✏️ እግዚአብሔር ይስጥልኝ። እርሱ ይመስገን።
ምድራችንን #በደም #ያጨቀየው $ህሊና #የነሳን፣ #ልቦናችንን #ያጨለመን፣ #ሰብእናችንን ያዋረደው:-
👉 የሕወሐታውያንናንየኦነጋውያን የንዑስ ማንነት የጎሣ ፖለቲካ የደንቆሮ ርእዮትና፣
👉 መርዛማን ጥላቻን ለ፶ ዘመናት ያከፋፈሉት የሐሰት ትርክት ናቸው።
✏️እንደ ዳግማዊ #ምንልክ ያሉ ከዋክብት መሪዎች፣ እንደራሴቻቸው፣ ደጃዝማቾችና ቀኝና ግራ አዝማቾቻቸው ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ብዙ ውለታ ውለውልናል:-
👉 በዘመነ ኦቶማንና አውሮፓ፣ በዘመነ መሳፍንት የተበታተነውን እና የተቆነጻጸለውን፣ ጎሠኛ የአርብቶ አደሮች መሬት ፍለጋ የደመሰሱትን ክርስቲያናዊ የግዕዝ/የነፃነት ሥልጣኔ አሻራ እንዲያገግም ደክመውልናል፤
👉 የጥንት አገርን እና ሕዝቦችን በከፊልም ቢሆን በመሰብሰብ ጠንካራና ብቸኛ የነጭ ቅኝነትንና ባርነትን በመከላከል፣ ከኦቶማን ቱርክ ወር ትናንት ውስጥ ጥረኛ አህመድ ግራኝ በመጋደል ልዩ የነጻነት ማንነት ያላትን አገር ብበቸኝነት በዓለም ካርታንላይ አቆይተዋል፤
👉 የሬማ ግዛት በጎሣ ተብልቶ ፲ ትንንሽ ሲሆን ከበበባውን ተቋቁማ በዝኃነታችን በተመጋጋቢ አንድነት ከ፹ በላይብቋንቋ፣ ከዓለም ትልልቅ እምነቶች ክትስትናን ፣ ይሁዲን፣ እስልምናን፣ የእረማውያንን ቅሪት የሆኑ የባህል እምነቶችን ሁሉን ይዛ በአውሮፓ በአርብ አምሳል ሳትሠራ ለእኛ አቀብዋል፤
👉 ወያኔና ኦነግ፣ ገንጣዩ ሻዕብያ፣ ከሃዲው የማርክሲስት የአእምሮ ባሪያን ስብስብ እስኪፈትናት ድረስ ራሷን የቻለች አገር እንድንፈጥር ያስተባበሩን ነገስታት የተመሰገኑ ናቸው።
አገር ሲያረጅ ጃርት ያብቅላል እንዱሉ:
መልስ ዜናዊ፣ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም፣ አብይ አህመድ፣ ኢስያያስ አፈወርቂ፣ ሽመልስ አብዲሳ፣ ስብሃት ነጋ፣ እነዚህ የሚጭኗቸው የአማራናንየሌሎች ክልሎች መሪዎችን ወበቀለች።
ከጻፊዎችም እነ አጼዎቹ፣ ክህነት ያገነነው አጼ፣ የታሪክ ንቅለ ተከላ፣ የኩሽ ሕዝቦች ወዘተ በራሱ ሐሰት ቄስሎ የሚያመረቅዝ የቆሰለ ስነ ልቦና በሚመራው አእምሮ መርዝን ለሀገር ልጅ የሚመግቡ ጸሐፊዎች ተፈጠሩ።
✏️ዛሬ የያኔው የቀደሙት አባትብእናቶቻችን ወራሪ የነጭ ባርነትና የኦቶማን ጂሃዳዊ ቅኝነት መከላከል መቻላቸው የሚያናድዳቸው ባእዳንን በመወከል----
👉 አንድም የእነዚያ ወራሪዎች ባርነት ለምን ቀረብን፣ ለምን ኦሮሞን በኬንያ በኩል እንግሊዝ፣ በሶማሌ በኩል ጣልያን፣ በጅቡቲ ፈረንሳይ ተካፍሎ ባሪያ አላደረገውም?
👉 ለምን ነባሩ እስልምና እና ክርስትና ጠፍተው የአውሮፓ ፕሮቴስታንት ወይንም ካቶሊክ ወይንም ጣኤት፣ ወይንም ዉሀብያ ጽንፈኛ አልሆንም?
👉ለምን ቋንቋና ባህላችን ተጠብቆ ቆየ?
ለምን የሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን አካል ሆነን ተገኘን? ---- ወዘተ የሚሉ --- ኦነጋውያንን ፕሮፓጋንዳ ታጥቀው ነገሥታትን በተሸናፊዎቹ አውሮፓውያንና ኦቶማን ቱርኮች ተወክለው ማጠልሸት የተለመደና ደም እያፈሰሰ የሚገኝ መሆኑን እናውቃለን።
✏️ ይሁንና #በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ውስጥ #መሽጎና በእርሷ ስም እየተጠቀመ የኦነጋውያንን ሰይጣናዊ ትርክት #ቅዱስ #የሲኖዶስ መልክ እስከማልበስ የደረሱ፣ ስለ ዘላለማዊት ነፍሳቸው ከመጨነቅ ይልቅ ለግዜአዊ የሥጋ ጥቅም ሲሉ ክርስቶስን እና ቅዱሳኑን በጎሣ ለመካፈል የሚደክሙትን ወንድሞቼን እባካችሁ ለሚያልፍ ፖለቲካ የማያልፍ ሕይወት #ክርስቶስ #አትለዩአት
እላለሁ።
✏️ ዛሬ ደግሞ የምታጠለሹትን ታላላቅ ሰው ፈጽማችው ጨርሳችሁ ብታጡ፣ ከምታጠለሹት የባህልና የእምነት ወገን ዘርን የማጥፋት ድርጊት ውስጥ መገኘታችሁ አላረካችሁምና ይህን ነውራችሁንና ድብቅ ዘር የመጥፋት አጀንዳችሁን የሚናገርባችሁ ሰው እንዳይኖር ነው መሰለኝ ወደ እኔ ወደ ትንሹና አላዋቂ ሰው ወደ #ፋንታሁን #ዋቄ ዞራችሁ።
✏️ እኔ ለክርስቲያኖች ይጠቅማል የምለውን የግል ምልከታዬን የማጋራ፣ የጭፍን የዘረኞች ቡድንን የምቃወም ሰው ነኝ።
✏️ ይህ የእኔ ምርጫ እንዳልተስማማችሁ አውቃለሁ። እኔ ምርጫ ከክርስቶሳዊነት የሚበልጥ ዘር ባለመኖሩ እርሱን መረጥኩ። እናንተ ደግሞ እንደ ናዚ ተከታዮች ፖለቲካ-ሠራሽ የኦሮሚማ ጣዖት አቁማችሁ አዲስ እና ከሊቀካህን ክርስቶስ ክህነት የማይፈልግ የሞት ካህን በጎሣ #ክህነት ወደ ደሞት ልትመሩን ተነሳችሁ።
አይሆንም ብያለሁ! ጆሮ ያለው ይስማ። ስድብና ሐስትን እመንጭቶ ማከፋፈል የላኪዎቻችሁ እና የኦነጋውይን ስለሆነ #ዝም #አልልም!!
እግዚአብሔር ይመስገን ያልኩት ከአቅሜ በላይ ከፍ አድርጋችሁ ነግሥታቱን እና ቤተ ክርስቲያናችንን በምታጠቁሩበት አንደበታችሁ እኔንም ለማስባረክ ስለምትሠሩ። አመሰግናለሁ።
ሳስበው ለመሆኑ
✏️ ለመሆኑ የትኛው የእኔ መልእክት ይሆን እንቅልፍ የነሳችሁ?
እኔ ስገምት 👉 ይህ ይመስለኛል ያቃጠላችሁ። ነው ሌላም አለ? ከሆነ እስቲ #በጥናትና #በመረጃ #ተከራከሩ
https://ethiopiaorthodoxchristian.blogspot.com/2025/03/blog-post_14.html
እውነት ስለሆነ ተቃጠላችሁ አይደል? ከመቃጠል ንስሐ ገብቶ መመለስ ብልህነት ነው።
ይህ ካልሆነ በዚሁ የብሎግ ገጽ ስለ እናንተ ብዙ ብያለሁና ያመለጣችሁን እያነበባችሁ ስደቡኝ። ለበረከት ይሆነኛል።
✏️ ድሮ ድሮ የጎሣ ነጻ አውጭዎቻችሁ በሐሰት ትርክታቸው የሚያጠለሹትና ሐሰታቸውን እውነት ለማድረግ ሲሉ ሩቅ ሄደው :-
👉ሺ መጽሐፍት፣ ሺ ጆርናል ከጀርመን ተረፈ-ናዚ እስከ ጽንፈኛው ዉሀብያ ጸሐፊዎች እንዳሰለፉ እናውቃለን።
👉 ከሐረር ከተማና ጨለንቆ ሎላ እስከ አኖሌ ለደም ማፍሰስናንሀገር ለማፍረስ ሐውልት እንደተከሉ እናውቃለን።
👉 የሰውን የማኅበረስብ ምስክርነት በአሰፋፈር ለመደምሰስ እልቂት እየፈጸሙ እንደሆነ በዓይናችን እያየን እና በየቤተሰቦቻችን ዋጋ እየከፈልንበት ነው።
እኔ እንኳ በግሌ አያቴን #ወ/ሮ ሙሉ ነሽ በለጠ ጉደታን እና ልጇን አጎቴን #ሽፈታው የተስፋዬን፣ እነ #ሚሊዮን በትሩ ግዛውን፣ #ለገሰ እበበን፣ #በቀለ አክሊሉን፣ እና ሎሌችን በደጃቸው በሕወሃት ፈቃድና አመቻችነት፣ በቤታቸው ውስጥ በኦነግ ታርደው፣ ገሚሱ እስከነ ነፍሳቸው ወደገደል ተጥለው ሞተዋል።
፴፰ ዓመት ሥልጣን ላይ ያለው ኦነጋዊ የኦፒዲኦ/ብልጽግና ፍትሕ ነፍጎን እንኖራለን እና ምስክር ነኝ።
👉 ቤተ ክርስቲያንን ለማዋረድ፣ የክህነትን ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ለመበጠስና ከእግዚአብሔር መንግሥት ለይቶን የዘለዓለም ሞትን ለማንገስ ሲል አቅዶና አልሞ #በኦሮምያ #ክልላዊ #መንግሥት ምሪት፣ በአብይ አህመድ ትዕዛዝ ሰጭነት፣ በእነ ዳንኤል ክብረት አማካሪነት፣ በሣዊሮስ፣ ዜና ማርቆስና ኤዎስታጤዎስ ተላላኪነት በወሊሶ የጎሣ ሲኖዶስ ፈጥረው ደም እንዳፈሰሱ እናውቃለን።
👉 እነዚሁ ክህነትን ለፖለቲካ፣ ለዚያውም ለደም አፍሳሽ እና ከፋፋይ ፖለቲካ በማደር ያለአንዳች መሰቀቅና መፍራት "#እኛና #መንፈስ #ቅዱስ ወስነናል" በማለት ያለ አንዳች ሀፍረት በድፍረት የአብይ አህመድንና የሽመልስን አብዲሳን ውሳኔ "የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ውሳኔ ነው" በማለት በዘር ፖለቲካ ትርክት ፶ ዓመታት የናወዘውን የኦሮሞ ወጣት ጣዖት ሊያስመልኩት ሞከሩ።
👉 የዘር ጳጳሳት ይህ ውሳኔ ቤተክርስቲያንን የናጠ፣ በሠራዊት ታጅቦ ፶ የጥምቀት ልጆችንና ካህናትን ያሳረደ ንቅናቄ መሆኑን እናውቃለን።
✏️ ይህ ሁሉ የሚሆነው ሐስትን እውነት፣ ርኲሰትን ጽድቅ፣ ብርሃንን ጨለማ ለማድረግ እኛን ክርስቲያኖችን ከሚፋለመን ከዲያብሎስ ሥራ መሆኑን እናውቃለን።
✏️ሰው በፈቃዱ ከእግዚአብሔር ተለይቶ ለጠላታች አገልጋይና ማኅደር ይሆናል።
✏️ የአገርን ትርክት በሐሰት ትርክት በመገልበጥ ተሰሚነት ለማግኘት እና የኦሮሞን ሕዝብ ከግዕዝ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከኦርቶዶክስ፣ ከጋራ ታሪክ ነጥሎ እነ ባሮን ፕሮችስካና ሄንሪ ኪሲንጀር እስከ ኸርመን ኮኸንና ማይክ ሐመር የተዘረጋውን የጥፋት ጉንገን ስታደሩ እናውቃለን።
✏️ እነዚህን በባርነት ያገለገል የጎሣ ነጻ አውጭ ምሁር፣ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ቀኖና እና ትውፊት ተጠቅሶ በጎሣ ልትከፈል እንደምትችል ለማጥናት የነገረ መለኮት ትምህርት ቤት ገብተው የብሔረስብ ሲኖዶስ ለመፍጠርና የሐሰት ትርክት ለመገልበጥ ዶክተር የሚሆን፣ የቲዎሎጂ ተማሪ የሚሆኑ ሰዎችን አውቃለሁ።
በክርስቶስ ስም ያላችሁ ንስሐ ግቡ፣ የዘር ጣዖትን ተጸየፉት።

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ