ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ከሰው የሚበልጥ ልማት እና ሥልጣኔ አለ ከተባለ ከዲያብሎስ ነው

#ከሰው #ልጅ #ክብር #የሚበልጥ #ልማት አለ ከተባለ  "የሞት ዕፀ-በለስን የሕይወት መደኃኒት ነው"   በማለት ተንኮል ምንም ስለ ሤራ የማያውቁትን የዋሐንን አዳምንና ሔዋንን  አታልሎ #ሞትን ካስታቀፍው   #ከሳጥንኤል   እና  #ከብልጽግና #ወንጌል #መንግሥት በስተቀር  ማንም ጥቅሙን አያውቅም።  

==========================


#የብልጽግና #ወንጌል   #ሃይማኖታዊ  #መንግሥት ማኅቀፈ-ዕሳቤ (worldview)  ይገርመኛል። 


የዚህ ሥርዓት መሪና አጃቢዎቹም ሆኑ ወላጆቹ ሕወሃትና ኦነግ፤ አዋላጆቹ ደግሞ ዉሀብያ፣ ተርፈ ናዚዎቹ፣ ጡጦ አጥቢዎቹ  ባዕዳን እንደመሩት 

👉 ሞትን ሕይወት፣ 

👉 መፍናቀልን እደገት፣ 

👉 መፍረስን ከፍታ፣ 

👉 መለያየትን ነጻነት፣ 

👉 ጦርነትን ሕግ ማስከበር፣ 

👉 እልቂትን abnormal-normal (በአብይ አህመድ አሊ በፓርላማ የተነገር ነውር)፣ 

👉 የታሪክ ንቅለ ተከላን ታላቁ ትርክት፣ 

👉 ሲኖዶስን ወደ ጎሣ ምክር ቤት ማውርድን  አካታችነት፣ ---- በሚል የሚተረጉም ከሰውልጅ ህሊና ፈልቆ  ለሰው ልጆች ጥቅም የተደረገ ነው ለማለት የማያስችል ጸረ-ሰብእ ትርጓሜ  በመስጠት የመከራ ሥርዓትን የሚመራ ነው። 


ሰማይ የተሰቀለለትን፣ ምድር የተዘረጋለትን ክቡር አዳማዊ ፍጡር #እያረዱና #እያሳደዱ ----  ያለ ሁፍረት በሬሳ ላይ ቆሞ፣ ደም ውስጥ እየዋኘ፣ በሚገፉት ወገኖቻችን ዕንባ እየታጠበ  ------

--- #ስንዴ፣ #ግድብ፣ #ወደብ፣ #ችግኝ፣ #ኮሪደር ልማት፣ ሰፊ #አስፋልት፣ ረዥም _ፎቅ፣ ደማቅ #መብራት፣ የፎቶ #ዲፕሎማሲ ----- ለሚጨፈጨፍ ክፍለ-ሕዝብ ምኑ ነው??


#ልማት እና  #ሥልጣኔ  ምናልባት እነርሱ  "ብልጽግና" የሚሉት ነገር ሰውን የማይመለከት አድርገው ለማቅረብ እጅግ ይደክማሉ።


የእነዚህ ዘረኞች ብልጽግናቸው እነርሱ ለመረጡት እናንልዩ ጥቅም ይገባዋል ለሚሉት ይወገን ብቻና ብቻ  ይመስላል። ለዚህም  ብልጽግናቸው ከሚጨርሱት፣ ከሚያፈናቅሉት፣ በባርነት ለአረብ ከሚሽጡት፣ በድሮን ከሚገድሉት፣ ከእምነታቸውና ባህላቸው ከሚያፈናቅሏቸው፣  ታሪካቸውንና ውርሳቸውን ከሚደመስሱበት የሃይማኖትና ይፕቋንቋ ክፍለ-ሕዝብ ፋር ግኑኝነት የለዉም።


ይህም ይታወቅ ዘንድ 30 + 8 በመዋቅራዊ መንገድ ከበደኖ ጀምሮ በሁሉም ማዕዘን እስከ እርሲ ስለሚፈጁት፣ ስለሚያፈናቅሉት ርስት ስለሚቀሙት ሕዝብ በፓርላማቸው: በፖለቲካ ጠፍጥፈው  ወደ አግልጋይነት  የቀየሩት ሲኖዴስና መጅልስ አጀንዳ እንዳይሆን ይከላከላሉ።


በ39 ል8 የጥፋት ዘመናት ሁሉ ፍትህ ያገኝና የተካሠ ተጎጅ፣ የተከሰሰ ጎጅ፣ ከሥልጣኑ የተባረረ እረኝነት የነፈገ ኃላፊ የለም።  

--- ከዙህ አንጻር የአብይ አህመድ አሊ  የጓዶቹ ብልጽግና የአሰፋ ጃለታና የሸምሰዲን ማጋላሞቱስ ናዚያዊንዘር የማጥፋት ፍልስፍናን የተከተለ ነው። 


---- ይህ መገታት ስለሚገባው ዒላማ የተደረገው ኦርዶሮክሳዊ ክርስቲያን እና በቋንቋ ዘውግ ዒላማ የተደረገው ብቻ ሳይሆን በብልጽግና ስም የጥፋት መሣሪያ የሆነው ቀሪው የዘር ፖለቲካ የአእምሮ ባሪያቸው የሆነው ወገን ነቅቶ መፍትሔ መስጠት አለበት።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

የሐሰት ትርክት ኦነጋውያንና የሕወሃታውያ የጋራ ስልት ከነግሥታት ወደ ተራ ግለሰቦች

✏️ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።  እርሱ ይመስገን። ምድራችንን #በደም #ያጨቀየው $ህሊና #የነሳን ፣ #ልቦናችንን #ያጨለመን ፣ #ሰብእናችንን ያዋረደው:- 👉 የሕወሐታውያንናንየኦነጋውያን የንዑስ ማንነት የጎሣ ፖለቲካ የደንቆሮ ርእዮትና፣ 👉 መርዛማን ጥላቻን ለ፶ ዘመናት ያከፋፈሉት የሐሰት ትርክት ናቸው። ✏️እንደ ዳግማዊ #ምንልክ ያሉ   ከዋክብት መሪዎች፣ እንደራሴቻቸው፣ ደጃዝማቾችና ቀኝና ግራ አዝማቾቻቸው  ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ብዙ ውለታ ውለውልናል:- 👉 በዘመነ ኦቶማንና አውሮፓ፣ በዘመነ መሳፍንት የተበታተነውን እና የተቆነጻጸለውን፣ ጎሠኛ የአርብቶ አደሮች  መሬት ፍለጋ  የደመሰሱትን ክርስቲያናዊ የግዕዝ/የነፃነት ሥልጣኔ አሻራ እንዲያገግም ደክመውልናል፤ 👉 የጥንት አገርን እና ሕዝቦችን   በከፊልም ቢሆን በመሰብሰብ  ጠንካራና ብቸኛ የነጭ ቅኝነትንና ባርነትን በመከላከል፣ ከኦቶማን ቱርክ ወር ትናንት ውስጥ ጥረኛ  አህመድ ግራኝ በመጋደል  ልዩ የነጻነት ማንነት ያላትን አገር ብበቸኝነት በዓለም ካርታንላይ አቆይተዋል፤ 👉 የሬማ ግዛት በጎሣ ተብልቶ ፲ ትንንሽ ሲሆን ከበበባውን ተቋቁማ በዝኃነታችን በተመጋጋቢ አንድነት ከ፹ በላይብቋንቋ፣ ከዓለም ትልልቅ እምነቶች ክትስትናን ፣ ይሁዲን፣ እስልምናን፣ የእረማውያንን ቅሪት የሆኑ የባህል እምነቶችን ሁሉን ይዛ በአውሮፓ በአርብ አምሳል ሳትሠራ ለእኛ አቀብዋል፤ 👉 ወያኔና ኦነግ፣ ገንጣዩ ሻዕብያ፣ ከሃዲው የማርክሲስት የአእምሮ  ባሪያን ስብስብ  እስኪፈትናት ድረስ ራሷን የቻለች አገር እንድንፈጥር ያስተባበሩን ነገስታት የተመሰገኑ ናቸው። አገር ሲያረጅ ጃርት ያብቅላል እንዱሉ: መል...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩. ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡  በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡  ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በቋንቋ መ...

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...