ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ኢትዮጵያን የሚመጥን መሪ ለመፍጠር መስፈርት ላይ ሀሳብ እናዋጣ!

ኢትዮጵያን የሚመጥን መሪ ለመፍጠር መስፈርት ላይ ሀሳብ እናዋጣ!

በሰው ደም ካልታጠቡ፣ በዜጎች ዕንባ ካልዋኙ አየር የተነፈሱ የማይመስላቸው  ድውያነ አእምሮ፣ የክፋት አበጋዞች፣ የሐሰት ምንጮች፣ የሤራ መሀንዲሶች እና የቁማር ሱሰኞች ዳግም እንዳይነዱን ከፈለግን ከጭፍን መንጋነትንወጥተን እናስብ!!!

እኔ ለማስጀመር እንዱህ ብያለሁ። እናንተስ?
👉 በነፍሱም በሥጋውም ርኲሰትን የሚጸየፍ፣ ውድቀት ሱያጋጥመው መልሶ በንስሐ የሚታደስብትሁት

👉 ሐቀኛ፦ ለፍትሕ እና ለእውነት የሚኖር፣ ሤራና ቁማርተኝነትን፣ በዜጎች መካከል እድልዎን የሚጸየፍ ደግ አባት/እናት

👉 የህፕገሩቷን የሺ ዘመናት ታሪክ አመዱን ከፍሙንለይቶ ለዛሬ ትውልድ ሙቀትና ከፍታ ወደ ሞተር የሚቀይት፣ የሐሰት ትርክትን፣ ታሪካዊ ጠባሳዎችን አጣምሮ እያጋነነ ለዜጎች ተዋህዶ እንቅፋት የማያኖር፣ የሚከላከል

👉 በሀገሩ ልጆች አእምሮ፣ ጥረትኔ ምክር የሚተማመን፣ የባዕዳን አሻንጉሊትና ተላላኪ ያልሆነ

👉 የቀጠናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም ዐቀፋዊ አውዱ ንባብና በሀገሩ ላይ ያለውን  አዎንታዊና አሉታዊ ተጽእኖ ተረድቶ ለሀገር ጥቅም በሁሉም ደረጃ  አመራር እንዲኖረን ስልት መንደፍና መተግበር የሚችል አቅም ያለው፣ እንደ ስድ አደግ ባለጌ ጎሮምሳ ዘለቄታዊነትንየሌለው ግኑኝነት የማፕፈጥር

👉 በጎረቤት ሀገራት መካከል ሰላም ለምስፈን ክሂሎትና ጥበብ ያለው፣ ያሉትን መልካም አጋጣሚዎች የሚጠቀም ብቻ ሳይሆን የሚፈጥር

👉 በሀገር ውስጥ ያሉትን ብዝኃ እምነቶችና ባህሎች። የስነ ምህዳር ብዝኃነት፣ የትፈጥሮ ህብት ብዝኃነትን ሁሉ ለግጭትና ለሽሚያ ያይደለ ለጉድለት መሞላላትና ሕብረታዊንየሕይወት አንድነት እንደ ተቃራኒ ጾታ ተዋህዶ ለፍሬ መምራት የሚችል

👉  ከሀሉ በላይ ክንረ-ሰብእ፣ ክብረ-ሀገር፣ ክብረ፣ ነባርብእሤትና ታሪክ ላይ ቅሚያ የሚሰጥ፣ ጎጠኝነትና ዘረኝነት፣ ሌብነትማ ብልጣብልጥነትን የሚጸየፍ

👉 የሀገሩን ጥበብና እውቀት በመዋቅሬዊ።መንግድ የሚያለማ፣ ሁለገብ የሀገር ጥገኝነትን የሚከላከል

👉 ለእህዚአብሔርና ለሚመራው ሕዝብ ተጠሪና በእረኝነት ተላልፎ የሚሰጥ፤ የማዘዣ ክፍልና የስለላ መዋቅር ተጠቅሞ ዜጎቹን ለጦርነትና ለግጭት  የማያሰልፍ ሰላም ወዳድ

👉 ለጋስና ስለ ዜጎዥ ፍትሕፕዊ ከሀብት ክፍፍል የሚገደው፣ ከሙስናና ሌብነት ጋር ግልፅ ጦርነት የሚያካሄድ

👉 ለሀገራችን ወዳጅ የሚያበዛ ዲፕሎማሲና ትስስር የመፍጥር አቅም ያለው፤ ጠላት የሚቀንስ፣ እንደተናካሽ እብድ ውሻ ሁሉን የማይለክፍና ተለዋዋጭ ያልሆነ

👉 መሪነቱን ለተሻሉ አእምሮዎች የሙያጋራ፣ አግባብነቱ በሌሎች ብልጫ እንደተወስደበት ሲመለከት ሥልጣኑን አስረክቦ በትህትና በአማካሪነት ለመሥራት በጎ ፈቃድ ያለው፣ ሥልጣን ላይ ለመቆየት በምርጫ ስም የማያጭበረብር፣ የሚበልጡትን ወገኖቹን እንደ ጠላት ፈርጆ የማያሳድድ የዋህ ቤተስብእ

👉 ማኬቬሉያዊ የደም እርካብና መንበርን የሚጸይፍ የእውነት ሰው

በሰው ደም ካልታጠቡ፣ በዜጎች ዕንባ ካልዋኙ አየር የተነፈሱ የማይመስላቸው  ድውያነ አእምሮ፣ የክፋት አበጋዞች፣ የሐሰት ምንጮች፣ የሤራ መሀንዲሶች እና የቁማር ሱሰኞች ዳግም እንዳይነዱን ከፈለግን ከጭፍን መንጋነትንወጥተን እናስብ!!!

አስተያየቶች

አስተያየት ይለጥፉ

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

የሐሰት ትርክት ኦነጋውያንና የሕወሃታውያ የጋራ ስልት ከነግሥታት ወደ ተራ ግለሰቦች

✏️ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።  እርሱ ይመስገን። ምድራችንን #በደም #ያጨቀየው $ህሊና #የነሳን ፣ #ልቦናችንን #ያጨለመን ፣ #ሰብእናችንን ያዋረደው:- 👉 የሕወሐታውያንናንየኦነጋውያን የንዑስ ማንነት የጎሣ ፖለቲካ የደንቆሮ ርእዮትና፣ 👉 መርዛማን ጥላቻን ለ፶ ዘመናት ያከፋፈሉት የሐሰት ትርክት ናቸው። ✏️እንደ ዳግማዊ #ምንልክ ያሉ   ከዋክብት መሪዎች፣ እንደራሴቻቸው፣ ደጃዝማቾችና ቀኝና ግራ አዝማቾቻቸው  ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ብዙ ውለታ ውለውልናል:- 👉 በዘመነ ኦቶማንና አውሮፓ፣ በዘመነ መሳፍንት የተበታተነውን እና የተቆነጻጸለውን፣ ጎሠኛ የአርብቶ አደሮች  መሬት ፍለጋ  የደመሰሱትን ክርስቲያናዊ የግዕዝ/የነፃነት ሥልጣኔ አሻራ እንዲያገግም ደክመውልናል፤ 👉 የጥንት አገርን እና ሕዝቦችን   በከፊልም ቢሆን በመሰብሰብ  ጠንካራና ብቸኛ የነጭ ቅኝነትንና ባርነትን በመከላከል፣ ከኦቶማን ቱርክ ወር ትናንት ውስጥ ጥረኛ  አህመድ ግራኝ በመጋደል  ልዩ የነጻነት ማንነት ያላትን አገር ብበቸኝነት በዓለም ካርታንላይ አቆይተዋል፤ 👉 የሬማ ግዛት በጎሣ ተብልቶ ፲ ትንንሽ ሲሆን ከበበባውን ተቋቁማ በዝኃነታችን በተመጋጋቢ አንድነት ከ፹ በላይብቋንቋ፣ ከዓለም ትልልቅ እምነቶች ክትስትናን ፣ ይሁዲን፣ እስልምናን፣ የእረማውያንን ቅሪት የሆኑ የባህል እምነቶችን ሁሉን ይዛ በአውሮፓ በአርብ አምሳል ሳትሠራ ለእኛ አቀብዋል፤ 👉 ወያኔና ኦነግ፣ ገንጣዩ ሻዕብያ፣ ከሃዲው የማርክሲስት የአእምሮ  ባሪያን ስብስብ  እስኪፈትናት ድረስ ራሷን የቻለች አገር እንድንፈጥር ያስተባበሩን ነገስታት የተመሰገኑ ናቸው። አገር ሲያረጅ ጃርት ያብቅላል እንዱሉ: መል...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩. ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡  በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡  ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በቋንቋ መ...

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...