ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ለፋኖ ሠራዊት፣ ለፋኖ መሪዎችና ለኦርቶድክሳውያን በሙሉ:- ከጸረ-ኦርቶዶክሳዊነት ሕዋስ ራሳችሁን ስለመጠበቅ

ለፋኖ ሠራዊት፣ ለፋኖ መሪዎችና ለኦርቶድክሳውያን በሙሉ

መግቢያ

 “እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም። (ማቴዎስ 5:13) እንዲል ተጋድሎአችን እንደ አሕዛብ ለሥልጣን፣ ለድሎት፣ ሌላውን አሳፍሮና አሳንሶ አሁን ባልፉት 50 ዓመታት እንደታዪት ዘረኛና አምላክ-የልሽ ገዥዎች  በሌሎች ላይ ከፍ ከፍ ለማለት ሳይሆን ለነፍስም የሚተቅም፣ እግዚአብሔርን የሚያስደስት፣ ለትውልድ ሰላምና አንድነት በር የሚከፍት፣ ፍትሕ እውነትና ሰብአዊ ክብር የሚመለስበት የተቀደሰ ተጋድሎ ነው። 

ይህ ተጋድሎ በአጭር ስሙ ፋኖነት ነው። ፋኖነት ስለ ክብረ-ስብእ፣ ስለ እውነት፣ ስለ ፍትሕ፣ ስለ ትውልድ የሚደረግ የተቀደሰ መስፈንጠር ነው።  ፋኖነት ከባእድ ወርሰው፣ ነባርነትን በጠላትነት ፈርጀው፣ አምላካቸውን ክደው፣ ንዑስ-ማንነትን ከሰባዊነትና ከሃይማኖት በላይ በጣዖት ደረጃ ከፍ አድርገው ላልፉት 50 ዘመናት ደም ሲያፈሱ አገር ሲያፈርሱ ከኖሩትና እየኖሩ ከሚገኙት የአገርና የሕዝብ መከራው ፈላፍይ ድርጅቶችና አስተሳሰቦች እጅጉኑ የራቀ ነው።    ይሁንና በፋኖነት ውስጥ የእንዚህ የአግር መከራ በር ከፋቾች እሳቤ ብልጭ ድርግም ሲል ቆይቶ አሁን ላይ ሞዐ ተዋህዶ ንቅናቄ እንደ መለኪያ ሆኖባቸው እየተጋለጡ ነው። 

መታወቅ ያለብት፦

ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ክርስትናን የሚያሳድድ ተጋድሎ እግዚአብሔርን ስለሚያሳድድ ጌታችን ለአሳዳጁ ሳዖል፣ ጨለማው ሲወግደለትና በትክክል ማሰብ ሲጀምር፣ ለመንፈስ ቅዱስ ማኅደርነት ሲምች ምርጥ እቃና  በጸጋ የዓለም ብርሃን  ለተሰኘው ቅዱስ ጳውሎስ   ‘“ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ?” የሚለውን ድምፅ ሰማ። ጌታ ሆይ፥ ማን ነህ? አለው። እርሱም አለው፡— “አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል።” ለምን ትሳደዳለች?(ሐዋ. ሥራ 9:4-5)  እንዲል። ዛሬም ፋኖ ነኝ፣ ለማራነት እሤቶችና አማራ ለተባለና የዘር ፖለቲካ ፈርጆ ለዘር ማጥፋት ዒላማ ላደረገው ክፍለ-ሕዝብ ቆሚአለሁ ከሚል ውገን ውስጥ ቤተ ክርስቲያንን ዒላማ የሚያደርግ እንክራደ ብቅ ማለቱን ቆሞ መመልከት ላልፉት ዘመናት ካጠፉን ጋር እንደመተባብር ስለሚቆጠር ይህን መለእክት እንደ ሞዐ ተዋህዶ መሥራችና ንቁ አባል ለማስተላልፍ ተገደድኩ።  በመልእክቱ ይዘት ተጠያቂው እኔ ነኝ። ምንጯ ግን የማያችን ብርሃን ቅድስት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ናት።

ለጥላትም ለወዳጅም ግልጽ መሆን ያለበት ወሳኝ ጉዳይ፦

እኛ ኦርቶዶክሳውያን ከአሁን በኋላ የኦርቶዶክስን ጀግና ውጣት በህልውና ስም አንቀሳቅሶና ደሙን አፍስሶ መልሶ ጸረ ኦርቶዶክስ ሥርዓት በኢትዮጵያ ለማስቀጠል የሚሠራ ማንኛውንም ታጣቂ፣ የፖለቲካ ድርጅት፣ ትምሀርት፣ ስብከት፣ ትርክት፣ ፕሮፓጋንዳ የሚታገስ ጫንቃ አይኖረንም። ፋኖ የፋኖነትን እሤት ይዞ መገኘት እንጂ የፋኖን ልብስ ለብሶ በገዛ የኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብ ደም፣ ሀብት፣ ጀግንነት በመጠቀም በጸረ ኦርቶዶክስነት ርእዮት እያሰቡና እየተመሩ ለሥልጣን ጥማቸው የሚሠሩትን የባእዳን ምክር ተመጋቢዎች ማዘል አንችልም።   ላባችን፣ ደማችን፣ ሀብታችን፣ ጀግኖቻችን፣ ዕውቀታችን፣ ማኅበራዊ ተቋሞቻችን ሁሉ ለእሤቶቻችንና፣ ለግባችን፣ ለሰባዊ ክብር፣ ለፍትሕና ለአገር ባለቤታችን  ብቻና ብቻ እንጂ ለጠባብ የሥልጣን ፍተወት ማርኪያ እና ለባእዳን አጀንዳ መሳካት እንዲውል አንፈቅድም። 

ኦርቶዶክሳውያን ዲዳና ደንቆሮ አየደለንም። እንደባለጉዳይና የአገር ባለቤቶች እንጂ እንደ እንግዳና እንደ እቃ ከሚጠቀምብን ጋር አንቆምም።   ጅግንነታችንን ለጦርነት፣ ሃይማኖታችንን ለቱሪስት ሸቀጥነት እየተጥቀሚ ታሪካችንን  እንደጠላት፣ ማንነታችንን እንደ ውራሪ፣ አስተምህሮአችንን እንደ ኃላቀር፣ ነባርነታችንን እንድ ሥልጣኔ አደጋ ቆጥረው በትውሶ ርእዮት እንመራችኋልን፣ ነገር ግን ድማችሁን ለድላችን ግባት እናውለዋለን ከሚሉት የክፋት ልጆች ጋር በጠላትነት እንጂ በወዳጅነት መቆም ራስን በራስ እንደማጥፋት የሆንብናልና በቃ! በለናል።


 ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና እርሷን ያሉ ሁሉ ለምን ይሳደዳሉ?


ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ እግዚአብሔር በድንቅ ምስጢር የፈጸመውን የማዳን ጸጋ የተቀበለችና የያዘች ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ በክርስቶስ ደም ከተመሠረተች በኋላ በአራቱም አቅጣጫ እየተስፋፋች ትገኛለች፡፡ በዚህ ሁሉ ሂደት ውስጥ ብዙ ውጣ ውረዶችንም አሳልፋለች፡፡ ከዘመነ ሐዋርያት እስከ አሁኑ ዘመን ድረስ በየዘመኑ ከተነሱ ዐላውያን ነገሥታት፣ ከጣዖት አምልኮ ተከታዮችና የሐሰት መምህራኖቻቸው፣ የሐሰት ትርክት ከሚያራምዱ ግለሰቦችና ቡድኖች፣ ዐለምን እንዳሻቸው ለመግዛትና ለመቆጣጠር ከሚታገሉ ኃይሎች፣ ጥቅማችን ይነካብናል ከሚሉ ሰዎችና ቡድኖች፣ የርእዮተ ዓለም ጥመት ከገጠማቸው ሰዎችና ቡድኖች፣ እንዲሁም አጋንንታዊ ትምህርትን ከሚያራምዱ ኃይሎች ብዙ ፈተና ደርሶባታል፤ እየደረሰባትም ነው፡፡

የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ጠንካራ መሠረት ከተጣለባቸው አገራት መካከል ደግሞ አንዷ ኢትዮጵያ ናት፡፡ ኢትዮጵያ ሀገራችን እግዚአብሔርን በማምለክ ታሪከ ውስጥ ምናልባት ከሌላው ዐለም ለየት ባለ መልኩ ሊባል በሚችል ሁኔታ ሦስቱንም ሕግጋት ማለትም ሕገ ልቦናን፣ ሕገ ኦሪትን እና ሕገ ወንጌልን በመቀበል ያልተቆራረጠ የረጂም ዓመት የአምልኮተ እግዚአብሔር ታሪክ ያላት ብቸኛ ሀገር ናት፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከትንቢት ወደ ወንጌል በፈቃዷ የተሸጋገረች መሆኗ በመጽሐፍ ቅዱስ የተመሰከረ ነው፡፡ ሕዝቡን እንደ ድር እና ማግ አስተባብራ የያዘች፣ ጠንካራ ማኀበረሰብን የገነባች፣ ብሔራዊ ስሜትን የፈጠረች፣ መንፈሳዊና ማኀበራዊ እሴቶችን የሠራች እና ለክርስትናው ዓለም ብዙ ምልክትነት ያላት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ አብዛኛው የዓለም ክፍል በቅኝ ገዢ እና ተገዢነት ስሌት ውስጥ ሲገባ እና በዚህም ዘርፈ ብዙ የሆነ የማንነት ጠባሳ ጥሎ ሲያልፍ፣ ኦርቶዶክሳዊ በሆነው አስተምህሮ የተገነባው ሀገራዊ አስተሳሰብ ግን ለማንም ቅኝ ሳይገዛ እንዲሁም ማንንም ቅዥ ሳይገዛ የራሱን ጠብቆ የሌላውንም አክብሮ የኮራ የደራ ታሪክን ይዞ እንዲኖር ያደረገው የተዋሕዶ ክርስትና አስተምህሮ ነው፡፡ ይህ ዓለምን በራሳቸው ፍላጎት ለመዘወር ለሚሹ ኃይሎች አልመች ያለው ኦርቶዶክሳዊ ክርስትና በሁሉ በኩል እንዲገፋ እና ሰደት የታሪኩ አካል እንዲሆን እያደረገው ይገኛል፡፡

ይህ በኦርቶዶክሳዊነት ላይ የተጠነሰሰው ነጻነትንና ማንነትን የመውደድ ሰብእና ከኢትዮጵያ ባሻገር ወደ መላው አፍሪካ ተዛምቶ ኢትዮጵያዊነት የሚል አስተሳሰብን ወለደ፡፡ ኢትዮጵያዊነት የአፍሪካን ክብር ለመመለስ እና በአፍሪካውያን ውስጥ የሀገር ፍቅር ስሜትን ለመቅረጽ ሰፊ እይታ ያለው የፖለቲካ እና የእምነት ነፃነትን ለማበረታታት ከመፈለግ የመነጨ እንቅስቃሴ ነው። እንቅስቃሴው አፍሪካውያን ላይ ያለውን ጭቆና እና ብስጭት አውጥተው ያወሩበት መንገድ ነበር፡፡ በተለይም በቅኝ ገዥዎች የሚደረግን ማንኛውንም ዓይነት መለያየት የመቃወም መንገድ እና ለነፃነታቸው ለመታገል የተደረገ እንቅስቃሴ ነበር። 

ኢትዮጵያዊነት እንደ ንቅናቄ የተጀመረው እ.ኤ.አ. በ1880ዎቹ መጀመሪያ ላይ ሲሆን በተለይ መዝሙረ ዳዊት 68፡31 “ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” የሚለውን የእግዚብሔር ቃል ታሳቢ በማድረግ፣ ኢትዮጵያ ጥንታዊት ክርስትና ያላት እና ከአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች ነፃነቷን ያላስደፈረች ሀገር ለመሆን የበቃችው እውነተኛ ሃይማኖት ያላት በመሆኗ ነው ከሚል መረዳት የተነሣ ነበር፡፡ ይህ እንቅስቃሴ በአፍሪካ ምድር ሳይወሰን በመላው ዐለም ያሉ ጥቁር ሕዝቦች ሁሉ ለነጻነታቸው ብሎም ለህልውናቸው ለመታገል የተነቃቁበት ምክንያት ሆኗል፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያዊነት ለአፍሪካውያን መነቃቃትን ሲፈጥር ለቅኝ ገዢዎች ደግሞ የእግር እሳት ሆኖባቸዋል፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንደ ምልክት እና የትግል መነሻ ተደርጋ በጥቁሩ ዓለም ስለ ተወሰደች፣ ዓለምን በራሳቸው ቁጥጥር ሥር ለማስገባት እየሠሩ ያሉ ኃይሎች ኦርቶዶክሳት ቤተ ክርስቲያንን ማሳደድ የሴራ ፖለቲካቸው አንዱ አካል ማድረግ ከጀመሩ ቆይተዋል፡፡   

ስለዚህም ዐለምን ከመቆጣጠርና የምድርን ያልነተካ ሀብት ከመመዝበር አንጻር ኢትዮጵያ አገራችንን ዒላማቸው ያደረጉ ኃይሎች ቤተ ክርስቲያኒቱንም ዒላማቸው ማድረጋቸው የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ይህ አገሪቱን ለማፍረስ በመጀመሪያ ኦርቶዶክሳት ቤተ ክርስቲያንን ማፍረስ አለብን የሚለው ስልታቸው ደግሞ ፈርጀ ብዙ ጫናን ፈጠረ፡፡ ይህም ምዕራባውያን በአፍሪካ ላይ ይከተሉት የነበረውን ከፋፍሎ የመግዛትና የማዳከም ስልት በኢትዮጵያ ላይም ለመተግበር ዕንቅፋቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ናት ብለው በማመናቸው ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያኗ ለዘመናት የዘለቀ የአንድነት ትምህርትና ይህ የመሠረተው ማኅበረሰባዊ የአንድነት መስተጋብር ሥር ሰዶ ኢትዮጵያውያንን ድር እና ማግ በማድረግ አስተሳሰራ የያዘቻቸው ቤተ ክርስቲያኒኗ ናት ብለው ስለሚያምኑ ነው፡፡ ስለዚህም በዘመናዊ ትምህርት፣ በኦኮኖሚ አጋርነት ሽፋን እና በፓለቲካ ጣልቃ ገብነት ከ1960ዎቹ ጀምሮ በኢትዮጵያ ኦርቶዶከሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና በአስተምህሮዋ ላይ እንዲሁም ለዘመናት ባካበተቻቸው እሴቶቿ ላይ የረቀቀና የማያባራ ዘመቻ ተከፈተባት፡፡

በዚህ ጸረ ኦርቶዶክስ እሳቤ የተቃኘው ዘመናዊ ትምህርትና የተለያዩ የሐሰት ትርክቶች ትውልዱን በራሱ አኩሪ ታሪክና ማንነት ላይ ኃፍረትና ጥላቻ እንዲሰማው እያደረገ መጣ፡፡ የዚህ ማንነቱን ከጠላት አፍ የሰማ ትውልድ ተሳትፎም እስካሁን ያለውን የሀገሪቱን ፖለቲካ እየዘወረ እና እያመሰ አለ፡፡ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቅኝት እስካሁንም ከዚህ ትውልድ አስተሳሰብ ጥላ ስር መውጣት አለመቻሉ ብቻ ሳይሆን ኦርቶዶክስ ጠል የፖለቲካ አስተሳሰብ የፖለቲካው ባህል እንዲሆን አደረገ፡፡ 

ቅኝ ገዢዎች አፍሪካን ቅኝ ለመግዛት ኢትዮጵያዊነትን እና ኦርቶዶክሳዊነትን ማጥፋት ዋና ስልት አድርገው በመቁጠራቸው ከፍተኛ የማጥላላት ሥራ ሠሩበት፡፡ ይህ አሁንም እንደ ቀጠለ ነው፡፡ ከአድዋ ጦርነት ሽንፈት በኋላ ኃያላን ሀገራት ኢትዮጵያ በጦርነት የማትሸነፍበት ምክንያት ምንድን ነው? በሚል ጥያቄ ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ ይህን ጥያቄ ለመመለስም በማስተማር፣ በዲፕሎማሲ እና በሃይማኖት ማስፋፋት ስም ወደ አገራችን የገቡ ሰላዮቻቸው በየፈርጁ ኢትዮጵያ ልትዳከምበት እና ልትፈራርስበት የምትችልበትን መንገዶች አጥንተዉ ከደረሱበት መደምደሚያ አንዱ ለአገሪቱ ኃይል እና ሕይወት የምትሰጠው የኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት መሆኗን በጥናታቸው አረጋግጠዋል፡፡ እነዚህ አካላት አሠልጥነው በሚልኳቸውና ወደ ሥልጣን በሚያወጧቸው አገር በቀል ባንዳዎች አማካይነት ዛሬም ቤተ ክርስቲያኒቱ በከፍተኛ ስደት ላይ ትገኛለች፡፡ 


ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንና ኦርቶዶክሳዊ ዜጋ ዘ*ሩ እንዲጠፋ ለረዥም ግዜ የተሰራበት ምሥጢር ምንድ ነው?


ከውጭ ቅኝ ገዥዎችና በኃይል እምነት የሚያስፋፉቱ ወራሪዎች፥ ከውስጥ ጭንጋፎቹ ፖለቲከኞች፦ ደርግ፥ ማርክሲስት ፓርቲዎች፥ የጎሣ ነጻ አውጭዎችና የአሁኑ መንግሥት ለምን ኦርቶዶክስና አመራ ጠል ሆነ!

ኢትዮጵያ ጥርስ የገባችው የዓለምን ሁኔታ የቀየረው የአዳዲስ እምነትና ፍልስፍና በአውሮፓና በመካከለኛው ምሥራቅ ከመፈጠር ጋር ተያይዞ ሲሆን ዋናው ምክኒያት ሁሉንም ሰው ሰራሽና መላምታዊ 


አስተሳሰቦች ከኖኅ መርከብ እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት በአንድነት ሳትለዋወጥ በመያዟ ያሳየችው ጽናት ነው። ተላዋዋጭና አዲስነትን በጉልበት፥ በራስወዳድነት፥ የሰው ዘር በማጥፋትና ርስት በመቀማት፥ እምነትን በኃይል ለመጫን የሚሹ ሁሉ ኢትዮጵያን ጠላት አድርገው ፈረጇት። 


በዚህ መሠረት የቀዳሚ ታሪካዊ፥ ባህላዌ፥ እምነታዊና ፍጹም የነጻነት መሠረት ናቸው ብለው ያመኑትን አማራንና የሕገ ልቡና፥ የሕገ ኦሪትና የሐዲስ ኪዳናትን በአምላክ ሰው መሆን ተርጉማ ልጆቿን በተቻላት መጠን በመጠበቋ ጠላት ተደረገች። አገርን የወረረና አዲስ ነገር ለማስተዋወቅ የሞከረ ፖለቲከኛ ሁሉ ጥፋት የሚጀምረው ከኦርቶዶክስ ሲሆን፥ ኦርቶዶክስ ናቸው የሚላቸውን በተለይ አማራንና ሌሎች ማኅበረሰቦችን ዒላማ ያደርጋል። በዚህ ቱርክ፥ ደርቡሽ፥ ጣሊያን/ቫቲካን፥ ግብጽ፥ ዚያድ ባሬ፥ ማርክሲዝም፥ የጎሣ ነጻ አውጭዎችና የብልጽግና መንግሥት፥ ዉሀብያና የጀርመን ክርስትና ወራሽ የሆነው የኦነግ ወላጅ የግንቢ ፕሮትስታነት በሙሉ ጠላታቸው ያደረጉት ኦርቶዶክስንና አማራን ነው። 



አሁን የኦነግ-ኦሮሙማ-ብልጽግና መንግሥት አማራና ትግሬን፥ ጉራጌን የሴም ዘሮች በሚል ፈርጆና ሌሎች የኩሽ ዘር በሚል የዘር ማጥፋት ዱላውን ሰንዝሮአል።


በመሆኑም 

በረዥም የታሪክ ጉዞ፥ የአውሮፓና የአረብ፥ የሌሎእ ክፍለ ዓለማት እጅና ፍላጎት ያለበትን የኢትዮጵያን ውስብስብ ፈተና ለመፍታት የሕወሃትንና የኦነግን ልጅ ብልጽግናን ማሸነፍ ብቻ አይበቃም። የፋኖ ተጋድሎ ጅማሮ ብቻ ነው። ብዙ መንገድ፥ ጥልቅ ዕሳቤ፥ ጥበብ የሞላበት እርምጃ ይጠይቃል። በጥይት ለጊዜው ከሕወሃትና ከኦነግ-ኦሮሙማ የዘር ማጥፋት ዘመቻ መዳን ይቻላል። 


በውስጥና በውጭ የተቀናጀውንና ዘመናትን የተሻገረውን ኢትዮጵያ ጠል መረብ መበጣጠስ ተጨማሪ ሥራዎን ስለሚጠይቅ በጦር ሜዳ ድል መበረታታት አንጂ መዘናጋት አደጋው ብዙ ነው።

ለቀጣይ የታሰበው አስፈሪ ነው። ግን መፍራት ብቻ በቂ አይደለም፥ ፍርሃትን የሚያስቀር ተግባር ነገ ወይ ዛሬ ሳይሉ መጀመር ነው። ሁሉም በአቅሙና በጸጋው ማድረግ የሚችለው ነገር አለ!  በሚል የተጀመረውን የሞዐ ተዋህዶ ንቅናቄ  ከቤተ ክርስቲያን መቅደስ ኮብልለው ለብልጽግና መንግሥት ሎሌነት የገቡ ጸረ ኦርቶድክሳዊያን ምንደኞች ያለመልኩ መልክ ሰጥተው ኦሮቶድኮሳውያን በአድነት እናዳይቆሙ ከፍተኛ ፕሮፓጋንዳ ሠሩበት። የፕሮፓጋንዳ ፍሬ አፍርቶ በፋኖ መካከል በአንዳድ መሪዎች ተገልጸ።


በፋኖ ውስጥ ኦርቶዶክስ ክርስትናን ማሳደድ ከሕወሃታውያና ኦርንጋውያን አልፎ  ዘሩ እንዴት ታየ?

አሁን አስጊውን አደገኛው  ሆኖ የመጣው የአማራ ሕዝብ ይህልውና አደጋ ውስጥ ግበቷል፣ ኦሮቶዶክሳዊያን በመላው ኦሮምያና በኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ተጸኖ ስር የሚኖሩ እንደ ቤኒሻንጉልና አንዳንደ የደቡብ ዞኖች ውስጥኦርቶድኮስ ክርስትና በማፈናቅለ፣ ከመነት በማፍለስ፣ ማንነታቸውን በማስቀይር ሲመች በመግደል ማጽዳቱ ተጠናክሮ በቀጠለብት እና ይህን ሁኔታ ለመቀልበስና ህልውናና ለማረጋግጥ በተነሳው ፋኖ መካከል ሠርጎ የግባ ጸረ ኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ምልክት የሚያሳይ ሕዋስ ብቅ ማለቱ ነው። 

ይህ ጸረ ኦሮቶድክስ በምሆኑ ጸረ አማራና ጸረ ኢትዮጵያ ከመሆን ሊቀር ያማይችል ሕዋስ በቀጥታ በባእዳን ገንዝብ፣ ምክር፣ ለሥልጣን የማብቃት ተስፋ፣  የዲፕሎማሲ ድጋፍ ጓጉቶ የፋኖን ዋና ዓላማዎች፦ ማለትም የሰውን ክብር-ማስምለስና በ50 የሕወሃትና የኦነገ ጥምር  የጎሣዊ ዘረኝነት ፖከቲካ የዘር ማጥፋት ዒላማ የተደረገውን የአማራ ሕዝብና አማራዊ የሰባዊነት፣ የፍትሕና የእውነት እሤቶችን  በመታደግና ለዘለቂታዊ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ህልውና የሚያረጋግጥ  ሰዋዊ ሥራአት መመሥርትን ፈጽሞ ይሚቃርነ ነው።

የአማራ ታጋይ ወጣት መሰዋእትነቱ፣ መቁሰሉ፣ መሰደዱ፣ ወላጆቹን ጧሪና ቀባሪ አሳጥቶ መዘመቱ ከዚህ ሁሉ ለሚበለጠው የህልውና መርጋገጥ፣ ለክብረ-ሰብእ፣ ለእውነትና ለፍትሕ  ሲሆን፣ እንዚህ ነገሮች በሥጋ ቢጎዱም በንፍስ ማትረፊያ፣ የትውልድ ተስፋና የአገር መጽናት መሠረቶች ናቸው።  ይህን የነጻንተ፣ የአንድነት፣ የሰላም እና የሰባዊነት ዋስትና መሠረት የሚንደው በሞዐ ተዋህዶ የተግለጡትን 7 የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ክርስቲያኖች ጥያቄ በመቃረን   በአማራ ኮድነት ህልውናው እንዲያከትም ጉራጌውን፣ ኦሮሞውን፣ ወላይታውንና ጋሞውን፣ ትገሬውንና አማራውን ሳይመርጥ ለማጥፋት -- ቀደም ሲል ከ180 ዘመናት ለሚዘልቅ በውጭ ባእዳን   ሲሠራበት የቆየ፤ ከ50 ዓመታት ወዲህ ግን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥአድጎ  በጎሣ ነጻ አውጭዎች ሤራ፣ በተለይ በኦነግና የሕውሃት ጥምረት    “የከፋፍለህ ግዛና የአጥፋ” ስልት የሚካሄደውን የሚደግም ምልክት ፋኖ ውስጥ ታይቷል።

የጸረ-ኦርቶዶክስ ሕዋስ በፋኖ ውስጥ ለመኖሩ የሚከተሉትን ምልክቶች መጥቀሰ ይቻላል፦

1) ሕወሃትና ኦነጋውያን ሐሰትን ፈብረከው፣ የፈበረኩትን አሰራጭተው፣ የተሰራጨውን እንደ እውነት አጽንተው፣ ያጽኑትን ሐስት መሠረት በማድረግ ኢትዮጵያን ሲያቆስሉ፣ ሕዝቡን ሲከፋፍሉ፣ አምራና ኦርቶዶክስን አጣምረው ደም ሲያፈስሱ እንደኖሩበትና አሁን በብልጽግና በኩል እንዳስቀጥሉት ሁሉ --- በፋኖ ውስጥ የግል ጠባብ የሥልጣንና አምላክ የለሽ መረን የለቀቀ ፍተወታቸውን ለማሳካት፣ የህልውና ትግሉን በሐሰት በክለው፣ ሐሰታቸውን አመነውና አሳምነው “ፋኖን አንድ እንዳይሆን እነቅፋት የሆነው በገዚአብሔር የሚያምን፣ ዳዊት የሚያነግት፣ የሚጸልይና የሚቆርብ ታጋይና መሪ ነው፤ እኛ “ሲኩላር/አምላክ ይለሽ ትግል ነው ይመንታገለው” የሚሉ ሰዎች ድምጽ በጎጥ ወግንተኝነት፣ በላዋቂነት ጨለማና በገንዝብ ኃይል በሚነዷቸው ማኅበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ መሰማቱ፤

2) የነባር ነባር፣ ከዓለም ሰው ሁሉ ለይቶ አባታችን ኖኅን ከጥፋት ውሃ ካዳነው ሃይማኖትና ምግባር  ሰው ሆኖ ፍጹምነትንና እውነትን እስከገለጥልን የክርስትናችን መሠረትና የቤተ ክርስቲያናችን ራስ እስክ እኢየሱስ ክርስቶስ ድረስ ያለተቆራርጠ እንግዚአብሔራዊ የክብረ-ሰብእ፣ የፍትሕ፣ የእውነት፣ የነፍስ እርፍት እና የሥጋን ከርኵስ ፍተወት ተጋድሎ የማሽነፍ ሕይወትን የኢትዮጵያዊነት እሤት መገልጫ ያደረገጭውን ቤተ ክርስቲያን ጠላት የማደርግ እና በባእዳን ቀመር አምላክ የለሽ ፖልቲካ፣ ነባር-ጠል አዲስነትን፣ ርዥም ታሪክን ከኦነግ፣ ከሕወሃትና እነርሱን ከላኩት ባእዳን እኩል  ማንቋሸሽ ከአንዳድ  በማእራር ደርጃ ከሚገኙ ሰዎች ንግግርና  በሚዲያ ከሚሰራጩ መለእክቶች መርዳት መቻሉ፣

3) ኢትዮጵያውያን በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በባህልና በካባቢያዊ ትርከቶች ላይ በሚመሠረት ኑዑስ-ማንነት ሳይክፋፈሉ  በሰብአዊነት፣ በነጻነት፣ በአገር ሉዓላዊነትና ክበረ-ሰብእ  በጸና አንድነታቸው ድል ያደረጉት ዘረኛ የአውሮፓ ቅኝ ግዥና ባሪያ ፈንጋይ በርዥም ዘምነ በዘመናዊ ተምህርት ስም አእምሮ አጥቦ የሠራቸው ወገኖች   ሞዐ አንበሳ፣   ሰለሞናዊ ሥረወ መንግሥት፣ ክብረ ነገሥት፣ አማራ፣ ኦርቶዶክስ፣ አጼዎቹ፣ ጨቋኝና የነፍጠኛ፣   የቀድሞ ሥራዓት ናፋቂዎች  ወዘተ በሚል ትርክት የነባርነት በጭፍን  የሚጠሉ ኦነጋውያንና  ሕዋታውያን የሚመሩበትን የሚደገም ኃይል በፋኖ ውስጥ ለመፈጠሩ በሞዐ ተዋህዶ ላይ በሐሰት የተከፈተው ዘመቻ ያሳያል።

ፋኖነት የእውነትና የፍትሕ አምድ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ከሚያሳድዱ ሠርጎ ገቦች ይጽዳ!


“ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ--ያልዚያ ድንጋይ ነው ብለው የጥሉሃል፣ በግራቸውም የርግጡሃል” እንዲል ፋኖነት በቅድስና ፋኖ ሆኖ ለመገኘት ከቁማረተኞች፣ ከሢራ መሪዎችና ከፕሮፓጋንዳ ተቀላቢ ይባእዳን ተላላኪዎችና እሣቤ ራሱን ማዳን የጠብቅበታል።  ወይንም “ፋኖ” የሚለውን ስም ሰርዞ በቀጥታ “የአማራ ነጻ አውጭ” በሎ ራሱን በመሰይም አገር ከገነጠሉት፣ ለመገንጠለ እየታገሉ ቤተ ክርስቲያንና አማራን  የህልውና አደጋ ላይ ከታሉት እኩል ራሱን ከርክሞ በድንክነት፣ በጸረ-ሰባዊነት፣ በጸረ-ነባርነትና በጸር-አንድነት ራሱን የግለጽ።    ሤራኛም፣ ቁማርተኛም፣ ሐሰተኛም፣ በሥልጣን ፈተውት መምራትንም አቅፎ እየኖሮ “ፋኖ” በሉኝ ማለት ከሃዲውን የጨልማ አባት ሳጥናኤልን  የብርሃን መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በሉት እንደማለት ያለ ዓይናችሁን ጭፍኑና ላሞኛችሁ ጭዋታ ይሆናል። 

በዚህ መንገድ የሠሩት የመከራችን መፈልፈያ የጎሣ ነጻ አውጭዎችም ራሳቸውን የሚጠሩት 

“ነጻ አውጭ”፣ 

“የእኩልነትና የራስን ዕድል በራስ መወሰን ጠበቆጭ”፣ 

“የፍትሕ ታጋዮች”፣ 

“የተዛባ ታሪካ አራሚዎች”፣ 

“የልማት፣ የብልጽግና፣ የሥልጣኔ በር ክፋችና መሪዎች”፣ 

“የነጠላ ትርክት ማቃናትና የብዝኃነት መገለጽና ማበብ መሪዎች”

“በመፈቃቅድ ላይ የተመሠረት አንድነት አምጭዎች”

“ገነትን የመትመስል ‘የአዲሲቷ’ ኢትዮጵያ አዋላጆች” ---- ወዘተ  ጭምብል ለብሰው ነው --- በመተግባር የሰውነትና የአገር ጠላት፣ የህልውና አደጋ ሆነው አሁን አማራ የሚሞትበትን፣ የኦሮቶዶክስ ክርስቲያን ዘር የሚጠፋበትን ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ስነ-ልቦናዊ ምህዳር የፈጠሩት። አሁንም ፋኖነትን በመጥለፍ ጸረ-ነባር የማድረግ ሂደት እንዳለ ታውቆ እና ይህን የሚመሩ ሠርጎገብ አመራሮች በየደርጃው ተፈትሸው እርምት ካልተደረግ መከርኛው አማራና ኦሮቶድክስ ክርሲያን ለሌላ እስካሁኑ ይከፋ የህልውና አደጋ እንደሚጋለጥ ሳይታለም የተፈታ ነው።

ለመላው የአማራ ሕዝብ፣ ለመላው ኦርቶድክሳዊ ክርስቲያን፣ ለመላው በሰው ክቡርነት፣ በፍትሕ፣ በእውነት፣ በአገር ፍጹም  አንድነት የምታምኑ የማንናዉም ባህልና እምነት ወገን ለሆናችሁ ኢትዮጵያውያን፣ ከሁሉ በላይ በእንዚህ በተጠቀሱት እሤቶች በማመናችሁና የመጣውን የህልውና አደጋ ለማስወገድ ራሳችሁን ለመስዋእትነት ላሰለፋችሁ የፋኖ ሠራዊትና እውነትኛ መሪዎች የሚከተለውን ወንድማዊ መልእክት አስተላልፌአለሁ። ይህን መልእክት ችላ በማለት፣ በሤራ፣ በብልጣብልጥነት፣ በግል ጠባብ ፍላጎቶችና በባእዳን ምክር ቤተ ክርስቲያንን ከሚያሳድድ አስተሣስብ ጋር የምትቆምይ ሁሉ የአማራን ሕዝብ የህልውና አደጋ ከማስወድ በተቃራኒ ለዘልቄታዊ የማያባራ መከራ በሚዳርግ መሥመር ላይ መሆናችሁን አትጠራጠሩ።

በአማራ ሕዝብ መካከል የጸረ ኦርቶዶክስ ሕዋስ ተፈጥሮ ችግር ያልሆኑውን ነገር ችግር ነው ብሎ አጀንዳ መፍጠር ምንጩ  ከየት እንደሆነ መመርመር   የሁላችሁ ድርሻ ስለሆነ ለጠላት እያገለገላችሁና የራሳችሁን ክቡር ተጋድሎ እያረከሳችሁ መሆኑን አስታውሱት፤

ይህችን የተለመደች ከሕወሃትና ከኦነግ የተወረሰች ቁማርተኝነት፣ ሐሰት ፈብርኮ መክሰስ፣ ክሱን ዳኛም መስካሪም ሆኖ የመቆም፣ ገድሎ ሞትኩ ማለት፣ በድሎ ተበደልኩ ማለትን በቀጥጣ በምቅሰም   እንዴት በተቃራኒው  ቅድስና እውነት፣ ፍትህና ሰብአዊነት ብቻ በሚገልጸው ፋኖነት ላይ ለማጣባቅ እንደተሞከር መርምራችሁ ድረሱበትና መፍትሔ ስጡት፣

በሞዐ ተዋህዶ ንቅናቄ አንጻር ሐሰት የሚዘሩ ሁሉ ጸረ-ኦርቶዶክስ ክርስትና ከሆነው የአገር ውስጥና የውጭ ኃያላት ጋር ትብብር የሚያደርግ፣ ለግል ሥልጣኑ ሲል የሚሊዮኖችን ደም የሚያባክን እኵይ ራስ ወዳድ (ናርሲሲስት) ግለስቦች፣    ሤረኞች እነማን ናቸው? የማንን አጀንዳ ነው የተሸከሙት? በማነው የሚዘውሩት? ብሎ ጠይቆ  መፍትሔ መስጠት መሬት ላይ ያላችሁ እና በፈሪሃ እግዚአብሔር ህሊናችሁን የምተገዙ እውነተኛ  ታጋዮችና መሪዎች ኃላፊነት በመሆኑ በፕሮፓጋንዳ ክርስትና ከማሳደድ እንድትቆጠቡ፣ ራሳችሁን ይህን ካደርጉና ከውደቁ ከደርግ፣ ከሕወሃት፣ ብቅርቡ ከሚወድቀው የሁልቱ ድቅል ክብልጽግና ተራ እናድትገኙ መርምሮ መስተካከል በእጃችሁ ነው፤

ይህን ማድረግ የማይችል ታጋይ እና የፋኖ ምሪ በከንቱ እየተጎተተ መስዋእትነቱን እንዳያባክን  እና ተጠልቅፎ ለህልውናና ለፍትሕ፣ ለሰባዊነትና ለእውነት፣ ለአገርና ለሕዝብ ሰላም የጀመረውን ክቡ ተጋድሎ ለጸረ ኦርቶዶክስ አምላክ የለሾች፣ ጎጠኞች፣ የአማራ አንድነት ጠላቶች፣ የጣሊያንና የቅኝ ገዥ ከፋፍለህ ግዛ ስልት ወራሾች  በከንቱ በማገለገል  ላይ የተጠመደና ራሱን ብራሱ ለማጥፋት “ሞዐ ተዋህዶ የተጋድሎአችህን እነቅፋት ነው” በሚል ብያኔ  ሳያውቀው “እግዚአብሔር አያስፈልገንም፣ ነባርነተ ጠላታችን ነው፣ አዲስነት መንግሥተ ሰማያችን ነው” ከኢሊ ስሜት ቀሰቃስ የፕሮፓጋንዳ ቀላቢ ናርሲሲስቶች  የአስተሳሰብ ባሪያና ጠፊ ነው።    

በሐስት አጀንዳ የመፍጠር፣ የመነታርከና ዓላማን የማሳት የጠላት ሤራ ድካም እንድታርፉ፣ በሤረኞችና ቁማርተኞች እንዳትበሉ ይህን እንደሚገባ በማሰተዋልና በመረጋጋት  ተመካከሩ። 

ጸረ ኦርቶዶክስ ክርስትና የሆኑ ሠርጎ ገቦችና የጠላት ሠራተኞችን መንጥሮ መለየትና ማርም ካልቻላችሁ የምታሳኩት አንዳች ድል እንደማይኖር ለመበየን ምንም ዕውቅትና ነብይነት አይጠይቅም።  ድል ማለት አሁን ታጥቆ አማራንና ኦርቶዶክስ ክርስቲያንን የሚፈጅ የበልጽግና መንግሥትና በሥሩ የተኮለኮሉ ዘርኞችና ጽንፈኛ ኃይሎችን ከሥልጣን ማሰወግድ ብቻ ከመሰላችሁ እጅጉን ተሳስታችኋል። ይህ በጠመንጃ የሚፋለም ጠላትን ማሸንፍ የመጀምሪያው እና ቁልፍ የድል በር እንጂ ለህልውና፣ ለክበረ-ሰብእ፣ ለፍትሐዊ ማኅበረስብ፣ ለሉዓላዊት አንዲት የሰላም አገር መፈጠር፣ ለማራ ከባህር ማዶ እስክ ሰፈር ለተፈጠረልት እሾኽ መነቀል ዋስትና አየደለም።   የሞዐ ተዋህዶ ነቅናቄ ከፋኖ ነቀናቄ አስቀድሞ የከርስቲያንን መግፋትና ሥራአታዊና መንግሥታዊ የዘር ማጥፋት  ተገንዝቦ የሚከተሉትን 7 ጠያቂዎች በኦርቶዶክሳውያን አማሮች፣ ተግሬዎች፣ ኦሮሞዎች፣ ጉራጌዎች፣ ጋሞዎች ወዝተ አንጻር ያነሳ ፋና ወጊና ፍጹም በሁሉም ፍትሕና ከበረ-ሰብእ በሚሹ እመነቶችና ባህሎች፣ በተለይ በማራ ፋኒዎች መሪ እ የትግል ጥያቄ መሆን የነበረበት ነው።  አለመታደል ሆኖ ጸረ ኦርቶዶክስ ሕዋስ በፋኖ ውስጥ በመብቅሉ “ሞዐ ተዋህዶ” በነቅፋትነት ተወቀሰ።   “ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ--ያልዚያ ድንጋይ ነው ብለው የጥሉሃል፣ በግራቸውም የርግጡሃል”  እንድሚባለው ፋኖ ለራሱ ሲል ኦርቶዶክሳዊነትን በቻ ሳይሆን ማንኛውንም አስተሳስብ መመዝን የሚገባው በነባርነት ላይ ቆሞ፣ ከጥላት ምክርና ከራስ ወዳድ ሥልጣን ናፋቂ ቆጠኞች ራሱን አርቆ፣ በህልውናና ፍትሕ፣ ብክብረ-ስብና እውነት ሚዛን ራሱን ይምራ። ይህን ካላደርገና የቤተ ክርስቲያን ፍላጎት ተቃራኒ ከሆን በእግዚአብሔር የተጠላ፣ አማራን ታይቶ ወደማይታወቅ ዘለቄታዊ ጥፋት የሚመራ አደገኛ መርዝ ነው። 

ኢትዮጵያን ለዘመናት ለማጥፋት በዚህ ምስል እነደታይው ሲጋድሉ ለኖሩ ባእዳን እሳቤ የሚሠራ ፋኖና የፋኖ መሪ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጠላት ተብሎ ሊፈረጅ ይገባዋል።


ለማታውቁት   የሞዐ ተዋህዶ ንቅናቄ ያቀረባቸው የኦርቶዶክሳውያን ጥያቄዎች የሚከትሉት ናቸው፡

7ቱ ጥያቄዎችና ማብራሪያዎቻቸው 

ጥያቄ 1፦ በሕገ-መንግሥት፣ በፖለቲካ ማኒፌስቶ፣ በመደበኛ ትምህርት፣ በሚዲያና መሰል መንገዶች ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮንና ኦርቶዶክሳዊያንን ለጥቃት የሚጋልጡ መልዕክቶች በአስቸኳይ በሕግ እንዲታገዱ ።

የተዛባ ታሪካዊ ግኑኝነት የሚል ቃል የተጠቀሙት ሕገ-ምንግሥቱን ያዘጋጁ የብሔር ፖለቲከኞች ናቸው።

የብሔር ፖለቲከኞች የተዛባ የሚሉት በሕገ መንግሥት ያጸኑት ታሪክ አላቸው፤

ኮሚኒስቶች ለሺ ዘመናት እሥራት ውስጥ ነበረች እንድተፈታ የቀደመውን ማጥፋት አለብን ይላሉ፤

በዚህ መሠረት ትምህርቱን፣ኪነቱን፣ ሚዲያውን፣ መዋቅሩን ተቆጣጠሩት፣ “ተዛባ” የባለው “ታሪክ” ከታሪካዊት ኦርቶዶክስ ክርስትና ክርስቲያን ማኅበረሰብ፣ ቅርሥ፣ ሀብት፣ ታሪካዊ ጀግኖች፣ መጽሐፍት፣ አስተመህሮ ጋር ተጣምሮ የማስወገድ ዒላማ ተደረገ፤

ኦርቶዶክሳዊነት ሀብት ለማደለብ፣ ለዲሞክራሲ የአስተዳደር ሥርዓት፣ ለዘመናዊ አኗኗር፣ ለሥራ ስነ-ምግባር እንቅፋት የሆነ፣   የድኽነት ምክኒያት ናት፤ በቁስ የደኸየ በሰማይም ተስፋ የለውም የሚል አስተምህሮ የሚያራምዱ ብዙዎችን አሳስተው ኦርቶዶክስ-ጠል ለማድረግ ሠሩ፤ ከኮምኒስት የመደብ፣ የብሔረሰብ እና የተጨቋኝ-ጨቋኝ የፖለቲካ ትግል ፅንሰ ሀሳብ ጀምሮ እሰክ ብልጽግ ፓርቲ እስተሳብ ድረስ ሁሉም ኦርቶዶክሳዊነትን ዒላማ አደረጉ፤ የአሁኑ ዘመን ፖለቲካም ኦርቶዶክሳዊና አገር በቀል እሴቶችን በጀርመኑ ሉተርና በማክስ ዌበር ትምህርት መተካት መበልጸግን እንደሚያስገኝ ይናገራሉ።   ከዚያ ለውጥ ሁሉ ነባሩን ማጥፋት ወደሚል ያዘነብላሉ፣

በውስጥና በውጭ ይህን ዝንባሌ ተከትለው ነባር ኦረቶዶክሳዊነት ላይ የተመሠረቱ ኢትዮጵያዊ እሴቶችንና ክርስቲያኖችን በማጥፋት የሚሳተፉ   ሌሎች እምነቶችና ባህሎችም  የ[ፖለቲካውን ዝንባሌ ተከትለው ኦርቶዶክሳዊነትን በመዳከም  ጥቃቱን ይቀጥላሉ፣ ቀጥለዋል። 

ጥያቄ 2፦ ኦርቶዶክሳዊያንን ለይቶ ከሥራ፣ ከመንግሥት ኃላፊነት፣ ከሀብት ማፍራት እድሎች የሚያገል ከቀበሌ እስከ ፌደራል የተዘረጋው ሃይማኖታዊ መንግሥትና መዋቅር በአስቸኳይ እንዲቆምና  ሃይማኖታዊ ሳይሆን ሕዝባዊ መሆኑን በተግባር እንዲያረጋግጥ  ።

o በርእዮት እና ደጋፊ ትርክት ላይ የተመሠረተ የኦርቶዶክሳዊነት ጥላቻን በተግባር ለመተርጎም እንደ ምእራባዊያን የፌሚኒስት (የሴታዊት) ፖለቲካ “ካሣዊ ድረጊት (አፊርማቲቭ አክሽን) በሚል ኦርቶዶክሳዊያንን ከአገራዊ ጥቅም ማገድ ተጀመረ፤ የገጠር መሬት፣ የከተማ የንግድ ቤቶች፣ የትምህርትና የሥራ እድል፣ የመንግሥት ቁልፍ የሥልጣን ቦታዎች፣ የሚዲያ፣ የመረጃ፣ የፋይናንስ፣ ወዘተ መዋቅራት የኦርቶስ ክርስቲያን ዜጋን ተሳትፎ በግልጽ በሚታይ ደረጃ ከሕዝቡ ብዛት በማይመጣጠን ደረጃ ቀነሰ።

o የቱሪዝም ምልክቶች ለዓለም ኢግዚብሽን ሲቀርቡ የኦርቶዶክስ በዝቷል ብለው በቅዱስ ላሉበላ ድንቅ ሕንጻዎች መትክ ቁልል እና ትክል ድንጋይ፣ ዋሊያና ዝንጀሮ ወይንም ሉሲ አጥንት ምሥል አንዲቀርብ የሚከራከሩ የባህልና የቱሪዝም ኤክስፐርቶች ይመደባሉ 

o ሃይማኖት ማለት መጽሐፍ ቅዱስና ቁራን ላይ መመሥረት ብቻ አይደለም

o ርእዮት፣ ባህል፣ ፖለቲካ፣ --- ራሱ አምላክ ሰው ሆኖ ካስተማረው በላይ ራሱን ከፍ የሚያደርግና ለመተካት የሚሠራ ሁሉ ሃማኖታዊ ነው

o መንግሥት ሃይማኖታዊ የሚባለው ምን ሲሆን 

ሕግን፣ ትምህርትን፣ ኪነትን፣ ምልክቶችን፣ ከአንድ የተወሰ አስተምህሮ ወስዶ ሌላውን ለመተካት የሚሠራ ከሆነ 

የሕዝቡን ቁጥር ያላገናዘበ የሥልጣን ክፍፍል ተደርጎ የተወሰኑት ከተገፉ --- 

ሕዝባዊ ሲሆን መሪዎቹ የራሳቸውን እምነትና ርእዮት እንደያዙ የሚመሩትን ሕዝብ ብዝኃ እምነት፣ ብዝኃ ባህል፣ ብዝሃ ፍላጎት ማዕከላዊ ጋርዮሻዊ ነጥብ ፈልጎና፣ 

o “ብልፅግና” የተባለው ከምዕረባዊያን ውሱን የፕሮቴስታንት ሴክት የተቀዳ የአሁኑ መንግሥት መመወሪያ ሴኩላር አይደለም። ለኢትዮጵያነ ባህሎች፣እምነቶችና እሴቶች ኤስማማም።  በተለይ ኦርቶዶክስ እና ማንኛውምን ነባር እሴቶች የሚጠላና እንደ ኮሚኒዝም በግዴታ ሕዝቡን መለወጥ የሚሞክር ርእዮተ ዓለም ነው። \ ለዚህ ማሥረጃው፡- (1) የመደመር መፅሀፍ አጠቃላይ ይዘት፣ (2) የብልፅግና ማሰልጠኛ፣  (3) የፓርቲው ሎጎ፣  (4) የባለስልጣናቱ ማነነት ከነባር ኢትዮጵያዊ እሴት የራቁ ሰዎች መመረጥ (ኦርቶዶክስ-ጠልነት)፣ (5) በንግግር፣ በአምልኮ ሥርዓት፣ በሚጠቀሙት ዜቤዎች ሁሉ ምዕራባዊና ወቅታዊነት፣ ብልጭልጭና ነባር-ጠልነትን ማንፀባረቅ፣ (6) ጨካኔና ሐፍረተ-ቢስነት፡-ለሰው ልጆች ሞትና ስደት ድንታ ማጣት፣  (7) የፓርቲው ስያሜው የብልፅግና መፅሀፍ ቅዱስ መመሪያዎች እና  ስርአት መሆን፣ (8)  ድረጅታዊ መዋቅር ሳይሆን ኃይማኖታዊ መምሰሉ እና በሁሉ እንቅስቃሴው  ከኃይማኖታዊ ተቁዋማት ጋር ተፎካካሪ መምሰሉ፣ (9)  በህልም እና በትንቢት መመራት፣ (10) በኦርቶዶክሳውያን ላይ የተፈፀመው ጥፋት በቀጥታ መርዳትና ፍትሕ መንፈግ፣  (11) በየደረጃውና በጊዜ ሂደት ሀገር አፍራሽ ሁኔታዎች መጨመር፣ (12)  ኦርቶዶክስን  ለማጥፋት  በኃላ ቀርነት፣ በጨቋኝነት መክሰስ፣ ቦታዋን መንጥቅ፣ በትምህርት ሥረዓትና በሕግ ደረጃ ማፈንና ማጥቃት ኦርቶዶክሳዊያን ታሪካዊያን ለአገር አንድነትና ነፃነት የደከሙትን ስም ማጥፋት፣ ቤተ ክህነትን በብሔር ዘውግ አንዲከፋፈል ክርስቶሳዊ ማንነትን በንዑስ ማንነት በሚለውጡ ምንደኞች ማመስ 

ጥያቄ 3፦ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን  በቋንቋና በተለያዩ ዘውጎች   ለመከፋፈል የሚደረገው  ፖለቲካዊ ጥረት፣ በጥናትና በምርምር ስም የሚደረጉ የመከፋፈል ዘመቻዎች እና ተግባራት  እንዲታገዱ።

ቤተክርስቲያን በክርስቶስ አንድ ያደረገችውን የጥምቀት ልጅ በሥጋ ልጅነትና በስሑት ርእዮት ማሳትና መበተን

የተበተነውንና በንዑስ ማንነት የተሰለፈውን አንዱን ደግፎ ሌላው ነቅፎና ገፍቶ ማፋጀት

መለያየቱ ዘለቄታዊና ሥር-ነቀል እንዲሆን ከውጭ ጠላት ጋር በመተባበር ሐሰተኛ ትርክትና የፖለቲካ ትንተናዎችን መጻፍና ማሳተም፣ ድጋፍ ሰጭ ፖሊሲዎች ማውጣት፣ ኦርቶዶክስን አግለለው የሚሠሩ የቴሌዥናና ሌለቾ ሚዲዎች ማስፋፋት

አገራዊ የኢኮኖሚ ችግር፣ የፖለቲካ ውጥንቅጥ፣ የማኅበረሰብ መፍረስና በፖለቲካ ሥርዓት አስተዳደር ብልሽ ወይንም መቃናት ሊጠፉና ሊስተካከሉ የሚገቡትን ሁኔታዎች ከኦርቶዶክስ ጋር ማገናኘት

ጥያቄ 4፡ -በኦርቶዶክሳዊያን ላይ ያነጣጠሩ የአካል፣ የሥነ-ልቦና፣ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ፣ የፖለቲካ፣ የማፈናቀል፣ ከአገራዊ ተሳትፎ የመገለልና የፍጅት ጥቃቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ።

ከጂጂጋ እስከ አዲስ አባባ፣ ከባሌ እስከ ወለጋና ቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ ከአጣዩ እስከ ጂማና መቱ የተዘረጋ ምንግሥታዊ ኦርቶዶክሶችን የማፈናቀል ሂደት፣ ኦርቶዶክሶችን የማድኸየት፣ ከምንግሥት ኃላፊንተ ውጭ ማደረግ፣ 

ጭፍጨፋና ማሳቀቅ

ካህናትን መግደል

ከልማት ግብአት አድልዎችና ልዩ ልዩ ቁሳዊ ትቅም ከእምንተ ማስወጣት

የአገልግሎት ቦታዎችን፡- ገዳማት፣ የቤተክርስቲያን ቦታዎቸ፣ የመስቀልና የጥምቀተ ባሕር ቦታዎችን  በቀጥታ፣ ሲያስፈልግ ሌሎችን አደራጅቶ በመላክማስነጠቅ

ጥያቄ 5 ፦ እስከ አሁን የተፈጸመው ጥቃት በዝርዝር ተገልጾ አጥፊዎች ለሕግ እንዲቀርቡ እና የተጎዱት እንዲካሡ።

በደርግ መውደቂያ ዋዜማ ኢሕአዴግና ኦነግ አሶሳ ሲደርሱ ከፈጸሙት ግድያ ጀምሮ በበደኖና አርባ ጉጉ፣ በወተርና በዶዶላ፣ በቤኒሻንጉልና በወለጋ፣ በቡራዩና በአጣዬ ወዘተ የቀጠለው ለይቶ የማጥቃት ሂደት ትኩረቱ ኦርቶዶክስ ላይ ቢሆንም ክርስቲያን ተባብሮ እንዳይከላከል በአማራ ብሔር ስም “ነፍጠኛ” በሚል ኮድ ነው። 

ባለፉት 31 ዓመታት በተለይ ባለፉት 4 ዓመታት በእቅድ የተካሄደው ማፈናቀልና ግድያ

እየተካሄደ ያለው ኦርቶዶክስን የመግፋት መንግሥታዊና መዋቅራዊ ትቃት በዝርዝር ታውቆ መፍትሔ አልተሰጠውም--- ይሰጠው--- ቀጣይነቱ ይገታ

ጥያቄ 6 ፦ በመላው አገሪቱ የተፈናቀሉ ኦርቶዶክሳዊያን ወደ ቀደመ ቦታቸው  እንዲመለሱ።

የአገሪቱን የአሠፋፈር ስብጥር ከኦርቶዶክሳዊያን ለማጽዳት በርእዮተ ዓለምና በተለያዩ እምነቶችና ባህሎች ጥምረት ከፍተኛ ማፈናቀልና ማሳደድ እየተካሄደ ነው። ይህ የሚስተካከለው የተሳደዱት ወደ ነበሩበት ሲመለሱ፣ ለደረሰባቸው ጉዳት ሲካሱና ወደተስተካከል ኑሮ፣ ማኅባረዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ሲመለሱ ብቻ ነው!  ይደረግ

ጥያቄ 7 ፦ “አዲሲቷ ኢትዮጵያ” በሚል ሽፋን ኦርቶዶክሳዊ አሻራዎችን የመደለዝ ፖለቲካዊ ሂደት በአስቸኳይ እንዲገታ እና በግልጽ ይቅርታ ተጠይቆ እርምት እንዲወሰድ።  

የሃይማኖት አሻራ መገለጫዎች ከቤተ መቅደስ ውች በሕዝብ ባህል፣ ጠባይ፣ ቁሳዊና የማይዳሰሱ ቅርሶች፣ ድመፀትና ኪነጥበብ ይገለጣል። እንዲሁም የእምነቱ ተከታዮች ያፈሯቸው የጦር ሜዳ ጀግኖች፣ የአስተዳደርና የአመራር አቅማቸው ለሰው ልጆች ነፃነት አስተዋጽኦ ባደረጉ፣ ለአገር አንድነትና የህዝቦች ውሕደት አመራር በሰጡ፣ ውስብስብ ፖለቲከዊና ዲፕሎማሰሳዊ ጥያቄዎችን በመለሱ ዜጎች ይወከላል። 

የሃይማኖት አሻራ በአስተዳደር፣ በሕግ፣ በባሕልና በማኅበራዊ የኑሮ ዘይቤም ይገለጣል።

አዲሲቷ ኢትዮጵያ ከላይ የተገለጡትን አሻራዎች ሁሉ ለመዋጋት ቀዳሚውን የማትለሸትና የማውደም፣ ተቃራናዊውን የማግንና አዳዲስ የመትከል፣ የሐሰት ትርክትን የማሰራጨት፣ የመደበኛ ትምህርት ይዘትን በሐሰተኛ ትርክት የመበከል፣ ምልክቶችን የመድምሰስ ሥራ ላይ በተጠመዱ ፖለቲከኞች ትመራለች።

ይህ ሂደት ቆሞ በእውቀት፣ በማስተዋል፣ በሁሉም ዜጎች የእኩል ተሳትፎ አገር ይመራ! ኦርቶዶክስን ማጥቃት ይቁም ነው!


የአደራ ቃል፦
ለፋኖ ሠራዊት፣ ለፋኖ መሪዎች፣ ለኦርቶዶክሳውያን ማኅበረስቦች ሁሉ የተላክ የእኔ መልእክት ነው።
ያጋሩት፣ የወያዩበት፣ ይሞግቱት።
ዓይናችንን በመክፈትና "በእውነት እንጂ በመንጋነትና በጫጫታ፣ በቁማርተኝነትና በማጭበርበር ፣ በባእዳን ምክርና እርዳት ህልውናችንን ማርጋግጥ አንችልም " በሚል መንፈሰ በፍቅርና በእውነት፤ የሰው-ክብርን እና ፍትሕን ማዕከል ያደረገ ክርከር እናድርግ።
አእምሮን ከሚያደበዝዝ፣ ሚዛናዊ ዕሳቤን ከሚገድብ፣ የእግዚአብሔርን እውነት እንድንክድ፣ የራሳችን የፍጡር ጀግና በህሊናችን ምትክ እንድናምን የሚያደርግ መንጋነትን እንዋጋ። ሁሉን በማስተዋል እናድርግ።
ጭፍን መንጋነት ከሚፈጥር ጎጠኝነት፣ ጉዳይን ትቶ ግለሶቦችን መከተል፣ ሰብአዊነትን አዋርዶ በቡድን እውርነት የሐሰት ትርክትን መሰባስቢያ ማድረግ፣ የማያውቁትን አዲስነትን እየተመኙ ነባርነትን መጥላት —- ያመጣብንን እና እየተካሄደ ያለውን የዘር ማጥፋት ሥርዓት ለማሸነፍ እኛም ጠላትን ከመምሰልና ከመውረስ ታቅበን በራስ በመተማመን ክርስቲያናዊ መንፈስ እንነጋገር። አደራ!!!! እላለሁ

ወደ ዚህ ቻናል ገብተው ይወያዩ

https://t.me/+wWBt4kzOx_ljOTI0

https://www.facebook.com/fwakie

https://www.youtube.com/@Orthodox_Secular_Fant


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

የሐሰት ትርክት ኦነጋውያንና የሕወሃታውያ የጋራ ስልት ከነግሥታት ወደ ተራ ግለሰቦች

✏️ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።  እርሱ ይመስገን። ምድራችንን #በደም #ያጨቀየው $ህሊና #የነሳን ፣ #ልቦናችንን #ያጨለመን ፣ #ሰብእናችንን ያዋረደው:- 👉 የሕወሐታውያንናንየኦነጋውያን የንዑስ ማንነት የጎሣ ፖለቲካ የደንቆሮ ርእዮትና፣ 👉 መርዛማን ጥላቻን ለ፶ ዘመናት ያከፋፈሉት የሐሰት ትርክት ናቸው። ✏️እንደ ዳግማዊ #ምንልክ ያሉ   ከዋክብት መሪዎች፣ እንደራሴቻቸው፣ ደጃዝማቾችና ቀኝና ግራ አዝማቾቻቸው  ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ብዙ ውለታ ውለውልናል:- 👉 በዘመነ ኦቶማንና አውሮፓ፣ በዘመነ መሳፍንት የተበታተነውን እና የተቆነጻጸለውን፣ ጎሠኛ የአርብቶ አደሮች  መሬት ፍለጋ  የደመሰሱትን ክርስቲያናዊ የግዕዝ/የነፃነት ሥልጣኔ አሻራ እንዲያገግም ደክመውልናል፤ 👉 የጥንት አገርን እና ሕዝቦችን   በከፊልም ቢሆን በመሰብሰብ  ጠንካራና ብቸኛ የነጭ ቅኝነትንና ባርነትን በመከላከል፣ ከኦቶማን ቱርክ ወር ትናንት ውስጥ ጥረኛ  አህመድ ግራኝ በመጋደል  ልዩ የነጻነት ማንነት ያላትን አገር ብበቸኝነት በዓለም ካርታንላይ አቆይተዋል፤ 👉 የሬማ ግዛት በጎሣ ተብልቶ ፲ ትንንሽ ሲሆን ከበበባውን ተቋቁማ በዝኃነታችን በተመጋጋቢ አንድነት ከ፹ በላይብቋንቋ፣ ከዓለም ትልልቅ እምነቶች ክትስትናን ፣ ይሁዲን፣ እስልምናን፣ የእረማውያንን ቅሪት የሆኑ የባህል እምነቶችን ሁሉን ይዛ በአውሮፓ በአርብ አምሳል ሳትሠራ ለእኛ አቀብዋል፤ 👉 ወያኔና ኦነግ፣ ገንጣዩ ሻዕብያ፣ ከሃዲው የማርክሲስት የአእምሮ  ባሪያን ስብስብ  እስኪፈትናት ድረስ ራሷን የቻለች አገር እንድንፈጥር ያስተባበሩን ነገስታት የተመሰገኑ ናቸው። አገር ሲያረጅ ጃርት ያብቅላል እንዱሉ: መል...