ለፋኖ ሠራዊት፣ ለፋኖ መሪዎችና ለኦርቶድክሳውያን በሙሉ መግቢያ “እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም። (ማቴዎስ 5:13) እንዲል ተጋድሎአችን እንደ አሕዛብ ለሥልጣን፣ ለድሎት፣ ሌላውን አሳፍሮና አሳንሶ አሁን ባልፉት 50 ዓመታት እንደታዪት ዘረኛና አምላክ-የልሽ ገዥዎች በሌሎች ላይ ከፍ ከፍ ለማለት ሳይሆን ለነፍስም የሚተቅም፣ እግዚአብሔርን የሚያስደስት፣ ለትውልድ ሰላምና አንድነት በር የሚከፍት፣ ፍትሕ እውነትና ሰብአዊ ክብር የሚመለስበት የተቀደሰ ተጋድሎ ነው። ይህ ተጋድሎ በአጭር ስሙ ፋኖነት ነው። ፋኖነት ስለ ክብረ-ስብእ፣ ስለ እውነት፣ ስለ ፍትሕ፣ ስለ ትውልድ የሚደረግ የተቀደሰ መስፈንጠር ነው። ፋኖነት ከባእድ ወርሰው፣ ነባርነትን በጠላትነት ፈርጀው፣ አምላካቸውን ክደው፣ ንዑስ-ማንነትን ከሰባዊነትና ከሃይማኖት በላይ በጣዖት ደረጃ ከፍ አድርገው ላልፉት 50 ዘመናት ደም ሲያፈሱ አገር ሲያፈርሱ ከኖሩትና እየኖሩ ከሚገኙት የአገርና የሕዝብ መከራው ፈላፍይ ድርጅቶችና አስተሳሰቦች እጅጉኑ የራቀ ነው። ይሁንና በፋኖነት ውስጥ የእንዚህ የአግር መከራ በር ከፋቾች እሳቤ ብልጭ ድርግም ሲል ቆይቶ አሁን ላይ ሞዐ ተዋህዶ ንቅናቄ እንደ መለኪያ ሆኖባቸው እየተጋለጡ ነው። መታወቅ ያለብት፦ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ክርስትናን የሚያሳድድ ተጋድሎ እግዚአብሔርን ስለሚያሳድድ ጌታችን ለአሳዳጁ ሳዖል፣ ጨለማው ሲወግደለትና በትክክል ማሰብ ሲጀምር፣ ለመንፈስ ቅዱስ ማኅደርነት ሲምች ምርጥ እቃና በጸጋ የዓለም ብርሃን ለተሰኘው ቅዱስ ጳውሎስ ‘“ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ?”...
This is a spot where I post and share part of my daily reality. I would love to hear from others too to learn how differently we interpret daily encounters including our imaginations. ይህ ሥፍራ የየዕለት ገጠመኞቼን፣ እንዴት በዕለቱ እንደተረደሁትና የማስበውን ለሌሎች ያማጋራበት ነው፡፡ የሌሎችን በመስማትና ምን ያህል ዓለማችንን በተለያየ መንገድ እንደምንመለከታት ለመማር እጓጓለሁ፡፡