ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

የፖለቲካ ጠላት የተደረገውና የህልውና አደጋ የተጋረጠበት ኦርቶዶክሳዊነት እና የተከዳው ኢትዮጵያዊነት

የፖለቲካ ጠላት የተደረገውና የህልውና አደጋ የተጋረጠበት ኦርቶዶክሳዊነት እና የተከዳው ኢትዮጵያዊነት 24-10-2015 ዓ/ም ካምፓላ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ። የቤተክርስቲያን የሕልውና አደጋ የአግርም ነው!!! 

  ዛሬ አደጋው ከውጭ አይደለም።

  በእርግጥ መርዛማው የኢትዮጵያዊነትና ኦርቶዶክሳዊነት ጠላት ፖለቲካ የሀሳብ ምንጩ ከውጭ ነው፤ 

  ይህ ፖለቲካዊ አመለካከት የተጣባው ትውልድ ማንኛውንም ነባር ባህልና እምነቶች የማጥፋት ዝንባሌውን ከራሱ ያመነጨው እስኪመስለው የተጋተው ከውጭ ነው። በቅኝ ገዥዎችና ከባዕዳን ከ700 ዓመታት አስቀድሞ የተጀመረ ሂደት ነበር፥ 

  የዛሬ 180 ዓመታት ገደማ አስቀድሞ ሸዋ አንኮበር ቤተመንግሥት የጀርመኑ ጆሃን ሀኒክራፍ ሉድዊግ በቤተክርስቲይን እና በነባሩ የኢትዮጵያ ስነ መንግሥት ላይ እሾኽ ተከለበት፥ 

  ያ እሾኽ ከተተከለ ከ50 ዓመታት በኃላ የዛሬ 130 ዓመታት ገደማ በጣሊያን ተኮትኩቶ አገር በቀል ተከታይ አፈራ፤ ከናዚ ሶሻሊሰት ፓርቲ መሸነፍ በኋላ ከጀርመን ያመለጡትና ወለጋ የተጠጉት “የጀርመን ክርስትና” የተሰኘ ለዘረኝነት የሚስማማ ፕሮቴስታንቲዝም ያነገቡ ሰባኪያን 

  የዛሬ 72 ዓመት ገደማ ሥር እንዲሰድ በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤትና በቀ/ኃ/ሥ ዩኒቭረሲቲ መዋቅራዊ የትምህርት አቅም ተሰጠው፤ 

 የዛሬ 60 ዓመታት አካባቢ የመጀመሪያው መርዛማ ፍሬ እሸቱ ታየ፥ በመንበረ ልዑል ቤተ መንግሥት ውስጥ መሪዎችን ሰውቶ የመጠፋፋት ባህልን አስተዋወቀ፥ 

  የዛሬ 50 ዓመት ገደማ በአገራዊነትና ነባርነት ላይ የሚያምፀው ትውልድ እግዚአብሔር የለሽ የፖለቲካ ርእዮተ ዓለምን ታጥቆ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ኢትዮጵያዊነትንና ኦእረቶዶክሳዊነትን ለመደመሰስ ንጉሥ፥ ጳጳስ፥ የባህልና የእምነት መሪዎችን በመፍጀትና ከኢትዮጵያ ማኅበረ-ፖለቲካና ስነ-ምንግሠት የመለየት አመፁን አቀጣጠል፤ 

  የመጀመሪው የአገርና የቤተክርስቲያን ጠላትነት ፍሬ ሰጥቶ፥ የዛሬ የ30 ዓመት ተንሰራፍቶና ሕገ መንግሥትና ተቋም ሆነ፥ አገራዊ የስነ መንግሥትና የአገር የፖለቲካ ርእዮት ሆኖ አሁን የምንገኝበትን መንግሥታዊ እና እምነታዊ ሁለንተናዊ ሙስና ላይ ደረሰን። አሁን ኢትዮጵያዊነትንና ኦርቶዶክሳዊነትን ማጥፋት ከውጭ የሚመጣ ሳይሆን አገር በቀል መስሏል፥ ሆኗልም። የመርዛማው ዘር ዘሪዎቹ የውጭ ባዕዳን ሚናቸውን ቀይረዋል። ዓላማቸውን የሚያሳካለቸው በቤተመንግሥት፥ በትምህርት ተቋማትና በመላው የፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ ሥር ሰድዶ ስለበቀለላቸው እንዳይጠቀልግና እንዳይጠፋ፦ 

  የገንዘብ፥ የቴክኒካል ምክር፥ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ድጋፍ፥ 

  የሐሰት ትርክትን በሳይንስ ስም ማሳተምና ማሰራጨት፥ 

  በክርስቲያኖች ላይ የሚካሄደውን ጥፋት ከዓለም ማኅበረሰብ መሰወር፥ 

  የጦር መሣሪያ በማቅረብ ላይ የተወሰነ ሆኗል። ዋናው ሥራ በቤተመነግሥት፥ በቤተ ክህነት፥ በልዩ ልዩ እምነቶችና ባሕል ውስጥ በተሰማሩ የመርዛማው ዘር ተለካፊዎች ናቸው። 

አሁን ያለችዋ አዲሲቷ ኢትዮጵያ መገለጫ ከኦርቶዶክሳዊነት፥ ከኢትዮጵያዊነትና ከማንኛውም ነባር ባህላዊና እምነታዊ፥ ታሪካዊና ማሕበራዊ እሴቶች ያፈነገጠ ነው። የዛሬይቷ ኢትዮጵያ ዜጎች በገዛ መንግሥታቸው ጥፉ ሕገ መንግሥትና መዋቅር ንዑሳን የማንነት ዘውጎች ተፈርጀው ለዓመታት ያለመቋረጥ የሚፈናቀሉባት፥ የሚታሠሩባት፥ የጅምላ ፍጅት፥ ሁለገብ ማኅበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ጥቃቶችን የሚፈፀሚባት ናት።

 የነገዋን መሪዎች በተግባር እንደሚነግሩን “አዲሲቷ ኢእዮጵያ” ከኦርቶዶክሳዊነትንና ከኢትዮጵያዊነት የፀዳች ትሆናለች። ሁለቱም አሁን ላይ የመጨረሻ ግብአተ መሬታቸውን ለመፈጸም ዋዜማ የቤተክርስቲያንን ሲኖዶስን ወደ ጎሣ ፌዴሬሽና በመቀየር ነው።

 እየተነጋገርን የምንኝበት የዛሬው ዕለት የኦርቶዶክሳዊነትና የኢትዮጵያዊነት የመጨረሻው ሕልውናን የማጥፋት ሰልፍ ላይ ቆመን ነው። የቆፈረውን መቃብር አፈር መሙላት፥ ገድለው የሚቀብሩትን እጅ መያዝ አይነት የግብግብ መሥመር ላይ እንገኛለን። ዛሬ በዚህ ጉባዔ በአካልና በርቀት የምንገኝ ዜጎች ምኞታችን ብቻ ሳይሆን ጥረታችን

  አንደኛውየኢትዮጵያዊነትና የኦርቶዶክሳዊነት ሥርዓተ ቀብር የመፈጸም ምኞት ማምከን ነው፤ 

  ሁለተኛው ዓላማችን አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ከውጭ መርዝ ተግተው የገዛ አገራቸውን ለማጥፋት የሚሠሩትን ፖለቲከኞች ተከትለው የአገር መሥራችና ነፍስ የሆነችዋን ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የጎሣ ጳጰሳት በመⶄም የአጥፍቶ ጠፊዎች የሲኖዶስ አባላትን ለመጨረሻ ጊዜ ቁሙ ለማለት ነው። ይህን ሂደት ማስቆም ይቻላል!!! 

 ኢትዮጵያዊነትንና ኦርቶዶክሳዊነትን ገዳይ ከሆነችዋ ከአዲስቷ የመንግሥትና የንዑስ-ማንነት ፖለቲካ ፍጡር ኢትዮጵያ እጅ ማዳን ይቻላል!! 

 ቀባሪዎቹንም አገራቸውን አጥፍተው ራሳቸውንና ቤተክርስቲያናቸውን ከሚያጠፋው ከዚህ የቁልቁለት ሩጫ ቆም ብለው እንደ ሰው፥ አንደ ዜጋ፥ እንደ ክርስቲያን፥ አንዲያስቡ መርዳት ይቻላል!! እንዴት ይቻላል? ምን ጥቅም ላይ ያልዋል እምቅ አቅም አለ? 
 1. አብዛኛው የእምነትና ፖለቲካ አስተዳደር ኃላፊነት ላይ የሚገኘው ሐሰተኛ፥ ራስ ወዳድ፥ አድርባይ፥ ሕዝብን የሚያታልል፥ አደራውን የበላና ቃሉን ያጠፈ፥ ሙሰኛና ዘረኛ መሆኑን በመስማማት አጥፊዎችን ከመከተል ሕዝቡ እንዲመለስ እና የራሱን መሪዎች እንዲያፈራ አመራር በመስጠት፤ 

 2. አሁን ያጋጠመንን የአጥፍቶ መጥፋት ሂደትን በሚመለከት ነገሮችን መሸፋፈን፥ በይሉኝታ የመታሠርን የቆየ ባህል፥ በይደር ለክፋት ሠራተኞች መጠናከርና መስፋፋት እድል የመስጠት ልማድን፥ ሌሎች ይወጡታል ብሎ ከአጥፊኦዎች መፍትሔ መጠበቅን፥ መሪዎች ያውቃሉ በሚል በነባርነት ላይ በአመፁት ነባር-ጠል እና አዲስነት-ናፋቂዎቹ በዝምታ መመራትን የሚቃወም ንቅናቄ በመፍጠር፥

 3. ዜጎችን ሁሉ በተለይ ዒላማ የተደረጉት ኦርቶዶክሳዊያን ምእመናን ራሳቸውን ከሚያዘናጋ እና ለበለጠ አደጋ ተጋላጭ ከሚያደርግ ባዶ ተስፋዎች፥ ብልጣብልጥ ንግግሮች፥ ብልጭልጭ ልማቶች ከመደንዘዝ እና አጥፊው ፖለቲካ ስምሪት ከሚሰጣቸው የባህልና የሃይማኖት መሪዎች ራሱን በመከላከል በዓላማና የጠራ ግብና ስልት እንዲመራ ደማድረግ፤ 

 4. ከአድርባይነት ራስን ነፃ በማድረግ እውነትን በፍቅር፥ እውነትን ለመፍትሔ፥ እውነትን ክፋትን ለማሸነፍ በግልፅና በተረዳነው መንገድ መናገርና የምንችለውን መልካም የሆነ ተግባር ሁሉ ለመፈጸም ሁሉም እንዲዘጋጅ መረጃና ርእኦቶችን በመስጠት፤ 

5. አድርባዮች የፖለቲካ፥ የባህልና የእምነት ተቋማትን የመምራት ሥልጣን ላይ ተቀምጠው 
 o ሆደ ሲፊነት o ይቅር ባይነት 
o ትዕግሥት 
 o አስተዋይነትና ጥበበኛነት 
o መንፈሳዊነት 
 o ስለ ሰላም ተብሎ የሚከፈል ዋጋ o ስለ አንድነት ---- ወዘተ --- በሚባሉ ከፍትሕና ከእውነት የተፋቱ፥ ግፈኞችን የሚያነግሡ፥ ከያዙት ኃላፊነት የመሸሻ መንገዶችን ሁሉ እየተከታተሉ በማጋለጥ፤ ሲቻል መቅጣት፤ 

6. ለቤተክርስቲያንና ለአገር ጉዳይ የሚጠቀሙ የባህል፥ የእምነት፥ የፖለቲካ ሥልጣን ላይ በመየደረጃው የሚገኙ ግለሰቦችንና ቡድኖችን ኃላፊነታቸውን መወጣት አለመወጣታቸውን ወይንም በተቃራኒው መንቀሳቀሳቸውን የሚከታተልና ግብረ መልስ የሚሰጥ አሠራር በመፍጠርና ከአጥፊዎች ጋር የሚሠሩትን በማጋጥ፤ 

 7. በቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ ለግል ድሎትና ለምቾት እንዲሁም ለቤተክርስቲያን ተልእኮ ለተቃራኒ አጀንዳ ይዘው በመግባት በአባትነትና በመምህርነት የተንሰራፉትን መንጥሮ ከምእመናን የሚለይ መንፈሳዊ፥ ማኅበራዊ፥ ሕጋዊና ፖለቲካዊ አሠራሮችን በማስተዋወቅና በመምራት፥ 

 8. የሐሰት ትርክት፥ የስሑት ነፅሮት፥ የክፉዎች ድልና ጉልበት መሆን የቻለው የእውነተኞች፥ የመልካሞችና የርቱዐን ዝምታ መሆኑን በማስገንዘብ --- እንዲሁም --- ሐሰተኞች በእውነተኞች ፊት እሣት እንደ ገላመጣቸው ጭድ፥ ክፉዎች በመልካሞች ፊት ፀሐይ እንደወጣባቸው የጠዋት ጤዛ፥ ስሑት የፖለቲካ ርእዮትና ሐሰተኛ የታሪክ ፈጠራ ትርክቶች በርቱዕ አስተምህሮና በእውነተኛ ታሪክ ዘንድ እንደጉም ተንነው እንደ አበሯ በንነው የሚጠፉ መሆናቸውን በመገንዘብ በማመንታት ለጥፊዎች መጠናከር ምንም አይነት እድል አመስጠት፥ የተጠናከሩት የሚፈራርሱበትን ሥራ ሁሉ መሥራት።

 ================// =================== 

 በዘመኑ ደካማ ተደርጎ የሚወሰድ ነገር ግን ነባርና ጠንካራ ጎኖቻችንን ማወቅና ዘመኑን መዋጀት፦ 

1. --- < ጠንካራ ጎኑ፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያን ተከታይ የሆነ ዜጋና ሕዝብ ከኖኅ እስከ ሐዲስ ኪዳን ባለው በታሪኩ ምክኒያት አመራርን የሚቀበለው ከላይ ወደታች ነው፤ 

  ሥልጣን ላይ ለሚገኝ ሁሉ የሚታዘዝ ሥርዓት ያለው ሥልጣን አክባሪ ሕዝብ ነው፤ 

  “ላይ” የተባለው ተዋረዳዊ የሥልጣን ሰንሰለትን አክባሪነቱንና አማኝነቱን ጠንካራ ጎኑ ነው ደካማ ጎኑ፦ በዚህ የአማፅያንና የክህደት ዘመን የቀደመ እሴቱን ይሙጥኝ ብሎ “ላይ” የተባለውን የሥልጣን ቦታ፥ ተማረ የተባለውን ልሂቅ ሁሉ በምብም መልኩ አቅደው ያጠፉኛል ብሎ ፦ 

o አለመጠራጠሩ፥ እታለላሁ ብሎ አለመገመቱን እንደ ደካማ ጎን የሚቆጥሩና ከነባር እሴቶቹ ያፈነገጡ ሕሊና ቢስ ልሂቃን አገሪቷን እንደቀሙት፥ ሃይማኖቱን ለማጥፋት ከ70 ዓመታት በላይ እንደሠሩበት አለመገንዘቡ 
o ጠላት ከላይ ይመጣል የሚል ግምት ፈጽሞ በልቡ ማሳደር ባለመቻሉ፦

  የአገሪቷ የፖለቲካ ርእዮት ወደ አምላክ የለⶄች እጅ ሲገባ፥  ቤተ መንግሥቱ ፀረ-ነባር ሕገ መንግሥት ሲደነግግና ወደ ተግባር ሲቀይረው፥ 

 ቤተ ክህነቱ በጎሠኞች፥ ሳያምኑ በሚካኑና መምህር በሚሆኑ፥ በምንደኞች፥ በመናፍቃን ሲወረር 

 ከቤተክህነትና ከቤተመንግሥት ውስጥ፥ ከአገሪቷ ታላላቅ የእውቀት ተቋማትና ምሁራን የሚመጣ በማንነቱ ላይ በጠላትነት የተነሳ ትውልድ እስኪጠናከር መተኛቱና --- --- በመጨረሻም የጎሣ ኤጲስቆጶሳትን ሕጋዊ ለማድረግ የሚሠራ ሲኖዶስ ላይ እስከመውደቅ መድረሱ ደካማ ጎኑ ነው በተቃራኒው በነባሩ እሴትና ስነልቦና የፀናው ኢትዯጵያዊ ዜጋን እንደመሣሪያ ተጠቅመው ራሱኑ የሚኣጠፉ፦ 

1. ከአገራዊ እሴቱ ያፈነገጡ እና በውጭ-ገብ ፍልስፍና ነባርነትን ጠልተው በጭፍን አዲስነትን የሚናፍቁ ዘመናዊያን የፖለቲካ ልሂቃንና --- በቤተ እምነት የተሰገሰጉ የድሎትና የምቾት ሎሌዎች በተደራጀና በመዋቅራዊ መንገድ በኢትዮጵያዊ ነባር ማንነት እና ኦርቶዶክሳዊነት ላይ ጦርነት መክፈት ችለዋል፤ 

 2. ከላይ ወደታች ብቻ በእምነት እየታዘዘና እያከበረ የሚነረውን ብዙኃን ዜጋ በውስጡ እንደ ቅንቅን ተሸጉጠው በኅቡዕ እየተደራጁ ከሥር ወደላ በሚፈፀሙት ሁለገብ ቡርቦራ አገሩን ነጥቀዉታል፤ 

 3. ከላይ በቤተመንግሥቱና በቤተ እምነቱ የነገሡት ነባርነት ላይ ያመፁና ብዙኃንን ለማታለል፥ የቻሉ ጥቂቶች በነፃነት ተስፋ፥ በመብትና በአዲስ አገር ግንባት ቅዠት እያማለሉ በአእምሮ ባርነት ብዙኃኑን እያማለሉ ራሱን በሚያጠፋባት ጎዳና ላይ እያስኬዱት ይገኛሉ።

 4. ነባር-ጠሉ ፖለቲካ በተግባር መዋቅራዊ ጥፋት እየፈጸመ መሆኑ ላይ ሙሉ መግባባት ያስፈልጋል። አሁን ያለው መንግሥትና ሌሎቹም የፖለቲካ ተቋማት፥ አብዛኛወፐቹ ዘመናዊ ልሂቃን ነባርና ኦርቶዶክሳዊ እሴቶችን፣ የታሪክ አሻራዎችን በመደምሰስ “አዲስቷ ኢትዮጵያ” የምትባል ፀረ-ኦርቶዶክስ አገር በመፍጠር ግብ ላይ እንደሚስማሙ መጠራጠር አያስፈልግም። ለዚህ ማስረጃው ላለፉት የ50 ዓመታት የነባርነት ጥቃት ዘመን አንዳቸዉም ለክፉ ፀረ-ነባር ርእዮትና ትርክት ምሁራዊ ምላሽ ሲሰጡ፥ ማታገያ የፖለቲካ አጀንዳ ሲቀርፁ አለመታየታቸው ነው። 

 5. በነባር ማንነታችን ጥንካሬ ምክኒያት የቅኝ ገዥነት እቅዳቸው የተጨናገፈባቸው የቀድሞ ቅኝ ገዥዎችና የዘሬዎቹ የአፍሪካን ተፈጥሮአዊ ብቻ ሳይሆን አእምሮ ሳይቀር እየዘረፉ አገሮቻቸውን የሚያኖሩ አገራት 

 ዛሬ በቤተ በፖለቲካዊ ቁንጮና በእምነት ቤት ውስጥ ለሚገኙ ነባር ጠሎች ሙሉ ድጋፍ እየሰጡ መሆናቸውን እንደሚገባ መረዳት፤ 
 እነዚህ የውጭ አካላት ከነባር እሴቶቻችንና አምነቶቻችን ጋር የሚቃረኑ ማንኛውንም የፖለቲካ ርእዮት፥ አምላክ የለሽ የአስተዳደር ሥርዓቶች፥ አሕዛባዊና ጠዖት አምልኮን እንዲሁም ውጭ-ገብ ነውረኛ ባህሎችን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ ባላሥልጣናትንና ንቅናቄዎችን በመፍጠርና በመደገፍ ላይ አንደሚገኙ ማወቅ፤ 

 በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችን፥ የአገርና የአገሪቷን ነባር እሴትና ትውፊት ሙሉ በሙሉ የመተካት ሂደት ፖለቲካዊ ሥርዓትና መዋቅራዊ መሠረት ያለው መሆኑን መረዳት

  የጎሣ እና በሌሎች መገለጫዎች ላይ በሚፈጠሩ ንዑሳን የፖለቲካ ማንነቶች መሣሪያነት የኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብ አንድነትን ለማጥፋት የሚካሄዱ ፖለቲካ-መር መንግሥታዊ ግጭቶችን እና መዋቅራዊ ጥቃቶችን በማንኛዉም መንገድ መሸነፍ ካልቻሉ ፈጽመው እንደማይቆሙ ከልብ መገንዘብ፤ 6. በኢትዮጵያ ውስጥ ለኦርቶዶክሳዊ ሰውና ተቋማቶቹ መንግሥታዊ ዋስትና በግልጽ መነፈጉን፥ ክርስቲያን እና ሌሎች ኢትዮጵያዊነታቸውን የሙጥኝ የሚሉ ሰዎች ሁሉ በምንም መልኩ እንደ ዜጎች ተቆጥረው ፍትሕ ማግኘት እንደማይችሉ በመሬት ላይ የሚገኘው ተግባር ያሳያል፤ ከዚህ በመነሳት፦ 

 ኦርቶዶክስ ሆኖ በአገር ውስጥ ተንቀሳቅሶ በሰላም በሁሉም ቦታ መኖር፣ እምነቱን በነፃነት መከተል፥ ቅርሥና ታሪኩን ማስከበር በመንግሥት አሠራር ወንጀል መሆናቸውን፥ 

 ክርስቲያን ሆኖ በአገር ጉዳይ ከዜጎች እኩል መሳተፍ በአጠቀላይ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ምብቶች ከዜጎች እኩል መጋራት ፈጽሞ በመንግሥት አሠራር መገደባቸውን --- --- ከግምት ያስገባ ሁለገብ ተጋድሎ መሳተፍና መምራት ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ፥ በተለይ ጥፋት ለታወጀባቸው ኦርቶዶክሳዊያን የቅድሚያ ሁሉ ቅድሚያ እንደሆነ ተቀብሎ በዚሁ ወደ ተግባር መሠማራት። 

 7. የቤተክርስቲያን የአስተዳደር መዋቅር እና ሥርዓቱ፥ የአመራር ግብና ፍላጎቱ ከቤተክርስቲያን ተልዕኮ ያፈነገጠና አጥፊ መሆኑ ባሳለፍናቸው የፖለቲካ ውጣውረድ ተፈትኖ ተጋልጧል፦ 

 አሁን ላይ የቤተክርስቲያን አስተዳደርና አገልግሎቱ በምንደኝነት፣ በመናፍቅነት፣ በዘርኝነትና በጥቅመኝነት ወደ ውስጥ የገቡ አገልጋዮች ለአፅራረ ቤተክርስቲያን አመቺ ብቻ ሳይሆን አመቻችነት ብቻ ሳይሆን ንቁ አስተባባሪዎች ሳእቀር ከውስጥ አብቅሏል፤ 

  የክርስቲያኖችን የውሳኔና የሥራ አጀንዳዎች በአንዛኛው የክእረስቲያኖችን አንድነት፣ የአገልግሎት መፋጠንና ጥራትን ከሚመለከቱ ጉዳዮች እጅጉን የራቀ፥ ከዘመኑ ፈተና አንፃር አግባብነት የሌለውና የውሳኔ ሰጭዎችን ግላዊና ጠባብ ፍላጎቶችን እና የፖለቲካውን ነፋስ የሚከተል መሆኑ አሁን በተከሰተው የሕገወጥ የጎሣ የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ሂደት የበለጠ ተጋልጧል፤

  የቤተክርስቲያን ዋና ተልዕኮ የሆነው ሐዋሪያዊ አግልግሎት (በጎችን ማብዛት)፥ ስብከት ወንጌል (በጎችን ማፅናት)፥ ሥርዓተ አምልኮና ምሥጢራትን መፈፀምና ማሳተፍ (በጎችን መቀደስና መጠበቅ)ን በሁለተኛ ደረጃ ላይ በማስቀመጥ ትኩረቱን በሌሎች ወቅታዊና ቁሳዊ ጉዳዮች ላይ አድርጓል፤ 

 8. ኦርቶዶክሳዊያን ክርስቲያን ምእመናን እና ካህናት የባርነት ስነልቡና ወይንም ነፃ አውጭና መፍትሔ ሰጭ ሌላ ሶስተኛ ወገን የመጠበቅ ጎጅ ስነ ለቦና ተጠቂ በመሆናቸው፦ 

  ምእመናን እና ካህናት ራሳቸውን በራሳቸው ኃላፊነት በመውሰድ ከሥር ወደላይ እና እንዲሁም ወደ ጎን ከመደራጀትና ችግራቸውን በራሳቸው ከመፍታት ይልቅ በአጥቢያና በማሥበር ድንበር ታጥረው፥ በወቅታዊ ጉዳይ ተጠምደው ለአጥፊዎች ጉልበት ሰጥተዋል፤

  በዚህ ምክኒያት ኦርቶዶክሳዊያን ክርስቲያን ዜጎች በቁጥር በአገሪቷ ብዙኃን ሆነው ሳሉ በአናሳዎች ሳይቀር የሚጠቁ፥ የፖለቲካ ሚናቸው የደከመ፥ ድምፃቸው የሰለለ፥ ጉልበታቸው የዛለ አልቃሻ፥ ተሳዳጅና ለእልቂት የተጋለጡ ሆነዋል፤ 

 በሐረር ከተማ፥ በሥልጤ ዞን በወራቤ፣ በድሬ ደዋና በአዲስ አበባ የተደራጁና በናበር-ጠሉ ፖለቲካው የሚመሩ ጥቂቶች በቀጥር ብዙኃን በሆኑ ኦርቶዶክሳዊያን ክርስቲያኖች ላይ ያሻቸውን ሁለገብ ግፍ መፈጸም አስችሏቸዋል፤ 

 9. ኦርቶዶክሳዊው ዜጋ በጎሣ መብትና ነፃነት፥ በፖለቲካዊ ለውጥን አዲስ አገር ግንባታ ሽፋን የሚካሄድበትን የተራዘመ፥ ሁለገብ፥ ሥርዓታዊና መዋቅራዊ ጥቃት እንደሚገባ በመረዳት ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ አጀንዳ አድርጎ ለተጋድሎ መሰለፍ አልቻለም፦ ---

 ልምዶች እንደሚያሳዩት 

  ኦርቶዶክሳዊያን በፋሽት ጣሊያን ዘመን የተካሄደበትን የተናጥል ልዩ ጥቃቶች እና በወቅቱ ተባባሪ የነበሩ አካላትን ታሳቢ ያደረገ ፖለቲካዊና ማሕበራዊ መፍትሔ ሳያበክ ቆይቷል፤

  የመንግሥት ለውጥ በነባር-ጠሎችና አምላክ የለሾች ተመርቶ አብዮተኞች፥ ነፃ አውጭዎችና ዘረኞች ፖለቲካውን በመመረዛቸው በኦርቶዶክሳዊያንና ኦርቶዶክሳዊነት ላይ የተካሄደውን ሁለገብ ጥቃት መርምሮ እንዳይደገም መፍትሔ አላስቀመጥም፤ 

  በዚያድ ባሬዋ ሶማሊያ በአገሪቷ ላይ ጠካሄደውን ወረራ ተከትሎ በምሥራቅ፥ በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያና በማዕከላውያን ክፍለ ሀገሮች ኦርቶዶክስና ኦርቶዶክሳዊያን ላእ ጠፈጸሙትን ሁለገብ ጥቃቶች መርምሮ እንዳይደገሙ ሥርዓታዊና መዋቅራዊ፥ ፖለቲካዊና ሕጋዊ መፍትሔ አልፈለገም፤ 

 በኢሕአዴግና በብልፅግ ፖለቲካ የተካሄዱትን መዋቅራዊ ጥቃቶች አንደሚገባ ተረድቶ መፍትሔ ከመፈለግ በተቃራኒ ለህልውና አደጋ የሚያመቻች የጎሣ ሲኖዶስ በመፍጠር ሂደት ላይ የሚገኝ “ሲኖዶስ” እና የሲኖዶስ አባላት ሰልፍ በግልፅ እየተመለከትን እንገኛለን፤ 

 መንግሥት የጎሣ ፖለቲካ ሥር በመደበቅ በተደበቁ ኢትዮጵያዊነትና ኦርቶዶክሳዊነት ጠላታችን ናቸው በሚሉት ስብስቦች የሚመራ በመሆኑ በመደበኛ ትምህርት ሥርዓት፥ በመገናኛ፥ በኪነ ጥብበና ማስታወቂያ፥ በባህል ልማት፥ ወዘተ ስም የሚያካሄደውን ሁለገብ ጥቃት ለመከላከል አይደለም የሲኖዶስና የምእመናን አጀንዳ እንዲሆን የሚያደርግ ሲኖዶስና ሊቀጳጳስ፥ ካህንና የአገልግሎት ማሥበር በአድማሱም ላይ አይታይም።

 ====================== // ===================== < መፍሔው፡

 አሁን እንደ አዲስ ከሥር ወደ ላይ፥ ላዩን ማረቅና ትክክለኛው መጠበቅ፥ ግልና ወልን በተዋሕዶ መረዳት ይቀረናል፦ 

በግል ኃላፊነትን፥ ድእረሻን ሳይወጡ የወል ውጤት ሊኖር አይችልም፥ የአንድ አካል ብልቶች እንደየጸጋቸው አስተዋፅኦ ካላደረጉ አካል የሕልውና አደጋ ላይ ይወድቃል፥ አካል የብልቶቹን አስተዋፅኦ አስተባብሮ ሥራ ካልሠራና የአንዱን ከሌላው ካላዋሐደው ብልቶች ሕልውናቸውን ያጣሉ። ሙታንም ይሆናል። የብልቶች ሞት በመጨረሻ የአካልን ሙሉ ሞት እንደሚያስከትል የታወቀ ነው። እኛም፦ 

 በግል እንደሚገባ ካለመሥራት ዳተኝነት በመውጣት ድሻችንን እንደሚገባ ወደ መወጣት መሸጋገር ይጠበቅብናል 

 የጋራ የሆንበትን ቅድስት ቤተክርስቲያን፥ የቅድሰት ቡተክርስቲያን የጠባቂ ቅዱስ ሲኖዶስን እና የአንድን ሀገረ ስብጀት ሊቀጳጳስ የአስተሳሰብ፥ የአሠራር፥ የጠጠሪነት፥ ለቤተክርስቲያን ቀኖናና ዶግማ የመታመን ጤንነቱን መጠበቅ፥ ማስጠበቅ ግዴታችንን መወጣት ይኖርብናል፤ 

 2. ያለ ይሉኝታ፥ ያለማምነታት፥ ያለማስመሰል፥ ነፃ አውጭና መፍትሔ ሰጭ ባለመጠበቅ በቤተክርስቲያናችን ተንሰራፋውን የአስተዳደር ኢቀኖናዊነትን፥ ነውረኝነትን፥ ጎሠኝነት፥ መናፍቅነትን፥ ዱማሳዊነት፥ ሊዎናዊነት፥ ሲሞናዊነት፥ ይሁዳዊነት በአፍ፥ በመጽሐፍ፥ በተግባር በተናጥልና በተደራጀ መንገድ በግልፅ መቃወም፤ 

 3. በዚህ ዘመን እንደቀድሞው ከላይ የሚጠበቅ አብርሃና አፅበሓ እብሮት በትብብር እርኝነቱን እንደሚገባ የሚወጣ አቡነ ሰላማ እንደሌለ፥ አሁን የምንገኘው በፓጋን ሮም እና በኦቶማን ቱርክ ዘመን አምሳል እንደሆነ፤ እየተዳደርን ያለነውም የኔሮን ቄሳር፥ የዲዮቅልጢያኖስንና የመክሲሚያኖስ፥ ኦቶማን ቱርክንና የናዚ ጀርመኑ የሂትለርን ጠባያት ቀይጠው በሚመሩ የፖለቲካ ልሂቃን መሆንን ተጫባጩን በመቀበል አግባብነት ያለውና ዘመኑን የሚዋጅ፦ 

  የሰማዕትነትና የአሸናፊነት ስነልቡና መያዝ፥ከላይ መፍትሔ መጠበቅን ማቆም፥ 

  አዲሲቷ የፖለቲከኞች ኢትዮጵያ ፀረ-ኦርቶዶክስ መሆኗን በመረዳት የሚገባ ሁለገብ ምላሽ ለመስጠት መንቀሳቀስ 

 ነፃ እውጭና መፍትሔ ሰጭ ከእኛ ሌላ ሁለተኛና ሶስተኛ ወገን መጠበቅን ነውርና ውጉዝ ማድረግ፥ 4. አዲስ ስነ ልቡና፥ አዲስ አሠራር፥ አዲስ የኑሮ ዘይቤ፥ አዲስ ኅርዓተ ማኅበር፥ አዲስ አመራር የግድ መሆኑን በመገንዘብ 

 በማኅበር፥ በሠፈር፥ በአጥቢያ፥ በፍጡር ጀግና ተከታይነት ምክንያት በወሳኝ አጀንዳዎች ያለመተባበር ክፉ ልማዶቻችንን ፈጽሞ ማስወገድ፥ በየተደራጀንበት አንፃር ልዩ ጸጋዎቻችንን በተመጋጋቢነት ማሰለፍ 

 እንደሚያስፈልግ መተማመንና በዚሁ መንገድ መሥራት፤ 

 5. በብዙዎቻችን ላይ ያለውን ደካማ ጎን ማወቅና መለወጥ ለመጣብን ሁለገብ አደጋ የመፍትሔ መጀመሪያና መሠረት ነው፦ 

  በአሁኑ ዘመን ኦርቶዶክሳዊያን እምነታቸውን ከሕየወታቸው የዕለት ተዕለት ተግባር፥ ከፖለቲካዊና ማኅበራዊ የመስተጋበር መመሪያነት ውጭ አድርገዉታል፥ --- በዚህ ምክንያት --

  በሕይወት ቅድሚያን የምንሰጠው ነገር በክርስትና ሚዛን ሲታይ በሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ መታየት የሚገባው ሆኖ ይገኛል፥ በተቃራኒው ከፍ ባአለ ደረጃ መገኘት የሚገባው የነፍስ ነገር፥ የቤተክርስቲያን ነገር፥ የአገርና የትውልድ ነገር --- ትርፍና የሲመች ደረጃን ወስዷል፤ --- ይህ የሚያሳየው --- 

  ኦርቶዶክሳዊ ትምህርታችን ጥገኛ እንጂ ዋና ማሰቢያችን፥ የሁለንተናዊ ሕይወታችን መመሪያ መሆኑ ቀርቶ እንደ ባህል ክት ልብስ እንደሆነ ይመሰክርብናል --- ስለዚህ ዘመኑን ለመዋጀት ይህን መርምረን ማስተካከል ግዴታ ነው! 

 6. የባእድን ነፅሮተ ዓለም የወረሱ አዳዲስ ውጭ-ገብ እምነቶች፥ ርእዮቶች፥ እና ሃይማኖት-አከል የሆነው የፖለቲካ ሠራሽ ባህሎች የአጥፊያ ፖለቲካ መሣሪያ ሆኖ ከፖለቲካ ተቋማት በቅንጅት ኦርቶዶክሳዊነትንና ሌሎች ነባር እምነቶችንና ባህሎችን የማጥፋት ፖሊሲ ሆኖ መተርጎሙን አውቀን አግባብነት ያለው አዲስ የፖለቲካ አካሄድና ድርጅቶች እንዲፈጠሩ መሥራት፥ መሳተፍ እና መምራት፤

 7. የጎሣ ቡድን ነፃ አውጭዎች በትላልቆቹ ታሪካዊ እሴቶቻች፥ እምነቶቻችና ትወፊቶቻችን ላይ በማመፃቸው ---- በኅቡዕ ተደራጅተው እስከ አገር መግዛት መድረሳቸውን ተገንዝቦ --- መደራጀት፥ የተደራጁትን ማቀናጀት፥ ከሥር ወደላይ፥ ወደ ጎን በፍጥነት መስፋትና መሥራት ፤ 

 8. በመጨረሻም ለዛሬ ጉባዔአችን ዋና መንስዔ የሆነው ባሳለፍናቸው 70 ዓመታት በቅድስት ቤተከርስቲያናችን ላይ ከተቃጡት ጥቃቶች ሁሉ በአይነቱ የተለየና የህልውና መሠረትን የሚያናጋው ፖለቲካ-መሩ የጎሣ ሲኖዶስ ኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ብያኔ፥ ሂደት፥ ድብቅነትና አመፅን በሚመለከት የሚያስከትለውን አደጋና መፍትሔ በመጠቆም አበቃለሁ፦ 

 8.1. ሂደቱ በዚሁ ከቀጠል የሚከተለው አደጋ ይፈጠራል፦

  ምእመናን በቅዱስ ሲኖዶስ ላይ ያላቸው እምነት አሁን ከወረደበት ደረጃ የበለጠ ያሽቆለቁላል፥ በየዘመናቱ በፈተና ጊዜ ከሚከሰተው በተለየ ፍጥነትና ስፋት ከእምነት የሚፈልስና በተኩላ የሚወሰደው ምእመን ይጨምራል፥ 

 በተለያዩ ጠጎሣ ካህናትና የጎሣ ‘ጳጳሳት ምክኒያት’ ትዳሮች ይፈርሳሉ፥ እድሮችና ማሥበራዊ ተቋማት ይላላሉ 

 ምእመናንን በጎሣ ተካፍሎ ሲያፋጅ፥ ሲያፈናቅል፥ ሲለያይና ርስት ሲያነጣጥቅ የሚገኘው የጎሣ ማንነት ፖለቲካ አዲስ የፈጠረውን የጎሣ ጳጳሳት ተደግፎ የበለጠ የዘር ማጥፋት ፕሮጄክቱን ያፋጥናል፥ የእርስበርስ ጦርነቱ ይጠናከራል። 

 የገዳማት አንድነትና መደጋገፍ በጎሣ ድምበት ተወስኖ ከኦርቶዶክሳዊነት ውጭ ይሆናል፤ 

 በኦርቶዶክስ ድምፅ፥ አልባሳት፥ መልክ አዳዲስ ለጎሣ ፖለቲካ የሚስማማ አዳዲስ ኑፋቁአዊ አስተምህሮዎች ይስፋፋሉ 

 ጵጵስና ከሐዋሪያት ክህነትና ሥርዓት ተነጥሎ በየመንዱ እንደሚታደለው የፕሮቴስታንት ፓስተር አቻ ሆኖ ስለሚዋረድ ከክህነት ተነጥሎ የፖለቲካ ሲመት የሚያደርገው ባህል በኢትዮጵያ ይተከላል 

 ከሲመቱ ሂደት በኋላ ሕገ በተክርስቲያን ዳኝነቱን አጥቶ ቦታውን ለሱኩላር የዲሞክራሲ ፅነሰ ሀሳብ ቦታውን ስለሚኣስረክብ የጎሣ ቡድኖች እጅ እያወጡ በምድፅ ብልጫ የላካቸውን የጎሣ ፖለቲካ ተልእኮ ለማሳካት በቤተክርስቲያነው ውስጥ በሲኖዶስ ስም የፈቀዱትን የወስናሉ፥ ያስወስናሉ፤ 

 ሲመቱን ተከተልሎ የፊንፊኔ መንበር፥ የአክሱም መንበር፥ የእገሌ ጎሣ ከተማ መንበር በሚል ክፍፍል ሲኖዶስ ይበተናል፥ የንብረትና የቦታ ክፍፍል በዚሁ ክፍፍሉን በፈጠረው መንግሥት ዳኝነት ይካሄዳል 

 ምእመናን ይበታተናሉ፥ የጎሣ ፖለቲካው የጀመረውን እርስ በእርስ የማጫረሱን፥ የፈቀደውን የማጽዳቱን ፕሮጄክት የጎሣ “ጳጳሳቱም” እየባረከሉት አጠናክሮ አጠናክሮ ይቀጥላል፥ 

 8.2. አስተቸኳይ የአጭር ጊዜ መፍትሔ ጥቁምታ 

 1. ምእመናን፥ ማበራትና ካህናት በአሁኑ ጊዜ ያሉት አብዛኛዎቹ የፖለቲካ ድርጅቶችና ንቅናቄዎች ዜጎችን በቋንቋ፥ በእምነትና በባህል፥ በፖለቲካዊ የንዑስ-ማንነት የመከፋፈል አካሄድ በጥምቀት አንድ የሆኑትንና አስተምህሮዋን የሚቃረን ኦርቶ ዶክሳዊነት ቤተክርስቲያንን በቀጥታ የሚወጉበትን አካሄድ ለማቆም የፖሊሲ ለውጥ በማድረግ እንዲያረጋግጡ የሚያስገድድ ጥሪ፥ የግንዛቤ፥ የተደራጀ ፖለቲካዊ ንቅናቄ በአስቸኳይ መጀመር፤ 

 2. ቅዱስ ሲኖዶስ በውግዘት፥ ሊቃውንትና መምህራን በእውቀታቸው የጎሣ የፖለቲካ ርእዮትና ከእርሱ የሚመነጩ ሕጎችና ፖሊሲዎች፥ አደረጃጀቶች እና በመደበኛና መደበኛ ባልሆኑ መንገዶች የሚተላለፉ ትምርቶችን ኢክርስቲያናዊነት ለምእመናን ይፋ በማስገንዘብ ክርስቲያኖች አንድነታቸውን እንዲያጠናክሩ፥ ለክርስትናቸው ተፃራሪ ለሆነው የፖለቲካ ሥርዓት አማራጭና ለዜጎች ሁሉ በእኩልነት የሚያገለግል፥ ለእምነቶችና ባህሎች አድልዎ የሌለው አገራዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዲፈጥሩ ግልፅ መልዕክት እንዲያስተላልፉ ተጋድሎ መጀመር፤ 

 3. በአሁኑ ጊዜ ከቀበሌ እስከ ፌደራል መንግሥት የተዘረጋው የሕግ አውጭው፥ የአስፈጻሚው፥ የፀጥታና የፍትሕ መዋቅራት ኦርቶዶክሳዊያንን በለመየት በግልፅ አድልዎአዊ አሠራር ሁለገብ ግፍ የሚፈፅመውን የመንግሥት መዋቅርና እና የፖለቲካ ሥርዓት ቅዱስ ሲኖዶሱ በግልፅ መግልጫ እንዲቃወም የሚቻለውን ግፊት ማድረግ በአስቸኳይ የማስቆም ፖለቲካዊ አጀንዳ ሆኖ የድርጊት መርሐግብር የትግላቸው አካል አድርገው በግልፅ እንዲያሳዩ፤ 

 4. እስከ ዛሬ ድረስ የሚካሄዱ ካለፉት 50 ዓመታት ወዲህ በፖለቲካዊ ፍላጎት በኦርቶዶክሳዊያን ላይ ያነጣጠሩ የአካል፣ የሥነ-ልቦና፣ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ፣ የፖለቲካ፣ የማፈናቀል፣ ከአገራዊ ተሳትፎ የመገለል እና የፍጅት የመፈፀሙ ሂደት የሚገታበት፥ ችግሩ መንግሥታዊና የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ እውቅና እንዲሰጡት የሚያስገድዱ እርምጃዎችን በመውሰድ ሕጋዊ፥ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ መፍትሔዎች እንዲተገበሩ ማድረግ፤ 

 5. በመጨረሻም ከላይ የተቀመጡት የመፍትሔ አቅጣጫዎች ሁሉ ትርጉም የሚኖራቸው የቤተክርስቲያን የውስጥ አንድነት ሲጠበቅ ብቻ እንደሆነ በመገንዘብ፤ ይህን አንድነት የበለጠ የሚጎዳውን ፖለቲካዊ የጎሣ የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ማስቆም፤ ምእመናን የሚነጣጥል የጎሣ ቤተክህነትና የሐዋሪያትን ቀኖና ሙሉ በሙሉ የሚቃረነውን የጎሣ ፖለቲካዊ የኤጲስ ቆⶑሳት ምርጫ በተደራጀና በተናጥል የሚቆምበትን ማንኛውንም ጥረት ማድረግ፤ የምእመናንን ጥረት በመተላለፍ ሂደቱ ቀጥሎ ሲመት የሚካሄድ ከሆነ ምእመናንና ካህናት ለተሿሚዎች ብቻ ሳይሆን ለሿሚዎቹ ሳይቀር የአባትነት እውቅና በመንፈግ ሂደቱ መልሶ እንዲጤን እርምጃዎችን ለመውሰድ ከወዲሁ መዘጋጀት፤.

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

የሐሰት ትርክት ኦነጋውያንና የሕወሃታውያ የጋራ ስልት ከነግሥታት ወደ ተራ ግለሰቦች

✏️ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።  እርሱ ይመስገን። ምድራችንን #በደም #ያጨቀየው $ህሊና #የነሳን ፣ #ልቦናችንን #ያጨለመን ፣ #ሰብእናችንን ያዋረደው:- 👉 የሕወሐታውያንናንየኦነጋውያን የንዑስ ማንነት የጎሣ ፖለቲካ የደንቆሮ ርእዮትና፣ 👉 መርዛማን ጥላቻን ለ፶ ዘመናት ያከፋፈሉት የሐሰት ትርክት ናቸው። ✏️እንደ ዳግማዊ #ምንልክ ያሉ   ከዋክብት መሪዎች፣ እንደራሴቻቸው፣ ደጃዝማቾችና ቀኝና ግራ አዝማቾቻቸው  ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ብዙ ውለታ ውለውልናል:- 👉 በዘመነ ኦቶማንና አውሮፓ፣ በዘመነ መሳፍንት የተበታተነውን እና የተቆነጻጸለውን፣ ጎሠኛ የአርብቶ አደሮች  መሬት ፍለጋ  የደመሰሱትን ክርስቲያናዊ የግዕዝ/የነፃነት ሥልጣኔ አሻራ እንዲያገግም ደክመውልናል፤ 👉 የጥንት አገርን እና ሕዝቦችን   በከፊልም ቢሆን በመሰብሰብ  ጠንካራና ብቸኛ የነጭ ቅኝነትንና ባርነትን በመከላከል፣ ከኦቶማን ቱርክ ወር ትናንት ውስጥ ጥረኛ  አህመድ ግራኝ በመጋደል  ልዩ የነጻነት ማንነት ያላትን አገር ብበቸኝነት በዓለም ካርታንላይ አቆይተዋል፤ 👉 የሬማ ግዛት በጎሣ ተብልቶ ፲ ትንንሽ ሲሆን ከበበባውን ተቋቁማ በዝኃነታችን በተመጋጋቢ አንድነት ከ፹ በላይብቋንቋ፣ ከዓለም ትልልቅ እምነቶች ክትስትናን ፣ ይሁዲን፣ እስልምናን፣ የእረማውያንን ቅሪት የሆኑ የባህል እምነቶችን ሁሉን ይዛ በአውሮፓ በአርብ አምሳል ሳትሠራ ለእኛ አቀብዋል፤ 👉 ወያኔና ኦነግ፣ ገንጣዩ ሻዕብያ፣ ከሃዲው የማርክሲስት የአእምሮ  ባሪያን ስብስብ  እስኪፈትናት ድረስ ራሷን የቻለች አገር እንድንፈጥር ያስተባበሩን ነገስታት የተመሰገኑ ናቸው። አገር ሲያረጅ ጃርት ያብቅላል እንዱሉ: መል...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩. ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡  በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡  ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በቋንቋ መ...

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...