"አሥር ጊዜ ደጋግመህ ለካ፣ አንድ ጊዜ ቁርጥ" ለአናፂ ከተነገረ ለሕዝብ ሕልውና ተጋድሎ "መቶ ጊዜ ምከር አንዴ ወስንና ፈጽም" የምትል ብሂል ብናቀንቅን ስህተት አይመስኝም።
==========
እንደምታዘበው ከሄነ የብሔር ፖለቲካ ነጋዴዎች የሚጠቀሙት ስልት ሁሉ ይመሳሰላል ልበል?
* በሕዝብ ስም መማል፣ ግን ሕዝቡን እቃቸው ማድረግ
* ደም፣ አጥንት፣ ቋንቋ፣ ትርክትን መሣሪያ አድርጎ ክብረ-
ሰብእን፣ እውነትን ሰብአዊነትን መድፈቅ፣
* ሤራ
* የሚመለኩ ጥቂት ሰዎችን ግን በብዙ መስዋእትነት መፍጠር
* ጎጠኝነት
* በሕዝብ ጀርባ ከባዕዳን ተወዳጅቶ ለሥልጣን መሥራት
* ሐሰተኝነት ወዘተ
ህወሃትን ኦነግ፣ ብልጽግና ወዘተ ነውር የሚፈጽሙት የቡድን ጠባብ ፍላጎታቸውን በኦሮሞ በትግራይ ሕዝብ "ጥያቄ" ስም ነው።
ሙስናቸውንም በልማትና በሕዝብ ሀብት የማፍራት ስም ራሳቸውን ያበለጽጋሉ። ይህን የመሰለ ክህደት በፋኖ መሪዎች ምልክት ከታየ የህልውናንታጋዮች ሳይሆኑ ጸረ-አማራ ሊባሉ ይገባል።
አማራ ይህ ሁሉ የጠላቶቹ ርኩስ ልማድ አይስማማውም ባይ ነኝ። ምክንያቱም ሤረኞች ትርክትብፈጥረው፣ ማኒፌስቶ ጽፈው፣ የሰውን ጠላት አበጅተው፣ ከባእዳን መክረው ያስጀመሩት የሕወሃትና የኦነግንአምሳል አይደለም። ራስን የማዳን የትቀደሰ የሰብአዊነትና የፍትህ ተጋድሎ ነው። ተፈጥሮአዊ ነው። ይህን ጠልፎ የጥቂት በሽተኞች መገልገያንለማድረግ መሞከር የወንጀሎች ሁሉ ወንጀል ነው።
===========
እሁን አሁን መሬት ላይ ከተንሠራፋው የባንዳነት ስነልቦና የተነሳ በአንድ ወጥ አስተሳሰብም የእማራን ትግል እንኳ ለመምራት አልተቻለም። ይህን ጉድለት ያመጣው በአብሮነት ከማሰብ ይልቅ ከጠላቶቹ መርዛማ ስልት የሚዋሱ ሰዎች ብቅ ብቅ ብለው መናወጥ ስለሚፋጥሩ ነው።
ቁማርተኝነት፣ ኮንቪንስና ኮንፊዩዝ፣ ጎጠኝነት፣ ሤረኝነት፣ ስም ማጥፋት፣ ተክለ ሰውነት ግንባታ፣ ስሜትን ከአመክንዮ ማግዘፍ፣ ኢአማኒነት፣ ፖለቲካን/ትግልን ከእግዚአብሔር አርቆ በአቃፊነትና የሴኩላሩስቶች የተውሶ አስተሳሰብ፣ በአንድነት ሽፋን ትግሉን ለሰይጣን ፖለቲካ መሣሪያ ማድረግ፣ በሕዝብ ጀርባ ከባእዳን ጋር መምከር፣ ወዘተ ከአማራነት እሤቶች የሚቃረን ከጠላት የተቀዳ እንቅፋት ነው!!
ሰው ለእግሩ መጠን ጫማ ለክቶ እንደሚገዛ፣ ነገር ግን እግሩን ለሚያንሰው ጫማ ለማስማማት እንደማይቆርጠው ሁሉ አማራን በሚመጥነው የአመራር እሤትና ጥበብ እንጂ አማራን በድውያን ልክ ከፋፍሎ የሚከረክም ናርሲሲስት ሥር ለማንገላታት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ስምሪት በመላው ዓለም መዘርጋት ምንኛ መርዛማነትና ጭካኔ ነው።
በድሮን የሚታጨደው፣ የሚፈናቀለውና የሚራበው ገበሬ፣ ልጆቹን ለሞት አሳልፎ ለህልውናው የሚሰዋን ማኅበረሰብ ብርሃን ከማጨለም የከፋ ግብ ያላቸውን የትግሉ እንቅፋቶች በግልጽ መሥፈርትና ሚዛን ማጥራት ይሉኝታና ዲፕሎማሲ አይፈልግም።
የአማራን የተቀደሰ የህልውና ትግል ባደጉበት የሤራ፣ የግለኝነትና.የጎጠኝነት ባህል ሊያረክሱት ጥርሳቸውን ነክሰው ብዞዎችን እስከማሳት ከደረሱት ድውያን መጠበቅ ለድሉ ዘለቄታዊ ጠቀሜታ ዋስትናው ይመስለኛል።
ተወላግዶ የሚያድግ ዛፍ ምን ቢረዝም ለእስር እንጂ ጣውላ እንደማሆን ቀጥ ብሎ የበቀለውን ቆልምሞ ለማጣመም የሚያደቡትን እጅ እንዲሰበስቡ፣ ከሰው የማይበልጡ እኩል አማሮች ብቻ እንደሆኑ መንገር ይገባል። ወልጋዳው ቀጥ ያለውን ሁሉ እኔን ምሰል፣ እኔን አክል ሲለው ቀጥተኞቹ ጉድለቱን እያሳዩ ትሁት እንዲሆን ካልተራዱት አብረው ይጣመማሉ።
የሕወሃትና የኦነግ ዲቃላው ብልጽግና ከወያኔ ጥፋት በትንሹ የተርፎ እና ያልተጠናቀቀውን ዘር የማጥፋት ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ በአማራና በኦርቶዶክስ ላይ ሥልጣን በያዘ ማግሥት በተለያዩ መንገዶች መዝመቱ ለቀባሪ አረዱት ይሆናል። ገዳዩ እንዴት ይገታ? ለመግታት በሚደረግ ትግል ውስጥ ምን እንቅፋት ያጋጥማል ማለት ይገባል።
የህልውና አደጋ ከትጋርጠባቸው መካከል ኤርቶዴስ ዜጋና አማራ ቀዳሚዎቹ ናቸው።
ኦርቶዶክሳውያን በምንደኛ እረኞቻቸው አደንዛዥነት ራራሳቸውን ለማዳን አንድ ሆነው አልተነሱም። ድንዛዜው የጥምቀት ልጅነትን ክርስቶስን አዲስ ዘርነትን አስረስቶ ጌሣና ብሔር ሆነው፣ ከክርስቶስ ይልቅ ህወሃትን ኦነግን አምልከው ልእልቂታቸው እንደተመቻቹ ይገኛሉ።
አማራ ግን ነቅቶ፣ ቀና ብሎ ቆሟል። መቆም ብቻ ሳይሆን የኦነግ አብይ አህመድን እና የሕወሃትን የጋራ ህልም የሚያጨልም እርምጃ በምውሰድ ላይ ይገኛል። እርምጃው ግን በናርሲስት ጎጠኛ በሽተኞች እንዳይሰናከል ያሠጋል።
የሚያሳስበውና ውይይት የሚፈልገው ጉዳይ ---+
በትግሉ ውስጥ የብሔር ነጻ አውጭዎቹን ስልት እንጂ ሌላ አዲስ ጠቃሚ መንገድ ማስመር የተሳናቸው ዘገምተኞችና የሤራ ዘመን ፍልፍሎች አማራ ተጸይፎት የሚዋጋውን የጠላት የትግል መርህና ስልት ቀድተው፣ ትግሉን የግልና የጎጥ መበልጸጊያና የሥልጣን ግብ አድርገው የሚንቀሳቀሱ የሩቅ አሳቢ ወገናቸውን ህልም በሆዳቸው መቃብር ውስጥ ሊከትቱ የሚሞክሩ ጥቂቶች በግልጽ መኖራቸው ነው።
እንዚህ እንቅፋቶች ከጠላት ምን ቀዱ ብትሉ፦
፩) ጎጠኝነትን ከአድዋ ባንዳዎችና ከወለጋ የጸሎት ቤት ፍልፍሎች፣ ከዚያድ ባሬ ተላላኪዎች ከጃራ አባገዳና ዋቆ ጉቱ ክህደት፤
፪) ሤረኝነትና "ልንገሥ" ባይነት ከአብይ አህመድ እና ከህወሃት የስራ መሪዎች፤
፫) የሐስት ትርክትና የሐስት የፕሮፓጋንዳ ሥራዊት ስምሪት ከሕወሃት፣ ከኦነግ፣ ከብልጽግና፤
፬) ይሉኝታ ቢስ ፕሮፓጋንዳን መንዛትና በእውነት ላይ ማመን ዘርን ከሂትለሩ ጎብል፣ ከኦነጉ የአስፋ ጃለታ የትርክት አመንጭና የመጽሐፍ ቅዱስ ቀያሪው በንቲ ቴሶ
፭) ነፍሰ ገዳይነትና አፈናን ከአብይና መንግሥቱ ኃ/ማርያም
እንደቀዱ አያለሁ።
በዚያ ላይ ከአብይ አህመድ ያዩትን ሮቦት የመስሉ የማይስቡ እና የትጋቱትን መልሰው እያስመለሱ የሚርጩ እክቲቪስቶችን ማሰማራት ጥሩ አድርገው የወረሱ አሉ።
ለጥንቃቄ ያህል ፦
ሮቦት መሳይ የሤረኞች ቅጥረኛ አክቲቪስቶችን በሚከተሉት ምልክቶች መለየት እንችላለን፦
(፩) ያልተጻፈ የሚያነብብ፣ ራሱን ችሎ ቆሞ ሀስብን የማይሞግት፣ እና በመቃወም ብቻ ላይ የተሰማራ፣
(፪) የአንዳች አንቀሳቃሽ ሞተር ተሽከርካሪ እግር ይመስል ምንም ቢያነብብ ባይገናኝም "በል" ያሉትን ብቻ በማለት ወደዘወሩት የሚሄድ፤
(፫) አስበው እንደማይናገሩት ፣ በገንዘብ ነዳጅነት እንደሚሽከረከሩ የሤረኛ መሪዎች አክቲቪስቶች መንጋ ሁሉ ያለ ጠቃሚ ሀሳብ ከማእከል በተሰጣቸው መጠን ሳይሰለቹ እንደ ሂትለር ጎብል ነገር መደጋገም፤
ራሳቸውን የቻሉ ሙሉ የህሊና ለከት ያላቸው ሰዎች እንደሚያደርጉት አስበውና አስላለው ለአነበቡትና ለሰሙት ነገር መስተካከል ወይንም መወገድ መሟገት ሳይሆን እንደ ራዲዮ ሌሎች የሚናገሩባቸው፤
ለመሄናቸው ድርቅናና ኢአመክንዮአዊ ንዝንዛቸው ያሳውቃል።
እኔ በግሌ ለእነዚ እንቅፋቶች የምመክራቸው የአማራ ትግል ውጤቱ ዓላማውን እንዲያሳካ የተፈጥሮ አእምሮአችሁን፣ ህሊናችሁን ከተላላኪነት ነጻ በማውጣት:-
፩ኛ) ሰው ከሆናችሁ ለምታነብቡት መልስ ስትሰጡ መጀመሪያ ራሳችሁን ለሆነ ቡድንና ግን ሰብእ ግዑዝ መሣሪያ ሳይሆን ለህሊናችሁ እና በአምሳሉ ለፈጠራችሁ ለእግዚአብሔር ታመኑ፤
፪ኛ) የተጫነልባችሁን የሤረኛ፣ የጎጠኛ፣ የኢአማኒ፣ የጠባብና ድውይ ሰዎችን ተልእኮ ይዛችሁ ራሳችሁን እስከማጣት መልከስከስ የስነልቦና ዘላቂ ጉዳት እንደሚያመጣ ከባለሙያ ተማክራችሁ ሽሹት፤
፫ኛ) ክቡር የእግዚአብሔር አምሳል ነጻ ሰው መሆንህን ሳይረሳ እና የህልውና ትግል ውጤት አንደኛው ትሩፋት ከማንኛውም አይነት ባርነት መገላግል ነውና ባሪያ ሆናችሁ ከተገኛዥሁ ለአማራንህልውናንሳይሆን ለጥፋቱ እንደምትሠሩ አስቡ፤
፬) ከሁሉ በላይ ከጭፍን መንጋነት ስትወጣ በአማራ ስም የሚናግዱትን፣ ደሙንና አጥንትን ለግል ጥቅማቸው መሳካት የሚያባክኑትን ተከትላችሁ አማራ በኪሳችሁ የየዛችሁትና አትንኩብኝ እያላችሁ ጥብቅና የምትቆሙለትና እንደ ግዑዝ መገልገያ ማገዶም፣ ተሸካሚያችሁም አድርጋችሁ መታበዩን ታቆማላችሁ።
ለዚህ ክብርን ታላቅ የህልውና መረጋገጥ በቆሙ እውነተኛና ጀግናንየአማራ ልጆች መካከል የጠላት ፍልስፍናን አዝላችሁ ቅዱሱን ትግል አታርክሱት።
አስተያየቶች