ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

የሕወሃት ሲኖዴስ የግዛት ጥያቄና ኢክርስቲያናዊነቱ

#የትግራይ #ክርስቲያን ሕዝብ ከሁለቱ #አጥፊዎቹ #ነጻ በማውጣት የተወሰደበትን #አገርን እና #ቤተ ክርስቲያኑን #ያስመልስ‼️

✏️ "የትግራይ #ሲኖዶስ የፌዴሬሽን ምክር ቤትና የምርጫ ቦርድን ውሳኔ በጽኑ ተቃወመ" ይላል አዲስ አድማስ ጋዜጣ ለይ የወጣ ዘገባ።

ራሱን #ቅዱስ ብሎ የሚጠራው #የሕወሃት ሲኖዶስ  " የኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት እና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያስተላለፉት ውሳኔ #ለዘመናት #አብሮ #የኖረን #ሕዝብ የሚነጥልና #አንድነትን #የሚያፈርስ ነው" ነው ይላል። 

✏️ በዚህ አባባሉ "የሕዝብ #አንድነት" ማለት  በወያኔ ሕገ መንግሥት መሠረት የተፈጠሩ አዳዲስ የጎሣ ክልሎችን የሚመለከት ነው። 

✏️ #አንድነት ፈጽሞ በጥምቀት አንድ የሆነውን የሥላሴን ልጆች  በክርስቶስ ግንድነት ላይ መጣበቅ አይደለም። 

✏️ ስለዚህ ይህ ስብስብ #የሕወሃት እንጂ #የክርስቶስና የክርስትና አስተምህሮ፣ እምነትና ተስፋ ላይ የተመሠረተ  አይደለም። መንግሥተ ሰማያት ሳይሆን የሕወሃትን ታላቋን ትግራይ የሚማልል ነው።  የህወሃትን ታላቋን  የዘር ሪፐብሊክ በኢትዮጵያና በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መቃብር ላይ ለመመሥረት  ተልእኮ የተቀበለ ኢክርስቲያናዊ ካድሬ ነው።

✏️ የሕወሃትን ሲኖዶስ  ያስቆጣው የአገር በዘር ሕገመንግሥት መፍረስና የቤተ ክርስቲያን መዳከም፣ የጥምቀት ልጆች ተበታትኖ  #ለጽንፈኞች እና  ፣#ለአብይ #አህመድ ጭፍጨፋ መጋለጥ፣  እንዲሁም የትግራይ ክርስቲያን ወጣት ከክርስትና እፕእምሮ ታጥቦ  የህወሃት የጥፋት ሠራዊት መሆን አይደለም።  

✏️ የስብስቡ ጭንቀት የወያኔና የባእዳን ሤራ ውጤት የሆነውን የፕሪቶሪያ ስምምናትና የአብይ አህመድ  ቤተደብን የማጋጨት ጥመድ ማስፈጸምና አገር እና የቤተ ክርስቲይንን አንድነት በትኖ የሕወሃትን  ሪፐብሊክ ለመፍጠር የሚደረገውን ሂደት መንከባከብ ነው።    

✏️ ስለዚህ  የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ያስተላለፈውን ውሳኔ መሠረት በማድረግ ምርጫ ቦርድ የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም የሰጠው መግለጫ  የወያኔ ሕገ መንግሥት በአገር መፍረስ ሊጠቀልላቸው አልሞ የከለላቸው እና የፈጠራቸው የአስተዳደር  ድንበሮችን እንደ ዓለም አቀፍ የአገራት ድንበር ጉዳይ አድርጎ በመቆጠር መቆጣቱ ነው።

✏️ በዚህ ዕሳቤ ላይ በመመሥረት  "ውሳኔው   ሰላምን የሚነሳ በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲታረም"  ሲልጠይቆ ከህወሃት ቀድሞ እንዳወገዘ ገልጧል ።

✏️ "ሲኖዶስ" ተብዬው እንዲህም ሲል #የግዛት #ጥያቄ አቅርቧል:- "በደቡብ ትግራይ ሀገረ ስብከት ስር ያሉትን #ኮረም፣ #ኦፍላ እና #ራያ #አላማጣ ወረዳዎችን፣ በሰሜን ምዕራብ ትግራይ #የጸለምቲ ወረዳን እንዲሁም #የምዕራብ #ትግራይ ዞን ሀገረ ስብከትን #ርስት በመንጠቅ ወደ አማራ ክልል በማካለል 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ እንዲካሄድ መወሰኑ" የተወገዘ ነው ይላል። 

👉 ይህ የጥፋት ስብስብ የክርስቶስ ልጆች በመላው አገሪቱ እንደ እንስሳ በሚታደኑበት፣ በኦሮምያ ክልል መንግሥት በቤተ ክርስቲያንን በሚያጠፋበት፣ የአማራና የትግራይ ሕዝብ አንድ ላይ ቆሞ ከዘር ጥፋት ራሱን እንዳይከላከል #ሕወሃት የተባለ የጥፋት ድርጅት #እንቅፋት በሆነበት በአሁኑ ግዜ  ክርስቲያኖችን ከማቀራረብ ይልቅ  እርስ በርሱ የማለያየት መግለጫ አውጥቷል። 

👉 እንዲህም ሲል ኢክርስቲያናዊ ስብስብ መሆኑን የበለጠ ግልጽ አድርጓል :-  ውሳኔው "ሕዝብን ከቀዬው ካፈናቀለ በኋላ ርስቱን የሚነጥቅና በትግራይና በአማራ ሕዝብ መካከል ሆነ ተብሎ መለያየትን የሚዘራ ተግባር ነው ሲል" ለዚህ ሀሉ መለያየትና እልቂት ሕወሃት ዋና የመርዝ ምንጭ መሆኑን ለመሸፈን ሞክሯል።  

✏️ የሕወሃቱ ሲኖዶስ የጥምቀት ልጆችን ሳይሆን የሕወሃትን አዲሱን "ትግራዋይነት" የተሰኘ የኦነግ ፖለቲካዊ የ "ኦሮሙማ" "ሃይማኖት" ጋር አቻ ፖለቲካዊ #የዘር #ጣዖት አምልኮ እንደሚወከል የሚያረጋግጠውን ጥሪ እንዲህ ሲል አስተላልፏል:-  

✏️ "በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችም ያላቸውን የፖለቲካ ልዩነት ወደ ጎን በመተው ለሕዝባቸው ህልውና እና ለግዛታዊ አንድነት  የሚያደርጉትን ጥረት እናደንቃለን። በቀጣይም ከሕዝባችሁ ጋር በመሆን ለህልውናው በጋራ እንድትመክሩና እንድትሠሩ እንመክራለን"  ይላል።
👉 በዚህም አቋሙ  ስለ ክርስቲያኖች አንድነት  ሳይሆን የበለጠ የተመሠረተለትን  የሕወሃትን ክርስቲያኖችን  ከፋፍሎ የማዳከም  መሠሪ ፕሮጀክት ለማሳለጥ የተፈጠረ እና በአብዛኛው  የኢአማንያን ዘረኛ መነኮሳት ስብስብ  መሆኑን ገልጧል። 

ኦርቴዶክሳውያን የክርስቶስ ልጆች ሆይ‼ መገንዘብ የሚገባን -----
👉 #የትግራይ  ኦርቶዶክስ ክርስትና ተከታይ ሕዝብ #ሙሉ #ኢትዮጵያ #ርስታቸው፣ #ሙሉ ቤተ ክርስቲያን #ቤታቸው መሆኑን ዘንግተው    ይህን መሠሪ  የፖለቲካ ድርጅት ተከታይ በመሆን ለ፶ ድፍን ዘመን ተሰቃይቷል። 

👉 በጦርነት አልቋል፣ በስደት ተበትኗል፣ ከሁሉ በላይ ለክርስቶስ የማይስማማውን ዘረኝነትና ጥላቻ በመጋት ነፍሱን ጎድቷል።  

👉 ከዚህ ሁሉ መከራ ለመገላገል በሴትና በወንድ ተራክቦ በሥጋ ከሚገኝ #ማንነት እና በሕወሃት ከተመረዘው #ብሔርተኝነት ተላቅቆ በጥምቀት ልጅነቱና በእኢትዮጵያዊነቱ  ከሕወሃት እና ከሕወሃት ፍጡርሮች የወንበዴ መነኮሳት ማህበር ራሱን ነጻ ማውጣትና ራሱን የማዳን ኃላፉነቱን ይወጣ‼️



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

የሐሰት ትርክት ኦነጋውያንና የሕወሃታውያ የጋራ ስልት ከነግሥታት ወደ ተራ ግለሰቦች

✏️ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።  እርሱ ይመስገን። ምድራችንን #በደም #ያጨቀየው $ህሊና #የነሳን ፣ #ልቦናችንን #ያጨለመን ፣ #ሰብእናችንን ያዋረደው:- 👉 የሕወሐታውያንናንየኦነጋውያን የንዑስ ማንነት የጎሣ ፖለቲካ የደንቆሮ ርእዮትና፣ 👉 መርዛማን ጥላቻን ለ፶ ዘመናት ያከፋፈሉት የሐሰት ትርክት ናቸው። ✏️እንደ ዳግማዊ #ምንልክ ያሉ   ከዋክብት መሪዎች፣ እንደራሴቻቸው፣ ደጃዝማቾችና ቀኝና ግራ አዝማቾቻቸው  ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ብዙ ውለታ ውለውልናል:- 👉 በዘመነ ኦቶማንና አውሮፓ፣ በዘመነ መሳፍንት የተበታተነውን እና የተቆነጻጸለውን፣ ጎሠኛ የአርብቶ አደሮች  መሬት ፍለጋ  የደመሰሱትን ክርስቲያናዊ የግዕዝ/የነፃነት ሥልጣኔ አሻራ እንዲያገግም ደክመውልናል፤ 👉 የጥንት አገርን እና ሕዝቦችን   በከፊልም ቢሆን በመሰብሰብ  ጠንካራና ብቸኛ የነጭ ቅኝነትንና ባርነትን በመከላከል፣ ከኦቶማን ቱርክ ወር ትናንት ውስጥ ጥረኛ  አህመድ ግራኝ በመጋደል  ልዩ የነጻነት ማንነት ያላትን አገር ብበቸኝነት በዓለም ካርታንላይ አቆይተዋል፤ 👉 የሬማ ግዛት በጎሣ ተብልቶ ፲ ትንንሽ ሲሆን ከበበባውን ተቋቁማ በዝኃነታችን በተመጋጋቢ አንድነት ከ፹ በላይብቋንቋ፣ ከዓለም ትልልቅ እምነቶች ክትስትናን ፣ ይሁዲን፣ እስልምናን፣ የእረማውያንን ቅሪት የሆኑ የባህል እምነቶችን ሁሉን ይዛ በአውሮፓ በአርብ አምሳል ሳትሠራ ለእኛ አቀብዋል፤ 👉 ወያኔና ኦነግ፣ ገንጣዩ ሻዕብያ፣ ከሃዲው የማርክሲስት የአእምሮ  ባሪያን ስብስብ  እስኪፈትናት ድረስ ራሷን የቻለች አገር እንድንፈጥር ያስተባበሩን ነገስታት የተመሰገኑ ናቸው። አገር ሲያረጅ ጃርት ያብቅላል እንዱሉ: መል...