ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ኦርቶዶክሳዊ ካህን ወይንም አባት እንዴት ይታወቃል?

ኦርቶዶክሳዊ ካህን ወይንም አባት እንዴት ይታወቃል? በአባትነት ስም የዘራፊዎች ኔትዎርክ የሚደግፉ ምእመናን ቆም በለው ማሰብ የጠበቅባቸእዋል። የጠበቅብናል። ከጭብጨባና ከእልልታ፣ ከሞንታርቦና ከሁካታ እንውጣ። ክህነት ለገቢ የሚገቡበት ሙያ አይደለም፣ ክህነት ክርስቶስን መስሎ የሰው ልጆችን ወደ እግዚአብሔር አብ እቅፍ የሚመሩበት፣ ከልጁ ከቃለ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በአባት ቀኝ እንዲቀመጥ ለማገልገል በራስ ላይ የሚጭኑት የሰማእትነት ሕይወት ነው። ክህነት የመንግሥተ ሰማያት መግቢያ መክፈቻ ቁልፍ ነው። ይህን መክፈቻ የሆድ መሣሪያ በማድረግ በሰው ፊት መንግሥተ እግዚአብሔርን መዝጋት የበደል ሁሉ በደል ይሆናል። (በስንክሳራችን ሰኔ 17 ቀን የሚነበበውን የአባ ለትጹን ታሪክ በማንበብ በክህነት ስም መቀለድ ምን እንደሚያስከትል መረዳት ይቻላል።0 አባት የሚባለው ቢያንሰ የሚከተለውን ካላሟላ ሊገሰጽ፣ በቆና ተዳኝቶ ከክህነት ጾታ ውጭ ሆኖ ሕዝባዊ ተንሳሒ መሆን አለበት፦ 1) ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ካህን የምትላቸው፦ 👉 ኦርቶዶክሳዊ ካህን በጋብቻ ውስጥ ንጽህ የጠበቀ 👉 ዝግተኛ 👉 ሱሰኛነትና ከጠጭነት የራቀ 👉 አመጽኛነትና ከመጣላት ፈጽሞ የራቀ ሰላማዊ 👉 ታማኝ፣ በሌብነትና በፍቅረ ንዋይ የማይታማ፣ በማጨብርበርና የማይከሰስ፣ 👉 በዘመደ አዝማድ ተክብቦ ሌላውን በማግልል በክርስቲያኖች መካከል ለመለያየት ምክንያት የማይሆን፣ 👉 በሚኖርበት ማኅበረሰብ በክፋት ስሙ የማይነሳ፣ (1 ጢሞ 3፣ ቲቶ 1) 2. የቤተ ሰብእና የትዳር መለኪያ፦ 👉 ቅስና በጋብቻ ወይንም በፍጹም ምንኩስና ውስጥ ብቻ የሚኖሩት የቅድስና ሕይወት በመሆኑ፦ 👉 ጋብቻ የሚፈጸመው ከእጅ መጫን አስቀድሞ ነው፣ የምንኩስና ቆቡም፣ ተጋድሎው ቅምሻውም ከቅስና ሥልጣን በኋላ የሚሰጥ ነው፣ 👉 አንድ ጋብቻ ብቻ ነው የሚፈቀደው፣ ከክህነት በኋላ መልሶ ማግባት አይቻልም፤ 👉 ካህን ለጆቹን በወልጌል በማሳደግ ለሕዝባውያን ቤተ ሰብእ አርአያ መሆን የጠበቅበታል፤ 👉 ገዳማውያን ወይንም መነኮስ ካህናት አኗኗራቸው ከርእሳነ መንኮሳት ቀደምት አብው ሕይወት የተገናዘበ ተሐራሚ መሆን አለበት ድንግልናቸው የተጠበቀ መሆን አለበት፤ 3. ካህን የግድ ቅዳሴአዊና መንፈሳዊ ስነ ሥርዓት ውስጥ መኖር፦ 👉 በግጻዌና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረትና ዑደት በጽሎት መገኘት (ሌሊት፣ ንጋት፣ ሰርክ --- እነደየ ሕጉ) ፣ 👉 ቀዳሴ መቀደስ፣ በቀዳሴው ውስጥ የሚተላለቅፉ ጥልቅ መንፈሳዊ መለክቶችንና ትምህርቶችን በቃልና በሕይወት ላለመቃረን የሚችለውን ተጋድሎ ሁሉ ማደረግ አለበት (የሚቀድ ሆኑ የሚዋሽ፣ የሚሰርቅ፣ ቡድንተኛ፣ ወርቅ አሳዳጅ፣ ሀሜተኛ፣ ስስታምና ሆዳም --- ከሆነ አሰናካይ እንጂ መንፈሳዊ መሪ ምሆን አይችልም) 👉 የአዋጅ አጽዋማትን በቻ ሳይሆን ራሱን ለመግዛትና አርአያ ለምሆን በልክ መመገብ 👉 መጽሕፍ ቀዱስንና የአበው መጽሕፍትን ዘወትር መመልከት 👉 የተነሳሒና የመንፈሳዊ ክርስቲያን ሥርዓትን በሕይወቱ የሚያስነብብ ----- የአንድ ኦርቶዶክሳዊ ካህን የጀርባ አጥንት ናቸው። 4. ካህናት የገቢና የሥራ ሁኔታን የሚመለክት መሥፈርት፡ በኦርቶዶክሳዊ ትውፊት ካህን፦ 👉 ካህን ከአራጣ አበዳሪነት፣ ማጭበርብር ካለበት ፈታኝ ንግድ፣ ወይንም የሌሎችን ጉልበት የሚበዝብዝ ሥራ፣ በአጠቃላይ በወንጌልም ይሁን በማኅበረሰቡ የግብረ-ገብነት ሚዛን ተናቁ ተግባራት ውስጥ ፈጽሞ መገኘት አይኖርበትም፣ ይህ ፈጽሞ ለክህነት አይስማም፤ 👉 መጠነኛ፣ ቅንጡ ያልሆነ፣ ከስስትና ንፍገት የራቀ ሕይወት መኖር የጠበቅበታል፤ 👉 በተቻለ መጠን ካህን ፈተና ላይ እንዳይወድቅና ክፉ ምሳሌ እንዳይሆን በሴኩላር ተቋማት ቁጥጥር ሥር በቅጥረኝነት ባይሰማራ ይመረጣል፤ 5. ክህነታዊ/የረኝነት ኃላፊነት አንድ ካህን የሚከተሉት ኃላፊነቶችን መወጣት ግዴታው ነው፦ 👉 ኦርቶዶክሳዊ ሃይማኖቱን ከምንጩ እንደ ተቀበለ ሳይቀንስ፣ ሳይጨምር፣ ሳያዛባ በትክክል ማስተማርና መጠበቅ፣ 👉 የረኝነት ሥራውን (ተነሳሕያንን መናዘዝና መከታተል፣ የታመሙትን መጎብኘትና መጸለይ/ምሥጢረ ቀንዲል መፈጸም፣ የታሰሩትን መጎብኘትና ማጽናናት፣ በኑፋቄ የሚናወጽትን ማጽናት) ፣ 👉 የአጥብያ ምእመናን አንድነት፣ መረዳዳት፣ በአጥቢያ አስተዳደር ነቀፋ የሌለበትና ለዓለም አስተዳደር ምሳሌ የሚሆን አመራር መስጠት፣ 👉 ከፋፋይ ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነትና የውስጥ ቅስቀሳዎችን በመከላከል መንፈሳዊነት ፖለቲካውን እንዲቀደሰው መመናንን ማብቃት፣ 👉 የትህትናና የአገልጋይነት ተምሳሌት መሆን። 6. ካህን ለመሆንም ሆነ ከክህነት የሚያሰወጡ ቀኖናዊ ማዕቀቦች 👉 ኑፋቄ 👉 ክህደት 👉 ንፍስ ማጥፋት፣ ወንጀለኛነት ረብሻ መምራት 👉 ከእረኝነት ሥራ የሚያሰናክል የአእምሮ ጤና መዛባት 👉 ግልጽ ማጭበረበርና ምእመናንን የሚያሰናክል ድርጊት/ጠባይ 👉 ለኦርቶዶክሳዊ ለሊቀ ጳጳሱ አለመታዘዝ አሁን በእኛ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚርመሰመሱ "ካህን/አባት" ስንቱ እጅ ነው በኦርቶዶክሳዊ ሚዛን ላይ ወጥቶ የማይወድቀው? ምእመናን እና ከኦርቶዶክሳዊ የክህነት መሥፍርት ያለወደቃችሁ አባቶች. አስቸኳይና ከባድ ኃላፊነት ወድቆባችኋል። እርሱም ሕዝብን ብጭብጨባና እልልታ፣ መዝሙር በሚመስል አዘናጊ ዘፈን፣ በሕንጻ ግንባታ፣ በቱሪስታዊ በዓል የሚያደነዝዙትን ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነትን ፈጽመው የማይረዱ ወይንም ለአጽራረ ቤተ ክርስቲያን የሚያገለግሉትን ለይቶ እውነተኛ አባቶች እና ካህናት የኦርቶዶክስን ቤተ ክርስቲያን እንዲጠብቁ መሥራት ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

የሐሰት ትርክት ኦነጋውያንና የሕወሃታውያ የጋራ ስልት ከነግሥታት ወደ ተራ ግለሰቦች

✏️ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።  እርሱ ይመስገን። ምድራችንን #በደም #ያጨቀየው $ህሊና #የነሳን ፣ #ልቦናችንን #ያጨለመን ፣ #ሰብእናችንን ያዋረደው:- 👉 የሕወሐታውያንናንየኦነጋውያን የንዑስ ማንነት የጎሣ ፖለቲካ የደንቆሮ ርእዮትና፣ 👉 መርዛማን ጥላቻን ለ፶ ዘመናት ያከፋፈሉት የሐሰት ትርክት ናቸው። ✏️እንደ ዳግማዊ #ምንልክ ያሉ   ከዋክብት መሪዎች፣ እንደራሴቻቸው፣ ደጃዝማቾችና ቀኝና ግራ አዝማቾቻቸው  ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ብዙ ውለታ ውለውልናል:- 👉 በዘመነ ኦቶማንና አውሮፓ፣ በዘመነ መሳፍንት የተበታተነውን እና የተቆነጻጸለውን፣ ጎሠኛ የአርብቶ አደሮች  መሬት ፍለጋ  የደመሰሱትን ክርስቲያናዊ የግዕዝ/የነፃነት ሥልጣኔ አሻራ እንዲያገግም ደክመውልናል፤ 👉 የጥንት አገርን እና ሕዝቦችን   በከፊልም ቢሆን በመሰብሰብ  ጠንካራና ብቸኛ የነጭ ቅኝነትንና ባርነትን በመከላከል፣ ከኦቶማን ቱርክ ወር ትናንት ውስጥ ጥረኛ  አህመድ ግራኝ በመጋደል  ልዩ የነጻነት ማንነት ያላትን አገር ብበቸኝነት በዓለም ካርታንላይ አቆይተዋል፤ 👉 የሬማ ግዛት በጎሣ ተብልቶ ፲ ትንንሽ ሲሆን ከበበባውን ተቋቁማ በዝኃነታችን በተመጋጋቢ አንድነት ከ፹ በላይብቋንቋ፣ ከዓለም ትልልቅ እምነቶች ክትስትናን ፣ ይሁዲን፣ እስልምናን፣ የእረማውያንን ቅሪት የሆኑ የባህል እምነቶችን ሁሉን ይዛ በአውሮፓ በአርብ አምሳል ሳትሠራ ለእኛ አቀብዋል፤ 👉 ወያኔና ኦነግ፣ ገንጣዩ ሻዕብያ፣ ከሃዲው የማርክሲስት የአእምሮ  ባሪያን ስብስብ  እስኪፈትናት ድረስ ራሷን የቻለች አገር እንድንፈጥር ያስተባበሩን ነገስታት የተመሰገኑ ናቸው። አገር ሲያረጅ ጃርት ያብቅላል እንዱሉ: መል...