#ከሰው #ልጅ #ክብር #የሚበልጥ #ልማት አለ ከተባለ "የሞት ዕፀ-በለስን የሕይወት መደኃኒት ነው" በማለት ተንኮል ምንም ስለ ሤራ የማያውቁትን የዋሐንን አዳምንና ሔዋንን አታልሎ #ሞትን ካስታቀፍው #ከሳጥንኤል እና #ከብልጽግና #ወንጌል #መንግሥት በስተቀር ማንም ጥቅሙን አያውቅም። ========================== #የብልጽግና #ወንጌል #ሃይማኖታዊ #መንግሥት ማኅቀፈ-ዕሳቤ (worldview) ይገርመኛል። የዚህ ሥርዓት መሪና አጃቢዎቹም ሆኑ ወላጆቹ ሕወሃትና ኦነግ፤ አዋላጆቹ ደግሞ ዉሀብያ፣ ተርፈ ናዚዎቹ፣ ጡጦ አጥቢዎቹ ባዕዳን እንደመሩት 👉 ሞትን ሕይወት፣ 👉 መፍናቀልን እደገት፣ 👉 መፍረስን ከፍታ፣ 👉 መለያየትን ነጻነት፣ 👉 ጦርነትን ሕግ ማስከበር፣ 👉 እልቂትን abnormal-normal (በአብይ አህመድ አሊ በፓርላማ የተነገር ነውር)፣ 👉 የታሪክ ንቅለ ተከላን ታላቁ ትርክት፣ 👉 ሲኖዶስን ወደ ጎሣ ምክር ቤት ማውርድን አካታችነት፣ ---- በሚል የሚተረጉም ከሰውልጅ ህሊና ፈልቆ ለሰው ልጆች ጥቅም የተደረገ ነው ለማለት የማያስችል ጸረ-ሰብእ ትርጓሜ በመስጠት የመከራ ሥርዓትን የሚመራ ነው። ሰማይ የተሰቀለለትን፣ ምድር የተዘረጋለትን ክቡር አዳማዊ ፍጡር #እያረዱና #እያሳደዱ ---- ያለ ሁፍረት በሬሳ ላይ ቆሞ፣ ደም ውስጥ እየዋኘ፣ በሚገፉት ወገኖቻችን ዕንባ እየታጠበ ------ --- #ስንዴ፣ #ግድብ፣ #ወደብ፣ #ችግኝ፣ #ኮሪደር ልማት፣ ...
This is a spot where I post and share part of my daily reality. I would love to hear from others too to learn how differently we interpret daily encounters including our imaginations. ይህ ሥፍራ የየዕለት ገጠመኞቼን፣ እንዴት በዕለቱ እንደተረደሁትና የማስበውን ለሌሎች ያማጋራበት ነው፡፡ የሌሎችን በመስማትና ምን ያህል ዓለማችንን በተለያየ መንገድ እንደምንመለከታት ለመማር እጓጓለሁ፡፡