ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

የመንፈሳዊነት ፖለቲካ፡- ሃይማኖትን ኢቀኖናዊ (ሊብራል)  የማድረግ ሂደትና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አዲስ ተጋድሎ

ለውይይት የዘጋጅ ረቂቅ ሰነድ

03-07-2015 ዓ.ም.

ፋንታሁን ዋቄ 

ዋና መልእክት

ለፖለቲካ የሚስማማ ሃይማኖት የመፍጠር ሂደት፣ ስልትና ውጤቱ አሁን የምንገኝበትን ግራ መጋባት፣ ውጥንቅጥ የሆነ ማኅበራሰባዊና ፖለቲካ ኪሣራ አፍርቶልናል። ከዚህ የባስ አንዳይመጣ፣ ወደተሻለ መልካም ማኅበራዊና ፖለቲካዊ መንግድ ለመመለስ ፖለቲካዊ መንፈሳዊነትን የመፍጠሩን ዘመናዊ ኑፋቄና ክህደት ጉዳይ አድርጎ መነጋገር ጊዜ የማይሰጠው ነው።  የአንድን ሃይማኖት መንፈሳዊ መገለጫዎች፣ የአገልግሎት አቀራረብ፣ አስተምህሮና የተከታዮቹን ማኅበራዊ መስተጋብርና እሴቶች በፖለቲካዊ ርእዮት፣ ሕግና መዋቅር የመቀንበብ የምዕረባዊያን ረቂቅ ልማድ ሲሆን በአገራችን ኢትዮጵያ ፊት ለፊት በአሳጅነትና በጅምላ ፍጅት የተገለጠ አደገኛ ፖለቲካ ሆኗል።  


ይህ ጽሑፍ ሥዝም ልሂቃን   ኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖትን የሚረዱበት መንገድ፣ ለአገራቸውና ለህዝባቸው እድገት (የቁሳዊ ሀብት ክምችት፣ ከተፈጥሮና ሰውሰራሽ አደጋን የመከላከል አቅም፣ የማህበራዊ መስጋብርና መዋቅር ለውጥ፣ ወዘተ) በሚመኙትን በሚያደርጉት ጥረት ከኦርቶዶክሳዊ ነገረ-ሰብእና ነገረ-መለኮት፣ ስነ-ኅበረተስብና ስነ-ብእል ማኅቀፍ ፈጽሞ የሚጋጭ  መሆኑን ማሰየት ነው። ክርስቲያን ትውልድ በተለይና ባለመዋቅ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን የሚከስሱ፣ የሚያጠቁና የሚያስጠቁ የአገራችን ልሂቃን በአድዋ የተዋረደውን የዳርዊን መላምታዊ አስተምህሮ በመከተል ራሱን የዝንጀሮ ልጅ ያደረገ ቅኝ ገዥ እያገለገሉ መሆናቸውን አውቀው እንዲመለሱ ለማንቃት ይሆናል።

ፖለቲካን ከሃይማኖት የመነጠል እና የበላይ የማደረግ ጉዞ እና የኦርቶዶክሳዊነት ተቃርኖ

በኢመድሎአዊነት ወይንም እኩለነትና ሚዛናዊነትን፣ ከብዝኃነትና ከመቻቻል ጋር በመቀመርና እውነት እንዳትነገር እንቅፋት በመፍጠር ሥዝምፍኛን የሃይማኖት መተኪያ የሚያደርግ ‘ሊብራል’ እና ‘ሴኩላር (ሥዝም )’ (ኢዶግማዊ፣ ንፅፅራዊ  ፖለቲካዊ ርእዮት) በቀጥታ ከእውነት ጋር ጦርነት ውስጥ ገብቷል። የ-ኢንፖር መሠረታዊ ዶግማዎች (“ኢንፖር” እያልኩ የምጽፈው አምላክ-የለሽ፣ ዶግማ የለሽ፣ ተለዋዋጭ፣ ንፅፅራዊ የሕዝብ አስተዳደርና አመራር ስልትና አስተምህሮ ያላቸውን ሁሉ ይሆናል።) ኢንፖር ፖለቲካ ያለ ሥዝምፍኛ ሊኖርና ሊታሰብ አይችልም (labral politics in unthinkable without secularism) ፡- 

1) እውነት ብዝኃነት አላት

2) እውነት ልውጣዊነት ያላት፣ በቦታና በጊዜ እንደባለጉዳዩ የምትተረጎም ናት

3) ሞራል (ክፉና ደግ፣ ነውርና ግብረ-ገም) ብያኔአቸው ዘለቄታዊነት የለውም፣ ንጽጽራዊና ለውጣዊ ነው (ርላቲቭ  እና ኢቮሉቲናሪ)።

4) ቋሚ ነገር ቢኖር ለውጥ ብቻ ነው። ስለዚህ ቋሚ የሚባል እሴት፣ እምነት፣ ተስፋ፣ መንገድ፣ የሞራል መሥፈርት፣ የእውነት መገለጫ፣ የሕይወት ትርጉም የለም።

5) ሰው ክብሩ ከማሰቡ፣ ማሸነፍ ከመቻሉ፣ በሌሎች ላይ በመንገሡና በዝናው የሚገለጥ ነው። የሚያከብርና የሚያዋርድ የሰብእና ሚዛን፣ ከሰው ውጭ የሆነ ፈራጅና መዛኝ የለም።


አምስቱም የ-ኢንፖር  መንበረ አእማድ በቀጥታ ከኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ወይንም ከእግዚአብሔር ትምህርትና ሕግ ጋር የሚቃረን ነው።  

ሴኩላርና ሊብራል ፖለቲካ ግልጽ የሃይማኖት ሽርሸራ ስልቶችና ኦርቶዶክሳዊነት


1) እውነት አንዲት፣ የማትለዋወጥና ዘላለማዊት ናት። እርሷም ክርስቶስ ናት።  እኔ እውነትም መንገድም ነኝ ብሏልና።(ዮሐ 9፣10)

2) እውነት አትለወጥም፣ አንዲት ናት፣ ዘላለማዊት ናት። ክርስቶስ እኔ እውነት ነኝ ብሏልና። በጊዜ በቦታ፣ በሁኔታ አትለዋወጥም። በተለያዩ ሰዎች የተለያየ ሚዛን አይሰጣትም።  

3) የመልካምንት መሥፈሪያነው መልካም የሆነው ፍጹሙ እግዚአብሔር ነው። እኔ ፍጹም ነኝና ፍጹማን ሁኑ ያለው የሰው ልጅ ሁሉ ይህን የመልካምነት ምንጭ አግዚአብሔርን ሊመስል ይጋደላል። ስለዚህ ሞራል ንጽጽራዊና ልውጣዊ ሳይሆን ማንጸሪያው የማይለዋወጠው የእግዚአብሐር ጠባያት ናቸው።

4) የፈጣሪ ንጉሥነትና ሁሉን ያዥነት፣ የሰው በእግዚአብሔር አምሳል መፈጠርና ለአርአያነቱ እንዲጋደል መፈጠር፣ ተስፋ መንግሥተሰማያትን የደስታና የምኞት መልሕቅ እድርጎ በፈቃደ እግዚአብሔር መኖርን ማሪፊያ ማድረግ፣ ክርስቶስን በሚያስመስል ሀሳብ፣ ንግግርና ድርጊት መኖር የሕይወት ሁሉ ትርጉም ነው። ቋሚና የማይለወጥ ነው።  

5) የሰው ክብሩ በፍጥረት እግዚአብሔር አምሳል መሆኑ፣ በተሰጠው ነፃ ፈቃድ ለነፍሱ ቅድስና አርአያ እግዚአብሔርን ለመንሳት መጋደሉ፤ በተጋድሎው ለሌሎች የሰው ልጆች በነፍሳቸው ከእግዚአብሔር መጣበቅና በሥጋቸው ከማይችሉት ኣሳች መከራ መጠበቅ  ሲል የሚከፍለው ዋጋ፤ በዚህ ዋጋ የክርስቶስ ምስክር (ሰማዕት) ሆኖ መገኘቱ ነው።  

ኢንፖር ሃይማኖትን (liberal religion) ስለመፍጠርና እግዚአብሔራዊ ሃይማኖትን ስለማጥፋት

ሃይማኖታዊ የመገለጥ እውቀትን ሕገ-ወጥ በማድረግ ሥዝምና ኢክርስቲያናዊ የእውቀት መንገድና “እውቀትን” ሕጋዊ የማድረግ ተቋማዊ የዓለምና የአገርአቀፍ ዘዴ ምንድነው?   

ሥዝም ልሂቃን ከመገለጥ እውቀት ራሳቸውን ነጥለው ዓለም አስቀድማ በሰራችላቸው የምርምርና የማወቅ መንገድ እንደ መናኝ መነኩሴ ጸንተው ሲያስቡና ሲመራመሩ ይኖራሉ። Maturana እና  Varela  የተባሉ የስነ ሕይወት ሊቃውንት የራስን በራስ  የማስተማር አእምሮአዊ ሥራ በሕይወታዊ አካል ራስን በራስ የማባዛት አንጻር እንደ ምሳሌ ወስደው “autopoiesis,” ያመሳስላሉ።   Luhmann የተባለ ምሁርም እንዲሁ የማኅበረሰብን ራስን በራስ የማደስና ከውድቀት መነሳትና መቀጠል፣ ቁርኝት ከሚገኙበት ሁኔታና የተፈጥሮ ከባቢ ለውጥ ጋር ራስን በራስ ማስማማት ሂደት ራስን በራስ የአእምሮአዊ ሂደት ጋር ያነፃፅረዋል።    መንፈሳዊ ሰው፣ መንፈሳዊ ቤተሰብና ተቋም፣ ማኅበረሰብና አገርም እንደዚሁ ራሱን በራሱ የመመመልከት፣ የመለወጥና የማሳደግ ጠባይ አለው። ለውጡ፣ እድገቱና እድሳቱ የሚካሄደው እግዚአብሔር ለው ልጆች በሰጠው ትምህርት ዶግማና ቀኖና  ማኅቀፍና እሳቤ ውስጥ ከሆነ ውጤቱ እግዚአብሔርንም፣ በአምሳሉ የፈጠረውን የሰው ልጅንም ሆነ ለሰው ልጆች አገልግሎት የተፈጠሩ ሌሎች ግዕዛን የሌላቸውንም ፍጥረታት ደኅንነት የጠበቀና በፍትሕ፣ በሞራል፣ በሃይመኖት፣ በማኅበራዊ እሴቶች ሚዛን ሁሉ ተቀባይነትና ተወዳጅነት ያለው ይሆናል። ዘለቄታዊነቱና ሁሉን-ጠቃሚነቱም ይረጋገጣል።

ይህ ድምዳሜ ቀጣይና አገራዊ መልክ እንዲኖረው ከብሔራዊያን ሊቃውንት፣ ከባህሎችና ከእመነቶች በላይ የሆነ ዳኛን የሚጋብዝ የትምህርት፣ የፖለቲካ ርእዮትና የአስተዳደር ሥርዓት ሊኖር አይገባም። በኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት አስትምህሮ መሠረት  ሥዝም ሳይነስ ወይንም እውቀት ተቀባይነት ያለውና የሚደነቅ፣ ስሙ በዘመናዊ መንግድ ተሰይሞ፣ ዓለም አቀፍ የአጥናንና የአቀራርበ ሥርዓት ተበጅቶለት አንደ አሁኑ ዩኒቨርሲቲውን ሁሉ ሳይቆጣጠረው (ሞኖፖላይዝ ሳያደርገው) ቤተክርስቲያን ለ2000 ዘመናት፣ ከዚያ አስቀድሞ ለ3000 ዘመናት በተጻፈ ማስረጃና አሻራው በሚታይ ደረጃ በአእምሮ ጠባይእ የሚገኘው እውቀት ለሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊ፣ አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ጠቀሜታ ስታውል ኖራለች። በክርስትና ሳይንስ እግዚአብሔር የፈጠራቸው ፍጥረታት የመስተጋብር ሕጎችን፣ በመስተጋብራቸው ለሰው ልጆች የሚያስገኙትን አዳዲስ ጠቃሚ ውጤት ተረድቶ ማስረዳት፣ ማስተላለፍና ለሰው ልጆች የማይነጣጠሉ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጠቀሜታ እንዲውሉ የሚደረግበት ብልሃት እንደሆነ በተግባር ታሳያለች። በዚህ ውስጥ ያልተፈጠረ ቀዳሚ እግዚአብሔር የፈጠራቸውን ፍጥረታት በአምስቱ የስሜት ሕዋሳት ከመረዳትና ከጥቅም ለማዋል ባሻገር በሥጋ የማይታወቁና በመንፈስ መገለጥ የሚደረስባቸውንም እውቀቶች ከፍተኛ ዋጋ በመስጠት የሁለቱን ተዋህዶ ለሰው ልጅ የበለጠ ጥቅም ታውለዋለች።

 ሥዝም ሳይንስ ቀመራዊና ተጨባጭ ስሌትን ይከተላል።  ዓለምን ሙሉ በሙሉ ቁሳዊና ተጨባጭ የማድረግ ጠባይ አለው። ሁሉም ገዜና ሁኔታ ውስጥ ቁሳዊ ተጨባጭነት የመፈለግና በሰው ልጅ የስሜት ሕዋሳትና አእምሮ ልክ የመወሰን ልኬት አለው።  በግል ተነሳሽነትና ጥረት አቅም ላይ የተወሰነ፣ ውሱን ዓለምን ባለተወሰነ ቁሳዊ ተጨባጭነት (objectively) ደረጃ ለመረዳትና ለመዋቅ የሚደረግ  ፍለጋ ነው። ፍለጋዉም ንፅፅራዊ፣ ለውጥ እና በቁጥርና ሰው ልጅ የንግግር ቃላት ብቻ የሚለካ ነው።   

መለኮታዊ እውቀት ግላዊ ጠባይ አለው። በቁሳዊ ተጨባጭነት ስሌትና መዝና ደረጃ የሚገኝ ኤደለም። ዓለምን ወደማቆስ (objectification) አይወስድም። እውቀቱ እየተገኘና እየተገለጠ የሚሄደው የሁሉ ምንጭ ከሆነው እግዚአብሔር እና እግዚአብሔር በአምሳሉ ከፈጠረው የሰው ልጅ ጋር በሚኖር የፍቅር ተዋህዶና መንፈሳዊ መስተጋብር ደረጃ ነው። 

ሁሉን ከያዘ፣ ከማይወሰነው እና በውሱን የሰው አእምሮ ልኬት ከማይወሰኑት አምላክ ጋር ውሕደት ማድረግ የማይወሰን እና ከቁሳዊ ተጨባጭነት ካለው ሳይንሳዊ እውቀት ውጭ የሆነ መረዳትን ያስገኛል። ይህ እውቀት ንፅፅራዊ፣ ተለዋዋጭ እና በአምስቱ የስሜት ሕዋሳት፤ የሰው ልጆች ቁሳዊና አእምሮአዊ መስፈረት የሚገደብ አይደለም።  ለዚህም ነው በኦርቶዶክሳዊ የነገረ መለኮት ቋንቋ ውስጥ አሉታዊ አገላለጾች (የማይወሰን፣ የማይደረስበት፣ ታውቆ የማይፈጸም፣ ቅርብና ያለ ነገር ግን ተፈልጎ ያማያልቅ፣ ---) የሚሉ አገላለጾች የሚበዙት። በኦርቶዶክሳዊ ዕሳቤና ንግግር ውስጥ እውቀት፣ እውነትና ተጨባጭነት የግድ እንደ ሥዝም ሳይንስ ለሁሉም ነገር በመጠንና በቁጥር፣ በገደብና በጊዜ ካልተገደበ በስተቀር የለም የማይባለው። 

እንዲህም ሲባል ሕያው አምላክ ራሱ ለእኛ በሥጋ ማሪያም ተገልጦልን፣ ተጨብጦና ተዳሶ፣ ታይቶና ተሰምቶ የሚረዳንን እና  ወደ በለጠ መረዳት የምንሄድበትን የእውቀት መንገድ  እና በር ሰጥቶ ነፃ የለቀቀን።   ይህ መገለጥ ግን ለፍጡር የማይታወቀውን መለኮታዊ ምሉዕነቱን አይደለም፣ በተዋሕዶ እኛን በሆነበት የሥጋዌ ወሰኑ እንጂ። የማይታየውን ስፉህና ረቂቅ ማንነቱን በመንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ተረድተን በዚያ ፍለጋና የአንድነት እውቀት ውስጥ እንድንኖር አደረገ ።

ሳይንሳዊ እውቀት በቤተ ሙከራና በስታቲስቲካዊ ዘዴ ይረጋገጣል። መለኮታዊ የመገለጥ እውቀት ግን በአማኞች ሕይወት ውስጥ በመገለጥ በልምድ ይረጋገጣል።     የመገለጥ እውቀትን በበቤተሙከራና በስታቲስቲካዊ መንገድ ማረጋገጥ ግድ አይሆንም፣ አንዲሁም የማይቻልባቸው ምክኒያቶች የበልጣሉ። ምክኒያቱም እውቀቱ የሚገለጥበት ስፋት፣ ጥልቀትና አይነት እንደሰውዬው ከእግዚአብሔር ጋር የፈጠረው አንድነትና ባለሟልነት በነፃ የሚታደሉት ነው። አንድነቱና ተዋህዶው ሰውንም ሆነ የፀጋው ምንጭ የሆነውን አምላክ ግድ የሚለው ነገር ሳይኖር በነፃ ፈቃድና በፍቅር የሚደረግ፣ ከሰጭው ቸርነት የሚነሳ ነው።   ሰው በእግዚአብሔር የተፈጠረና ነፃ ፈቃድ ያለው ቢሆንም በፋቃዱ ተነሳስቶ በፍቅር ራሱን ለአምላኩ ሲሰጥና ሲያስገዛ የሁሉ ባለቤት ለሆነው አባት ልጅ ይሆናል፤ ልጅ በመሆኑ የአባቱ  ወራሽ ስለሚሆን አባቱ ሰው በሥጋዊነቱ ብቻ ሊረዳው የማይቻለውን እውቀትና ጣዕመ-ሕይወት ይገልጥለታል። የእግዚአብሔር መንፈስቅዱስ የፀጋው ማደሪያ ቤት ስለሚሆን እንደ ቤቱ (ልቡ) ስፋት(ንጹሕነት፣ የዋህነት)  መጠን የእግዚአብሔር የሆነውን እውቀት ያውቃል።   

ስለዚህ የመገለጥ አምላካዊ እውቀት የሚረጋገጠው እግዚአብሔርን በመውደድ ትዕዛዘቱን  በመጠበቅ በግል ደረጃ የሚታደል ይሆናል። እያንዳንዱ በጥምቀት የእግዚአብሔር ልጅነትን ያገኘ ሁሉ በአባቱ ቤት ውስጥ ያለውን ለማወቅ በክርስቶስ ኢየሱስ ለሱታፌ የተጠራ ነው፡- “ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር ቢሆን ወይም እኔ ከራሴ የምናገር ብሆን ያውቃል።”   

እንዲሁም መጽሐፍት ይህንን እውቀት ለማግኘት እንድንጋደል ያበረታቱናል፡- “እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም፤ በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው።”  “ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤”።   

እንደምንመለከተው በሳይንሳዊ እውቀትና በመለኮታዊ የመገለጥ እውቀት መካከል ግጭትና ተቃርኖ ሊኖር አይችልም። ምክኒያቱም ሁለቱም በራሳቸው መንግድ የሚፈለጉ፣ የሚሠሩ ናቸው። ሁለቱም ለዚያው ለአንዱ የሰው ልጅ ግልጋሎት የሰጣሉ። ሁለቱም ለሰው ልጅ ጠቃሚና አስፈላጊ ናቸው፣ ነገር ግን እኩል አይደሉም። ለብቻ ዋጋ ይውጣላቸው ከተባለ ፈጽመው አይወዳሩም። ፍጡር የሆነው አእምሮ ፍጥረትና መስተጋብራቸውን መርምሮ የሚያገ እውቀት፣ ፈጣሪ ከፈጠረው የሰው ልጅ ጋር ባለው አንድነት በፍጥረት ሊታወቅ ከሚችለው በላይ የሆነ መለኮታዊ እውቀቱን በጸጋ ሲያድል ሊወዳደሩ አይችሉም።  በሥጋ የተገኘ ለሥጋ ቢያገልግል አንጂ ለነፍስ የሚተርፈው በመለኮታዊ እውቀት እልቅና ሲመራ ብቻ ነው።  በዓለማዊ ነገር ላይ ብቻ የሚያተኩሩ ሰዎች በነፃ ፈቃዳቸው ራሳቸውን ከእግዚአብሔር ከሚሰጠው እውቀት በማራቆት ለሥዝም ሳይንሳዊ እውቀት ብቻ ቅድሚያ በመስጠት ነፍሳቸውን ያገሳቁላሉ። ሕይታቸውን ሙሉ በዚህ ምድራዊ ጉዳይ ላይ ብቻ እንደታሠሩ የቁሳዊው ዓለም ባሪያ ሆነው የመንፈስ ቅዱስን ፍሬ ሳያፈሩ፣ ጣእሙን ሳይቀምሱ፣ ተስፋ መንግሥተ ሳማያትና የእግዚአብሔርን ቅርበት ሳይገነዘቡት ያልፋሉ።   እንዲሁም ራሳቸውን በመገለጥ እውቀት ብቻ ለመወሰን የሚሞክሩና የተፈጥሮ አእምሮአዊ ጻጋቸውን ለምርምር የማይጠቀሙ ሰዎች በዚህ ምድር የሰው ልጆችን ተፈጥሮአዊና አስገዳጅ ፍላጎቶች ለማሟላት እድል የሚሰጠውን ሳይንሳዊ እውቀት ሳይገለገሉበት ይቀራሉ።    

ሳይንሳዊ እውቀት የዕለት ተዕለት ፍላጎታችንን በቀላል መንገድ እንድናሟላ ይረዳናል። መጓጓዣው፣ የሰው ለሰው ጎንዮሻዊ መገናኛው፣ ሕክምናው፣ የግብርና ኢንዱስትሪ እድገቱ ሁሉ የሳይንሳዊ እውቀት ውጤት ናቸው። መለኮታዊው የመገለጥ እውቀት በበኩሉ የማይመጠን የማየት አድማስን የከፍታል፣ ወደላይ ግኑኝነት የምናደርግበትን፣ ለመኖራችንና ሰው ለመሆናችን ትርጉም ይሰጠናል፣ የሥራና የባህል መንገዶቻችንን በቅድስና መንገድ ያስኬድልናል፣ ሳይንሳዊ እውቀቱንም ለኃጢአትና ለርኵሰት እንዳናውለው፣ ነገር ግን ትዕዛዘ እግዚአብሔርን በስፋትና በቅልጥፍና ለመፈጸም እንድንችል ይመራናል።  የቤንዛንታይን፣ የአሁኑ አውሮፓ ሳይንሳዊ አውቀት ያለ ክርስትና ፈጽሞ አይታሰብም። ለሃይማኖታዊ ሥራና ጠቀሜታ ሲሉ የተፈጥሮን መስተጋብር ያጠኑ፣ የሰውን ድካም ለማቃለል የተለያዩ ምርምሮችን የጀመሩ ገዳማዊያን  ናቸው። በእርግጥ ሳይንሳዊ ግኝቶች እያደጉና ገዳማዊያኑ እየተበረታቱ ሲሄዱ ይህ መንገድ  የምእረባዊያን ነገረ መለኮት ተጠየቃዊ ምርምር እንዲጫነው አድርጎት ጉዳት አስከትሏል። የቤተክርስቲያን መሪዎች በሂደቱ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን በመወሰን በሳይንሳዊ የምርምር መንገድና መንፈሳዊ የተዋህዶ መንገድ መካከል ግጭት እንዲፈጠር አድርገዋል። ይህ በእኟ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የለም። የሚጣላና የሚጋጭ መንገድ ጀምራም አታውቅም። ዘመናዊው ትምህርት በ1942 ወደ አገራችን በመንግሥት በጀት ሲተከል አገራዊ መንፈሳዊ እውቀቱ ከሕዝብ አውድ እንዲለይና በቤተክርስቲያን አገልጋዮች ብቻ እንዲወሰን ተፈርደበት። 

ሥዝም እውቀት አስፈላጊ ነው፣ ነገር ግን የሰው ልጅን የሕይወት ግብና ዘላለማዊነት ለሚያገናዝብ ግዴታ አይደለም።  ከሁሉም በላይ ፍጽምት፣ ለፍስ መዳን የምትጠቅም  እውነተኛ ያለችው በእግዚአብሔር የመገለጥ እውቀት ውስጥ ነው።  ይህች እውነት በቁሰዊ መስተጋብር ምርምር በቁሳዊ ተጨባጭነት (obejective) አትገኝም፤ እንዲሁም ልናቆሳት (objectivize) አይቻለንም። ከእግዚአብሔር ጋር በፍቅር በመዋሐድ የምተገኝና የምተታውቅ የሰላም፣ የውበትና የነፃነት እውነት ናት።  ያገኛትን ሰው የምትጠቅም በግል የምትታወቅ አውነት ናት።  የክርስቶስ የሆነች እውነት ናት፣ ወይንም በትክክል ለማስቀጠል ራሱ ክርስቶስ ናት፤ አርሱም የነበረ፣ ያለና የሚመጣ፣ ለዘላለምም የሚኖረው እውነት ነው።     

 በዚህ አውድ ውስጥ የዘመናችን መደበኛ የትምህርት ተቋማት በዓለም አቀፍ ዥም ሉላዊ ተቋማት ፍልስፍና፣ ሕግና ሥርዓት ሥር የሚተዳደሩና ጥበቃ የሚደረግባቸው መሆኑን ስናውቅ ለክርስትና የለውን አንድምታ እንረዳለን።  ሃይማኖትን ሊብራል (ኢቀኖናዊ ንዝኅላል ፖለቲካዊ ርእዮት (ኢንፖር)) የማድረግ ሂደት ኢስላማዊ መንግሥታት በጥንቃቄ ከሚመሯቸው አገራት ውጭ የሁሉም አገራት ሕዝቦችና እምነቶች ተገድደው ይሳተፉበታል። አማራጭ በማቅረብ የመገለጥ እውቀት ላይ የተመሠረቱ እውነቶችና እይታዎችን በማዳቀልም ሆነ መዋሐድም ሥዝም እውቀትን መቀደስ ፈጽሞ ክልክል ሆኗል።    በመሆኑም በአገራት የሚካሄዱ የመንግሥት፣ የሕግ፣ የትምህርት ሥርዓት፣ የማኅበራዊና ፖለቲካዊ አደረጃጀት ሙሉ በሙሉ ሃይማኖትን ኢቀኖናዊና ከሥዝም ማያ በታች የሆነ የፖለቲካ መገልገያ ወደማድረግ አድርሶታል።  ለውጦችን የሚጀምሩ ንቅናቄዎችና መንግሥታት ሁሉ ጅምራቸው ነባርነትን በተለይ መለዋወጥ የሌለባትና ዶግማዊ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ከማጥቃትና ለማስወገድ ከመሥራት ራሳቸውን ማቀብ አይችሉም፣ ደርግ፣ ወያኔ፣ ኢሕአፓ፣ ኦነግ፣ ብልጽግና ወዘተ ሁሉ እርስበርሳቸው እየተዋጉና እየተጠፋፉ ኦርቶዶክሳዊነትን በማጥፋት ላይ ሁሉም ይስማማሉ።

በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ (ሥልጣኔን በሥዝም ሚዛን በሚሰፍሩ ማኅበረሰቦች)  በመንፈሳዊነትና በሃይማኖተኝነት መካከል ድንበር ተቀምጦ በትውልዱ መካከል እንዲተዋወቅ እና የሰብአዊ ፍጡር እርስ በእርሰና ከአንድ እግዚአብሔር ጋር መኖር የግድ የሆነው መንፈሳዊ ተዋሕዶ የሚለው ነባር አስተምህሮ ቀርቶአል።  ሁሉ ነገር በግል እንዲታሰብ፣ እንዲቀመስ፣ እንዲተረጎም እና ትርጉም እንዲያገኝ ለማድረግ የሚቻለው መንግሥታዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ትምህርታዊና መኅበራዊ ጫና ይደረጋል። 

ሰዎች “እኔ መንፈሳዊ ነኝ ነገር ግን ሃይማኖተኛ አይደለሁም”  ሲሉ መስማት የተለመደ ነገር ሆኗል። ሃይማኖት ፈጽማ ከእግዚአብሔር ለቅዱሳን የተሰጠች፣ ሰዎች የሚጋደሉላት ከሆነ፣ መንፈሳዊነት በሃይማኖት ሆኖ በፍቅር ከባልንጀራ ጋር ተባብሮ፣ በረቂቅ የፍቅር ገመድ ተዋሕዶ በዚያ መሰላልነት ከእግዚአብሔር መዋሀድ ነው፤ ይህ አስተምህሮና የቀዳማዊያኑ የክርስቲያኖች ሕይወት  ለአዲሱ ዘመን ማኅበረስብ ትውልድ አዲስ አባባል፣ ትርጉም አልባ ብቻ ሳይሆን አዲስ ክህደት ነው ። 

ሃይማኖተኛ አይደለሁም የሚሉ ሰዎች ምን ማለት እንደሆነ ሲገልጹ ዶግማ ያለው፣ የታወቀ ሲኖዶሳዊ ማንነት ያለው አካል አባል አልሆንም ማለታቸው ሲሆን “መንፈሳዊ ነኝ”  ሲሉ ስሜቴንና ፍላጎቴን፣ ስነልቦናዬን አዳምጣለሁ እንደማለት ነው።    ይህን ከክርስትና አስተምህሮና ተግባራዊ ሕይወት የሚቃረን አስተሳሰብ  በመደበኛ ትምህርትና በመገናኛ ብዙኃን፣ በሲኒማና በተለያዩ ማስታወቂዎች በማራገብ የግል ሥጋዊ ፍላጎት የሁሉም ነገር መሪና ማዕከል ተደርጎ እንዲታሰብ ዓለም አቀፍ ዘመነቻው ተጧጡፎአል። 

በለውጥና በመሻሻል፣ አዲስነት እና በእምርታ ስም ሁሉም የለውጥ እርምጃ የሚጀምረው ከግል እና ለግል ነው። የጋራ የሚባል ነገር ከቤተሰብ ጀምሮ ትርጉም እንዲያጣ ተደርጓል፤ ሂደቱ በአገር ደረጃ ሲታይ ታላለቅ በካምፓኒዎችና የፖለቲካ ልሂቃን የመንግሥትን መዋቅርና ሀብት በመቆጣጠር የሕይወት መሠረታዊያንን እና የመኖር ዋስትና የሆኑ ሀብታትን እጅ በማድረግ ትውልድ ለሁሉ ነገር ትርጉም ሲሰጥ መደበኛ ትምህርትና የወቅቱ የፖለቲካ የበላይነት ያገኘው አካል ብያኔ ብቻ እንዲወሰን ተደርጓል። በዚህ ውስጥ ሃይማኖት፣ ታሪክ፣ ትውፊትና ባህል ቦታ የላቸዉም።    ስለዚህ ሃይማኖትም መንፈሳዊነትም፣ እግዚአብሔርም፣ መዳንና መሞትም፣ ሲኦልና መንግሥተ ሳማያትም ትርጉማቸው የግል ሆኗል። 

የጋራ ነገር በሌለበት የሚመሩበት ዶግማ፣ የሚጠብቁትና የሚጠበቁበት ቀኖና አይኖርም። ሁሉም በሕገ-መንግሥት፣ በፖሊሲና በፖሊስ፣ በካሜራና በስለላ ተቋማት ተተክተዋል። የመገለጥ እውቀት በተገለለበት፣ በአእምሮ ጠባይ በሚገኝ ሥዝም ሳይንሳዊ እውቀት አምባገነንነት ሰብአዊነት እንኳ ትርጉም በሚያገኝበት አውድ ውስጥ ማኅበረሰብ ሕይወት ያለው ተቋም ሳይሆን ለገበያ የሚገናኙ የሰጥቶ መቀበል፣ ተወዳድሮ የመሸናነፍ መስተጋብርና ምድራዊ ብቻ ይሆናል። በዚህ አውድ   ማኅበረሰብ ውስጥ “ሰውነት” ትርጉሙ አዲስና ቋሚነት የሌለው፣ በጋራ የማንረዳው ዝግመተ ላውጣዊና የፖለቲካ ፍጡር ነው።  እዚህ ደረጃ የሚደረሰው ከላይ ስለ መለኮታዊ እውቀትና ሳይንሳዊ እውቀትና ጠቀሜታ ላይ በሚኖረን አግባብ ያልሆነ መረዳት ነው። 

ኢንፖራዊያን ሕይወትን ሁሉ በአእምሮ ጠባይ ብቻ በሚገኝ የቁሳዊ ፍጥረት ሥረዓተ መስተጋብርን በማጥናት በሚገኝ ሳይንሳዊ “ዕውቀት” መረዳትና የሰውን የመኖር ትርጉም መበየን እንደሚቻል ያስባሉ። መንፈሳዊ ነን ሲሉም ሳይንስ ብቻውን ሰውን የመኖር ትርጉም ማጎናጸፍ እንዳልቻለ በመመለከት ስሜትን፣ ስነልቦናንና የሰዎችን ግኑኝነት፣ ከቁሳዊ ሀብት ውጭ ሌላ ተስፋ የሚደረግ ነገር ፈጥሮ ለራስ ማሳመንን የሚጨምር ፍለጋ  እንዳስፈለጋቸው ያሳያል። ግራ መጋባታቸውን ያገልጣል።   

በተጨማሪ ራስን መለወጥ/ማባዛት/የራስን አካል ብልት ወይንም ሁለመናውን ማደስ (“autopoiesis,”) በሚል ጽንሰ ሀሳብ በመነሳት በሥዝም ማኅቀፈ-እሳቤ ውስጥ ሃይማኖትን ከመንፈሳዊነት፣ ሰውነትን ከእግዚአብሔር፣ ምድርን ከሰማይ በመለየት ፖለቲካን (ሕዝብና አገር አስተዳደርን፣ የቤተሰብ አመራርንና የሰውን ግኑኝነት) መበየን ዓለምአቀፍ አስተሳሰብ እስከመሆን ደርሷል። 

ኢቀኖናዊነትና ንዝህላልነትን ዶግማው ያደረገ ፖለቲካ ዶግማና ቀኖና ያላትን ኦርቶዶክሳዊት ክርስትና የፖለቲካ መጠን እንዲኖራት ማንኛውንም ተጽእኖ ያደርጋል። ዛሬ በአገራችን የመንግሥትና መንግሥትን የሚፃረሩ የፖለቲካ ድርጅቶችን ጨምሮ የሚከተሉት የትምህርት፣ የፖሊሲና የፍልስፍና ማኅቀፋቸው ሲፈተሽ ኢንፖራዊ ነው። 


መንፈሳዊነትና የኢንፖር ሃይማኖት አመጣጥ  


ኢንፖር ታሪካዊ አመጣጥ የሚጀምረው ከቤተክርስቲያን የወጡ ኬሌቄዶዋኒያን በየዘመናቱ በክርስትና ውስጥ የሚፈጠሩ ኒፋቄዎችን እንደ እድል በመጠቀም የተፈጠሩ የዘመነ አብርኆት የክህደት ትምህርት ነው። ለእነዚህ ትምህርቶች መጠናከርና ወደ መንግሥታትና የፖለቲካ መመሪያነት ማደግ፣ ብሎም ቀዳሚት ክርስትና በቀጥታ መዋጋት መጀመር አስተዋጽኦ ያደረጉ ኢንፖርታዊያን ምሁራን መካከል የሚከተሉት በዓለም ዙሪያ ስም ያላቸው ናቸው፡-


ከቀደማዋያኑ  Laozi፣ Aristotle፣ ሂዩማኒዝምን ያራመዱ እነ Niccolò Machiavelli፣ Desiderius Erasmus፣ Thomas Hobbes፣ John Locke፣ Voltaire፣ Adam Smith፣ Immanuel Kant፣ David Ricardo፣ Alexis de Tocqueville፣ Herbert Spencer፣ John Dewey፣ Max Weber ፣ John Rawls፣ ወዘተ የሚያመነጩት ትምህርቶችም በሥርዓት ውስጥ እያካተተ ከሺ ዘመናት በላይ ተጉዞ ዛሬ ላይ ፀረ ኦርቶዶክሳዊ አቋሙን ግልጽ ያደረገ ርእዮት ነው።  

አንድ The Restructuring of American Religion በሚል ርእስ   በ1988 በተደረገ ጥናት ማዕከላዊነት ያላቸው የእምንት ክፍሎች እንዴት ቀስ በቀስ እንዴት ተሸርሽረው በግለሰቦች አስተሳሰብና ዝንባሌ መወሰን እንደጀመሩ ያመለክታል።  ጥናቱ ይህ ከማኅበራዊነት ወደ ግላዊ እምነት የመፈጠር ጉዞን በ1960ዎቹ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መስፋፋት ጋር መያያዙን ይጠቁማል።   

አዳዲሶቹ ሥዝም ትምህርት ቤቶች የባህል አብዮትን በማስተዋወቅ ትውልዱን ከወላጆቻቸው እምነት፣ ትውፊትና ታሪክ በመነጠል የየዘመኑን ተፅእኖ አሳዳሪ ፍላጎትና መረዳት በመከተል የሚበየን ነበር። የፖለቲካ ልሂቃንና የባለሀብቶች ጥቅማቸውን በብዙኃን ላይ ለመጫን በትብብር የትውልድን አስተሳሰብ የመቀየርና የመቆጣጠር ሥርዓትን በመላው የምዕራቡ ዓለም ዘረጉ።  በዚህ ሥርዓት በቅኝ ገዥነትና በባሪያ አሳዳሪነት ደረጃ እስከ ማስገገድ የተራመዱበት ዘመን ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰበት ነው። 

በሌላ በኩል በመቻቻል ስም የጥቁር አሜሪካን ባሮችን በፃነት የመቀበል ዝንባሌም የታየበት ሲሆን “ሰውን ባሪያ” ከማድረግ ስሑት ርእዮት ወደ ሌላ “ሰው ሁሉ የሚያስበውን በግሉ ያድርገው” ወደሚል ሌላ ስሑት ፍልስፍና ተሸጋገሩ።  በዚህ ጊዜ በአሜሪካ ለሴቶች መብትና በተወሰነ ደረጃ ሥልጣን መሥጠትን መለማመድ ጀመሩ ፣ ሃይማኖትን ከመንግሥታዊና ሲቪል መስተጋብርና ታሰትፎ እንዲለይ አደረጉት። በዚህ ሂደት እምነቶችና ባህሎች ኢንፖራዊ (ሊብራይዝድ) እየሆኑ መጡ። ሂደቱን የሚቃወሙ የእምነት አካላትና ስብሰቦች በየቦታው ሲፈጠሩ ራሳቸውም የጥፋቱ አካል በሚያደርጋቸው መልኩ አዳዲስ እምነቶችና የማይመሳሰሉ በመሆን ሕዝቡን የበለጠ ተጋላጭና ግራ የተጋባ አደረጉት። 

ሥዝም ሊቃውንታና ፖለቲካው ይህንን የእምነት ክፍሎች መከፋፈል እንደ እድል በመጠቀም ዛሬ ላይ በኢትዮጵያችን የብልጽግና መንግሥት እንደ ቁምነገር ከምዕራባዊያን ቀስሞ በኦርቶዶክስ ላይ የንደሚደርገው አይነትን የመካፈልና እንደ ትናንሽ ድርጅት ቸርቾችን በፈቃድና በፈቃድ እድሳት ቁጥጥር የሚደረግባቸው ምድራዊ ተቋማት አደረጓቸው።  

የአዳዲሶቹ የእምነት ተቋማት መሪዎች ተቋማቱን ለፖለቲካው እያማስሙና ፈቃድ እያገኙ ለማስቀጠል በየዘመናቱ የፖለቲካውን ስሜት እያገለገሉ ከኑፋቄ ወደ ፍጹም ክህደትና የርኵስ መናፍስት መገልገያነት ተሸጋገሩ።  ሥዝሙ የፖለቲካ ልሂቅ ቀድሞዉን ግለሰቦችን እንደ ምርት ግብአት ለመቆጣጣር ሲያደርግ የኖረው ጥረት አንደ አዲስ በነፃነት ስም በግል ደረጃ ልቅነትን፣ በማኅበረሰብ  ደረጃ ሥዝም ሕግን በማስቀመጥ ብዚኃኑን ግለኛ፣ አምራችና ሸማች ሮቦት አደረገው። በዚህ ሂደት ውስጥ “ሃይማኖት የለኝም ነገር ግን መንፈሳዊ ነኝ”የሚል አዲስ አስተሳሰብን ማስተዋወቅ ተቻለ። በዚህ መንፈስ ውስጥ እንደ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከሐዋሪያት ጀምሮ ሳትለዋወጥ የኖረች፣ በዶግማና ቀኖና የምትጠበቅ፣ ሕብረታዊና በአንድነት ብቻ የምተገለጥን ቤተክርስቲያን ጠላት አድርጎ የሚሰራ ፖለቲካዊ ርእዮት ዓለም አቀፋዊ መልክ ያዘ።


ዘመናዊው ትውልድ በዚህ ግለኛነት፣ ኢቀኖናዊና ንዝኅላል የፖለቲካ ርእዮት ውስጥ ራሱን ያገኘው እንደ ኦርቶዶክሳዊ ሰው፦

 ወደ ክርስቶስ አካል ብልትነት በሕብረት መዋሐድን መፈለግ ሳይሆን በተቃራኒው ቀዳማዊ የሆነውን ሁሉ በመጣልና በመቃወም የማያውቁትን አዲስ ነገር ወደ መፈለግ አዘነበሉ። ስለዚህ የፖለቲካ ልሂቃን ዝንባሌ ላይ የተመሠረተው ነባር-ጠል አዲስነት ሃይማኖታዊ ዶግማን በመተካት በራሱ ፖለቲካዊ-ዶግማ አድርጎ ተከሰተ። በኢትዮጵያ አውድ ውስጥ ሲታይ ይህን በነባር-ጠልነት ላይ የሚመሠረት የአዲስነት ክስተት መቃወምና በትምህርት መሞገት መሞከር ሕግ-መንግሥት የተባለ የፖለቲካ ዶግማና ቀኖናን እንደመጣስ ተቆጥሮ የሚያሰድድ፣ የሚያሳስርና የሚያስገድል መሆን ጀመረ። “ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን መጠበቅ” የተባለውና ሕገ እግዚአብሔርን የሚተካ፣ ታሪክን የሚሽር፣ ከሰብአዊ ፍጡር በላይ ክብር የተሰጠው የዘረኞችን (የወያኔ የኦነግ) ሰነድን ለመከላከል ዜጎችን በጅምላ እስከ መፍጀትና ማፈናቀል የተፈቀደ ተግባር ሆነ። 

በፕሮፓጋንዳ ደረጃ መንግሥትና የፖለቲካ ተቋማት በተለይ በንዑስ የብሔር ማንነት የሰከሩ መሪዎችና ካድሬዎቻቸው ይህን አዲስ እሳቤ ለመከላከልና በሃይማኖት ሥፍራ ለመተካት በሚደርጉት ጥረት “ለአዲስ ነገር ክፍት መሆን፣ የልቦና ውቅር፣ ለውጥ፣ ዘመናዊነት፣ እድገት፣ ሥልጣኔ” የሚሉ አዳዲስ አጃቢ ቃላት በመጠቀም ነባርነትን በተለይ ኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ላይ ሥርዓታዊና መዋቅራዊ ጥቃታቸውን አፋፋሙ። 

በነባርነትና በቅድሰት ቤተክርስቲያን ላይ የሚደረገው ጦርነት ዘለቄታዊና ርእዮታዊ ሆኖ ክርስትና እድትጠፋ ግብ በማስቀመት ሠራዊት ለማግኘት በጭፍንና የማያውቀውን የሚናፍቅ ትውልድ ማዘጋጅተ አስፈላጊ እንደሆነ በመበየን ሐሰትን በትውልድ አእምሮ ውስጥ በተለያዩ መንገዶች ላለፉት 50 ዓመታት አሳደሩ። ይህ ትውልድ የፖለቲካ ሥልጣን ሲያገኝ የመጀመሪያው ዒላማው ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንና ጸጋዎቿን ማጥቃት ልማትና እድገት መስሎ ይታየው ጀመር። ደርግ፣ ኢሕአፓ፣ ወያኔ፣ ኦነነግ ወዘተ በተለይ አሁን ያለው የብልጽግና/ኦሮሙማ ፖለቲካ በግልጽ ዘር እስከማጥፋት የተሻገረ መዋቅራዊና ሥርዓታዊ ተግባር ውስጥ ተገኘ።


ኢንፖር በቀጥታና በተዘዋዋሪ ኦርቶዶክሳዊነትን ከሚዋጋባቸው መንግዶች መካከል የሚከተሉት በአገራችን በኢትዮጵያ ጎልተው የሚታዩ ናቸው፡-

1. የሴት እና የሕጻናት  መብት፣ የቤተሰብ ሕጎች፡- በዚህ ሽፋን ቤተሰብ ማፍረስ፣ የተቀደሰ የክርስቲያን የትዳር ትርጉምን ወደ ሥዝም አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ጉዳይ ማውረድ፣ ትዳርና ቤተሰብ የእግዚአብሔር መገለጫ መሆናቸው ቀርቶ የመንግሥት ጣልቃ ገብነትን ሙሉ ማድረግ፣ ተዋሕዶን በማፍረስ ግለኝነትን ማስፈን።

2. ባህል፡- ከረዥም ዘመናት የማኅበረሰቦች መስተጋብር፣ በተለይ በክርስትና ላይ በቅለው፣ ሃይማኖትን በተግባር የሚገልጹ ባሕሎችን ጎጅ ባህላዊ ድርጊቶች፣ በኃላቀርነት፣ በሥልጣኔ እንቅፋትነት በመክሰስ ከትውልድ ልብና ሕሊና ማራቅ

3. ማህበራዊ መዋቅራትን ፡- በነባር ባህሎች፣ እምነቶች፣ አስተምህሮና እሴቶች፣ አሠፋፈርና አኗኗር ላይ የተመሠረቱ መሠረታዊያን የማኅበረሰብ መዋቅራትን ማፈራረስና፣ በባእዳን ትምህርት መሠረትና በዚያ ትምህርት በሠለጠኑ ሰዎች የሙመሩ አዳዲስ መዋቅራትን መፍጠር። በሃይማኖት ላይ የተመሠረቱ ቀዳሚ መዋቅራትን ማዋረድና መሪዎቻቸው ከትውልድ ክብርና ተሰሚነት እንዳያገኙ ማድረግ

4. መደበኛ ትምህርት፡- የተምህርት ይዘት፣ ሥርዓትና መሪነት ከአገራዊ እሴት፣ እምነትና ባህል የተነጠለ፣ ነባሩ ፈጽሞ በአዲሱ ትውልድ ውስጥ ምንም አይነት ሚና እንዳይኖረው፣ ፍልስፍናውና እሴቱን መደምሰስ

5. ኪነጥበብ፡- ስነ ጽሑፍ፣ ተውኔትመ ፊልም፣ ዘፈን፣ መዝሙር፣ ቅርሣ ቅርሥ፣ ስነ ስዕል በመደበኛ ትምህርት፣ በሚዲያና በፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ሐሰትና እውነትን መለየት ባልቻሉና የየዘመኑን ባለሥልጣን እሳቤ በሚያገለገሉ የኪነጥበብ ባለሚያዎች እንዲመራ ተደረገ፤ በመሆኑም የኪነጥበብ ውጤቶች ነባርነትን የሚያጠቁና በሥሑታኑ የፖለቲካ መሪዎች ምናብ የተሳለችዋን ምናባዊ አዲስ እና ከነባር እሴቶችና ኦርቶዶክስ ነጻ የሆነች ኢትዮጵያ ለማዋለድ አጋር ሆኖ የክፋት መልዕክት ማሰራጫና አእምሮ ማጠቢያ ሆነ።

ዝሙት፣ ሰዶማዊነት፣ ሐሰት፣ በፈጠራ ስም ዶግማና ቀኖናን መዳፈር፣ የተከበረውን ማዋረድና ወራዳን ከፍ ከፍ ማድረግ፣  ተዋረዳዊ የቤተሰብና የማኅበረሰብ ግኑኝነትን ማዋረድና ክፉ ምሳሌ በመፍጠር ከፍተኛ ሚና ተርጫወታለች

6. የተፈጥሮ ሀብት አጥቃቀም ሕጎች፡- የከተማ ቦታ፣ የገጠር የእርሻና የደን መሬት፣ የቤተክርስቲያን ገዳማትና አድባራት የአገልግሎትና የገዳማዊያን የሰብልና እንስሳት ስፍራዎች ክርስቲያኖችን እና ቤተክርስቲያንን በሚጎዳ መንገድ ታስበውና ታልመው ፖሊሲዎች ይዘጋጃሉ፣ ፖሊሲ በሌለበትም ርእዮቱንና አስቀድሞ በሚፈጠር አሉታዊ የሐሰት ትርክት መሠረት አድልዎ መፈጸም በኢትዮጵያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ክርስቲያኖች አሰድዷል፣ ከእምነታቸው አንዲወጡ ጫና ፈጥሯል፣ ብዙዎችን አስገድሏል፣ አሰድዳል፤ እዲሁም  በሺዎች የሚቆጠሩትን አቢያተክርስቲያናት ከአገልግሎት ውጭ አድርጓል፣ ለተተኪነት የታጩ አዳዲስ እምነቶችና ባህሎች በመንግሥት ቀጥተኛ ድጋፍ የጦር መሣሪያን ጨምሮ በሃይል እየተመሩ የኦርቶዶክሳዊያንን ሀብታት ዘርፈዋል።  አሰፋፈር ለመቀየር በሚል በተለይ በኦሮሚያ መንግሥትና በዚህ መነግሥት ቅምጥነት በሚሠሩ የቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ የሲዳማና የአማራ ክልል የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከሚሤ እልቂት እየተፈጸመ ይገኛል

7. ትርክት፡- ኢቀኖናዊ ንዝህላል የፖለቲካ ርእዮትን የዜጎች ሁሉ የመኖር ትርጉምና ነጽሮተ ዓለም ለማድረግ በሚደረግ ፖለቲካዊ ፕሮጄክት የአገር፣ የነግሥታት፣ የቅዱሳንና የቤተክርስቲያን ታሪክ ፈጽሞ ከትውልድ ወደ ትውልድ እዳይተላለፍ የመንግሥት ዋና ሥራ ሆኖ በሐተኛ ትርክት እንዲተካ ተደርጓል። በዚህ ሂደት የአገሪቱ መደበኟ ትምህርት ሥርዓትና ይዘት፣ የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን፣ የምንግሥት ፖለቲካ ሐልዎት ፈጣሪና ደጋፊ ልሂቃን ተባብረው ሐሰትን ሳይንሳዊና እውነት ለማስመሰል ረዥም ርቀት ተጉዘዋል። አያሌ መጽሀፍትን፣ ዶኩሜንታሪዎችን ከመሥራት መጽሐፍ ቅዱስን እንደ ሂተለር ከፖለቲካው አንዲስማማ አርትኦት እሰከማድረስ፣ ብዙ የታሪክና የእምነት መጽሐፍት የተጻፉባቸውን ፊደላትን ቋንቋ ለማጥፋትና ትውልዱ እንዳይገለገልበት በፖሊሲ ደረጃ እየተሠራበት ነው።

8. የመደብና የማንነት ፖለቲካ የዚህ ኢቀኖናዊ ንዝኅላል የፖለቲካ  ርእዮት ልሂቃን በጥምቀት ልጅነት በክርስቶስ የተዋሐዱ የሰማይ ዜጎችን ለመከፋፈልና ለመካፈል    የመደብ ጭቆና፣ የብሔር ጭቆና፣ የጾታ ጭቆና፣ የዕድሜ ጭቆናና በአንፃሩ ጨቋኝ ክፍሎችን በሐሰተኛ ትርክት  በመፍጠር፤ እንዲሁም ለተፈጠረው የሚያጋጩ አካላት መፍትሔ ነው የሚሉትን ስሑት ርእዮት ላይ የተመሠረተ መንገድ ተልመውና ራሳቸውን የመንገዱ መሪና አሻጋሪ አድርጎ በመሰየም  ነባር እምነቶችን፣ መዋቅራትን፣ ማኅበራዊ መስተጋብርን ሁሉ የመበጣጠስ መንግሥታዊ ድረጊት ላይ ይጠመዳሉ።

9. የመከላከያና የፖሊስ ኢንዶክትሪኔሽን ኢንፖር መንግሥት ፖሊስና ሥራዊ ት የሚያሰለጥነው የአገሩን ታሪክ፣ እሴት፣ ነባር ባህሎችና እምነቶችን ሳይሆን ሥልጣን ላይ ወጡ ብድኖች ለራሳቸው ሥልጣንና ምናባዊ ግብ መሳካት የሚጽፉትን ሕገ መንግሥት፣ ሕገ መንግሥቱን ወደ ተግባር የሚለውጡ የማስፈጸሚያ ሕጎች፣ ፖሊሲዎችንና ደንቦችን እንዲጠብቅ፣ ለእርሱ ብሎ አንዲሞትና ዜጎቹን እንዲገድል ነው። ይህ በኢትዮጵያ ለብዙ ዓመታት ተፈጽሞ አሁን ወደ ዘር ማጥፋት ደረጃ አድጓል።

ስለዚህ ፖሊሲና መከላከያ ኢንዶክትሪኔት ሲደረግ ዜጋ ሰውን ሳይሆን ተጻፈ ወረቀትን ለመከላከል የተደራጀ እንዲመስለው ተደርጎ ስለሆነ “ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ሊፈርስ ነው”! ሲሉት ዚጎችን ከማሰር፣ ከማፈናቀልና በጅምላ ከመፍጀት አይመለስም፣ በተግባርም እየታየ ነው። 

10. ብዙኃን መገናኛ መቆጣጠር “መገናኛ ብዙኃን” የሚል መልካም ስም የተሰጠው ተቋማ የሕዝብ አእምሮ ማጥቢያና መለያያ እንዲሆን ይዋቀራል፣ እንደነትና ነባርነትን፣ ቀኖናዊነትን ታሪካዊነትን፣ ተዋረዳዊ ግኑኝነትንና ትሥሥርን የሚበጣጥሱና ዜጎች ዋስትና እንዳይሰማቸው፣ በሁለንተናቸው የምንግሥትን የፖለቲካ ተቋማት እንደ ብቸኛ መሲህ አንዲያመልኩት ለማድረግ ይጠቀሙበታል።  ኢንፖር መገነኛ ብዚኃንን የሚገለገለው ነባርነትን ለመዋጋትና ዜጎች ማንነታቸውን አጥተው ልቅነትን ከጥገኝነት፣ በራስ መተማመንን በፖሊካዊ በርነት ተክተው ለገቢና ለሆን ከመኖር ውጭ ምንም ስለ ዶግማና ቀኖናዊ ማንነታቸው እንዳይጨነቁ ማድረግ ነው።

11. ሃይማኖትና ፖተለካ ይለያያል የሚል ማደናገሪያ ኢንፖር ዶግማና ቀኖና ያላቸውን ሃይማኖቶች እንደ ጠላትና ለለውጥ እንቅፋት እንደሚሆኑ በመበየን በግልጽና በሰውር፣ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ይዋጋቸዋል። በትርክት፣ በስሑት ርእዮትና ትምህርት፣ አማራጭ ውጭ-ገብና ሰው ሰራሽ እምነቶችን በማስተዋወቅና ለኢንፖር ትውልድን በማመቻቸት ነባርነትን ይዋጋል።  

“ፖለቲካና ሃይማኖት ይለያያል” በሚል ማደናገሪያ ሃይማኖት በአገራዊ ሕግ ድንጋጌዎች፣ ፖሊሲዎች፣ በአስተዳደርና በቤተሰብ ላይ ተጽእኖእ እንዳይኖረው ያደርጋል። በተቃራኒው ሃይማኖትን የሚቃረኑ ሕጎችንና አሠራሮችን፣ ፍልስፍናዎችን የትውልድ መመሪያ የሚያደርግ ፕሮጄክቶችን ይተገብራል። 

12. እምነቶች ሁሉ እኩል ናቸው የሚል “እምነት” ትውልድን ከቀኖናና ዶግማ የማስተወጣት ስልት በመከተል “እውነት ብዝኃነት ያላት፣ እንፃራዊና የግል ናት” በሚል የክህደት ፍልስፍና በመመሥረት ትወልድን በአብድ ቀዳሚ፣ ዶግማዊና ቀኖናዊ ሃይማኖትና ነባር ትውፊት እንዳይጸና ይደርጋል።   “እምነቶች ሁሉ እኩል ናቸው” በሚል መርኅ ሥር “ሁሉም እምነቶች” ሥልጣን ያላቸው ኢ-ሀገራዊ ልሂቃን ከሚጽፉት “ሕገ-ምንግሥት በታች ናቸው” የሚል ድምዳሜ ላይ ይደርሳል። 

የኦሮሙማ/ብልጽግና መንግሥት ለምሳሌ “ኦሮሙማ ከአንዚያ እምነቶች ሁሉ በላይ ነው” (እነዚያ እምነቶች የተባሉት አቶ ሽመለስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚደንት “የረብና የአይሁድ ስሞች” ይጠቀማሉ ያላቸው ነባር እስልምናና ኦርቶዶክሳዊት ክርስትናን ነው። 

13. ጊዜ አንዱ ትውልድን ከሕገ እግዚአብሔር በመለየት ልቅና ኢቀኖናዊ ማድረጊያው መንገድ ከወላጆቹና ከማኅበረሰቡ፣ ከቤተእምነቶችና ከባህላዊ ኵነቶች ጋር በቂ ጊዜ እንዳይኖረው ማድረግ ነው። ይህ የሚፈጸመው ከአገራዊነት እጅጉን የራቀና የሚፃረረውን መደበኛ ትምህርት የሚማርበትን ጊዜ ማስረዘምና ከሚያስፈልገው በላይ አብዝቶ ልጆችን ጊዜ ማሳጣት፤ ጊዜ ሲኖር ወደ ማንነታቸው እንደሳያስቡ መዝናኛ በሚል ውጭ ገብ ጨዋታዎችንና ጌሞችን፣ የባእዳንን ሲኒማና ሽርሽር ማዘጋጀት፤ ሰንበታትን ጠብቆ መንግሥታዊ ሥራዎችን፣ ኵነቶችን፣ ስብሰባዎችን፣ የሚዲያ መዝናኛዎችን ማቅረብ። 

14. ምልክት ነባር ምልክቶችን ትርጉሞች መቀይርና የቱሪስት ሸቀጥ ማድረግ፣ መደምሰስ፣ ወደ ውጭ መሸጥ፣ በጠላትነት ከሚፈርጁት ማኅበረስብና የታሪክ ኵነት ጋር በማቆራኘት ማስጠላት፣ አዳዲስ ምልክቶችን በሐሰተኛ ትርክት ድግፎና በፖሊሲ አስገድዶ ማስተዋወቅ።  አሁን ያለው ትርክት ነጠላ እና የኦርቶዶክሳውያን በመሆኑ በዙ አዳዲስ አምጥተንበት እንትካዋለን የሜለው ዘመቻ በተግባር እየዋለና ኦርቶዶክሳውያን ሕየወታቸውን እንዲያጡና አሠፋፈራቸው ሳይቀር እየተቀየረ የሚገኝበት ትግባራዊ ሂድት እጃችን ላይ አለ።


የፆታን ትርጉምና ሚና ከተፈጥሮና ከነባር እምነቶችና ባህሎች በተቃረነ መንገድ መቀየር

ኢንፖር አንድን ማኅበረሰብ ከዶግማና ቀኖና ለማስወጣት ከፍተኛ ትኩረት የሚደርገው በፆታ ጉዳይ ላይ ነው። ይህን ሤራ በመላው ዓለም ላይ እያስፋፉ የሚገኙት ምዕራባዊያን በተለይ የአሜሪካ ጥቂት ፖለቲካ ልሂቃን ዋና የውጭ ግኑኝነት ፖሊሲ አካል እስከ ማድረግ ደርሰው የሴት መብት፣ የፆታ እኩልነት፣ የሕጻናጽ መብት በሚል ሽፋን ቤተሰባዊ ሥርዓትን በመደምሰሱ ግንባረርቀደም ሆነዋል። በዚህ መንግድ የትዳር መፍረስ፣ ውርጃ፣ ዝሙት፣ ሰዶማዊነት፣ ጾታን በሕክምና መቀየር መብት ሆነው መደንገጋቸው ብቻ ሳይሆን በግድ በደካማ አገሮች ላይ የሚጫኑ የንግድ፣ የልማትና የብድር ቅድመ ሁኔታዎች ሆነዋል። የዚህ አይነቱ ሂደት እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገርና ሃይማኖት፣ ሕዝብና ታሪክን ዋጋ የሚሳጡ ደካማ ስብስቦችና ዘረኘች ሥልታን ላይ ሲወጡ አመቺ ሁኔታ ስለሚገኝ ትውልዱን በፍጥነት ከሰብአዊነት ወደ ፍጹም ልቅ አራዊትነት የሚቀየር ለመሆኑ በኢትዮጵያ ወገኑን የሚዘርፍ፣ በጅምላ የሚሳድድና የሚፈጅ መዋቅረን በደስታ የሙሳተፉበት የጎሣ ዘረኞች ፖሊሲና ታጣቂ ማየቱ ይበቃል። ሰዶማዊነትና ውርጃ እንደ ቋያ ተቀጣጥሏ፣ ፍቺና ከጋብቻ ውጭ ወሲብ ባህል ሆኗል።  ኢንፖር የሚያስከትለው ፍሬ ሁሉ በኢትዮጵያ ታይቷል። አሁን የመጨረሻዋን የሞራልና የሰብአዊነት ልኬት ኦርቶዶክስን ሳይቀር መንግሥት የሐሰት የዘር ሲኖዶስ ለመፍጠር ሙሰኞችም፣ አመንዝራዎችንና ዘረኘቾን ሰብስቦ “ሲኖዶስ” በማለት በጠመንጃ ሰው እየገደለላቸው ወደ ቤተመቅድሰ ሲያስገባ ይስተዋላል።

በኢትዮጵያ ብቻ ከሚታየው የግድያውና ማሳደዱን ዘረኛ ሕይወት ትተን ሌላው ሁሉ በአሜሪካ ማኅበረሰብ ውስጥ ተገልጣል።   ከ1960ዎቹ እስከ 1990ዎቹ ባለው ጊዜ ውስጥ ግልጽና ከፍተኛ ልውጥ በማኅበረሰቡ ላይ እንዲታይ ፖለቲካው የትውልዱን አእምሮ በከፍተኛ ዘመቻ አበላሽቶታል። ለምሳሌ አንድ ጥናት እንሚያመለክተው “ትውልዱ አሁንም አዳዲስ ነገሮችን መፈለጉን ቀጥሏል። ፍለጋውም አላቋረጠም--- ፍለጋው የተለያዩ እምነቶች፣ ባህሎች፣ በማኅበራዊ ሳንስና ፍልስፍና የሚመጩ አስተሳሰቦችን ሁሉ በመቀይጥና በተናጥል የመመርመርና የመሞከር ነው --- ፍለጋው ምንም መርህና ሕግ የሌለው እያንዳንዱ ሰው ለግሉ የሚስማማውን እምነት፣ አስተሳሰብና የአኗኗር ዘይቤ “በነፃነት”  ይፈልጋል፣ ይሞክራል፣ ያጋባል፣ --- ስለዚህ ሃይማኖት የቀኖና አጥር የሌለው፣ ባህል የሌለው፣ ጠባቂና አባት የሌለው የግለሰቦች የአስተሳሰብ ውጤት መስሏል።  እዚህ ላይ ነው “መንፈሳዊ ነኝ ነገር ግን ሃይማኖት የለኝም፣ በድርጅት ውስጥ በመሆን አይዳንም፣ ሁሉም እምነቶችነ ለድኅነት ያበቃሉ ወዘተ” የሚሉ የፕሮቴስታንትና የአዲሱ ዘመን ንቅናቄ አስተምህሮዎች የኢንፖር አገልጋይ እና ወደ ኢአማኒነት የሚያመሩ የምእራባዊያን ሸቀጥ መሆናቸው ግልጽ የሚሆነው። የዛሩዎቹ የብልጽግና መንግሥት መሪዎች፣ ካድሬዎችና ልሂቃን የዚህ መሥመር ምርኮኞች ናቸው። እዚህ ላይ የአቶ ሽመልሽ አብዲሳና ፓርቲው “የቆሞ ቀሮች፣ የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂዎች ወዘተ” ዘለፋና ፖሊሲ ትርጉሙና ምንጩ ግልጽ የሚሆነው።

በምዕቡ ዓለም “የመመርጥ መብት” ሲባል  የዋሑ የአገረሬ ሰው መሪ መምረጥ ብቻ ይመስለዋል። ትርጉሙ ከዚዯ በላይ መሆኑ ግልጽ የሚሆነው እምነትህ የመምረጥ መብት፣ ጾታህን የመምረጥ መብት፣ ትዳር የማፍረስ መብት፣ በውርጃ ስም ነፍሳትን በማሕፀን ውስጥ መግደል መብት፣ የሚሉ በተፈጥሮና በእግዚአብሔር ሕግጋቶች መመራት ያለባቸውን የማኅበረሰብ አጥሮች ሲያፈራርሱ ስትመለከቱ ነው።  

አንዳንዶቹ የኢንፖር ኢሕገ-እግዚአብሔራዊ የልቅነት አስተምህሮዎችና ፖሊሲዎች ብዙኃኑን በቀላሉ ለማሳመን ሲባል ምክንያት ይፈጠርላቸዋል፡- ለምሳሌ፡

1. የውርጃን አስፈላጊነት ለማሳመን የወላጆች የማሳደግ አቅም ማጣት፣ የሕዝብ ብዛት ከቁጥጥር ውጭ መሆን እና የተፈጠሮ ሀብቱና መሬት መሸከም በላይ መሆንን ለመከላከል፣ የእናትን ጤና ለመጠበቅ፣ ጥቂት ወልዶ በጥሩ ጤናና በጥሩ ትምህርት ማሳደግ የሚሉ ምክኒቶች ይሰጣሉ። ሁሉም ምክኒያቶስ ጠጋ ብለው ሲመረምራቸው ውሃ አያነሱም። ኢንፖር ልቅ ዝሙትን፣ ሽሚያን፣ አልጠግብ ባይነትን፣ ግለኝነትን በማስፋፋቱ ምክኒያት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ከሕዝብ ብዛት ጋር በሐሰተኛ የሳይንስ አጠናን ዘዴና ፕሮፓጋንዳ ውርጃን መፍትሔ አደርጎ ያበረታታል።

2. ሰዶማዊነትና ጾታ መቀየር፡- የሰው ልጅ ሲፈጠር በአካል  ከሚያገኘው ሴት ወይንም ወንድ ከመሆን ውጭ በራሱ ፈቃድ ስሜቱን እያደመጠ ትክክለኛውን በመምረጥ ደስተኛ መሆን ይችላል። ይህ ደግሞ ልክ አንደሌላው የፕሮፓጋንዳ ሳይንስ ሁሉ ይህንንም ሳይንሳዊ ነው የሚሉ ሠራተኞች ተቀጥረውለት የዓለም ጭፍን ተከታዮች ሁሉ ያንኑ ያራግባሉ። ይህ ፕሮፓጋንዳ በእውነተኛ ምርምርና በቅዱሳት መጽሐፍት ሁሉ ስህተት፣ የተወገዘ፣ ለጤና ጠንቅ፣ ኃጢአት ቢባል እንኳ አጀንዳው የሃያላን አገራት የፖለቲካ ልሂቃንና ኢአማኒያን ባለሀብቶች ስለሆ ተቀባይነት አያገኝም። ተቃዋሚዎች አፈናና አደጋ ይደርስባቸዋል፣ አገራት ከሆኑ ይገለላሉ።

3. ከጋብቻ ውጭ የሚደረግ ዝሙት፡- ሰው ከመጋባቱ አስቀድሞ በሩካቤ እየተዋወ ቀ ቢጠናና ተስማሚነታቸው ተመዝኖ ለትዳር ቅድመ ዝግጅት ይጠቅማል፣ እድሜው የደረሰ ሁሉ ስሜቱን ያለገደብ በማርካት ራሱን መግለጽ ደስታ ይሰጠዋል የሚሉ ፕሮፓጋንዳዎችና የዘማ ምስሎችና ቪዲዮዎችን በማሰራጨት ትውልዱን ሕግ አልባ መረን እንሰሳ ያደርገዋል። ይህን የሚቃወም ቤተሰብና ማኅበረሰብ ወግ አጥባቂና ጨቋኝ ተሰኝቶ በመገናኛ ብዙኃን፣ በመደበኛ ትምህርትና በሕግ መዋቅር ይዘመትበታል። 

በአጠቃላይ ኢንፖር መር መንግሥታት ትውልደ የራሱን ባህላዊና ነባር አስተሳሰብ፣ እምነት፣ አኗኗር፣ ማኅበራዊና ቤተሰባዊ ግኑኝነት ሁሉ ከመዳፈር ወደ መቃወምና የራሱን አዲስ ወይንም በጭፍን ከውጭ የሚየው እንዲከተል የሚያደርግ ኢ-ሃይማኖታዊ የፖለቲካ አዲስ እምነት ነው። በዚህ መርህ መሠረት ግለሰቦች የጋራ ሳይሆነ የግል የመንፈሳዊንተ ትርጉም በማበጀት ምንም አይነት የጋራ እሴት፣ ግዱታ፣ ኃላፊነትና የሚጠያየቁነት ቀኖና እንዳይኖራቸው ይሆናሉ።  እዚህ ደረጃ ላይ ሲደረስ ሥልጣን የያዙ ልሂቃን በራሳቸው ዶግማና ቀኖና ሆነው ብቅ በማለት እነርሱ የማይወዱትን ሁሉ የሚቀጣ ሕግና አሠራር፣ ወይንም ከሕግ ውጭ የሆነ ድርጊትን በዜጎች ላይ ለመፈጸም በሩ ወለል ብሎ ይከፈትላቸዋል። የጋራ ነገር ከታየ በመሪዎቹ የተፈቀደላቸው መንጋዎች የሚያደርጉት የመነዳት ያህል አድራጊ እንጂ ከውስጥ በአሴት፣ በእምነት፣ በርእይና በግብ የሚስማሙና የተሣሰሩ፣ የሚኖሩለትና የሚሞቱለት ተስፋ ያላቸው ሰዎች አይሆኑም። አሁን በኢትዮጵያችን በትግራይና በኦሮሚያ ክልል መንግሥት የተፈጠረው ትውልድ የዚህ አይነት በመጂዎቹ የሚመራ፣ አጠገቡ ያለውን ሰው እስከ መፍጀት የሚታዘዝ በልሂቃኑ እጅ የተያዘ መሣሪያ ሆኗል። የኦሮሚያን ክልል እልቂትና ስደት፣ የትግራይን ወጣት በወያኔ እየተነዳ በማይካድራ ሰው መጨፍጨፍ፣ ጦርነት መክፈት መመልከቱ ተግባራዊ የኢንፖር መርህ አስተዳደር ውጤት ናቸው።


ዶግማና ቀኖና ከሌለ፣ ሃይማኖት በግል መንፈሳዊነት ከተተካ፣ በሕሊናና አግዚአብሔር ፈንታ የጎሣና ወይንም አንዳጭ የሚመለክ የፖለቲካ ጀግና ከተተካ አንድንተ ትውልድ በርእይ፣ በፈሪሐ እግዚአብሔር፣ በፍትሐዊነት፣ በጋራ ተስፋና እሴት ማገናኘት እንዴት ይቻላል? መሪዎች የዚህ የኢንፖር ሰለባ ሲሆኑ የዜጎች ደኅነነት እንዴት ዋስትና ያገኛል? ፖለቲካና አመራር ቁማርና ሤራ ሆኖ መሪዎቸችየሚኮሩበት “ጥበብና ዕወቀት” መሆኑን ማን በምን ሚዛን የቃወማል? 

ይህን የኢንፖርን ታሪካዊ አመጣት ያጠና Schmidt (ሽሚድት) የተባለ ተመራማሪ ሃይማኖት አልና የግል መንፈሳዊነት ክስተት የፕሮቴስታንትና የዘመነ አብርሖት አምላክ የለሽ ፍልስርና መስተጋብር ነው ይላል።      “Transcendentalists, romantic Unitarians, Reform Jews, progressive Quakers, devout disciples of Emerson and Whitman, Spiritualists, questing psychologists, New Thought optimists, Vedantists, and Theosophists, among sundry other wayfarers.” በመጥቀስ ለኢንፖር ሞተር በመሆነ እንዳገለገሉና አሁንም ዓለም ላይ መልሕቅ አጥቶ ግራ ለተጋባው ትውልድ ተጠያቂ እንደሆኑ ያወሳል። ይህን በአገራችን ውስጥ የሚታየውን የትውልድ ግራ መጋባት፣ የመንግሥት ዋልጌነትና ፀረ-ነባር እሴትንነት፣ ኢፍትሐዊነት፣ እልቂት መፈጸምና ለኢህ ጥፋቱ የሚተባበር ትወልድ ማግኘትን በመገምግም ኢንፖር መር መንግሥት ፈተና መሆኑን እንረዳለን።


በኢንፖር ምክኒያት ከነባር ሃይማኖት ወደ ግል መንፈሳዊነት የሚወርድ ትውልድ አባል የሚገለጽባቸው ተግባራዊ ምልከቶች አሉት፡-

ለብቻ መቆዘም ወይኒም ሜዲተሽን

ለብቻ መሆን (ከብዙ ሰው ጋርም ሆኖ ለብቻ እንደ አለ ሰው ከግል ስሜት ጋር መጣበቅና ምንም የጋር ግብ ማጣት)

ቅዥትና ሕልሞችን መከተልና ያንን እንደ መንፈሳዊ እድገት መቁጠር 

ሩቅና በተግባር የማይደገፍ ምኞትና ተመስጦ

አንዳች መንፈሳዊ ፀጋ እንዳላቸውና በምናባቸው አምላክ ብለው የፈጠሩት አካል ከአነርሱ ጋር እንዳለ ማመንና በእርግጠኝነት ይህን መናገር

ነባር እምነትን በተለይ እንደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክረስትና ዶግማና ቀኖና ያላትን ማጣጣል፣ ማስጠላትና ጥሎ መሄድ

ምንታዊነት የተጫነው ስሜታዊነት የሚያይልብት ለማኅበራዊ ጉዳይ ራስን መሲህ በማድረግ ያገባኛልን ማሳየት፣ ነገር ግን በተቃራኒው ውጤቱን ለግል ጥቅም፣ ለዝናና ለሀብት ወይንም ለሥልጣን መጠቀም ---

በእነዚህ መገለጫዎቸችሚዛን ኢንፖር አዲስ ራሱን የቻለና የሃይማኖት ተቃራኒ እምነት ነው። 

በSchmidt (ሽሚድት) ጥናት መሠረት ይህ የኢንፖር አዲስ ሃይማኖት የራሱ የሆኑና ሌሎች እምነቶችን እሴቶች ለመሸፈንና ትርጉም ለማሳጠት የሚጠቀማቸወ ቃላቶችና ንግግሮ አሉት፡-

“እምነቶች መልካምን ለትውልድ ቀረጻ የሚጠቅሜ ናቸው” (መንፈሳዊ፣ ሰማያዊና ነፍሳዊ ዋጋቸውን ለማሳጣትና በሞራል መሣሪያነት ብቻ እንዲታዩ የማድረግ መንገድ መሆኑን ልብ ይሏል)።

“ሃይማኖት አንድ ብቻ አይደለም፣ አገላለጹም እንደ አካባቢውና እንደ ሁኔታው፣ እንደየባህሉና እንደ አማኙ ፍላጎት ነው” (አንድ አምላክ ለአንድ ፍጡሩ የሰው ልጅ ድኅነት የገለጣት ሃይማኖት አንዲት ብቻ መሆኗን፣ የሰው ልጅን በአግዚአብሔር አንድ መሆንና ለአንድ ተስፋ ሊሄድበት የሚገባው ጠባቢቷ የተባለች ሃይማኖት ዶግማና ቀኖና እንድ መሆኑ በተዘዋዋሪ የሚዋጋበት አስተምህሮ መሆኑን ልብ ይሏል)።

ሰው በነፃነት የተፈጠረ በመሆኑ በነፃ መርምሮ በገባውና በወደደው ማመንና መንፈሳዊ መሆን ደስተኛና በራሱ የሚተማመን፣ ከምንም ተቋማዊና ቋሚ ሕጎች ነፃ መሆን ይገባዋል (በዙህ አስተምህሮ ሰዎችን ከእግዚአብሔር በመለየት ልቅነትን የዓለም ባህል የማድረግ በአንፃሩ ሰው ጥቁትና ሀብትና ሥልጣንን የሚቆጣጠሩ ልሂቃን የሚያወጡት የጋራ ባሪያ እንዲሆን የማድረግ መንግድ መሆኑን ልብ ይሏል)። 

በአጠቃላይ አስተምህሮው እንደ ማኅበረሰብ የሚያስተሳስር፣ ብሎም ለአንድ አምላክና ተስፋ በጋራ መጣበቅና መደጋገፍ ውስጥ የሚያኖር ምንም ነገር እንዳይኖር የማድረግና ሰውች ያለ እረፍት አዲስ ነገር በመፈለግ እንዲጠመዱ ማድረግ አንዲቻል ተደርጎ የተቀመር ኢአማኒነት ነው።       በዚህ ሁኔታ ውስጥ የሚገኝ ባለሥልጣን የዜጎችን ታሪክ፣ እምነትና ባህል አያከብርም፤ ከዚያም አልፎ ለማጥፋት ይሠራል፤ ወጣቶች የወላጆቻቸውን ማንነት ይጠሉታል፣ በምትኩ ጉዳቱና ጥቅሙን ሳያመዛዝኑ አዲስ የመሰላቸውን ማንኛውንም አይነት ሀሳብ፣ እምነት፣ አኗኗርና ጠባይ ይለማመዳሉ። ይህን ጠባይ ነፃነት፣ ሕዳሴ፣ አዲስ አገር መገንባት፣ አዲስነት ብለው ይጽናኑበታል። 

በዘመናዊው ዓለም በተለይ በአሜሪካ ትውልዱ ነፃና ፈላጊ፣ መርማሪና ፈጣሪ በሚሉ አስተሳሰቦች ራሱን በመሸንገል ወደ ምንምነት ወርዶ ሩካቤው ከቁስና ግብረ ሥጋ ጋር ብቻ ወደመሆን ደርሷል። ቁስንም ቢሆን በተቋም ደረጃ በተዘረጋው ዓለም አቀፍ የዘረፋ መርሐግብር፣ በጦርነትና በኢፍትሓዊ ንግድ ሲሰበሰብ፣ ግብረ ሥጋን ከነውረኛው ግብረሰዶምነት ጀምሮ ከእንስሳት እስከመገናኘት ዘቅጧል። ይህን የማኅበረሰብ ውደቀትና የግለሰብ ልቅነት  ነፃነት ይሉታል። ነፃነት እንዲባልም አስገዳጅ በሆኑ የዓለም አቀፍ ተቋማት ሕጎች ውስጥ ተደንግጎ መንግሥታት ለመተግበር ይፈርሙታል።  መንግሥታት በዜጎቻቸው ላይ ይህን እያስፈጸሙ ለመኖር የሚያሽችላቸውን ስሑት አስተምህሮና አኗኗር ሊብራል መንፈሳዊነት በሚል መብት አድርገው ይዘዉታል። ከዚያም አልፎ ሌላው ዓለም ይህን እንደከተል ሁለገብ ጫና ያደርጋሉ። ይህን የማይቀበል የመቻቻል መርህን የጣሰ፣ ለሌሎች ጥላቻ ያለው፣ ኃላቀር፣ ለእድገትና ወደፊት ለመራመድ የማይመች ተደርጎ ፖለቲካዊና ሁለገብ ጥቃት ይፈጸምበታል። በኢትዮጵያ አገራችን የብልጽግና ወንጌል የሚመራው መንግሥታችን የሚራመደው በዚሁ በምዕራባዊያኑን መንገድ ነው። “ኦርቶዶክስ ክርስትና  ለሀብት ማካበትና  ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እትሆንም “ የሚለው የብልጽግና የካድሬ ማሰልጠኛ ሰነድ የምእራባዊያኑ ኢንፖር ታማኝ አገልጋዮች አገር አገሪቷን እንደተረከቧትና ነባርነቷን በማይታወቅ አዲስነት ለመለወጥ እስከ ጭፍጨፋ የሚራመዱ መሆናቸውን በተግባር እየገለጹ ነው። 


የፖለቱካ ልሂቃን ሕዝብን የሚያማልሉትና የሚያታልሉባቸው የተለመዱ  ጽንሰ ዐሳቦችና የፕሮፓጋንዳ መልዕክቶቻቸው፡-

  አሁን የምትገኝበት እግር ምንጩ ከአለፉት ሥርዓትና እምነቶች፣ ባህሎችና ማኅበረ-ፖለቲካዊ ግኑኝነቶች ናቸው፤

  ደስታን፣ የኑሮ ዋስትናንና ቁሳዊ ሀብትን የምታሳካው ራስህንና አካባቢህን ከቀድሞውና ከተለመደው ሁሉ በተለየ መንግድ ስታስተናግደው ነው (ይህ ሃይማኖትን ይጨምራል)

  አብዛኘው ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና አካባቢያዊ እግሮች ምንጫቸው የዲሚክራሳዊ ነፃነት መታጣት ነው፣ ይህን ያሳጣህ እኛ ሥልጣን ላይ ያለነው ሳይሆን ያለፉት ሥርዓቶች፣ ሥረዓቶቹ የቆሙበት ሃይማኖት፣ ባህልና ታሪክ ነው፤ በዚህ መሠረት እኛን ብትከተል አዲስ አገርን ሠርተን እንሰጥሀለን፤

  እድገት ለውጥ ነው፤ ለውጥ ደግሞ የቀደመውን መተው ነው፤ መተው እኛን የፖለቲካ ልሂቃንን መከተል፣ የጻፍነውን ሕግ እንደ ሃመኖት መጠበቅ፣ አዲስ ባህልና ሃይማኖት መከተል፤

  እገሌ የሚባል ጠላት አለህ፣ ጠላትህን አንድናጠፋልህ የምንልህን ሁሉ ፈጽም።

ሲጠቀላል ኢንፖር ለዓለም ያስረከበው የማኅበራዊ፣ ፖለቲከዊ፣ ኢኮኖሚያዊ አካባበያዊ ፈተናዎች ምንጭ ሁሉን ነገር ግላዊ በማድረግ የሰው ልጆችን የጋራ ግብ፣ ከራስ ሥጋዊ እርካታ በላይ ርእይ ያለው ማኅበራዊ አንድነትን ማፈራረሱ ነው። ይህን የፈረሰ ማኅበረሰብና በግለሰብ ጥርቅምነት ሕዝብ የሚባል ስብስብ በኢንፖር የአስተዳደር ሥረኣት ልሂቃን ሥር አገር ሙሉ የጥቂቶች የአእምሮ ባሪያና ተስፋ ቢሶች ማድረግ ተችሏል።  በነፃነትና በራስ መተማነት ስም ባልና ሚስት፣ ልጅና ወላጅ ሳይቀሩ አንድነታቸው እንዲፈርስ ሆኗል፣ ክስትናን ለማጥፋት “በክርስትና” ስም ክህነትም ሆነ ሰማያዊ ዓላማ የሌላቸው ፓስተሮች ሕዝቡን መጫወቻ አድርገውታል። በእኛ አገርም የብልጽግና መንግሥት የምእራባዊያኑን ሞዴል ለመተግበር የኢኣማኒያንና የሙሰኞችን ማኅበር ሰብስቦ “ሲኖዶስ ነውና ተቀበሉት” የሚል ትዕዛዝ ለቅዱስ ሲኖዶስ ለማስተላፍ ሰርቷል፤ በጠመንጃም ጭምር ደም እያፈሰሰ ቀጥሎበታል። ይህ ሂደት “ነፃነት” ከሚለው ጋር የሚቃረን ይመሰላል። ነገሩ ወዲህ ነው። ነፃነት የተፈለገው ከሕገ እግዚአብሔር ውጭ በመሆን በተቃራኒው ለሕገ ልሂቃን ባሪያ መሆን ነው። ይህ በጥቅሉ ሲታይ የሰይጣን ነው። 


የኢንፖር ዶግማ ግልጽ ነው፡- ሰዎች በግላቸው ነፃ መሆን አለባቸው፤ ይህ ነፃነታቸው ግን የሌሎችን ነፃነት መንካት የለበትም፤ ይህን እንዲከበር የፖለቲካ ልሂቃን ሕግ አውጭ አድርገው  በሕገ-እግዚአብሔር  ፈንታ ይተኩታል፣ ራሳቸውንም ሕግ አስከባሪ አድርገው እግዚአብሔርን ተክተው “ነፃ” የሚሉትን ክቡር የሰው ልክ ጀፈጣሪው ለይተው ባሪያቸው ያደርጉታል። ዛሬ በአገራችን የኦሮሞ ወጣት የኦነግ/ብልጽግና ባሪያ ነው፣ የትገራይ ወጣት የወያኔ ባሪያ ነው። እነዚህ ተቋማት ባህልም፣ እምነት፣ መጅሊስም፣ ሲኖዶስም ሰርተው፣ የአገር ድንበር አስመረው፣ ትውልዱ ምን መናገር፣ ምን ማመን፣ የት መኖርና አለመኖር እንደሚገባው ይበይኑለታል፣ የተቃወመውንና አዲሱን እምነት የማይከተሉን ከማሳደድ በጅምላ እስከመፍጀት እርስበርሱ ያዋጉታል። 


ለአዲሱ የኢንፖር ፈተና ከክርስቲያኖችና ከቤተክርስቲያን የሚጠበቅ የመፍትሐየ አርምጃዎች

1. የኢንፖርን አስተምህሮ፣ ፖለቲካዊና ሕጋዊ አሠራር ክርስቲያኖችን በግልጽ እንዲያውቁት በስፋትና በዝርዝር፣ በዘመቻና በቋሚነት ማስተማር

2. አገርን፣ የመንግሥት ሥልጣንና ሀብትን ተቆጣጥሮ ነባርነትን በተለይ ኦርቶዶክሳዊነትን የሚያጠፋ ሥርዓት በአገሪቷ መተከሉን በስፋት ግንዛቤ መፍጠር ይህን ሥርዓት በአዲስና አገራዊ እሴቶች ላይ በተመሠረተ አገራዊ ሥርዓት ለመለወጥ ዜጎችን ማስተማር፣ ማደረጃትና መምራት

3. ኢንፖር ላይ የተመሠረቱ የትምህርት ሥርዓት፣ ይዘትና አቀራረብን አንዲስተካከል መደረግ የሚገባውን ሁሉ ማድረግ

4. በዚህ ሰነድ ከገጽ 15-17 ኢንፖር ኦርቶዶክሳዊነትን የሚዋጋበቸው ተብለው የተገለፁትን ዘርፎች በመተንነትን ለእያንዳንዳቸው ሕጋዊ፣ ዕውቀታዊ፣ ፖለቲካዊና መኅበራዊ መፍትሔ ማስገኘት።

ከዚህ ከላይ ያነሳነውን የኢንፖር ፖለቲካ አካሄድ ከግምት በማስገባት እኛ ኦርቶዶክሳውያን የሚከተሉትን ጥያቄዎች በግልጽ የመመለስ ሽክም ወድቆብናል፦

1. በዓለመ ሥጋ እንደሚኖር ማንኛውም ዜጋ አገር፣ ርስት፣ እምነት፣ ቤተ ሰብ፣ ማኅበረ ሰብእ ሊኖረን ግድ የሆነብን ፍጡራን ነን። እነዚህ ሀብታት የግልም የወልም ሆነው እያንዳንዱ ሰው በነጻ ፈቃዱ የሚሳተፍባቸውና የሚፈልጋቸው ብቻ ሳይሆን መንግሥታዊ፣ ማኅበራዊ እና ሃይማኖታዊ አስገዳጅ ዕቀባና ድጋፍ የሚደረግባቸው ሁኔታዎች አሉ። በዚህ አውድ እኛ በአገራችን ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሳዊ ፖሊሲዎችና አሠራሮች ላይ ሊኖረን የሚገባው ተጽእኖ ምንድነው? እንዴት? ለምን? 

2. ፖለቲካና ሃያማኖት፤ መንግሥትና ቤተ ክርስቲያን የለያያሉ የሚለው ትርክት እና ተገባራዊ አገላለጹ በምድር መንግሥትና በሰማይ መንግሥት መካክል ያለውን እና ሊኖር የሚገባውን ግኑኝነት እንዴት ይበይናል? በብያኔው ፖለቲካዊ ሂደትና የዘት ደርጃ የኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ግላዊ፣ ወላዊ እና በቤተ ክርስቲያን ተቋም ደረጃ ሊኖር የሚገባው ሚና  ምን አይነት መሆን የገባዋል? የተሳትፎ ገደቦች ምንድናቸው? እንዴትና በምን መሥፈርት የበየናሉ?

3. በአሁኑ ግዜ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከውስጥና ከውጭ የኢደረጉባት ሁለግብ ጫናዎች፣ የመመናና ካህናት እልቂት፣ ስደትና ከእምነት እንዲፈልሱ መደረግ የምን ውጤት ነው? ለዚህ አስከፊ ሁኔታ መፈጠር ክርስቲያኖች በገልና በወል፣ ቤተ ክርስቲያን እና የበላይ አባቶች እንደ እረኛ ምን ማድረግ ሲገባቸው ባለማድረጋቸው ነው? ለወደ ፊቱ ምን አይነት የስነ-ልቦና፣ የአስተምህሮ፣ የአደረጃጀት፣ የሁሉ አቀፍ አገራዊ ተሳትፎ ሊደረግ የገባል?




አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

የሐሰት ትርክት ኦነጋውያንና የሕወሃታውያ የጋራ ስልት ከነግሥታት ወደ ተራ ግለሰቦች

✏️ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።  እርሱ ይመስገን። ምድራችንን #በደም #ያጨቀየው $ህሊና #የነሳን ፣ #ልቦናችንን #ያጨለመን ፣ #ሰብእናችንን ያዋረደው:- 👉 የሕወሐታውያንናንየኦነጋውያን የንዑስ ማንነት የጎሣ ፖለቲካ የደንቆሮ ርእዮትና፣ 👉 መርዛማን ጥላቻን ለ፶ ዘመናት ያከፋፈሉት የሐሰት ትርክት ናቸው። ✏️እንደ ዳግማዊ #ምንልክ ያሉ   ከዋክብት መሪዎች፣ እንደራሴቻቸው፣ ደጃዝማቾችና ቀኝና ግራ አዝማቾቻቸው  ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ብዙ ውለታ ውለውልናል:- 👉 በዘመነ ኦቶማንና አውሮፓ፣ በዘመነ መሳፍንት የተበታተነውን እና የተቆነጻጸለውን፣ ጎሠኛ የአርብቶ አደሮች  መሬት ፍለጋ  የደመሰሱትን ክርስቲያናዊ የግዕዝ/የነፃነት ሥልጣኔ አሻራ እንዲያገግም ደክመውልናል፤ 👉 የጥንት አገርን እና ሕዝቦችን   በከፊልም ቢሆን በመሰብሰብ  ጠንካራና ብቸኛ የነጭ ቅኝነትንና ባርነትን በመከላከል፣ ከኦቶማን ቱርክ ወር ትናንት ውስጥ ጥረኛ  አህመድ ግራኝ በመጋደል  ልዩ የነጻነት ማንነት ያላትን አገር ብበቸኝነት በዓለም ካርታንላይ አቆይተዋል፤ 👉 የሬማ ግዛት በጎሣ ተብልቶ ፲ ትንንሽ ሲሆን ከበበባውን ተቋቁማ በዝኃነታችን በተመጋጋቢ አንድነት ከ፹ በላይብቋንቋ፣ ከዓለም ትልልቅ እምነቶች ክትስትናን ፣ ይሁዲን፣ እስልምናን፣ የእረማውያንን ቅሪት የሆኑ የባህል እምነቶችን ሁሉን ይዛ በአውሮፓ በአርብ አምሳል ሳትሠራ ለእኛ አቀብዋል፤ 👉 ወያኔና ኦነግ፣ ገንጣዩ ሻዕብያ፣ ከሃዲው የማርክሲስት የአእምሮ  ባሪያን ስብስብ  እስኪፈትናት ድረስ ራሷን የቻለች አገር እንድንፈጥር ያስተባበሩን ነገስታት የተመሰገኑ ናቸው። አገር ሲያረጅ ጃርት ያብቅላል እንዱሉ: መል...