የቤተ ክርስቱያን ሚዲያዎች የማንን ተልእኮ እያራመዱ ነው??
‼️
#ለመከላከል ያይደለ ለመስተካከል ማድላት ትህትናና የንስሐ ልብ ላላቸው ነው።
በተቃራኒው መቆም የአጥፉነትና የጥፊነት የአምባገነን ፖለቲከኞች ጌጅ ስነ ልቡና ነው።
ለቤተ ክርስቲያን የመረጃና ትምህርት ማሰራጫ ሚዲያዎች ወቀሳ አለኝ። ያሚጠቅም የቤተሰብ ውፕቀሳ ነው። በከንቱ በአድርባይነት እየተውፕዳደሱናንባዶ ክብር እየተቀባበሉ ከመስጠም መራራውን እውነት እየትጋቱ በንስሐ ትንሳኤ በምህረት ክንፎች መብረር ይበልጣል።
ያኛው ለአሁኑ ሆድ መሙያ ለኋላው የዘላለም ሞት ነው‼️
እንደ ቤተ ክርስቲያን አካል አንድ ብልት ህመሟ ህመሜ ነውና ወቀሳዬ እነሆ፦
#"የቤተ ክርስቲያን" የሚል ቅፅል ቀጽላችሁ ነገር ግን ቤተክርስቱያንን ቤተክርስቲያን የሚያሰኟትን በክርስቶስ መሠርትነት ላይ ስለተገነቡ ግድግዳዌችና ስለተዘረጉ ጣሪያዎች #አይመለከትንም ማለታችሁን ልመስክርባችሁ።
‼️
"የቤተ ክርስቲያን" የተቀጸለበት ሁሉ ምእመናንና ካህናትንም የሚያካትት ከሆነ ሚዲያው እኛን እንጂ አጥፊዎቻችንን ማገልገል ማቆም አለበት ‼️
በክርስትናችን ትውልዳዊ ቀጣይነት አንጻር ወሳኝ በሆኑት ጉዳዮች ስትመዘኑ የማጽናት፣ የማሳደግና የማስፋት ያይደለ #በማጥፋት መንገድ ላይ #ቆማችሁ ትታያላችሁ ‼️
በእንፃሩ በዚህ ዘመን ለቤተክርስቲያን ህልውና እንቅፋት በመሆናቸው ምእመናን እንኳን ዐውቀውት በአንድ ልብ ሆነው ሊከላከሉት የሚገባቸውን አደጋ #እንዳያውቁ ታደርጋላችሁ።
አውቀው ለማሳወቅ የሚጥሩትን ለማፈን እንደ አምባገንን ፖለቱካዊ ሥርዓት በቃላትና በጥቅስ በሚጀምር ነገር ግን ጥቅሱን በሚቃረን ፕሮፓጋንዳ ልትዋጉ ርሞክራላችሁ።
#ጠላትን አቅርባችሁ ወዳጅን ታርቃላችሁ። ለጭብጨባና ለእልልታ፣ ለውዳሴና ለሽልማት፣ ለገንዘብና ለዝና የሚኖሩትን ከንቱዎች ተከትላችሁ በቁስላችን ላይ ጨው ትነሰንሳላች።
አሁን ይባስ ብላችሁ በተግባራቸው ለሚቃረኑት ቡድኖች፣ ከንስሐ እየሸሹ ራሳቸውን ከእውነት ለሚከላከሉ የቤተ ክርስቱያን እንቅፋቶች በአፈቀላጤነት ስትሰሩ ምእመን አማራጭ ጠዋሚ ሀሳብና መረጃ እንዳያገኝ ፦
👉 ምእመናን የቱን ሚዲያ መስማት እንደ አለባቸውና እንደሌለባቸው ጥሪ ታቀርባላችሁ፣
👉 እውነትን እንደ ክርስትናው በማስርጃ፣ በቀኖና እና በተግባራዊ ሕይወት መግለጽ ሳይሆን በሸፍጥ ፖለቲካዊ ዘይቤ በፕሮፓጋንዳ ጥፋትን ልማት ለማስመል ትጋደላላችሁ፣
👉 #የሐርያትን ቀኖና፣ ለዚያውም የመንግሥተ ሰማይ መግቢያ ቁልፋችንን #ክህነትን የሚነካ ጥሰትን ወደ ቦታው መልሶ የማስተካከልን እንገብጋቢነት እና ስልታዊነት ሰውራችሁ በተባራሪ ዕለታዊ ወሬና መግለጫ ወሳኝ አጀንዳዎችን ትቀብራላችሁ፤ ----
ዛሬ ላይ የምንመለከተው ነገር እየተሻሻላችሁ ሳይሆን እየባሰባችሁ መሄዱን ነው።
ስለምንሰማውና ስለማንሰማው ሚዲያ ቀኖና ለማንበር ስትጥሩ በእንጻሩ ስለምንድንበት የኤጲስቆጶሳት የሲመት ቀኖና መናድ ታድበሰብሳላችሁ።
አንዳች ፈሪሃ እግዚአብሔር የላችም? በጌሣ ክህነትና ሱኔዶስ ሱፈጠር፣ ሲኖዶስ ያወገዘውን በግላቸው እንደንካቶሊክ ፖፕ የሀሉ የባላይ፣ ክህነቴ በውግዘት የማይሻር በሚል አይነት ዕሳቤ ሱባርኩ አጀንዳ አይሆንም? እናንተ ዘገባችሁ በፓትሩያሩኩ ድርጊት የሚመጣውን የክህነት ሞታችንን ሳይሆን አጥፍተው ሲመለሱ በትፕቃራኒው አልምተው ተመለሱ በሚል የአቀባበል ድምቀት ፕሮፓጋንዳ በመሥራት ምእመናን የመጣውን ጥፋት እንዳያስተውሉ መጋረድ ነበር። ግን እስከ መቼ? ለምን ዓላማ? ባህልን ወይስ ምንጩን እምነትን ነው የምንጠብቀው?
‼️
ሚዲያዎች በቀጥታም ባይሆን እንደ አቅጣጫ "ሌላ ሚዲያ አትስሙ" ከማለታችሁ አስቀድሞ እግዚአብሔርን በመፍራት ለጳጳሳቱ "ምእመናን እንዲታዘዟአችሁ በመጀምሪያ፦
👉 እናንተም በእደባባይ የሻራችሁትን መልሳችሁ ለሐርያት ቀኖና በመታዘዝ ለክርስቶስ መታዘዛችሁን አሳዩአቸው፤
👉 በተግባርም በአላዊ ንጉሥ ደብዳቤ የሻራችሁትን የሐርያት ቀኖና ወደ ቦታው መልሱ፣
👉 በጎሣና በገንዘብ፣ በጎጥና በዘመድ የተግበስብሰው የሲኖዶስ አባላት የሆኑትን በቀኖናው ወንፊትነት አጣርታችሁ እና ለይታችሁ በትክክል "ብፁዐን" የሚያሰኛቸው ሕይወትና ግብር ባላቸው ኦርቶዶክሳውያን ካህናት ተኩ" እና ----
--- ከዚያ በኋላ ሚዱያችን ሁሉ ተአማኒ እንዲሆን እርዱን" በሏቸው።
እንዳው በባዶ ሜዳ "አድምጡን" ብሎ መወራጨት ለአጥፊዎችህ ማደንዘዣ እንድንወጋህ በጀ በለን አይነት ፌዝ ይሆናል።
እንደወረደ የአጥፊዎቻችን ተላላኪዎችን ሁሉ መልእክት እያሰራጫችሁና የሚጠቅመንን እየቀበራችሁ እኛን ብቻ ስሙ ማለት "እስክትጠፉ ድረስ ንቅንቅ ሳትሉ ተሰልፋችሁ በድንዛዜ ቆዩ" እንደማለት ነው። "የቤተ ክርስቲያን" በሚለው ቅጽል መርካት አንችልም። በራሳችን ሀብት ጠላትና የውስጥ ሠራተኛ #አታገልግሉብን ‼️
ለማንኛውም እንደምገነዘበው #የምትበረቱበትን እና #የምትለግሙበትን የመረጃ አይነት በጥቂቱ ልጠቁማችሁ ወደድኩ።
ይቅርታ አድርጉልኝ፣ #እውነት ካልተነጋገርን የጀመርነው #የውድቀት ጉዞ #አይገታምና ለሁላችን መዳን ምክንያት ለመሆን እናገራለሁ።
ይህንን ነገሬን እንደተለመደው ለፕሮፓጋንዳ "አለማክበር"‼️ አድርጋችሁ ከወስዳችሁት መደምደም የሚቻለው በእርግጠኝነት ጥፋታችሁን ለማስቀጠል ያላችሁን ቁርጠኝነት ብቻ ነው።
ለቤተ ክርስቲያን ሳይሆን ለአንዳች ሰይጣናዊ ግብ የተሰለፋችሁ ፣ ለክርስትና ሕይወታችንም ሆነ ለቤተክርስቲያን የማትጠቅሙ ብቻ ሳይሆን ከመንግሥትና ከዘመኑ የፖለቲካ ሽፍጥ የተቃጣባትን የህልውና አደጋ የምታጠናክሩ ናችሁ ለማለት እደፍራለሁ።
በቃ እኮ በ፯ቱ አመት ሞትና ስደት ዓይናችን ተገልጧል።
ምነው የእናንተ እምቢኝ አላችሁ?
እንደሚረዳኝ እየተሸነጋገሉ ተያይዞ ከምሞት #መራራዋን እውነትን በፍቅር እየተነገሩ ሕይወት ማግኘት በእጅጉ ይልቃል ‼️ እናም ታገሱና በእኔ በግልንዓይኔ ከአለው ምሶሶ ጀርባም ሆኞ ቢሆን ለሁላችንም ይጎዳል ያልኩትን ጉድፍ ልንገራችሁ፦
ልባችሁን አደንድናችሁ ዘመን ለወለደው ንጉሥ ለወደደው ሁሉ የምታጎበድዱ የማትሸነፋዋን የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የውስጥና የውጭ ጠላቶቿን በምታሸንፍበት በቅርብ ዘመን በብልጠት እንደምታስቡት ምእመናኑን ብቻ ሳይሆን ራሳችሁንም #ተጎድታችሁ ታገኙታላችሁና ወቀሳውን በበጎ ውሰዱት።
ምርጫው የእናንተ ነው።
ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ነው ነገሩ‼️
🤓 የምትበረቱበት ዜናና መግለጫ በሚከትሉትን ጉዳዮች ዙሪያ ሲሆንላችሁ ነው:-
፩) የፖለቲካና የዘመኑ ፖለቲካ የወደዳቸው ነገር ግን በቀኖናዊ ሚዛን በጥምቀት ልጆች የማይወደዱ፣ በኢ-ክርስቲያናዊ ግብራቸው በክርስትናችን አጠቃላይ አቋም ላይ መናጋት ያመጡ ግለሰቦችና ቡድኖችን ተክለ ሰውነት በመግንባት፣ በማወደስና በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኙ በመወትወት ዙሪያ፤
፪) ለቤተክርስቲያንና ምእመናን ከዘመኑ ሁኔታ አንፃር አንገብጋቢ፣ ጠቃሚና ወሳኝነት የሌላቸው ብልጭልጭና አዘናጊ አጀንዳዎችን ማራገብ፤ ለምሳሌ የመንግሥት የኮሪደር ልማትና ለቤተክርስቲያን ያደረገው (፼ እጥፍ የተደረገባትን ለመቅበር)፣ የሕንፃ ግንባታ፣ ከቀኖና ውጭ እንደ ወታደር ከቦታ ቦታ ምቾትና ገቢ ለማሳደግ የሚሟሟቱትን ጳጳሳት ዝውውር፣ የቤተክርስቱያንን አንድነት አጽንተው ሳይሆን #አፍርሰው የሚመለሱትን ለምሳሌ እንደ አቡነ #ማትያስ የቅርቡ ተግባር (የመንበረ ሰላማ አዳራሽ አሜሪካ ተጉዞ መባረክን) "ሐዋሪያዊ ጉዞ" በማለት እውነትን በመቃረን ፕሮፓጋንዳ መሥራት፣ የሐሰት ምስክር መሆን፤
፫) የፈለሱትን ሚሊዮኖች ምእመናንና ምክንያቱን ጨምሮ በመዘገብ የመፍትሄ አጀንዳ እንደመፍጠር ይህን አንገብጋቢ የቤተክርስቲያን ህልውና ጉዳይ ደብቆ እና ለማረሳሳት በጠረፋማው የአገሪቱ አካባቢዎች በምእመናን ጥረት የሚጠመቁ መቶዎችን ምእመናን አድምቆ በማቅረብ ከአጠቃላይ ተጨባጩ ሁኔታ ተቃራኒ መልእክት በማስተላለፍ ምእመናንን ማስተኛት፤
፬) ምእመናንን ሳይጎበኝ፣ ተጋድሎአቸውን ሳያጠናክር አዲስ አበባ ከረማ በምቾት እየከረመ አልፎ አልፎ እንደ መዝናኛ ሀገረ ስብከቱ ደርሶ ምእመናን አውኮ፣ ካህናትን አስለቅሶ፣ ሰንበት ትምህርት ቤት አፍርሶ፣ የፖለቲካን ተልእኮ ተቀብሎ፣ የምእመናን ራስን የመከላከል ጥረት አምክኖ የሚመለስ ጳጳስ ፣ አሜሪካ ዘልቆ የሥጋ በሽታውን ታክሞ፣ ጎሣዎቹን አደራጅቶ፣ የሚያርፍበትን ቤተክርስቲያን በውጭ መሥርቶ። ምእመናንን ከፋፍሎ እና ተዝናንቶ የሚመለሰውን ጳጳስ "ሐዋርያዊ አገልግሎት ፈጽመው ተመለሱ" ብሎ በመዘገብ የተሠራውን ኢ-ክርስቲያናዊ ተግባራት ትሰውራላችሁ፤
፭) ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም አቅደው በግልፅ በመዋቅራዊ አሠራር ምእመናንን ሲያፈናቅሉ፤ ከሰንበቴ፣ ማኅበራዊ ተቋማቶቻቸው፣ ከምጣኔ ሀብት መሠረቶታቸው፣ ከታሪካዊ ርስታቸው፣ ከአጥቢያቸውና መንፈሳዊ አባቶቻቸው ለይተው እንዲበተኑ የሚያደርገውን ፕሮጀክት በመደገፍ "እንደዚህ ዘመን ለቤተክርስቲያን የተመቸ የለም፣ ምእመናን ንፁሕ ቦታ ሰፈሩ፣ ተማሪዎች ምቹ ትምህርት ቤት አገኙ" የሚሉ ጳጳሳትና መነኮሳት፣ የነፍሳትን መጥፋት ሳይሆን የቱሪዝም ባለሙያ መስለው "ከተማው አማረ" የሚል የውበት ፕሮፓጋንዳ የሚሠሩ አድርባዮችን ተከትላችሁ #ግፍን #እየቀድሳችሁ ዘገባ ትሠራላችሁ።
🙈 #የምትለግሙበትና ለጠላት እንደምትሠሩ የሚመሰክርባችሁ አንገብጋቢ #የቤተክርስቲያንና #የምእመናን #አጀንዳዎች፦
፩) የምእመና እና የካህናት በአርሲ፣ በባሌ፣ በሐረርጌ፣ በከሚሴ፣ በአዲስ አበባ፣ ሻሸመኔ፣ ትግራይ ፣ በአማራ፣ በጉምዝ፣ በሶማሌ፣ በደቡብ ወዘተ በመንግሥታዊ መዋቅር ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ መንገድ በስፋት መገደል፣ መፈናቀል፣ ከእምነት መፍለስ፣ በመንግሥት ሤራ እርስ ብርሱ መጠፋፋት እንዳይነገር ፣ ምእመን ነቅቶ የሚደጋገፍበትን ንቃትና እንዳያገኝ ክፍያ የትቀበላችሁ ይመስል ትንሽ እንኳን ጥቆማ አትሰጡም፤
፪) የክርስቲያኖች በመላው ኦሮምያ፣ ጉምዝ በስፋት መጨፍጨፍ፣ በእቅድ ከገጠርና ከከተማ መሬት፣ ከንግድና ሥራ መፈናቀልን በሚመለከት ከአጥቢያ ጀምሮ በተዘረጋው መዋቅር ሰብስባችሁ በየቀኑ መዘገብ ስትችሉ ንክች አታደርጓትም፤
፫) በከተማ ልማት ስም ክርስቱያኖችን ዒላማ ያደረገ ሁለገብ ጥቃት ሲፈጸም ምን ያህል ማኅበራዊ፣ መንፈሳዊናንሁለገብ ጉዳት በክርስቲያኖችና ቤተክርስቲያን ላይ እንደደረሰ ለመናገር ፈቃደኛ አይደላዥሁም፤
፬) በቤተ ክርስቱያን ውስጥ ስለተፈጠረው የጎሣና የሙስና ቡድን፣ ፖለቲካው በዚህ ውስጥ ያለው ሚና እና በመንደሳዊ ሕይወታችንና በአጠቃላይ በኦርቶዶሳዊነት ላይ ያለውን ጉዳት ለማሳወቅ ምንም ጥረት አታደርጉም፤
፭) በሕወሃትና ኦነግ አስተምህሮ፣ በጽንፈኛ ዉሀብያ በእምነታችን ላይ የሚካሄደው ሁለገብ የተጣመረ ጥቃትና መፍትሄውን በሚመለከት አጀንዳ ሆኖ አደጋው እንዲገታ አስተዋጽኦ ለማድረግ ምክንያትብየሚሆኑ መረጃዎችና ኲነቶችን በመዋቅራዊ ሰንሰለቱ እየሰበሰባችሁ በተቻለ መጠን ለማቅረብ አትሹም።
አሁን ደግሞ
ይባስ ብላችሁ ምእመናን እንዳይነጋገሩና እንዳይመካከሩ፣ ለቤተንክርስቲያን የሚጠቅመውን ምክረ ሀሳብ እንዳያንሱ፣ ግልጽ ለሆነ ጥፋት ግብረ መልስና ምክር እንዳይሰጡ እንደ አምባገነን መንግሥታዊ ሥርዓት አፍ ለመዝጋት ለሚሞክሩት ሙሰኞችና ለአጥቂው ፖለቲካ ለሚላላኩት አፈቀላጤ በመሆን መግለጫ ታሰራጫላችሁ ።
ወገኖች ‼️ #የምንድነው እውነት ስንነጋገር እንጂ በሀሰትና በአድርባይነት ገዳይ የሆነ የግብዞች ክብር ስንለዋወጥ አይደለም።
ይህንንሁሉንወቀሳ ሳወርድባችሁ ያላችሁበትን የውስጥናንየውጭ ተጽእኔ አጥቼው አይደለም። በዚህ ውስጥ ሁሉ ግን የሚቻል አያሌ ሥራ እያለ መለገማችሁ ብቻ ሳይሆን ተቃራኒውን የአጥፊዎች ፕሮፓጋንዳ በማራገባችሁ ነው። ፍላጎቱ ካለ ጢስና ጀግና መውጫ አያጣም።
እንጸልይ።
አስተያየቶች