አገር ያጠፋው፣ ትውልድን ያከፋው፣ የደም አባላ እያስከፈለን የሚገኘው ከሁሉ በላይ ----
ሰው ክቡር ፍጡር ነውው። ግን ነፃ ፈቃዱን ተጠቅሞ ከዱር አራዊት የከፋና ዱያብሎስን የሚያስቀና እኲይ መሆን ይችላል።
ህሊና፣ ፈሪሃ እግዚአብሔርን፣ ፍትሕ እና ክበረ-ሰብእን ወዲያ ጥለው ወይንም ትፕስውሮባቸው #ምላስና #ሆድ #ብቻም የሆኑ፤ --- በአምሳለ እግዚአብሔር መፈጠራቸውን የካዱ እና በዚህ ምክንያት ለሰውነት ትርጉም ከሚሰጠው ከሕያው እግዚአብሔር በመለየታቸው #ሰውነትን #የማያሟሉ #የቁም #ሙታን ናቸው።
#ሻዕብያን፣ #ደርግን፣ #ሕወሃትን፣ #ኦነግን፣ #ብልጽግናን እና የመሳሰሉትን በአምሳላቸው ለጥፋት ፈጥረው #የሚመሩ #ሰዎች በፈቃዳቸው ራሳቸውን #ከሰውነት #ያጎደሉ የቁም #ምውታን ናቸው።
ሕዝብን፣ ትውልድን፣ አገርን #ገድለው ሁለተኛ ሞት በንፍስም በሥጋም የሚሞቱ የዓለማችን ዕዳዎች እነዚህ ናቸው። በሕዝብ ስደት፣ ረሃብ፣ እልቂት ከእምነት መፍለስ፣ መፈናቀል፣ መደኸየት ምንም የማይሰማቸው ብቻ ሳይሆ በግፍ የሚደሰቱ ናቸው።
እንደ #አብይ #አህመድ #አማካሪ አይነቱ #ከ፻፳ ሚሊዮኑ ፲ሩ ሚሊዮን ሰላም ቢያጣ የቀረው ሰላም ነው" ነው በማለት የሰው ልጅን እንደ እቃ በቁጥር የሚለካ #ዳርዉናዊና ናዚያዊ የቁም ሙት የሚመራት አገር የፈጠርነው ከሰውነት የጎደሉ ሰዎች ሰውን እንዲመሩ ጤናማዎቹ ብዙኃን በዝምታና በፍዘት በመፍቀዳችን ነው።
የሚገርመው እነዚህን #ከሰብእና #የጎደሉትን #የተበላሹ #ፍጡራን በውትድርና፣ በፖሊስነት፣ በጄሮ ጠቢነት፣ በአማካሪነት፣ በዲፕሎማሲ፣ በካድሬነት፣ በተለይ በእምነት ቤት ውስጥ ተልእኮ ወስደው የቅድስናን ቦታ እና ምንጭ ለማራከስ የሚሞክሩ እየገድሉ ብፁዕ የሚባሉ፣ ጎሣ ጠቅሰው ንጹህ ተብለው የሚጰጵሱ ከንቱዎች በፈቃዳቸው ሰውነታቸውን ላጎደሉ አጥፊዎች የሚያገለግሉ በየዘመኑ መኖራቸው ነው።
ለሻዕብያ ተልከው አገር ወግተው ያስገነጠሉ፣ #የትግራይን ሕዝብ ኢትዮጵያን አስጥለው በክልል ያሠሩና ከገዛ ቤተሰቡ የሚያዋጉ፣ #የኦሮሞን ሕዝብ በሐሰት ትርክት የተሸነፈላቸውን ያህል አጎሳቅለው በበታችነት የስነ ልቦና ስሜት ውስጥ በማስገባት ያገኙትን ውስን ወጣት ለፍጅት ያሰማሩ፣ #የአማራን ሕዝብ አደንዝዘው የባንዳ መፈልፈያ ያደረጉ፣ ሌሎችንም ወገኖች ወደ ጠራፋማ ባእድነት የገፉና ከጋራብትርክትናብእሤት የበለጠ አፍራሽ ንዑስ ትርክትን የብዙ ---- እነዚህ ከደምሰውነት የጎደሉና የፖለተካ ሥልጣን የጨበጡ፣ በሐሰት እውቀት በተባለ ከንቱ ድንቁርና #ምሁራን የተባሉ ፤ ሳያምኑ የእምነት አባትነትን ለምንዳ ሲሉ የተጣበቁ ጎዶሎ ሰዎች ናቸው።
እነዙህ ናቸው ትውልዱን ግራ እያጋቡ አሁን ለሚገኝበት መለያየት፣ አለመተባበር፣ መሳደድና እልቂት የዳረጉት።
እነዚህ ናቸው #በምርጫ ስም ትውልዱ ግራ ተጋብቶ #መግደል-እትንፋሱ የሆነ ከሰብ እናብ የጎደለ መሪዎችን እንዲመርጥም፣ እንዲያጨበጭብለትና እንዲታዘዘው የሚያደርጉት።
እንንቃ!!!
ከታች የተያያዘውን #የታማኝ #በየነ #የቩዲዮ መልእክት ሳደምጥ ይህ ከላይ የገልጽኩትን እንዳጋራ ገፋፋኝ።
መልእክቴን የተረዳና #ከሙታን የፖለቲካ የአእምሮ ባርነት ነጻ የሆነ፣ #ሰው #ሁሉ #በእግዚአብሔር #አርአያ የተፈጠረ #ክቡር እርሱን ፈጣሪውን በቅድስና፣ በመልካምነት፣ በአፍቃሪነት፣ በለጋስናት፣ በይቅርባይነት፣ በታዳጊነት እና በመሳሰሉት ሁሉ ለመምሰል ለመጋደል የተጠራ መሆኑን የሚያምን፣ ----
በተቃራኒው ግን በነፃ ፈቃዱ ክፋትን መርጦ በቁሙ ልክ ዛሬ እንደሚያሰቃዩን እንደ ጎሣ የማንነት ፖለቱካ ልሂቃን በቁሙ ሙት እንደሚሆን፣ በምዉታንነቱ ሕያዋንን በሥጋ እንደሚገድል #የሚያምን እና የተረዳ ሁሉ "ትክክል" እያለ ግብረ መልስ ይስጠኝ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ