#በፋኖነት ውስጥ እንክርዳድ እንዴት በቀለ? ማን ዘራው?
#አማራ ንቃ! ጠላቶችህ በሥጋህ እየገደሉህ ነው፣ ከዚህ ለመዳን በመስዋእትነትህ ምላሽ እየሰጠህ ነው፤
ግና ከጉያህ ተሸጉጠው በነፍስ ሊገድሉህ በክርስትናህና የተቀደሰው ታሪክህ ላይ የሚደራደሩ እጅግ እጅግ ጥቂት የአረሞች ምልክት እየታየ ነው።
=======================
#አማራ የሥጋን ሞት እየተዋጋህ የነፍስን ሞት በጓሮ በር የሚያስገቡ ድውያነ አእምሮ ሰርጎ ገቦች የጠላት ሰይጣንን ፍላጎት ያስቀደመ፣ የትግሉን መርህና ዕሳቤ የሚከልስ ሂደት ብቅ ብቅ እያለ ነው።
ነገር ግን ---
እግዚአብሔር ይመስገን። እንኳንስ ሳይረፍድና አረሙ ፍሬ እፍርቶ ሳይረጭ ተገለጠ።
የማረሙ ኃላፉነት በሁሉም ክርስቲያኖች ጫንቃ ነው። በእርግጥ ከቤተ ክህነቱ ምንደኛ የብልጽግና መንግሥት አውዳሾች ምንም አይጠበቅም።
============
#አማራ
ዋጋ የምትከፍልለት ተጋድሎህ ለሥጋዊ ህልውናህ ብቻ ሳይሆን ለዘላለማዊ ሕይወትም ዋጋ ያለው የሙሉ ሰብእና ማሳያ ይሁን! ዛሬን ከሥጋ ሞት ለመዳን ስትል እምነትህን በስልት ሊያስጥሉህ፣ ሊከፋፍሉህ፣ የሥልጣን መወጣጫ እርካብን በደምህና በአጥንትህ ሊያቆሙ ከሚሯሯጡ ግለኞች ራስህን ጠብቅ።
የባእዳን ዕሳቤና ፖለቲካዊ ርእዮት ወራሽ የሆኑ ጥቂት የሳቱ ልጆችህ በረቀቀ መንገድ በክርስትህና ነባር ታሪክህ ላይ በራስህ መስዋእትነት ጥፋት ለማድረስ ተልእኮ ተቀብለው ከአድዋ እስከ ብልጽግና ወንጌል ያልተሳካውን የጠላት ዓላማ ሊያሳኩ እየሞከሩ ነው! ንቃ!!!
================
#አማራ!
የህለውናህ ታጋዮችህን ደም ከንቱ የሚያደርጉ ጸረ ክረስትና ቡድኖች በታጋዮቹ መካከል ተመድበዋል።
የአድዋ የውርደት ቁስላቸውን ለመቶ ዓመመታት እያከኩ የበቀል በትራቸውን በማይጨው የጋዝ መርዝ የጀመሩት፣ ቀጥለውም በአገር በቀል የስኳላ ደንቆሮዎች በኩል ጥቃቱን ከዛሬ አድርሰው በ #አብይብ አህመድና ሕወሃት በኩል ጥቃታቸውን አጠናክረውና አስፋፍተው ቀጥለውበታል :-
ጥቂቶቹን የጥቃት መገለጫዎች ለማስታወስ ያህል:-
፩) በግርማሜና መንገሥቱ ንዋይ
፪) በዋለልኝ መኮንንና የ፷ዎቹ ተማሪዎች
፫) በደርግ
፬) በጀበሀና በሻዕብያ
፭) በወያኔ፣ ኦነግ፣ ኦበነግ፣ ሲነግን ወዘተ
፮) በኢሕአዴግና ድቅል ልጁ የብልጽግና ወንጌል
፯) በእርዳታና ልማት ድርጅቶች በልማት ሽፋን ጥገኝነትን በመፍጠር አና ትውልዱን ከኦርቶዶክሳዊና ነባር ኢትዮጵያዊነት ማነሸራተት
፰) የጀርመን ክርስትና አራማጆች የኩሽና ሴም ትርክት ፈልሳፊና ዘር የማጥፋት ፕሮጀክት ገፊዎች
፱) ኢአማንያን ጳጳሳትና ተሐድሶ መናፍቃን ሲኖዶሱን ከቅድስና ማስወጣት
፲) በዓለም ባንክ፣ በዓለም የገንዘብ ድርጅት፣ በዓለም የንግድ እና ሌሎች ዓለም ዐቀፍ ተቋማት በኩል በሚደደረግ ረቂቅ ጥቃት ሁሉ ተደጋግፈው ቀጥለዋል።
መረሳት የሌለበት ቁልፍ ጉዳይ :-
አማራነነት፣ ኦርቶዶክሳዊነነት፣ ነባር እሤቶቻችን እና ትርክቶቻችን ላይ የቆመውን ኢትዮጵያዊነት በመሸርሸርና በማዳከም ፻ ዘመን ተጉዘናል።
ከ፶ ዓመታት ወዲህ ግን ጥቃቱ በሀገር ልጆች ውክለና እየተጠናከረ ሄዶ #በአብይ አህመድ የብልጽግና ወንጌል አስተባባሪነትና መሪነት፣ በወያኔ መሰሪ አመቻችነት
* ኦነነግ/ኦሮሙማ፣
* ኦሮ-ዉሀቢዝም፣
* ኦሮ-ናዚዝም፣
* ዋቂፈታ (ሀሰተኛ ትርክት አምራች፣ መጽሐፍ ቅዱስ ቀያሪ የናዚ ክርስትና አቀንቃኞች የግንቢ ሆስፒታሉ አረም)፣ የሞተ ጣዖት አመልኮን ትንሳኤ የሚመኘው የኦፒዲኦ/ኦነግ ፖለቲካዊ ዋቂፈታ)
ሁሉ በአማራነት፣ በኦርቶዶክሳዊነት፣ በነባር እስልምና፣ በኢትዮጵያዊነት ላይ በግልጽ ጥቃት እየፈጸሙ ነው። ጥቃቱ ከሚገለጽባቸው ብዙ ዘርፎች መካከል የአማራን ሕዝብብዒላማ አድርጎ ማጥፋት ወይንም በቁጥር ማሳነስ፣ በእሤትና እምነት ከነባርነቱ መንቀል ነው።
ለዚህ ሁሉ ጥቃት መሰወሪያ አማራ የተባለውን ሕዝብ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ለኦርቶዶክሳዊነትና ለኢትዮጵያዊነት ማጥቂያ ኮድ/ጠልሰም አድርገው ዘር የማጥፋቱን ፕሮጀክት በአደባባይ ግልጽ በማድረጋቸው ምክንያት ለዘመናት በዝምታ መከራንየኖረው አማራ ተስፋንጥሮ ፏነነ።።
ይህን ጥፋትም ለመመከት ---- #ፋኖ ዳግም #ተወለደ።
የመጀምሪያው ፋኖ የአውሮፓን ወራሪ ሊፋለም፣ ሁለተኛው ፋኖ የተሸናፊውንየባእድ ወራሪ መንፈስ ወራሽ የሆነውን ሀገር በቀልና ዘር አጥፊ ርእዮት የተሸከሙትን ሊፋለም ነው።
በዚህ መሠረት :-
#ፋኖ የተወለደው አማራን በሥጋን ታድጎ በነፍስ ሊገድለው አልነበረም!!
#ፋኖ የተወለደው አማራን ከነባር ትርክቱና እምነቱ ለይቶ ጠላቶቹ ለ፸ ዓመታት የደከሙለትን ኦርቶዶክሳዊነትን የመደምሰስ ጦርነት በአማራ የህልውና ትግል ሥር ተደብቆ ለማሳካትም አይደለም!!
#ፋኖ ሰሎሞናዊ ትርክትንና ታሪክን ከኢትዮጵያንለመፋቅ በባእዳን የጸረ አማራ፣ የጸረ ኦርቶዶክሳዊ ክርስትናና ነባር ኢትዮጵያዊነት ላይ የተጀመሩትን ፕሮጀክት በራሱ በአማራ ደም ለማሳካት አይደለም!!
#ፋኖ የተወለደው እምነትን ሳይጥሉ በባእዳን አስተሳሰብ በተበከሉ የክርስትና ጠላቶችን ማሸነፍ፣ በሃይማኖት ጸንቶ መሞት በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ መዐዛ ያለው የክርስቲያኖች የሰምዕትነት ሕይወት መሆኑን የሚያውቅ እንጂ፣ እምነቱን በትግሉ ስም ለመደምሰስና በአምላክ የለሽ የሕወሃትና ኦነግ "የብሔርተኝነት" ቀመር አማራን ከስውነት ወደ ቡድን ባርነት ለማውረድ አይደለም።
እናም አሁን #በፋኖ ውስጥ በውጭም በሀገር ውስጥም ተቀናጅቶ ጸረ- ኦርቶዶክስና ጸረ-ነባር እሤት ርዮትን የሚያራምደው ጥቂት ቡድን እንዴት ራሱን ቀና አድርጎ የቤተክርስቲያንን ዓላምና ተልእኮ ለመገዳደር ደፈረ?
ይህ ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ ተጋልጦ መላው ታጋይ እንዲያውቀውና ከመካከሉ እንዲያርመው መደረግ አለበት። መረጃዎችን የበለጠ አጋሩኝና ማጋለጡን ልቀጥል።
አሁን ትኩረት የሚፈልግ ጉዳይ በፋኖ ውስጥ እየታየ ነው። እርሱም #የኦርቶዶክስ #ክርስትና #ጸር ርእዮት ያነገቡ የፋኖ አመራሮችና የሀሳብ መሪነትን ለመቆጣጠር ሀገራዊና ዓለም ዐቀፋዊ የጎጥና የኑፋቄ እምነት መረብ ዘርግተው እየተንቀሳቀሱ ነው።
ዝንባሌያቸውን ለማወቅ ለሚፈልግ በንግግሮቻቸው ሁሉ
ሊብራል
ተራማጅ
የአዲስ ሀሳብ ባለቤት
የአዲስንትውልድ ልዩ አመራር አስፈላጊነት
የነባር ትርክት ኋላቀርነት
----
ወዘተ በሚል ---
ከግርማሜ ንዋይና ዋለልኝ መኮንን ጸረ ነባር "የአዲሲቷ ኢትዮጵያ" መርዛማ ህልም የተጨለፈ ቃናንይታይባቸዋል። በተግባር ያንኑ መርዛማ ዕሳቤ ያስቀጠለ እና በባእዳን እሳቤ በመመራት የአድዋ ቁስለኛው ዘረኛ ወገንን ለማስደሰት፣ እንደ ክፍያም ለሥልጣን ለመብቃት ይረዱናል በሚል ነውረኛ የክህደት ስሌት "ጸረ ኦርቶዶክሳዊ" ፕሮፓጋንዳን በተራቀቀ መንገድ ወደ አማራ ትግል እያስገቡ ለመሆናቸው ምልክት ይታያል።
የሰርጎ ገቦቹ የማነት መለያ ምልክቶቹ:-
* ወደ ትግላችን ሃይማኖት አታስገቡብን
* ሃይማኖት ከፋፋይ ነው
* ሞዐ ተዋህዶ ንቅናቄ ጸረ አማራ ነው
* ሥልጣንና መሪነት ለእኔና ለእኔ ብቻ የሚገባ የግል ገንዘቤ ነው
* የሰሎሞን ሥረወ መንግሥት ናፋቂዎች እና የነባር ማንነታችን አሻራዎች የትግላችን እንቅፋቶች ናቸው
* የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ሸቃላዎች የትግላችን ውስጥ ጠላት ናቸው
* አማራ በኪሴ የያዝኩት መጠቀሚያዬ ሆኗል፣ "ሌሎች" ምን አገባችሁ
* እገሌ የሚባል ሰው ዘሩ "እንትን" ነው፣ እና ምንም ጠቃሚ ዐሳብና ሥራ ቢኖረው እኛ ካላዘዝናችሁ አማሮች አትስሟቸው
* #አማራ የእኔ የብቻዬን የሥልጣን መወጣጫዬ መሰላል፣ እቃዬ ነውና የትግሉን ዓላማ ጠልፌ ምንም ወደ ፈቀድኩበት ብወስደው አትተቹኝ፣ * * ከተቻችሁኝ "የአማራ ጠላት" ብዬ በመንጎቼ በኩል እዘምትባችኋለ* ኢትዮጵያኒስት ጎራ እና የአማራ ብሔርተኝነት የሚለውን ንግግር ይደጋግማሉ
* የእኛ ትውልድ ያረጀ ያፈጀ ትርክትን አይቀበልም
ወዘተ የሚሉ ንግግሮችን ታዩባቸዋላችሁ።
* በጠባያቸው ልታይ ልታይ ያጠቃቸዋል፣ #ናርሲሲስት ባሕርያትን በሙሉ ያሳያሉ፤
* እንደሴትኛ አዳሪ ከዳበሳቸውና ለሥልጣን ይበቃናል ከሚሉት ባእድ ጋር ሁሉ እየተገናኙ በአማራ ሕዝብ ነባር እምነቶች፣ እሤቶችና ነባር ኢትዮጵያዊነት ላይ መደራደር፤ በአማራነት ነባር እናቶች በተለይ ኦርቶዶክሳዊነት መቃብር ላይ ሥልጣን እንዴት እንደሚጨብጡ እያሰሉ የሚያጎበድዱ ራስ ወዳዶች ሆነው ይገለጻሉ።
* የኦርቴዶክስ ክርስትናና እስልምና ምልክቶችን በአካላቸው ላይ በማሳየት፣ ተወዳጁን ንጉሥ ምንልክን ለማስታወስ አነጋገራቸውንንይኮርጃሉ፣ * ራሳቸውን ለአማራ ብቸኛ ታዳጊና አዋቂ አድርጎ በማሳየት፣ በብእርስም እና በማጋቸው በኩል ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሀሰት ወሬ በማሰራጨት፣ ለትግሉ መሳካት ሳይሆን ለግል ጠባብ ፍላጎቶች መሳካት የሚፈስሰውን የአማራን ልጅ ደም መጫወቻ ያደርጋሉ፤
* ከሁሉ በላይ ---- እና የአማራን ትግል ጠልፎ #ለኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ጠላቶች ማመቻቸት፣
በመጨረሻም አማራን በሥጋ ከእልቂት የተረፈ ነገር ግን የነፍስ ሞትን የታቀፈ ሕዝብ ሊያደርጉት ይመስላሉ።
አሁን በሥጋ ከሚገድለው ሥርዓት እና ከሚዋጉት ጠላት በከፋ ደረጃ እምነቱንናንየተቀደሰ ማነቱን እፕጥፍተው የሞት ሞት ሊደርቡለት በማወቅም ባለማወቅም እየሠሩ ያሉ ወገኖች አሉ !!!
እነዚህ ወገኖች የአድዋ ቁስለኞች የበቀል ምኞት ሙሉ በሙሉ የተሳካ እንዲሆን እና ተሳካ የሚባለው የሚባለው:-
፩) ኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ከኢትዮጵያ ነፍስነት ተነቅሎ በባእዳን እምነት ሲተካ
፪) አማራው ስነ ልቦናና ሕዝብ ከተቻለ ሲጠፋ ካልሆነ ወደ አናሳና ተጽእኖ አልባ ማኅበረሰብነት ሲወርድ
፫) ክብረ ነገሥታዊ ትርክትና ረዥም ታሪክ ወደ ትውልድ እንዳይተላለፍ ሲደረግ
፬) የአማራ አስተሳሰብ፣ ፍላጎት፣ ርእይ ሁሉ ከእግዚአብሔር አስትምህሮ ተቃርኖ ሲገኝ
፭) ኢትዬጵያ በጎሣና በሃይማኖት ተከፋፍላ የሄንሪ ኪሲንጀር እቅድ ሲሳካ ነው።
ታዲያ የእማራ #ፋኖ የስንዴ ማሳ መካከል የጠላትን ፍላጎት የሚያሳካ እንክርዳድ የሚዘራ ጸረ ኦርቶዶክስ ፍሬ እንዴት በቀለ?
አስተያየቶች