የመንግሥት 10 ዋና ተግባር እና ቀዳሚ ኃላፊነት 1) የዜጎችን ደኅንነት ማረጋገጥ፣ 2) ከሁለገብ ሥጋት መከላል፣ 3) የማንኛዉም ዜጋ አካልና ነፍስ፣ ሞራልና ህሊና እንዳይቆስል መከላከል፤ 4) የታወቁ መሠረታውያን መብቶችን መጠበቅና ማስጠበቅ፣ የ 5) ተረጋጋ የዜጎችና ማኅበራዊ መስተጋብሮቻቸው በታውቁና ተገማች፣ ተአማኒ የሕግና የፍት ሥርዓት ማረጋገጥ፣ 6) የምጣኔ ሀብት እደገት፣ የማኅበራዊ ልማት፣ ትምህርትና ጤና ወዘተ በሚፈለገው ፍጥነት፣ ስፋት፣ ነጻነት እንዲሄድ መሥመር ማሳየት እና --- ለሚፈጽሙት ዜጎች እድል ማመቻቸት --- የግልና የወል ጥረቶችን መደግፈና መጠበቅ 7) ከውጭ ጠላት መከላከል 8) የዓለም አቅፍ ግኑኝነቶችንና ጂኦ ፖለቲካዊ ፍላጎቶችን በጠበበ ጠቃሚ ማድረግ 9) ሕግ ማስከበር 10) ብዝኃነትን ማመጋገብና ጠቅላይ፣ አናባቢ የጋራ ትርክትና እሤቶችን ማጠናከር፣ አፍራሾቹን መከላከል ለምን እነዚህ 10ሩ አስፈላጊ ሆኑ? ምክንያቱም ያለ አተቃላይ የዜጎችና የማኅበራዊ መስተጋብሮቻቸው ድኅንነት፡ 1) ሰዎች መሥራት፣ መማር፣ ቤተ ሰብ መመሥረትና ማስተዳደር አይችሉም 2) ነጋዴዎችና አራሾች፣ ተመራማሪዎችና የፈጠራ ሰዎች ውጤት ተስፋ አድርገው መዋዕለ ንዋያቸውን፣ ጉልበታቸውንና ዕውቀታቸውን አያፈሱም፣ ቢያፈስሱም መተግበርና መፈጸም አይችሉም፤ 3) ማኅበረሰቦች እርስብርሳቸው አይተማመኑም፣ የጋራ ግብና ርእይ ላይ አይተባበሩም፣ ለውስጥ ቀውስና ለውጭ ወረራ የተጋለጡ ይሆናሉ 4) መንግሥታዊና ማኅበራዊ ተቋማት ኃላፊነታቸውን ለመወጣት የሚያስችላቸው አፈጻጸም ማረጋገጥ አይችሉም፤ ...
This is a spot where I post and share part of my daily reality. I would love to hear from others too to learn how differently we interpret daily encounters including our imaginations. ይህ ሥፍራ የየዕለት ገጠመኞቼን፣ እንዴት በዕለቱ እንደተረደሁትና የማስበውን ለሌሎች ያማጋራበት ነው፡፡ የሌሎችን በመስማትና ምን ያህል ዓለማችንን በተለያየ መንገድ እንደምንመለከታት ለመማር እጓጓለሁ፡፡