ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

በዓለም አቅፍ ደረጃ እና በኢትዮጵያ በተለይ ሁኔታ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ለምን የጥቃት ዒላማ ሆነች?


ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ዒላማ የሆነችባቸው ምክንያቶችና ጠላቶቿ ብዙ ቢሆኑም ከመሠረቱ እንዴት የዓለም ዐቀፍ ተቋማትና የቀድሞ የቅኝ ገዥ አገራት በእንድነት ሳይለያዩ ጠላት ሆኑባት? የሚለው ጥያቄ በከፊልም ቢሆን ኦርቶዶክሳዊነትና የሠይጣን መንግሥት በሚለው መጽሓፌ መልስ አግኝቷል። መጽሐፉ የተረጎምኩትና አንዳንድ መረጃዎችን ከግሌ ምርምር የጨመርኩበት ነው። ሙሉውን አንብቡት። 

አንዱ መዕራፍ እዚህ ላይ ለማሳያ አስቀምቼአለሁ ---


ምዕራፍ ሁለት ~ የተባበሩት መንግሥታት - የተ.መ. (UN)


ሚያዚያ 17/1937 (25th April, 1945) በሳን ፍራንሲስኮ የሃምሳ ሀገራት ልዑካን የተባበሩት መንግሥታት የዓለም አቀፍ ድርጅት አንድነት (United Nations Conference on International Organisation) ብለው በሰየሙት ስብሰባ ተገናኙ። ከዘጠኝ ሳምንታት ኃይለኛ ውይይት በኃላ ባለ አሥር ሺህ ቃል ቻርተር በሁሉም ልዑካን ፀድቆ አለፈ። ልክ በአራት ወሩ ጥቅምት 14 (October 24th) አባላቱ ሁሉ ከተፈራረሙ በኋላ የተባበሩት መንግሥታት በይፋ ተቋቋመ። የዚህ ድርጅት ርእይ በጥቅሉ “ሰብዓዊነትን በአንድ ጎጆ” (“humanity under one roof”) እና በመሳሰሉት መልካቸውን ባሳመሩና መልካም አስተሣሰብ ያላቸው ሰዎች በምንም መልኩ ሊቃወሟቸው በማይችሏቸው መፈክሮች የተሸፈኑ ናቸው። የዚህም ድርጅት የተከለሰና ዓለም አቀፋዊ የሆነውን ርዕይ በ1940 ዓ.ም. (1948) “የሰብዓዊ መብቶች ሁለንተናዊ መግለጫ” (Universal Declaration of Human rights) በማለት ይፋ ያደረገ ሲሆን አሁንም እንደተለመደው የተጠቀሙት ቋንቋ የሚቃወመውን ማንኛውም ሰው እንደግብዝ እና ቅንነት እንደጎደለው አድርጎ በሚያስቆጥር መልክ በጥንቅቃ የተዘጋጁ ነበሩ። የተ.መ. ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ  በማንኛውም የተፈጥሮ አደጋም ሆነ “አምባገነን መንግሥታት”  በሕዝቦቻቸው ላይ “ከመጠን ያለፈ ኃይል”   በሚጠቀሙበት ወቅት በቅድሚያ የሚጠራ ደርጅት ሆኗል። ይህ መልካም ዓላማ እንደ ቢቢሲ ባሉ “ተዓማኒ” ምንጮች [ድብቅ አጅንዳቸውን ለማያውቅባቸው ብዙኃን ሕዝብ ተአማኒ የሆኑ] የሚቀርብ ነው። በመሆኑም ምርመራ በማይደረግባቸው የተቋማትና ቡድኖች በኩል የተ.መ.  በእያንዳንዱ የሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ራሱን ማስገባት ችሏል። ነገር ግን በቀጣይ እንደምንመለከተው እውነታው በእጅጉ ከዚህ የራቀ ነው። የተ.መ. የተቋቋመው እንደ የሉሲፈር ትረስት (Lucifer Trust) መሥራች ኤሊስ ቤይሊ (Alice Bailey) ያሉና ሌሎች ዓላማዋን በሚደግፉ መሰል ሰዎች ነው።  እነዚህ ሰዎች ማስፈን የሚፈልጉት የአዲሱ ዘመን መርህ (New Age principles) የተባሉና ከክርስትናና ከማንኛውም ሰብአዊ አስተምህሮ የሚቃረን ፍልስፍና ላይ የተመሠረተ  ነው። 




አሊስ ማናት?

Alice Ann Bailey ጁን 16 ቀን 1880 በኢንግሊዝ አገር በማንቸስተር የአንግሊካል ቸርች ተከታዮች የተወለደች እና በዚያው ቸርች ትምህርት ያደገች ናት። እርሷ አንደምትለው አንድ ረዥም የማላውቀው ሰው ተገልጦ እንዲህ ሲል ነገረኝ “ዓለምን ሁሉ ለሚለውጥ ተልእኮ ራስሽን አዘጋጂ ብሎኝ ከዚያ በኃላ 19 መጽሐፍትን ጻፍኩኝ” ትላለች።  በ1907 በ22 ዓመቷ በክርስቲያን ወጣቶች ማኅበር (ወክማ) ሥር ሕንድ ለቸርች ተልዕኮ አገልግላለች። ዘለቄታዊና ቋሚነት ያለው የሞራልና የዶግማን ነገር የሚፃረር አመለካከት ያላቸው 24 መጽሐፍትን ጽፋለች። አብዛኛውን ጽሑፏ የሂንዱና የቡድሀ አስተምሮ የተጫነው ይመስላል። ስለ ቲቤት እምነት ደጋግማ ታነሳለች። የአዲሱ ዘመን ንቅናቄ የሚል ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀመችው እረሷ ናት።  በ1907 ወደ አሜሪካ ተጉዛ ቀሪውን ሕይወቷን  አሳልፋለች። ዲሴምበር 15 ቀን 1949 በኒዮርክ በሞት ተለየች።   ሁለት ባል አግብታ የፈታች ሲሆን የመጀመርያው ባሏ እንደርሷ ለስብክት ወደ ሕንድ አገር የተጓዘ   Walter Evans (1907–1915) የተባለ ሰው ነው። ከ15 ዓመት በኃላ የሶስት ልጆቿን ይዛ ተፋታች። ወደ አሜሪካ ከተሰደደች በኃላ ለምሥጢር ተቋማት በጻፊነት ይሠራ የነበረውን ሁለተኛ ባሏን Foster Bailey (1921–1949) አገባች።   የሉሲፈር ትረስት እና በመጨረሻም የሉሲን ማተሚያ አቋቁማለች።


በመጀመርያ የምንመለከተው ከክርስትና ጋር የሚቃረነውንና በመጨረሻም በኦርቶዶክስ ክርስትና ፀንተው ከሚኖሩ የሰው ልጆች ጋር በቀጥታ ወደግጭት ወደሚያመራው ከየተ.መ.   ፍልስፍና ነው። በክርስትናና በየተ.መ. ፍልስፍና መካከል ከፍተና ግጭት ለመኖሩ ፍንጭ አለ። በህዳር 2009 የአውሮፓ ሕብረት/ኢዩ(EU) የሩስያን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የአውሮፓውያንን  ሊብራል ባህል [ኢቀኖናዊ] (liberal culture) የምትቃወም ሲል ከአክራሪ የፖለቲካ እና የእምነት ቡድኖች ጎን ፈርጇታል። ምዕራባውያን ሊብራሎች (ኢቀኖናውያን) ከወዲሁ የማስጠንቀቂያ ተኲስ ወደ ቤተክርስቲያኒቷ ተኩሰዋል።

መገናኛ ብዙኃኑ የተ.መ. ከእምነት ነፃ የሆነ ድርጅት ነው እያሉ ያቀርቡታል። ነገር ግን ዓላማውን ጠልቀን ለመረዳት ከፈለግን የያዘውን የእምነት መርህ በዝርዝር መፈተሽና መመርመረ ያስፈልጋል። የተ.መ. አባል አገራት  ተስፋቸው ድርጅቱ  “የሰው ልጅ  ለአለው የሰላም ናፍቆት ምላሽ ይኖረዋል ፣ ለሰላም መሠረት የሚሆን ማኅበራዊ ሥርዓትን በዓለም ላይ ያስፈናል” የሚል እምነት አላቸው።  ይህ ተስፋ ትክክል እንዳልሆነ የሚረዱ ጥቂት ሰዎች ወይንም የአገራት መሪዎች ብቅ ብለው  የሚቃወሙት ከሆነ  የተቃዋሚዎቹን መከራከሪያ ምክኒያቶች ለማዳመጥ ፈቃደኛ አይሆኑም። አንዲያውም ከሃይማኖት እንዳፈነገጠ በመቁጠር በክፉ መናፍቅነት  ያወግዟቸዋል። እውነታው ግን የተ.መ. አጠቃላይ አጀንዳ በአብርሆት (Enlightenment)  መርህ የሚነዳ ነው። የተ.መ.  የሚመራበት ሁለት መርህዎች ያሉት ሲሆን በጥልቀት እንመለከታቸዋለን። እነዚህም የመጀመርያው የሰው ልጅ የሚድነው በሕግ ነው የሚል ነው። ሁለተኛው በሥነ ምግባራዊ ወይም በዘላለማዊ እውነት ላይ የተመሠረተ ፍፁም እምነት ሕግን ይጻረራል የሚል ነው [ሁሉ ነገር መንፈሳዊም ሆነ ቁሳዊ የግድ ዝግመተ ለውጣዊ (evolutionary) መሆን ይገባዋል የሚል ዶግማ አላቸው] ። የተ.መ.  በሀገራት መካከል ሰላም ሊፈጠር የሚችለው ዓለም አቀፍ ሕጎች ተግባራዊ ሲደረጉ ነው ብሎ ያምናል። ቻርተሩ ራሱ የተ.መ.ን ተግባር “ሁለንተናዊ ሰላም መፍጠር” በማለት ያስቀምጠዋል። እስከዚህ ሰዓት ተ.መ. ግብ አድርጎ የሚገለፀው  ር የጋራ ደኅንነትን ማረጋገጥ  ሲሆን ይህም ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ሊተገበር የሚችለው አገራትን የጦር መሣሪያ ትጥቅ በማስፈታት ነው ብሎ በማሳመን ይህንኑ ያስፈጽማል።   በሌላ አነጋገር ሉዓላዊ ሀገራት ለሰው ዘር ሁሉ ጥቅም ሲሉ የሀገራቸውን እሴት የመወሰን እንዲሁም የማስጠበቅ መብታቸውን አሳልፈው መስጠት አለባቸው የሚል ኅቡዕ መልዕክት ይዟል [ይህ አባል መንግሥትታትን ብቻ ሳይሆን የእምነቶችንና የባህሎችን እሴቶች ሁሉ ይመለከታል]። ይህን ለማስፈጸም የመጅመርያው የተ.መ. ቻርተር ሊፈጥር የፈለገውን ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አይነት በሰነዱ በግልጽ አስቀምጧል። በዚህ መሠረትሁሉም የሰው ልጅ “አንድ የሞራል እሴት”   ሊኖረው ይገባል የሚል ዓለም አቀፍ እምነት ማስፈን ነው [ሊፈጠር የተፈለገው እሴት ኢክርስቲያናዊ እና ሴኩላር(secular) እንደሆነ ይታወቃል]። ለዚህ ሃሳብ መመርያ የሆኑ መርሆችን  በቅርበት እንመልከት።

የመጀመርያው መርህ ሁለንተናዊ ሰላም የሚገኘው  በዓለም አቀፍ ሕግ ብቻ ነው የሚል ነው። የተ.መ.ን የመጨረሻ ግብ ከክርስቲያኖች የድኅነት አስተምህሮ ጋር አንድ አድርገን ብንምለከተው የበለጠ መረዳት እንችላለን። ምክንያቱም የተ.መ.ም ሆነ   ቤተክርስቲያን  ግባቸው የሰው ልጆች ድኅነት ማረጋገጥ ነው። [በእግዚአብሔር መኖር፣ በነፍስ ዘልዓለማዊነት ለማያምን ለተ.መ. “ደኅንነት”-ነፍስን ታሳቢ ማድረግ አይቻለውም።  በሌላ በኩል ቤትክርስቲያን ደግሞ ሥጋንም ነፍስንም ያስተባበረ ደኅንነትን ታሳቢ ያደረጉ እሴቶች፣ ከእሴቶቹ የሚመነጩ ሕግጋቶችና አኗኗሮችን ታስተምራለችም ትኖራለችም]። “ሕግ ነው ሚያድነን”  የሚለው አስተሳሰብ በሁለቱም በይሁዲ እና የማኅበራዊ ወንጌል ፕሮተስታንቲዝም (social gospel Protestantism) አስተምህሮ ውስጥ በስፋት ይገኛል። ይህ አቋም ከኦርቶዶክስ አስተምህሮ በቀጥታ የሚቃረን ነው። ሕግ ለፍርድ ብቻ ሲሆን የዘለዓለም ድኅነት ደግሞ በክርስቶስ ነው። ሕግ ማኅበረሰብን ከጦርነት ሊያድን አይችልም ምክንያቱም የጦርነት መንስኤው የሰው ልጅ ለሕግ [ምድራዊ] አለመገዛት ሳይሆን  የሰው ልጅ በኃጢያተኝነት የጎሰቆለ ስብእናው (ከእግዚአብሔር የተለየ ሰውነት) ነውና። ምንም ያህል ሰብአዊ ሕግን ብንደነግ ለዚህ ዓለም ሰላምን ልናመጣ አንችልም። [የሰው ልጅ ጦርነት ለመጀመርና ለማካሄድም ስሜቱን በመከተል አንደየርእዮተ ዓለሙ “ጦርነት የመጀመርና የመዋጋት ሕግ” ብሎ ይጽፋል ይገብራል።] ግጭትን ሊያርቅ የሚችለው በውስጣችን ገብቶ ሥራውን በሚሰራ በመንፈስ ቅዱስ ብቻ ስለሆነ። የተ.መ. በተመሠረተበት ቻርተር ራሱን “የሰው ልጅ ከጦርነት መከራ የሚድንበት ብቸኛው መንገድ” በማለት ይሰይማል። ስለዚህም የሰውን ልጅ በሰው ልጅ ጥረት ለማዳን ይጣጣራል። ተ.መ. የሰው ልጅ ፍላጎቱን የተሟላ ማድረግ የሚችለው አመክንዮአዊ አቅሙን በመጠቀም ብቻ ነው ይላል [ይህ ምልከታ የመገለጥ እውቀትን እና የመንፈስ ቅዱስን ሥራ የዘነጋ ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ የፍላገቱና የስሜቱ ሎሌ በመሆን የመኖር ትርጉሙ ሁሉ ሥጋዊ ፍላጎቱን ማሟላት ብቻ አንደሆነ የበየነ ነው]።

የተ.መ. ሁለተኛው መሪ መርህ ከመጀመርያው መርህ ይወለዳል። ይህም “የሕግ የበላይነት”  የመጨረሻው የሞራል ጥግ ሁኖ እውቅና ሊሰጠው ይገባል የሚል ነው። የዚህን መርህ አስከፊነት ለማየት በዚህ ሕግ ስትመራ የነበረችውን ዩ.ኤስ.ኤስ.አርን (U.S.S.R)[ የተባበሩት ሶቪየት ሶሻሊስት ሪፐብሊክ] ወደኋላ ተመልሶ መመልከት በቂ ነው። ለማየት ያክል ሕግ ራሱ በአውጪው አካል ወይም ሀገር ላይ የተመሠረተ መሆኑን በሺህዎች የሚቆጠሩ ክርስቲያን ሰማዕታት እግዚአብሔርን ማመን ሕገወጥ ተደርጎ ሲታይ ሕግ ምን ያህል ሰይጣናዊ ሊሆን እንደሚችል እማኞች ናቸው። [በስታሊን(Stalin) ሥር በነበረችው የቀድሞዋ ሩስያ እ.አ.አ. ከ1937-1941 ባለው ዓመት ብቻ 106,300 የሚሆኑ ካህናት ተገድለዋል]። [“የበላይነቱ”  እንዲከበርለት የተፈለገው ሕግ ኮሚኒስታዊ ስለነበር በሕገ እግዚአብሔር የሚኖሩ ካህናት ተፈጁ። ካህናትን መፍጀት “ኮሚኒስታዊ ሕግ ከእግዚአብሔር ሕግ በላይ ነው” የሚለውን ድምዳሜ በተጠየቅና በአመክንዮ፣ በብዙኃን ፍላጎት ሚዛን ሳይሆን የበላይ ነው ባሉት ሕግ መሰረት ሰውን መፍጀት ተቻለ።] 

አንድን የዓለም አቀፍ ሕግ ከሌላው ሁሉ በላይ እንደሆነ ተቀብሎ የበላይነቱን ለማስከበር መላው ዓለም የሚስማማበት እውነት፣ እውነት የምትገለጥበት እሴት፣ የእውነት ምንጭና ባለቤት ላይ መስማማት ያስፈልገዋል። ታድያ ክርስቲያናዊ እሴቶች ከዚህ ዓለም ሊሆኑ ስለማይችሉ ክርስቲያኖች ከዚህ ዓለም የአገዛዝ ሥርዓት ጋር መቃረናቸው አይቀሬ ነው።  እዚህ ላይ ጥንቁቅ ልንሆን ይገባናል፣ ምክንያቱም “እውነት ከሰላም የበለጠ ዋጋ አለውና” ። በተ.መ. መርህ መሠረት የዓለም አቀፍ ሕግ መደንገግ የሚገባው የሰው ልጆች ፍላጎትን ለመፈጸም በሚያስችል እሴት ላይ በመመሥረት ሲሆን ይህ  ክርስቲያናዊ [ኦርቶዶክሳዊ] ከሆነ እሴት ጋር ፈጽሞ ይጋጫል፡፡ ምክኒያቱም ከእግዚአብሔር የተገኘ  የተፈጥሮ ሕግ መኖሩን ፈጽሞ የሚክድ በመሆኑ ነው። በእርግጥ የወደቀውና የጎሰቆለው የሰው ልጅን ፍላጎቱን ለመሙላት በሚያወጣው ሕግና በእግዚአብሔር ፈቃድ መካከል ምንም አይነት መጣጣም ሊኖር አይችልም። በተ.መ.  ዶግማ መሠረት ግን የጎስቋላውን የሰው ልጅ ዕሳቤ ሕግ አድርጎ በዓለም ሁሉ ላይ ሊጭን ይታገላል። [ለዚያውም እንዚህ ሕግ አውጭዎች ከመነሻቸውም እግዚአብሔርን ከሰው ልጆች የአስተዳደር ሚና በማሰወገድ በአውሮፓው የ17ኛውና 18ኛው መቶክፍለዘመን የአብርሆት ምርህ እየተመሩ የሚደነግጉትን ሕግ ከሁሉ በላይ እንዲሆን አገራት በጦርነት እስከማፍረስ ይራመዳሉ።] እዚህ ላይ ነው ክርስቲያኖች አደገኛ የሆነ ወጥመድ የሚገጥማቸው ። ይህን ልዩነት ለማስወገድ የተ.መ. በሕጎቹ ውስጥ የተለያዩ የምንፍቅና አይነቶችን ብቻ ሳይሆን የሁሉንም እምነቶች መርህ ለማርካት ይጥራል። የተ.መ. የተለያዩ ሥራዓተ እምነቶች ያሏቸውን እሴቶች ቀስ በቀስና  ደረጃ በደረጃ በመጣል እንዲጠፉ የሚሠራ አካል ነው። ይሀን ለማስፈጸም የተለያዩ ስምምነቶችን በመንግሥቶቻቸው በኩል ያስፈርማቸዋል ። ስምምነቶቹን ሲፈጽም ዓለም አቀፋዊ ሊያደርገው የሚፈልገውን እሴት በራሳቸው እንዲተኩ ያስገድዳል። አይነኬ ከሆነው ቀኖናቸው ጋር ጥብቅ ቁርኝነት ያለቸው የእምነት ተቋማት የተ.መ.ን እሴቶች እና ፍላጎቶች የማይቀበሉ ከሆነ የወንድማማችነትን፣ የአንድነትን እና የፍቅርን እሴት የማይቀበሉ ተደርገው እንዲታዩ ማድረግ አንዱ ስልቱ ነው። በቀጣይ እንደምናየው “የእምነቶች የአንድነት ጉባኤ” የኦርቶዶክሳዊነትን የተለየ መልዕክት ለማጥፋትና ክፉ ገፅታ ለመስጠት ሆን ተብሎ የተመሠረተ ነው። 

ማስተዋል ማጣት የተ.መ.ን የዓለም አቀፍ ሕግ መሠረታዊ አካል የሆነውን የጋራ እሴትን የመያዝ አስተሳሰብ ወደ መቀበል ይመራናል። ሀገራት የራሳቸውን የእምነት ሥርዓትና የሥነ-ምግባር መሠርት የሚያስቀጥሉ ከሆነና የአንዱ ሀገር ከሌላው ጋር ፈጽሞ የሚፃረር ከሆነ በምን መልኩ ነው ይህ ዓለም አቀፍ ሕግ ወደ አዲሱ የማኅበረሰብ ሥርዓት ሊጠቀልላቸው የሚችለው? መሠረታዊው ጥያቄ ሕግ “አውጪዎቹ የጋራ መሠረት የሚሆናቸው እሴትና ርእዮት የሚያገኙት ከየት ነው? እነዚህስ ሕጎች ሊመሠረቱበት የሚገባው የጋራ እሴት ምንጭና ይዘት የትኛው ነው? የሚለው ነው። ቻይና ከብዙ ምዕራባውያን ሀገራት ጋር የምትጋራው እሴት ባይኖራት እንኳን ኃያል ሀገር በመሆኗ በተ.መ. የራሷን ሚና ትጫወታለች። ምክንያቱም ይህ ዓለም አቀፍ ሕግ እንዲሠራ ኃያል ሀገራት በጫዋታው ተሳታፊ ሊሆኑ ይገባል። ይህ አሠራር የዓለም አቀፉ ሕግ መሠረቱን የጣለው በጋራ እሴትና መርህ ላይ ሳይሆን በአሸናፊዎች ፍላጎትና ፈቃድ ላይ መሆኑን ያመላክታል። የተ.መ. ሥነ-ምግባርን እና እውነትን መሠረት ያደረገ ሳይሆን የኃይል አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ነው። [የኃይሉ ምንጭ ምንም ይሁን ምን፣ የሚገኘው ከዘረፋ፣ ዘር ከማጥፋት፣ አገራትን ቅኝ ከማድረግ፣ ሰውን ባሪያ አድርጎ በመግዛት፣ በማታለልም ይሁን   “ኃይለኛ” (ሌላውን ማሸነፍና ማዋረድ መቻል) የሆነ አገር የሚመሩ የፖለቲካ ልሒቃን የተሸናፊዎቹን አገር የፖለቲካ ልሒቃን በውክልና እየተጠቀሙ ዜጎችን እሴት፣ እምነት፣ ባህልና ሥርዓት፣ የአስተዳደርና የፍትሕ መንገድ ሁሉ ይደመስሱታል።]

የተ.መ. መሠረታዊ ችግር ተቃውሚ እንዳይገጥመውና ድብቅ አጀንዳውን ለማስተግበር የግድ ራሱን “ሰብዓዊነት” በሚል ጥላ ሥር ቆሞ መገለጥ  መሆኑ ነው። ሰብዓዊነት (Humanism)  ደግሞ የሰው ልጅ ፍላጎቱን ለሟሟላት ዓለምን በራሱ በተረዳው እይታ መጠንና መንገድ  የመቅረጽ አቅም አለው ለሚለው የአብርሆት ዕሳቤ ነፀብራቅ ነው። የተ.መ. ቻርተሮች  “ሁሉም የሰው ልጅ የተ.መ.ን መርህ ተቀብሎ በእርሱ መኖር አለበት” በማለት ገልጦ ያስቀምጠዋል። በቻርተሩ ላይ ፊርማቸውን ያላኖሩ ሀገራት እንኳን ተገደው በዚህ መርህ መሠረት እንዲንቀሳቀሱ ይደረጋል።  ለምሣሌ የተ.መ. “የሰብዓዊ” “መብት” መግለጫ እንደሚያስቀምጠው በአንድ ሀገር ባሉ እምነቶች መካከል እኩልነት ሊኖር ይገባል ይላል። ታድያ እያንዳንዱ ሀገር የራሱ የሆነ በሕግና በባሕል የተገለጠ የእምነት መዋቅሮች እና የማንነት ልዩነቶች አሉት። ነገር ግን የተ.መ. ዓለም አቀፋዊ ያለውን አይነት የሰው ልጅ ማንነት ለመጫን ሲል እነዚህን ሁሉ ደምስሶ ያጠፋል። ሰብዓዊነት የተለያዩ እምነቶች እና ሥነ-ምግባራት መኖራቸው የሰው ልጆችን ይከፋፍላል የሚል አቋም አለው፤ የሰው በአንድ ቋሚ ሥርዓት ወይም ቀኖና መጓዙ እንዲሁም በአንድ ብሔራዊ ማንነት መወሰኑ መልካምነቱን እንዲያጣ ያደርገዋል ብሎ ያምናል።

የተ.መ. ሕጎች ለክርስቲያኖች ፈተና ከሚሆኑባቸው ምክንያቶች መካከል አንደኛው ለሕጎቹ መሠረት የሚሆን የአባል አገራት የጋራ ባህልና ታሪክ አለመኖር  ዋንኛው ነው።  ሁለተኛው ሕጎቹ ከመለኮታዊ መገለጥ የሚገኝ መሆኑን ታሳቢ ያደረገ  ይዘት አለመቀበላቸው ነው። በዚህ ምክንያት በዓለም ላይ ያሉ ማኅበረሰቦች ሁሉ ሕጎቹን እኩል በሆነ ደረጃ ለመቀበልና ለመተግበር ይቸገራሉ። የተ.መ. ዓላማ የሕዝቦችን የጋራ እሴት ማልማትና ማጠናከር ሳይሆን በጥቂት ኢአማኒያን ምሑራን የሚቀመሩ አዲስ እሴቶን በመላው ዓለም ማስፈን ነው፡፡ ታድያ ሴኩላር-ሰብዓዊነት [ሰው በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል የተፈጠረ፣ የዘላለማዊ ሕይወት ተስፋ ያለው የሚለውን ክርስቲያናዊ አስምህሮ በመቃረን ሰው ፈጣሪ አልባ በዝግመት ለውጥ ከእንስሳት የተገኘ ብሎ የሚያምን]  ሃይማኖታዊ ከሆኑ እሴቶች ጋር የሚቃረን በመሆኑ እነዚህን አስተሳሰቦች መጨቆን ወይም ፈጽሞ ማጥፋት ይኖርበታል። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት መካከል እንኳን የፌደራል አብያተ-ክርስቲያናት ምክር ቤት(Federal Council of Churches) በተሰኘ አይሁዶችን፣ ፕሮቴስታንቶችን እንዲሁም የሮማ ካቶሊክን ያጠቃለለ ማኅበር የሰው ልጆችን ሁሉ በአንድ ውሳጣዊ [ነባር ባህላዊ እምነታው አስተምህሮዎችን በመተካት] የሞራል ሕግ አንድ የሚያደርግ የአዲስ ዓለም ሥርዓት ለመፍጠር ሃሳብ ቀርቦ ነበር።

የሚያስገርመው የዓለም አብያተክርስቲያናት ምክር ቤት የተ.መ. ጠንካራ ደጋፊ መሆኑን ነው። ወደኃላ እስከ 1956 ዓም (እአአ 1963) ተመልሰን ስንመለከተው ፓፓ ዮሐንስ 23ኛ (Pope John XXIII) “ሰላም በምድር ሁሉ”    (Pacem in Terrist = Peace on Earth) በሚል መልዕክቱ ከክርስትና አስተምህሮ ነፃ የሆነ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብእ ስለመፍጠር ጥሪ  አቅርቦ ለተ.መ.  ድጋፉንም  ያቀርባል። አሁን ያለውም ፓፓ ፍራንሲስም (Pope Francis) ተመሳሳይ የሆነ ጥሪ ያደረገ ሲሆን “የዓለም ሰላም በተ.መ. ላይ የተመሠረተ ነው” ሲልም ተናግሯል ። የችግሮቻችን መንሥዔ በሰው ልጆች መካከል ያለ ዓለመግባባት እንጂ የሰው ልጆች ከእግዚአብሔር እየራቁ መምጣታቸው አለመሆኑን ይገልፃል ። 

መሠረታዊ የሆነው የተ.መ. ፍልስፍና በሰብዓዊነት ሽፋን የሚቀርብ ሲሆን በሚያሳትሟቸውም ጽሑፎቻቸውም የሚጠቀሟቸው ቋንቋዎች መፍትሔዎቻቸውን እንድንቀበል የሚገፋፉ ናቸው። የአምላክ የለሽ ሰብዓዊነት (atheistic humanism) በፊት ገጽታው አምላክ የለሽ የምዕራብ ዓለም ለመፍጠር የሚሠራ ቢመስልም እውነታው ግን ከመሠረቱ ጀምሮ የሚመራው በሰይጣን አምልኮ ነው። ተ.መ. ስለሚሠራው ሥራ ምሣሌዎችን ከማየታችን በፊት ማን እንደሚመራውና መሠረታዊ መርሆቹ ከየት እንደተገኙ እንመልከት።

አሊስ ቤይሊ ዛሬ የአዲሱ ዓለም ንቅናቄ (New Age Movement) ተብሎ የሚጠራውን ከመሠረቱ መሥራቾች ውስጥ አንዷ ናት። ሉሲፈር ትረስት የተባለ ድርጅት መሥራች ስትሆን ይህም ድርጅት ሌሎች ቡድኖችን በማቋቋም በእነርሱ በኩል ተጽዕኖ ፈጣሪነቱን አስፍቷል። ዛሬ ያለው የተ.መ. ዋና መሥሪያ ቤት የቆመበት ሥፍራ አሊስ ቤይሊ የሉሲፈር ትረስትን ባቋቋመችበት ቦታ ላይ ነው። እሷ ያስቀመጠቻቸው መርሆች ዛሬ በዓለም ላይ እየተካሄደ ላለው በሰው ልጆች ላይ አሉታዊነት ያላቸው  ሥርዓታትን በመፍጠር  እንዴት መመሪያ እንደሆኑና ጽሑፎቿ ምን ያክል በተ.መ. አጠቃላይ ፍልስፍናና ግብ ላይ ተጽዕኖ እንደፈጠሩ ዝርዝር ማስረጃዎችን እናቀርባለን። ይህን ከማድረጋችን አስቀድሞ ግን የአሊስ ቤይሊ ማንነት ባጭሩ መዳሰስ ወደማስረጃዎቹ ለመንደርደር ይጠቅመናል። 

አሊስ ቤይሊ በሙሉ ስሟ አሊስ ላትሮብ ቤትማን (Alice Latrobe Bateman) እአአ በ1880 ተወልዳ በ1949 ሙታለች። ታድያ ተ.መ. እውን ሲሆን ለማየት በቂ ዘመን ኖራለች። ያደገችው በሀብታም የእንግሊዝ ማኅበረሰብ ውስጥ ሲሆን በዘመነ ቪክቶርያ [ንግሥት ቪክቶርያ የገዛችበት እአአ ከ1837-1901 ያለው ዘመን (Victorian England)] ለነበረው ድኅነት ተጠያቂ እና ለማኅበረሰቡ መበላለጥ መንስዔ ነው ያለችው በእሷ አጠራር “የጥንቱ ሥነ-መለኮት” (“theology of the past”) በዋናነት ባህላዊ ክርስትናን ነበር።  በጻፈችው ግለ ታሪክ ከአምስት እስከ አሥራ አምስት ባለው የዕድሜ ክልሏ ውስጥ “ሕይወት ለመኖር የምትገባ አይደለችም” በሚል ሦስት ጊዜ ራሷን ለማጥፋት መሞከሯን አምናለች። በሃያ ሁለት ዓመቷ የኤፒስኮፖሊያን ፕሮቴስታንት ቸርች (Protestant Episcopal Church) መሪ የነበረ ዋልተር ኢቫንስ የተባለ ሰው ያገባች ሲሆን እሱም ይደበድባት እና ያሰቃያት ነበር። በ1915 ከደረጃ ላይ ገፍትሮ ከጣላት በኃላ ፍቺ ፈጽማለች። በዚህ ሰበብ ከዚህ ከክፉ ሰው ጋር ብቻ የተለያየች ሳይሆን ከክርስትናም ጋር እንደተቆራረጠች ተሰምቷት ነበር። 

በዚሁ ፍቺ በፈጸመችበት ዓመት ነበር የቲኦሶፊካል ማኅበርን (Theosophical Society) [የመናፍስት አምልኮ የሚያስተምርና የሚፈጽም ማኅበር] የተቀላልቀለችው። ይህ ቡድን ራሱን የሰይጣን አምልኮ ማኅበር ያደረገ ሲሆን፣ ዓላማው የዓለምን ማኅበረሰብ በሙሉ ጠቅልሎ  በዚሁ አምልኮ ሥር  ማስገባት ነው። አሊስ ቤይሊ በማኅበሩ ውስጥ በፍጥነት የሥልጣን እድገት በማግኘት የማኅበሩ መጽሔት አዘጋጅ ሆነች። በጻፈችውም ግለ ታሪክ  በ1919 ጀምሮ ለቀጣዮቹ ሠላሳ ዓመታት በማይታይ መንፈስ ስትጎበኝ እንደነበረ እና ለጻፈቻቸው ሃያ ዘጠኝ መጻሕፍት  መሠረት የሆኑ ትምህርቶቹን እንድትመዘግብ እንዳደረጋት ገልፃለች።  በ1919 የወደፊት ባለቤቷና ስሙን የወረሰችው ሠላሳ ሦስተኛ ዲግሪ ፍሪሜሰን (thirty-second degree Freemason) ፎስተር ቤይሊ (Foster Bailey) የተባለ ሰው የብሔራዊ ቲኦሶፊካል ማኅበር ዋና ጸሐፊ ሆነ [ፍሪሜሰን፦ በ14ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ የተመሠረተ ማኅበር ነው። ትልቅ እና ዓለም አቀፍ ምሥጢራዊ ማኅበር ሲሆን በእንግሊዝ ሥርወ መንግሥት ጋር አብሮ የተስፋፋ ነው። አባላቱ በዓለማችን ትላልቅ የሚባሉ ቦታዎችን እንዲሁም ስልጣኖችን የያዙ ናቸው]። ቤይሊ የሚያናግራት ድምጽና የሚጎበኛት መንፈስ የቲቤት የቡድሃ መምህራን መንፈስ እንደሆነ በእርግጠኝነት ትናገር ነበር። ይህም ከማኅበሩ ለመለየቷ ምክንያት ሲሆን ነገር ግን የማኅበሩን አስተሳሰቦች ማስተዋወቋን እና ማራመዷን ቀጥላበታለች። ቁልፍ ከሆኑት አመለካከቶቿ ውስጥ አንደኛው የሰው ልጆች የአዕምሮ ዝግመተ ለውጥ ከሃይማኖት በላይ ነው ብላ ማመኗ ነው። እንደውም ለሰው ልጆች መከፋፈል ምክንያቱ ክርስትናና ሌሎች እምነቶች ናቸው በማለት ትከራከር ነበር። መሠረታዊ አስተምህሮዋ ኢኪውሚኒዝም ነበር፤ ይህም ማለት በእምነት ተቋማት ውስጥ ከሚታየው ልዩነት በበለጠ አንድነቶቻቸው እና የጋራ እሴቶቻቸው የጠነከሩ ስለሆኑ አንድ ሊሆኑ ይገባል የሚል ነው። በዚህ እምነቱዋ መሠረት አንድ የዓለም ሥርዓት ለማምጣት ያስችላል ያለችውን  ባለ አሥር ነጥብ እቅድ ነድፋለች። ከታሪኳ እንዲሁም ከአመለካከቷ ስለማንነቷ ከተረዳን ዛሬ በዓለማችን እየተፈፀመ ያለውና ]በተ.መ. ሕጎችና መርሆዎች የተካተቱት አንጾች] ከአሊስ ቤይሊ እቅድ ጋር ምን ይህል የተቆራኘ እንደሆነ እንመለከታለን።  

የቤይሊ የመጀመርያ ነጥብ እግዚአብሔርንና ወደርሱ የሚደረግ ማንኛውም ጸሎት ከሁሉም ትምህርት ቤቶች እንዲወገዱ ማድረግ ያስፈልጋል የሚል ነው። ይህ በአሜሪካ የተሳካ ሲሆን በእንግሊዝ በአብዛኛው ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ ተደርጓል።[በኢትዮጵያም ከ1966ቱ ዓ.ም. አብዮት ወዲህ ተግባራዊ ተደርጎ እስከ ዛሬዋ ኢትዮጵያ ቀጥሏል።] የዚህን ተግባር ዓላማ “ሕፃናት ክርስቲያናዊ ከሆነ ባህል ጋር ቁርኝነት እንዳይኖራቸው ማረጋገጥ ነው” በማለት ትገልጸዋለች። ዓላማው በእግዚአብሔር ማመን አንደትርፍ እንዲቆጠርና በትምህርት ቦታዎችም ትኩረት እንዳይሰጠው ማድረግ መሆኑን በግለጽ ትሞግታለች፣ [የተ.መ. የሳይንስ፣ የትምህርትና የባህል (ዩኔስኮ) ይህንኑ መርህ እንደሚከተል አሁን በዓለም ዙሪያ በታዳጊ አገራት ላይ የሚጫነው የትምህርት ፖሊሲ ይመሰክራል።]።

ሁለተኛው ነጥብ ወላጆች በልጆቻቸው ላይ ያላቸውን ሥልጣን  መቀነስ ነው። የእዚህ ዓላማው በእሷ አገላለጽ “በወላጆችና በልጆች መካከል ያለውን ትግባቦት መስበር” ብላ ታስቀምጠዋለች። የክርስትና እምነት አስተምህሮ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፈው በዋናነት በቤተሰብ በኩል [በትውፊት፣ በክርስቲያናዊ አኗኗር፣ በታላቅና ታናሽ የመከባበርና የመደማመጥ ሥርዓት] በመሆኑ  የቀደሞውን ለማጥፋት አሁን ያለውን ማጥቃት በሚል አስተሳሰብ ታምናለች። የሚያስገርመው የእንግሊዝ መንግሥታት ጥሩ የሆነ የህፃናት እንክብካቤ እንዲኖር የሚያመቻቹ ሲሆን ከዚህም ባለፈ በእናትና በልጅ መካከል ያለውን ትስሥር ለመበጠስ ታልሞ ልጅ ወልዶ ለማሳደግ የሚሆነውን የቤተሰብ ገቢ ከመጨመር ይልቅ የሰው ልጅ ወስደው ለሚያሳድጉ የገንዘብ ድጋፍ ይደረጋል።

ሶስተኛው የቤይሊ ነጥብ ባህላዊ የሆነ ክርስቲያናዊ የቤተሰብ መዋቅርን የማፍረስ አስፈላጊነትን የሚገልጽ ነው። ባህላዊ   የቤተሰብ ሥርዓት በልጆች ላይ ጫናና ቅጣቶችን የሚያበዛ ነገር ግን ለሀገር ግንባታ መሠረት እንደሆነ ታምናለች። ሰዎችንም ከቤተሰቦቻቸው ነፃ በማውጣት የሀገርን መፍረስ ማየት እንደሚቻል ታምናለች። ይህም ዓላማዋ ግብ እንዲመታላት በመገናኛ ብዙኃን በኩል ከበርካታ ሰዎች ጋር ወሲብ መፈጸምን ወይም አመንዝራነት እንዲስፋፋ ትሠራ ነበር። ቴለቪዥንን እና ማስታወቂያዎችን ብንመለከት ይህ ነጥብ ምን ያህል እንደተሳካላት እንረዳለን። 

አራተኛው የቤይሊ ነጥብ ውርጃን ለሁሉም ሰው ተደራሽ ማድረግን የተመለከተ ነው። የውርጃ ክሊኒኮች እንዲሁም ተማሪዎች አገልግሎቱን እንዲያገኙ የሚያማክሩ የጤና አማካሪ ክሊኒኮች በየትምህርት ቤቱ ሊከፈቱ ይገባል በማለት ትከራከራለች። አንዳንድ የእንግሊዝ ትምህርት ቤቶች የእርግዝና መከላከያ እንክብሎችን ከቤተሰብ እውቅና ውጪ ለተማሪዎች በነፃ እንደሚያቀርቡ ይፋ አድርገዋል። ቤይሊ ወጣቱ የአመንዝራ ህይወት እንዲኖር ካስፈልግ ይህ አገልገሎት ሊሟላለት እንደሚገባ ተረድታለች። በተጨማሪም ክርስትና ለውርጃ ያለው አመለካከት የሰዎችን መብትና  ፍላጎት የሚጋፋ ነው ብላ ታምናለች።

አምስተኛው ነጥቧ ሰዎች በህይወታቸው በጋብቻ ከመወሰን እንዲለዩ ማደረግ ነው። ይህን ዓላማ ባደረገ መልኩ ቤይሊ ቀላልና ፈጣን ፍቺዎች እንዲደረጉ የሚያስችሉ ሥርዓቶችን ታበረታታ ነበር። በዚህ መልኩ የጋብቻ ክብር እንዲሁም ዓላማ ቀሎ እንዲታይ ለማድረግ ያስችላል ብላ ታምናለች።

የቤይሊ ስድስተኛ ነጥብ ግብረሰዶማዊነት እንደ አንድ የአኗኗር ዘይቤ እንዲወሰድ ማድረግ ነው። አሁንም የክርስትናን እሴት እና አስተምህሮ እንደ ጨቋኝ በማየት ሰዎች ነጻ መሆን አለባቸው [በእግዚአብሔር አርአያ የተፈጠሩና በምድር ሲኖሩ ዓላማቸው አምላካቸውን ለመምሰል እና ወደ እርሱ ለመድረስ መሆኑን እንዲዘነጉ ሊደረጉ ይገባል የሚል መርህ አላት] ትላለች፤ ስለዚህም ስምምነት እስካለ ድረስ ከማንኛውም ሰው ጋር ተራክቦ መፈጸም ይችላሉ ትል ነበር። ይህ ከራስ ቤተሰብ ጋር የሚደረግን ተራክቦን እና በአመንዝራነት የተመሠረቱ መቀራረቦች እንዲስፋፉ ይረዳል ብላ ታምናለች። ይህ ደግሞ ከግብ ሚደርስበት ብቸኛው መንገድ “መቻቻል” እና “አቃፊነት” በሚሉ ቋንቋዎች ሲሸፈን እንደሆነ ትገልፃለች።  ዋና ዓላምው ግን የፆት ልዩነቶችን ማጥፋት ነው። ታድያ ቀደም ሲል እአአ በ2017 ዓም ፆታ አካላዊ ወይም የተፈጥሮ ጉዳይ ሳይሆን የምርጫ ጉዳይ ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል የሚሉ የኢቀኖናውያን ድምጾች ተሰምተዋል።

የእቅዷ ሰባተኛው ነጥብ ኪነጥበብን ማበላሸት የሚል ነው። ኪነጥበብ የማኅበረሰብን ባህል የሚቀርፅ መሣሪያ እንደሆነ በመረዳት የተበላሸ ኪነጥበብን [ከባህል ከወግ እንዲሁም ከሃይማኖታዊ እሴቶች ውጪ የሆኑ ይዘቶችን የያዙ የኪነጥበብ ውጤቶች] በመጠቀምና ለዘብተኛ ሰው በመፍጠር ነባርና ተቀባይነት ያላቸውን የማኅበረሰብ ሥርዓቶች እና እሴቶችን ማጥፋት እንደሚቻል ገልፃለች። ዓይነ ህሊናን በመበከል የሰዎችን አዕምሮ አስሮ ይዟል ካለቻቸው “ጊዜ ካለፈባቸው አስተሳሰቦች”  [በእምነት እና በባህል ላይ ከተመሠረቱ አስተሳሰቦች] ማላቀቅ ይገባል በማለት ትከራከራለች። ባህላዊ ኪነጥበብ ሰዎችን መንፈሳዊ ወደሆነ ስሜት ሊያደርስ ይችላል ብላ በማመን ሊወገዱ ይገባልም ትላለች።

የቤይሊ ስምንተኛ ነጥብ የሰዎችን አስተሳሰብ በመገናኛ ብዙኃን በኩል መቀየር ነው። “የሕይወት ዋና ዓላማ መደሰት ነው” የሚል አስተሳሰብ (hedonism) በሰዉ ዘንድ በማስረፅና የቀደመውን ሃይማኖታዊውን የሕይወት ዓላማ በማስጣል አዲስ የሆነ የኑሮ ዘይቤ እንዲፈጠር ጥራለች፣ [ተሳክቶላትም]። “ዊል ኤንድ ግሬስ (Will And Grace)” የተሰኘ ተከታታይ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጆች ሰዶማዊ ገጸባህሪያትን በመጠቀማቸው ከትምህርት እና ከፖሊሲዎች በበለጠ ግበረሰዶማዊነት በአሜሪካ ማኅበረሰብ ተቀባይነት እንዲኖረው ተጽዕኖ መፍጠር እንደቻሉ ተናግሯል።

ዘጠነኛው ነጥቧ ዓለም አቀፍ የሆነ የእምነቶች ጥምረት ንቅናቄ መፍጠር ነው። በዚህ መንገድ ክርስትና የተለየ ነው የሚለውን አስተሳሰብ ማጥፋት ይቻላል ብላ ታምናለች።  በተጨማሪ የመቻቻልን ቋንቋ በመጠቀም እምነቶች ሁሉ እኩል ናቸው የሚል ዕሳቤን በተለይ በህፃናት አዕምሮ ላይ ማስረፅ እና ቀጣዩ ትውልድ አንድ የዓለም እምነት እንዲቀበል ማድረግ ይቻላል ትላለች። ይህ እቅድ ምን ያህል እየተተገበረ እንደሆነ ኦክላሆማ (Oklahoma) የሚገኝ አንድ የሰይጣን ቤተመቅደስ ያወጣው መግለጫ አመልካች ነው። መግለጫውም በከተማው በሚገኝ ጥንታዊ አሥርቱ ትዕዛዛትን በሚያሳይ ሐውልት አጠገብ ሁለት ሜትር የሚሆን የሰይጣን ሐውልት ማቆምን በተመለከተ ነው። የከተማው ባለሥልጣናትም ምክንያታዊ ነው ብለውታል። ይህ የሰይጣን አምላኪ ቡድንም “ዓላማችን የሌላውን እምነት ለማንቋሸሽ አይደለም። ይህን ብናደርግማ የትምህርት ሥርዓቶቻችንን እንጻረራለን። ነገር ግን የተለያዩ ሥርዓቶችን እና የእምነቶችን ታሪክ መማርና ተሞክሮ መውሰድ ያስፈልጋል።” ሲሉ ገልጸዋል።

በ2017 ፕሬዝዳንት ፑቲን ለሀገሩ ዜጎች ባደረገው የገና የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱ ለምዕራባውያን መውደቅ ምክንያት ከሆነው ውስጥ አንዱ በመቻቻል ስም ክርስትናን ከሰይጣን አምልኮ ጋር እኩል የሚያደርግ ፖሊሲ መከተላቸው ነው ሲል ገልጿል። ይህ ፖሊሲ የቤይሊን እቅድ ወደ ተግባር የተረጎመ  መሆኑን ፑቲን ንግግሩ የበለጠ አጋልጦታል።

አሥረኛውና የመጨረሻው ነጥብ ሌሎቹ ዘጠኝ ነጥቦች የመንግሥታት ሕግ ሆነው ሊደነገጉና ክርስቲያናዊ በሆኑ አካላትም ተቀባይነት እንዲያገኙ ሊደረግ ይገባል የሚል ነው። ዓላማው ክርስቲያኖች እምነታቸውን እና በክርስትና ላይ የተመሠረቱ እሴቶቻቸውን ማስጣል ሲሆን ይህን ግን ዕውን ለማድረግ የሚቻለው እነዚህን ዘጠኝ ነጥቦች ተግባራዊ በማድረግ ነው ብላለች። በአጠቃላይ ሥራዋ ጠላት ያደረገችው ሌሎች እምነቶችን ወይም ደግሞ ንጹሐኑን የሚጨፈጭፉ የአክራሪ ቡድኖችን አይደለም ክርስትናን እንጂ። [በዚህም ዝንባሌዋ ለሠይጣን የተገዛችና በእርሱ ማኅደረነት እንደምትሠራ ማወቅ ይቻላል። የእርሷን መርሆዎች ሳይሸራርፍ ፖሊሲ በማድረግ በመላው ዓለም ላይ የሚጭኑት የተ.መ. የተለያዩ ድርጅቶችም በአሊስ ቤይሊ አድራሽነት የሰይጣን አገልጋይ ተቋማት ሆነው እየሠሩ ይገኛሉ።]

ምዕራቡ ምን ያክል የቤይሊን መንገድ ይዞ ወደ አዲሱ የዓለም ሥርዓት እንደተጓዘ ስንመለከተው በጣም የሚያስጨንቅ ነው። ከነጥቦቿ ውስጥ በማኅበርሰባችን መካከል ተፈጻሚ ያልሆነ የለም። የቤይሊ ዕቅዶች በብዙ ሰዎች በማይታይ መልኩ ተግባራዊ ተደርገዋል ፤ አየተደረጉም ነው።  እነዚህ ሃሳቦች በጥልቀት የተተከሉ በምዕራቡ ዓለም ሲሆን በእስያ፥ በአፍሪካ እና በደቡብ አሜሪካ እስካሁን በጥልቀት መሠረት እና ሥር አልያዙም። በእንግሊዝ የአንግሊካን ቸርች (Anglican Church) ትላልቅ ጉባኤዎች በሚደረጉበት ወቅት ሚድያው ሲንሰፈሰፍና በወቅቱ ያለው የአንግሊካን ቸርች ዋና መሪ ከአፍሪካ ለመጡ የሃይማኖቱ መሪዎች የምዕራባውያንን አመለካከት በተለይም ፆታዊ ጉዳዮችን ሊሰብኳቸው ሲጣጣሩ ይታያል። የእንግሊዞቹ የአፍሪካዎቹን አቻዎቻቸውን እምነት እና አስተሳሰብ እንደ ኋላ ቀር በመቁጠር በአንድ ቤተክርስቲያን አባልነት በመገኘታቸው ያፍሩባቸዋል። በመሆኑም ምዕራባውያኑ በዓዲሱ ዓለም ሥርዓት የታደሰውን ዘመናዊውን የአንግሊካን ቸርች ገፅ በአፍሪካዎቹ ላይ ለመጫን ይሞክራሉ።


ቤይሊ ከ1945 ጀምሮ ላለው የምዕራባውያን ባህል ለውጥ ፕላን ነድፋ ተግባራዊ እንዳስደረገችው ማየት እንችላለን። አመለካከቷ በተ.መ. ልብ የተተከለ ብቻ ሳይሆነ ድርጅቶቿ ምን ያህል ሥራቸውን አስፍተው  በተ.መ. የተወካዮች ስብሰባ ላይ ተጽዕኖ እንደሚፈጥሩ እንመልከት። የሉሲፈር ማተምያ ድርጅት በ1920 በቤይሊ የተቋቋመ ሲሆን መጠሪያ ስሙ ግን አጋላጭ ነው በሚል ወደ የሉሲ ትረስት ተቀየረ። ዛሬ የሉሲ ትረስት በተ.መ. የአማካሪነት ሥልጣን አለው። ይህ ሥልጣን ለአባላቶቹ በሳምንታዊው የተ.መ. ስብሰባ ወንበር የሚሰጥ ሲሆን በቀጥታ በተ.መ. አባላት ላይም ሆነ በራሱ በተ.መ.  እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር አስችሎታል። ነገር ግን የሉሲ ትረስት ተጽዕኖ የሚፈጥረው በተ.መ. መቀመጫው ብቻ አይደለም፤ እንደራሴዎቹ በሆኑ እንደነ ጆን ሮክፌለር (John Rockefeller)፣ የቀድሞው የአሜሪካ አምባሳደር ቶማስ ዋትሰን (Thomas Watson)፣ ሄነሪ ኪሲንጀር (Henry Kissinger) እና ሌሎች እነርሱን በሚመስሉ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ምክር ቤት አባላቶች በኩል ነው። በተጨማሪም ዊንድሶር ባንክ (The Windsor bank) የሉሲ ትረስት አስተዋፅዖ አድራጊ መሆኑን አምኗል (በአሁን ወቅት ባንኩ በድህረገፁ የነበረውን ዝርዝር መረጃ አውርዷል)። የቀድሞው የተ.መ. ረዳት ጸሐፊ የነበረውና የዩኔስኮ የሰላምና የትምህርት ሽልማት ባለቤት ሮበርት ሙለር (Robert Muller) ትምህርት ቤት የከፈተ ሲሆን ሥርዓተ ትምህርቱ የአሊስ ቤይሊ እንደሆነ በይፋ ተናግሯል። የቤይሊን አስተሳሰብ ለመዝራት በህፃናት አይምሮ ላይ በስፋት ይሠራል።

የምዕራብ ጀርመን ገዥ ከነበረው ከሄልሙት ስክሚዲት (Helmut Schmidt)፣ የቀድሞው የኦውስትርያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ከማልኮም ፍራሰር (Malcom Fraser)፣ ከሺሞን ፐረዝስ (Shimon Peres) እንዲሁም ከጂሚ ካርተር (Jimmy Carter) ጋራ ሥምምነት ያለው ዘወርልድ ጉድዊል ድርጅት (The World Goodwill organisation) የተመሠረተው   በ1932 በሉሲ ትረስት አባላት ሲሆን በተ.መ. የኤን.ጂ.ኦ ደረጃነት ተሰቶታል። ግቡ በግልጥ መናፍስታዊ ሲሆን ዓላማውም ሰይጣንን በመጠቀም ፖለቲካን ወደ አንድ የዓለም መንግሥት መምራት ነው። ዘወርልድ ጉድዊል ድርጅት ከዓለም ጤና ድርጅት፣ ከቴይል ሃርት ማእከል (Teilhardt Centre) እንዲሁም የዓለም የዱር እንስሳት ፈንድ ጋር ጥብቅ ትሥሥር አለው ። ይሄው ድርጅት ለዪኒሴፍ፣ ለቴድ ተርነር (የሲ.ኤን.ኤን (CNN) መሥራች)፣ ለአሜሪካ ተልዕኮ በተ.መ. እንዲሁም ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል ድጋፍ እና እውቅና ይሰጣል። ልክ እንደ የሉሲ ትረስት ዘወርልድ ጉድዊል ድርጅት በተ.መ. የአማካሪነት ሥልጣን ተሰጥታል። ድርጁቱም ራሱን ሲያስተዋውቅ የሚሰራው “በሰው ልጆች መንፈሣዊ ዝግመተለውጥ” ላይ እንደሆነ ይናገራል። ይህ አሊስ ቤይሊ በጽሑፏ “ታላቅ የሆነው ሲመጣ [ሃሳዊ መሲህ] በፍሪሜሶናዊነት ተጠብቆ የነበረው ሃይማኖት ለሕዝብ ይፋ ያደርጋል” ብላ ከገለጸችው ሀሳብ ጋር አንድ ነው። ሌሎች በሉሲ ትረስት አባላት ከተመሠረቱ ድርጅቶች ውስጥ ፊንድሆርን ፋውንዴሽን (Findhorn Foundation)፣ በተ.መ. የኤን.ጂኦ ደረጃ የተሰጠው ዘቴምፕል ኦፍ አንደርስታንዲንግ (The Temple of Understanding)፣ የዓለም የመንፈሳዊ እና የፓርላማ መሪዎች መድረክ (Global Forum of Spiritual and Parliamentary Leaders፤ የዚህ መድረቅ ከተወሰኑ ውሳኔዎች ውስጥ ቀዳሚው የዓለምን የሕዝብ ብዛት መቀነስ ነው)።

በተ.መ. ሕንፃ ውስጥ በሉሲ ትረስት የሚጠበቅ አንድ የጥሞና ክፍል አለ። በውስጡ እስከዛሬ ከተገኙ የማግኒታይት ድንጋዮች ትልቁ የሆነ ቁመቱ 1.2 ሜትር የሚሆን አንድ ወጥ ጥቁር ድንጋይ ቆሟል። መናፍስት አምላኪዎች እንደሚያምኑት እንደዚህ ባለ መግነጢሳዊ ድንጋይ አጠገብ ለረጅም ሰዓት በጥሙና መቀመጥ ረቂቅ የሆኑ ኃይሎችን መቆጣጠር ይስቻላል ይላሉ። ለዚሁ ዓላማ ተብሎ ድንጋዩ በክፍሉ መሠረት ላይ እንዲተከል ተድርጓል። ሁለተኛው የተ.መ. ዋና ጸሐፊ የነበረው ዳግ ሃመርስክሆልድ (DagHammarskjold) ድንጋዩን ሲገልጸው “የሁሉ አምላክ ለሆነው ምልክቱ” ነው ይለዋል። ይህ ክፍል የተገነባው በእርሱ መገፋፋት ሲሆነ በተወሰነ ልኬትና ጫፍ በሌለው ሦስት ማዕዘን ቅርጽ አምሳል የተሰራ ነው። ሃመርስክሆልድ  ተ.መ. ለሚሠራው ሥራ ሁሉ ማዕከሉ መንፈሣዊ የተፈጥሮ ህልውና ሊሆን 

ሃመርስክሆልድ ራሱ በጻፈው ጽሑፍ ላይ ስለ ጽሞና ክፍሉ ሲያብራራ፤ የተሰራው ባዶ መሠዊያ መታሰቢያነቱ “የሰው ልጅ ለሚያመልከው ብዙ ስም እና መልክ ላለው አምላክ ወካይ” ነው ብሏል። ይህም የሃሳዊ መሲህን መምጣት ለሚጠባበቀው አንድ የዓለም እምነት ብለው ለሚጠሩት መሠረት ነው። የእነዚህ ሰዎች እምነት እንደ ክርስቲያኖች አስተምህሮ ሳይሆን የሚመጣው መሲህ ሁሉንም እምነቶች አንድ የሚያደርግ እና ጉድለቶቻቸውን የሚሞላ ነው ብለው ያምናሉ፣ ያስተምራሉ። ይህ አይነቱ አገላለጽ በቤይሊ እና ቴይልሃርድ ጽሑፎች ላይ የተለመደ ሲሆን የቀድሞው የተ.መ. ምክትል ጸሓፊ ሲያስተጋባው እንዲህ በማለት ተናግሯል “በተቻለን መጠን ወደ አንድ የዓለም መንግሥት፣ ወደ አንድ የዓለም ሃይማኖት፣ ወደ አንድ የዓለም መሪ መግባት አለብን።”  በዚህ የጽሞና ክፍል ግድግዳ ላይ 27 የሦስት መዓዘን ቅርጽ፣ በሦስት መዓዘን ውስጥ ያለ ዐይን እንዲሁም ሌሎች ትርጉማቸው በጥቂቶች የሚታወቁ ቅርጾች ያሉበት ሥዕል ተንጠልጥሏል። በመካከሉም የፊኒክስ ወፍ ሲወለድ ያሳያል ነገር ግን ከእሳት ወይም ከአመድ ሳይሆን እንደ እባብ ከቀድሞው ቆዳው ነው። እንዲህ አይነቱ የጠለቀ ገለጻ ጤነኛ አይምሮ ላለው አብዛኛው ሰው እንደ ቀልድ እና የማይታመን፤ ከተራ ሰው ሕይወት ውስጥ ሊኖር የማይችል ይመስላል። ሆኖም ግን ይህ ድርጅት ህይወታችንን ለመወሰን በየጊዜው የሚሰበሰብ እና ዓላማ ይዞ የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነው ። ተ.መ. ከግብ ለማድረስ እየሰራቸው ያሉትን ሥራዎችና ከጀርባቸው ያለውን እውነታ እንመልከት።

     የተ.መ. የ2030 አጀንዳን በ70ኛው ዓመታዊ ስብሰባው የቀረጸ ሲሆን ዓላማው ለመላው ዓለም የጤና ጥበቃን ተደራሽ ማድረግ ነው። ዓላማው ሲታይ መልካምነት የተሞላ ነው። ነገር ግን ፕሮግራሙ ሀገራት የፆታ እና ሥነ-ተዋልዶ የጤና አጠባበቅን በግድ እንዲቀበሉ የሚያደርግ ነው። ይህም ማለት በሀገሪቱ ምንም አይነት እምነት እና ባህል ይኑር የውርጃ አገልግሎቶች እንዲሁም የእርግዝና መከላከያዎች ተደራሽ እንዲደረግ ያስገድዳል። ካሁኑ እንደምናየው የተ.መ. ለሚያደርገው እርዳታ  ይህን ፖሊሲ መቀበል እንደ ቅድመ ሁኔታ ተቀምጧል። ሌላው የአጀንዳ 2030 እቅድ እስከ 2030 ድረስ በዓለም ላይ ያሉ ሕፃናትን ክትባት መስጠት ነው። ልክ እንደ አሊስ ቤይሊ ሕፃናት በመርኀግብሩ ቁልፍ ተጨዋች ተደርገው የተወሰዱ ሲሆን በአጀንዳ 2030 ህጻናትን የለውጥ ማሳለጫ መሳሪያዎች አድርገው ሊገለገሉባቸው ወሥነዋል። መርኃግብሩ የጤና ጥበቃን ከማቅረብ ባለፈ ዓላማው ሥርዓተ ትምህርትን በመቆጣጠር ለህፃናት ብዝኃነትን፣ ዜግነትን እንዲሁም ዘላቂ ልማት በሚል ሽፋን ዓላማቸው የሆነውን የሕዝብ ብዛት ቁጥጥር በትውልድ ዘንድ ተቀባይ እንዲሆን ማድረግ ነው። መርኃግብሩ የተ.መ.ን ዓላማ ለማሳካት አስፈላጊ ናቸው ያላቸውን አዲስ እሴቶችን እና እምነቶችን ለሕፃናት መስበክና ማሳመን ላይ ያነጣጥራል። የ2030 አጀንዳ በሙሉ ድምጽ የጸደቀ ሲሆን የካቶሊኩ ፓፓ ፍራንሲስም “አስፈላጊ የተስፋ ምልክት” በማለት ገልጸውታል።

ሌላው መርኃግብር ብዙዎቻቸን ሰምተነው የማናቀው በ2016 የተስማሙበት አዲሱ የተ.መ. የከተሞች አጀንዳ ነው። መርኃግብሩ ዓላማ ያደረገው የከተሞችን አደረጃጀት በኣካባቢያዊ ዘላቂነት መሠረት መወሰን ነው። “አረንጓዴ” የሚለው ስያሜ ተ.መ. የሉዓላዊ ሀገራትን መብት ለመቆጣጠር መንገድ መክፈቻ ነው። ይህ ስልት የተጅመረው ከአሥርት አመታት በፊት አጀንዳ 21 በጸደቀበት ወቅት ሲሆን በእዚሁ እለት ጆርጅ ቡሽ በብዙኃኑ ጆሮ ያልተሰማውን “የዓዲሱን የዓለም ሥርዓት” ስለመመሥረት ንግግር አድርጓል። አጀንዳ 21 የተ.መ. የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስን እንደ ሥጋት እና ማሳመኛ በመጠቀም በመካከለኛ የኑሮ ደረጃ ያሉ ሰዎችን እና የቀን ሰራተኞች ዝቅተኛ ደሞዝን፣ የሕዝብ ቁጥር መቀነስን፣ ውርጃን እና በአጠቃላይ የወረደ የኑሮ ደረጃን በግድ እንዲቀበሉ ያደርጋሉ። ይህን አልቀበልም የሚል ድምጽ ወድያውኑ በቢቢሲ እና መሰሎቹ ከሃዲ የሚል ታርጋ ይለጠፍበታል። ቢል ጌትስ (Bill Gates) የተ.መ.ን የጤና መርኃግብር ሲያወድስ “በዓለማችን ዛሬ 6.8 ቢልዮን ሰዎች ይኖሩባታል። በትንሽ ጊዜ ወስጥ ወደ ዘጠኝ ቢልዮን ይገባል። ታድያ በአዳዲስ ክትባቶች፣ በጤና ጥበቃ እና የሥነተዋልዶ ጤና አገልግሎቶችን በማቅረብ ጥሩ የሆነ ሥራ ከሠራን ቁጥሩን በአሥር ወይም በአሥራ አምስት በመቶ እጅ ማውረድ እንችላለን” በማለት ተናግሯል። በመገናኛ ብዙኃኑ ሰፊ የሆነውን ሀብቱን ለሰባዊ እርዳታ የሚሆኑ ክትባቶችን የሚያመርት ተብሎ የሚመሰገነው ሰው ድብቅ ዓላማው የሰውን ልጅ ለማዳን ሳይሆን የዓለምን ሕዝብ ቁጥር ለመቀነስ መሆኑ ያመለክታል።  ይህን ጉዳይ በሌላ ምዕራፍ በሰፊው እንመለከተዋለን።  

ዓለማችን ላይ በተፈጠሩ ቀውሶች ተ.መ. ጣልቃ የሚገባ ቢሆንም ጥሩ ውጤት ያስመዘገበት ጊዜ ግን ጥቂት ነው። በተጨማሪም ለአንዳንድ የጎሳ ቡድኖች የሚያሳዩት ጥላቻ ብቻ ሳይሆን ባለ ሰማያዊ ኮፊያዎቹ የተ.መ. ሰላም አስከባሪዎች በገቡባቸው ቦታዎች ሁሉ ሴተኛ አዳሪነት እና የአደንዛዥ ዕፅ መበራከት የአደባባይ ሚስጥር ከሆነ ቆይቷል።  ስለ ተ.መ. በመገናኛ ብዙኃኑ ተስሎ የሚቀርብልን ሌላ ሲሆን በዓይናችን የምናየው እውነታው ግን የተለየ ነው። እንደዚህ አይነቱ በሰይጣን አምላኪዎች ከፍተኛ የሆነ ተጽዕኖ ያለበት ድርጅት ምንም ያህል ራሱን እንደ ደግ ቢያቀርብ በፍጹም ለመልካም ነገር ሊሠራ አይችልም። በየአካባቢያችን ያለውን የባህል እና የማኅበረሰብ ለውጥ ስንመለከት ምን ያህል የአሊስ ቤይሊን እቅድ ድርጅቱ ተግባራዊ እንዳደረገ ግልጽ ይሆንልናል። የትኛውም ለውጥ በድንገት ወይም እንደሚባለው በማኅበረሰባዊ ዝግመተ ለውጥ የመጣ አይደለም ነገር ግን መንፈሳዊ የሆነውን የተ.መ. አጀንዳ በሚመሩ ሰይጣናውያን እንጂ። በኋላም እነዚህ ለውጦች በምን መልኩ ሊሳኩ እንደቻሉ እንዲሁም የቤይሊን ራዕይ ከግብ ለማድረስ የሚተጉ አካላት በምን መንገድ እንደሚሠሩ የምናይ ይሆናል። እስካሁን ያየናቸው አንድ የዓለም መንግሥት፣ ሥርዓተ ትምህርት፣ ሥነ-ፆታ፣ መገናኛ ብዙኃን እና የመሳሰሉት ገጽታዎች በሰፊው ዳግመኛ ይዳሰሳሉ። በቅድሚያ ግን ከተ.መ. ሌላ ዓለማችን በምን መንገድ እንደምትቀረጽ የሚወስኑ ኃያል ቡድኖችን እና አጀንዳቸው የተመሠረተበትን ዓላማ እንመለከታለን።

መጽሐፉን በዚህ ማፈንጠሪያ በመከተል መዛትና ማስተዋወቅ ይችላሉ  https://a.co/d/0bLSmDqy




አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

የሐሰት ትርክት ኦነጋውያንና የሕወሃታውያ የጋራ ስልት ከነግሥታት ወደ ተራ ግለሰቦች

✏️ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።  እርሱ ይመስገን። ምድራችንን #በደም #ያጨቀየው $ህሊና #የነሳን ፣ #ልቦናችንን #ያጨለመን ፣ #ሰብእናችንን ያዋረደው:- 👉 የሕወሐታውያንናንየኦነጋውያን የንዑስ ማንነት የጎሣ ፖለቲካ የደንቆሮ ርእዮትና፣ 👉 መርዛማን ጥላቻን ለ፶ ዘመናት ያከፋፈሉት የሐሰት ትርክት ናቸው። ✏️እንደ ዳግማዊ #ምንልክ ያሉ   ከዋክብት መሪዎች፣ እንደራሴቻቸው፣ ደጃዝማቾችና ቀኝና ግራ አዝማቾቻቸው  ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ብዙ ውለታ ውለውልናል:- 👉 በዘመነ ኦቶማንና አውሮፓ፣ በዘመነ መሳፍንት የተበታተነውን እና የተቆነጻጸለውን፣ ጎሠኛ የአርብቶ አደሮች  መሬት ፍለጋ  የደመሰሱትን ክርስቲያናዊ የግዕዝ/የነፃነት ሥልጣኔ አሻራ እንዲያገግም ደክመውልናል፤ 👉 የጥንት አገርን እና ሕዝቦችን   በከፊልም ቢሆን በመሰብሰብ  ጠንካራና ብቸኛ የነጭ ቅኝነትንና ባርነትን በመከላከል፣ ከኦቶማን ቱርክ ወር ትናንት ውስጥ ጥረኛ  አህመድ ግራኝ በመጋደል  ልዩ የነጻነት ማንነት ያላትን አገር ብበቸኝነት በዓለም ካርታንላይ አቆይተዋል፤ 👉 የሬማ ግዛት በጎሣ ተብልቶ ፲ ትንንሽ ሲሆን ከበበባውን ተቋቁማ በዝኃነታችን በተመጋጋቢ አንድነት ከ፹ በላይብቋንቋ፣ ከዓለም ትልልቅ እምነቶች ክትስትናን ፣ ይሁዲን፣ እስልምናን፣ የእረማውያንን ቅሪት የሆኑ የባህል እምነቶችን ሁሉን ይዛ በአውሮፓ በአርብ አምሳል ሳትሠራ ለእኛ አቀብዋል፤ 👉 ወያኔና ኦነግ፣ ገንጣዩ ሻዕብያ፣ ከሃዲው የማርክሲስት የአእምሮ  ባሪያን ስብስብ  እስኪፈትናት ድረስ ራሷን የቻለች አገር እንድንፈጥር ያስተባበሩን ነገስታት የተመሰገኑ ናቸው። አገር ሲያረጅ ጃርት ያብቅላል እንዱሉ: መል...