና ኢትዮጵያዊነት በጠላት በጠለሸ ትርክት እየተመሩ "ሃይማኖታዊ መብቶችን ካነሳን አንድ መሆን አንችልም" የሚል ውሃ  የማያነሳ ማደናገሪያ ከፊት አስቀድመው በኦርቶዶክስ ክርስትና ላይ መርዛቸውን የሚረጩ አንዳንድ ድብቅ ተልእኮ ይዘው ፋኖ ውስጥ የሰረጉትን ወገኖች በጥንቃቄ መመልከትን ችላ አንልም።  
አንድነትህን ያደነቃቀፈው እስልምናና ክርስትና ሳይሆን የሥልጣን ጥምና ጎጠኝነት፣ ሤረኝነትና ራስ ወዳድነት፣ ከዚያንካለፈ ድብቅ የጠላት ተልእኮ፣ ተሸካሚነት ወይንም  ይትግሉን ውስብስብነትና የሚጠይቀውን ጥንቃቄ ያለማወቅ ድንቁርና ሊሆኑ ይችላሉ። 

አማራን እንደ ኮድ አድርጎ ኦርቶዶክስን ለማጥፋት ፶ ዓመት ሙሉ የመጥውን አስተሳሰብ ለማሸነፍ  የሚዋጋው ወገን እንደ ጠላቱ "እግዚአብሔር አያስፈልገኝም፣ የኦርቶዶክስ ንቅናቄ የእማራ ትግል  ጠላት ነው" ለማለት ደፈረ? ይህ መልእክት  መልእክት በዝግ የማኅበራዊ ሚዲያ  ቡድን ሲብላላ ቆይቶ የሚቃወም የለም በሚል ስሌት አደባባይ ወጣ።

በዚህ ጉዳይ ፋኖዎች ትኩረት ሰጥተው መምከር ይኖርባቸዋል። ተሸፋፍነው ቢተኙ የመገላለጥ ሰዓት መኖሯ አይቀርም።  በአማራ ትግል ውስጥ ከሚሳተፉ ሰዎች መካከል በሚከተሉት ደዌ የተለከፈ ከአለ ይመርመር፦
- ጸረ ሰሎሞናዊነት
- ጸረ ኦርቶዶሳዊነት
- ጸረ ኢትዮጽያዊነት
- ጸረ ነባርነትና ታሪክ ክለሳ 
- ጎጠኝነት
- አማራ "ንብረቴ፣ መጠቀሚያዬ፣ የብቻዬ" የሚል የዘር ነጻ አውጭ መንፈስ ቁራኝነት
- ናርሲሲስት #አብይ-ነት ( የበዛ ራስ ወዳድነትና ማን-አህሎኝነት)። 

የዚህ አይነት ደዌኛ ሲገኝ በፍጥነት ከአማራ ታጋዮችና ሕዝብ ለይቶ  በማቆያ መእከል ማከም ይገባዋል። በሽታው ተላላፊና መጨረሻው አሁን አማራ የተጸየፈውን እና የሚዋጋውን  ኢሰብአዉነት፣ ኢፍትሀዊነት፣ ጭፍን መንጋነት እና ስግብግብነት መልሶ  ከጠላቶቹ በመውረስ ከሕወሃትና ኦነግ/ብልጽግና እኩል የሚያዋርድ ነው።

ይህን በዝምታ ማለፍ ለአማራ የሥጋ ህልውናውን ማሳጣት ብቻ ሳይሆን የዘላለም ሕይወቱንም መንጠቅ ይሆናል። በዚህ መንገድ የተጓዙት  ሕወሃትና ኦነግ/ብልጽግና ያስከተሉትን መንጋ ከእምነት አስወጥተው ብሔርተኝነትን በጣዖት ደረጃ ያስመለኩ፣ ሲኖዶስና መጅልስን የጎሣ አገልጋይ ያደረጉ፣ በአድባባይ ይግራዋይነት እና ኦሮሙማ ከሃይማኖት ይበልጣል እስ ከማለት የደረሱ፣ መነኮሳትና ካህናተ  ክትስቶስን በዘር ደልድለውና የክልል ሲኖዶስ ፈጥረው አንደ እካለ-ክርስቶስ ምእመናን በፕሮፓጋንዳ አጨልመው ንጹህ ዘርና ዲቃላ ያሰኙ ጽቋቁርብሂትለሮች ሆነዋል።
 አማራንም "ለህልውናህ" እየታገልኩልህ ነው ብለው ራሳቸውን ለመስዋእትነት ያቀረቡ ወጣቶችን እየማገዱ ከእግዚአብሔር የሚለይ መንገድ ለመውሰድ ማሤር የነውር ነውር፣ የግፍ ሁሉ ግፍ ነውና ኦርቶዶክሳዊንየሆነ ብቻ ሳይሆን ሰው በእምነት መኖርንየሚገባው ፍጡር መሆኑን የሚቀበል ሁሉ ሉቃወመው ይገባል። 

ለሥጋህ ህልውና ቆሜልሃለው፣ ነፍስህ ግን ገሃነም ትግባ የሚል ፋኖ ሱገኝ የአማራ ጠላትብእንጂ ወዳጅ ሊባል አይችልም። እንዲህ አይነት ስውር ጠላቶች ሀሳብን በሀስብ መሞገት ስለማይችሉ ሤራቸውን ሰውረው በስሜታዊ ጉዳዮች ያጭበረብራሉ። ከማጭነርበሪያዎቻቸው መካከል የሚከተሉት የተለመዱ የፋሽቶች ስልቶች ናቸው:-

፩) የተቺውን ደምና አጥንት ቆጥሮ "አንተ በአማራ ጉዳይ ማን ፈትፋች አደረገህ"

፪) አንተ  ለምሳሌ እኔን "ጃል ዋቄ" ነህ

፫) ሃይማኖት ይዘህ አትምጣብን (ትግላችን አምላክ የለሽ እና የጠላቶቻችን አምሳል አራዊታዊ ነው እንደማለት ያል አማራን የማይመስል ክርክር)

፬) እኛ እገሌ የሞባል መሲህ፣ ዐስበን የፈጸምነው  ፍጹም ሀሳብ ስላለን ሌላ ማሰብ አያስፈልገንም፣

፭) አማራ የማያስብ፣ እኛ ብቻ የምናስብለት በእጃችን ያለ ግዑዝ መሣሩያችን ስለሆነ ሌላ መልእክት አታስተላልፉለት

፮) ጥልቃ የምይገቡብን ሥልጣን ፈልጋችሁ፣ እኛን ለመከፋፈልና ለማዳከም ነው ---- ወዘት ይሏችኋል። 

ቁም ነገሩ ይህ አይነት ማደናገሩያን እየሰሙ ጸውስጥ ጠላትን ሤራ እንዳይገለጥ የሚከላከሉ የዋሀን  መብዛት  አደጋውን ማክፋቱ ነው። ከትግራይ ሕዝብን ነጻንላደርጋችሁ ነውንተከተሉኝ ብለው ሀገር አስግንጥለው፣ ሌላውን አናልሰው፣ ሀገሩን ዘርፈውና ሕዝቡን አለያይተው፣ በመጨርሻ ከታላቅ ሀገሩ ይልቅ መንደርንእያሰበ በአውራጃና ወረዳ ይገባኛል የሚገድልና የሚሞት ትውልድ ፈጠሩ፣ መቶ ሽዎች እናቶችን ያለ ልጅ አስቀሩ።
አማራ  ከዚህ ተምሮ ትግሉን ግልጽ በሆነ መርህ፣ እግዚአብሔርንና ክብረ-ሰብእን ማእከል ባደረገ ዕሳቤ  የህልውና ይግሉን ከግብ በማድረስ ለሰው ሁሉንፋይዳ ያለው ሥርዓት ማቆም  ይጠይቃል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

የሐሰት ትርክት ኦነጋውያንና የሕወሃታውያ የጋራ ስልት ከነግሥታት ወደ ተራ ግለሰቦች

✏️ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።  እርሱ ይመስገን። ምድራችንን #በደም #ያጨቀየው $ህሊና #የነሳን ፣ #ልቦናችንን #ያጨለመን ፣ #ሰብእናችንን ያዋረደው:- 👉 የሕወሐታውያንናንየኦነጋውያን የንዑስ ማንነት የጎሣ ፖለቲካ የደንቆሮ ርእዮትና፣ 👉 መርዛማን ጥላቻን ለ፶ ዘመናት ያከፋፈሉት የሐሰት ትርክት ናቸው። ✏️እንደ ዳግማዊ #ምንልክ ያሉ   ከዋክብት መሪዎች፣ እንደራሴቻቸው፣ ደጃዝማቾችና ቀኝና ግራ አዝማቾቻቸው  ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ብዙ ውለታ ውለውልናል:- 👉 በዘመነ ኦቶማንና አውሮፓ፣ በዘመነ መሳፍንት የተበታተነውን እና የተቆነጻጸለውን፣ ጎሠኛ የአርብቶ አደሮች  መሬት ፍለጋ  የደመሰሱትን ክርስቲያናዊ የግዕዝ/የነፃነት ሥልጣኔ አሻራ እንዲያገግም ደክመውልናል፤ 👉 የጥንት አገርን እና ሕዝቦችን   በከፊልም ቢሆን በመሰብሰብ  ጠንካራና ብቸኛ የነጭ ቅኝነትንና ባርነትን በመከላከል፣ ከኦቶማን ቱርክ ወር ትናንት ውስጥ ጥረኛ  አህመድ ግራኝ በመጋደል  ልዩ የነጻነት ማንነት ያላትን አገር ብበቸኝነት በዓለም ካርታንላይ አቆይተዋል፤ 👉 የሬማ ግዛት በጎሣ ተብልቶ ፲ ትንንሽ ሲሆን ከበበባውን ተቋቁማ በዝኃነታችን በተመጋጋቢ አንድነት ከ፹ በላይብቋንቋ፣ ከዓለም ትልልቅ እምነቶች ክትስትናን ፣ ይሁዲን፣ እስልምናን፣ የእረማውያንን ቅሪት የሆኑ የባህል እምነቶችን ሁሉን ይዛ በአውሮፓ በአርብ አምሳል ሳትሠራ ለእኛ አቀብዋል፤ 👉 ወያኔና ኦነግ፣ ገንጣዩ ሻዕብያ፣ ከሃዲው የማርክሲስት የአእምሮ  ባሪያን ስብስብ  እስኪፈትናት ድረስ ራሷን የቻለች አገር እንድንፈጥር ያስተባበሩን ነገስታት የተመሰገኑ ናቸው። አገር ሲያረጅ ጃርት ያብቅላል እንዱሉ: መል...