ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ
ናዚና ገዳ ጥቁርና ነጭ እንዴት ተመሳሰlu? እውነት ካልተነጋገርን እንጠፋለን! በተላላኪነት ኢትዮጵያ ላይ እንደ መቅሰፍት ከተጫኑ የጨለማ ዘመን መግቢያ መክፈቻ የሆነው በወያኔና ኦነግ የጋራ ፕሮጄክት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከተመረጡ ዘርፈ ብዙ ስልቶች መካከል አገራዊ የጋራ ትርክቶቿን መደምሰስ ዋንኛው ነው። በዚህ ዘርፍ ሕዝቡን በጎሣዎ፣ በእምነቶችና በባህሎች ተገዳዳሪ ተርክትና ፖለቲካዊ እምነቶች የጋራ ሀገራዊ ተርክትን ማዳከም ዋናው ነው። አስተሣሣሪ ትርክቶችን፣ ብዝኃነት ያላቸው አሐዳዊ አገራዊ እሤቶችና ዕይታዎችን በማዳከም ሕብር ተበትኖ በተለያየ በንዑስ ማንነት ላይ የተመሠረተ አሠፋፈሮች ለመፍጠር መሠረት መጣል ነው። ቀጥሎም የአገራችንን ዜጎቿን መክፋፈልና ማፋጀት የሚያስችል ሁኔታ በመፍጠር ደርጃውን ጠብቆ ከትርክት ወደ ሕግ፣ ከሕግ ወድ ፖሊሲ፣ ታጣቂነት፣ ቀጥተኛ ሁለ-ገብ ጥቃትመፈጸም አሁን የማየው ነው። ከውጭ የአራችን ልዩ የነጻነት እሤቶች ምንጭ የሆኖ እምነቶች፣ ባህሎች፣ ማኅበራዊ ሥሪትን ዒላማ ካደርጉት የውጭ ወራሪዎች ትምህርት፣ ምክርና ተላላኪነት ተቀብለው ከሚሠሩ የሕወሃትና የኦነግ እንዲሁም የሁለቱ የፖለቲካዊ ርእዮቶች ለዚህ ጥፋት የተመረጡ ባህሎችና እምነቶች መካከል የኦሮሞ ባህላዊ እመነት፣ የዉህብያ ጽንፈኛ ኢስላም፣ የጀርመን ናዚ ትራፊ በሆነውና ኦነግንን በወለደው በግንቢ ሆስፒታል ውስጥ የተዘራው ፕሮቴስታንት ሲሆን የሁሉም ዒላማቸው የማንኛዉም ጎሣ አባልና ቋንቋ ተናጋሪዎች የሆኑ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ተከታይ ማኅበረሰቦች እና አማራ እንደ ብሔር ተፈርጆ በመለየት ናቸው። ኦሮሙማ የተባለው ፖለቲካ ሠራሽ አዲስ እምነትና የአምልኮ ሥራዓታት ከእስልምናና ክርስትና ሁሉ በላይ የሆነ ረእዮት ሆኖ ቀርቧል። ርእዮቱ ወደ ተግባራዊ መንግሥታዊ አቋም አድጎ የሕግና ፖሊሲ አካል ሆኗል። ይህንን በኦፒዲኦ/ኦነግ ኦሮሙማ የብልጽግና መንግሥት በአደባባይ አውጀዋል። ከአደባባይ አዋጁ አስቀድሞና በኋላም በተግባር ዒላማ የተደረገውን ወገን በአካላዊ፣ ስነ ልቦናዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊ፣ ፖልቲካዊና ሃይማኖታዊ ጥቃት በማጠናከር አሳይተዋል። ዛሬ ላይ ይህን መልእክት በአጭሩ የምጽፈው “ናዚ በገዳ ምድር፦ የናዚ ፓርቲ የጀርመናዊነት ርእዮት እና የኦሮሙማ ፕሮጀክት የሃይማኖት አንድነት” በሚል በቅርቡ በአንድ አጥኚ ከሚታተመው መጽሐፍ ጥቂት ነጥቦችን በመቀንጨብ ይሆናል። የጀርመኑ ናዚ ፓርቲ እንደ ፓርቲ ተመሥርቶ የመንግሥትነት ሥልጣን ከተቆናጠጠ በኋላ ስለ የአርያን ዘር የበላይነት እና የአርያን ዘር ሃይማኖት ቅዱስነት የሠራው አዲስ ትርክት የለም፡፡ የናዚ ፓርቲ ያደረገው እርሱ ወደ ሥልጣን ከመምጣቱ ከስድሳ እና ከሰባ ዓመታት በፊት የተሠሩትን ትርክቶች ወደ ተግባር እንዲቀየሩ የማስፈጸሚያ አደረጃጀቶችን በማመቻቸት ተግባር ላይ ማዋል ነበር፡፡ የናዚ ባለ ሥልጣናት ‹‹ሃያ አምስቱ የጀርመን ሃይማኖት አዕማድ›› ያወጁት አዋጅ ፈጥረውት ሳይሆን ቀደም ብሎ በዘርኛ ምሁራን ፈጠራና አፈታሪክ ላይ ተመሥርተው ነው። ጀርመኖች ከፈላስፎቻቸው በተጨማሪ በሚስዮኖቻቸው በኩልም ዓለምን በመዞር የአርያን ዘር ፍለጋ አድርገዋል፡፡ ብዚህ ፍለጋቸው የሚባል ነገር እንደሌሉ ቢረዱም ትርክቱን ለምን አንፈጥርም በሚል ብያኔ ከኢትዮጵያ ውስጥ ኦሮሞውች ‹‹ጥቁር ጀርመኖች›› ናቸው ብለን ትርክት እንፍጠር በለው አደረጉት። ጀርመኖች ጥቁር ጀርመን ያሉትን የኦሮሞ ሕዝብ በራሳቸው አስተሳሰብ፣ ባህል፣ ሃይማኖት እና ትውፊት ቀርጸው ለመለወጥ ከመቶ ዓመታት በላይ ጥረት አድርገዋል። ብዙ ጀርመናውያን ይህንኑ ተግባር ለማከናወን ወጣትነታቸውን ሠውተዋል፤ ውድ ሕይወታቸውን ገብረዋል፤ ገንዘባቸውን አፍስሰዋል፡፡ በመጨረሻም ሐሳባቸውን የሚገዟቸው ትውልድ ለማፍራት ችለዋል፡፡ እነዚህ የጀርመኖች ሐሳብ የገዙ ጥቂት የኦሮሞ ልጆች ‹‹እኛ ጥቁር ጀርመኖች ነን›› ከማለት አልፈው የጀርመኖችን ባህል፣ሃይማኖት እና ትውፊት፣ የናዚን የባንዲራ ቀለም በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ለመጫን ጥረት ማድረግ ከጀመሩ ከሃምሳ ዓመታት በላይ ደክመው ዛሬ “ኦሮሙማ ከእመነቶች ሁሉ ይበልጣል” የሚል መንግሥታዊ አቋም ያላቸው መሪዎችን የኢትዮጵያ ገዥ ለማብቃት ችለዋል። በእርግጥ ታሪክ ደጋግሞ እንደሚነግረን የናዚን ሐሳብ ሙሉ በሙሉ መተግበር ባይቻልም አገርን ለመበጥበጥ፣ ለማፍረስ፣ በከፍተኛ ደርጃ እልቂት ለመፈጸም ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንድሚችል ታውቋል። በኢትዮጵያ ይህን እልቂትና መበታተን ለመፍጠር ሂድቱ ተጠናክሮ ቢቀጥልም እንደሚፈልጉት ለማስኬድ አብዛኛው የኦሮሞ ሕዝብ ከኢትዮጵያዊነት ስሜት ያልወጣ ከመሆኑ ባሻገር ሃይማኖቱን፣ ባህሉን እና ትውፊቱን መልቀቅ አለመፈለጉና ከእነዚሁ የጀርመናውያንን ሐሳብ ከገዙ ጥቂት የኦሮሞ ልጆች ጋር ትግል የጀመሩ (ምናልባትም ትግል ለመጀመር የሚቀድሙ) የዐረቦችን ሐሳብ የገዙ የፖለቲካዊ እስላም ታጋዮችም ከእነርሱ እኩል እየተንቀሳቀሱ ስለ መሆኑ፣ አንጠፋም የሚሉ የህልውና ታጋዮች በስሜና በደቡብ፣ በማእከል ኦርቶዶክሳውያን ኦሮሞዎች መንቀሳቀሳቸው እንቅፋት እየደቀነባቸው ነው። ባለፉት ሃምሳ ዓመታት እነዚህ ሁለት ‹‹ታጋዮች›› የጋራ ጠላታችን ነው ብለው ያመኑትን (አማራን እና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን) በጋራ የሚዋጉ ቢሆንም የየራሳቸውን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ተመልሰው ሲገፋፉና ሲገዳደሉ ቆይተዋል ፡፡ ፖለቲካዊው እስላም ሲያይል እስልምናን በኦሮሚያ ውስጥ ለማስፋፋት የሚሠራ ሲሆን ‹‹ጥቁር ጀርመኖች ነን›› የሚሉት ሲያይሉ ደግሞ ፕሮቴስታንትን ለማስፋፋት ሲሠሩ ቆይተዋል፡፡ በዚህ መሐል ሳንካ የሆነባቸው የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ የሆነው ኦሮሞ ሲሆን እርሱን ለማጥፋት ባለመቻላቸው ሌላ ሃይማኖት አቀረቡለት፤ ‹‹የአባትህ ሃይማኖት›› የሚሉት ዋቄፋና! ይህንን ዋቄፋና መሬት ለማስያዝ የሃይማኖቱን ምንነት፣ ሥሪት፣ የአተገባበሩ ሥርዓት፣ በዚያ ውስጥ የሚነገሩ መነሻ ሚቶሎጂ (Mythology) ማዘጋጀት ግድ ይል ነበር፡፡ ይህንን ሲፈልጉ ቀድሞ በጀርመናውያን የተሠሩ ሚቶችን ወስዶ የማዋዋጥ (Adaptation)ሥራ መሥራት ነበረባቸው። ይህንንም በእነዚህ ሃምሳ ዓመታት ውስጥ ሠርተው ስላጠናቀቁ አሁን መንበረ ሥልጣኑን ሲቆጣጠሩ እንደ ናዚ ሁሉ ወደ ተግባር ለመቀየር እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡ የዚህን የኢሬቻ በዓል ለማከበር በሚደርግ ዝግጅት ዙሪያ የእምነቱ ምሁራን ነን የሚሉ ሰዎች፣ እድሉን በመጠቀም ኦርቶዶክስ ክርስትናን ለማጥቃት የሚተባበሩ የዉህብያ ሙስሊሞች ክፍተኛ ጸረ ኦርቶዶክስና አማራ፣ ግዕዝና ነባር ኢትዮጵያዊ ትርክቶች ላይ የከፈቱትን ጦርነት አድምቀው ታይተዋል። የኦሮሙማ ፕሮጀክት የሚባለውም በፓርቲ ደረጃ የኦሮሞ ነፃ ኦውጪ ግንባር (ኦንግ)፣ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲዊ ድርጅት (ኦሕዴድ)፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣ የእስላማዊ ኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (እኦነግ)፣ የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦብኮ)፣ የኦሮሞ ብሄራዊ ፓርቲ (ኦብፓ)፤ አባ ገዳ፣ ብልፅግና ወዘተ እየተባለ ስም ቢሰጠውም ዓላማው እና ግቡ አንድ የሆነ ፕሮጀክት በመሆኑ ‹‹ለኦሮሞ›› ተብሎ የተዘጋጀውን ማዕቀፍ የሚወክል ነው፡፡ ይህንንም እኔ ስም ሰጥቼው ሳይሆን ራሳቸው አሁን የሆነው እና እየሆነ ያለው የኦሮሙማ ፕሮጀክት መሆነን በጥናቶቻቸው ስለገለጹት ነው፡፡ ፕሮጀክቱ በተግባር የሚገለጸው ሐሰተኛ ትርክትን ማጠናከርና ክርስትናን፣ ኢትዮጵያዊ ዕሳቤዎችን አማራነትን በማጠለሸት ላይ ከማተኮር ጎን ለጎን ፓርቲዎች ጫካና ከተማ፣ ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ቢሆኑም በአንድነት ሁለገብ ጥቃት በመፈጽም የመንግሥትን ሥልጣን እንደ መጨርሻ እድል ተጠቅሞ ማጠናቀቅ የሚል ነው። በዚህ መሠረት በመደብኛ ወታደርና የክልል ታጣቂዎች፣ ጫካ ገብተው ንጹሐንን በኦርቶዶክሳዊ ሃይማኖታቸው እና በአማራዊ ማንነታቸው ሲጨፈጭፉ የነበሩት የብልጽግና መንግሥት «ሸኔ» የሚላቸው፣ እነርሱ ግን የኦሮሞ ነፃ አውጪ ሠራዊት «ኦነሠ» ናዚያዊ ውርስ በሚመስል ደረጃ እልቂት እያከናወኑ ነው። ከመንግሥት ጋር እንደሚሠሩ የሚጠቁመው ፍጅት እና ማፈናቀል ሲፈጽሙ ከነበሩት መካከል በእነ ጃል ሰኚ የሚመራው «የሰላም ትግል» በሚል የዳቦ ስም የብልጽግና መንግሥት ባለ ሥልጣናት ሆነው ጫካ ሆነው ማጥፋት ያልቻሉትን ሕዝብ በመንግሥታዊ ሥልጣን እንዲጨፈጭፉ አቅም ተገንብቶላቸው መገኘቱ ነው፡፡ የስው ልጅን በማንነት ልይቶ መጥላት፣ ማሳደድና መጨፍጨፍ የሚያስችል ስነ ልቦና ለመገንባት ጥምረት ከፈጥሩት 3 አስተምህሮዎች መካከል አንዱ ፖልቲካዊ ዋቂፈታና ገዳ የተባለው አስተሳስብ ነው። የዉህብያ ገዳና የጀርመን ናዚ ክርስትና እድሉት የሚጠቀሙ አጋሮች ናቸው። በናዚ የጀርመን ሃይማኖት እና በኦሮሙማው ፕሮጀክት የዋቄፋና ሃይማኖት መካከል ያለው የአስተምህሮ፣ የሥነ አምልኮ እና የርእዮተ ዓለም አንድነት በመጽሐፉ አዝጋጅ ጥናት እንደተረጋገጠው ከፍተኛ ዝምድና ብቻ ሳይሆን በሚሽነሪዎችና በኦነግ ፕሮፓጋንዳና አስተመሆሮ ከፍተኛ ተመሳሳይነት አሳይቷል። የናዚ እና ኦሮሙማ የአስተምህሮ አንድነት የሚያሳምኑ ማስረጃዎች ከታሪክ ሰንዶችና ከጥናቶች በተጨማሪ በብልጽግና/ኦሮሙማ መንግሥት እየተካሄድ የሚገኘው ተግባርም ምስክር ነው። በእንዚህ የሰንድና የተግባር ማስረጃዎች መሠረት የናዚ እና የኦሮሙማ ፕሮጀክት ዋቄፋና (ፖለቲካዊ ዋቄፋና) ሥሪት፣ ስለ ፈጣሪ እና ፍጡራን ያላቸው ርእዮት፣ ስለ ዶግማ እና ቀኖና ያላቸው አስተምህሮ፣ ስለ አምልኮ ቦታዎች ያላቸው ፍልስፍና፣ ስለ አማልክት መናፍስት ያላቸው ተመሳሳይነት፣ ስለ ካህናት፣ መሥዋትና በዓላት፣ ስለ ምሬትና አጥንት ያላቸው የአስተምህሮ በንጽጽር ተመዝነው አንድ አይነት ሆነው ተገኝተዋል። ለዩነቱ ያለው ናዚዎች ክርስትናን ለመቃወም ቅድመ ክርስትና የነበረውን ባዕድ አምልኮ መልክ በማስያዝ እና ትርጉም በመስጠት የናዚ ሃይማኖት ለመፍጠር እንደ ሞከሩት ሁሉ የኦሮሙማ ፕሮጀክት መሪዎችም በማንኛውም የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ውስጥ እንደሚገኘው በኦሮሞ ሕዝብ ውስጥ የሚገኘውን የባዕድ አምልኮ ተግባር ከናዚዎች አስተምህሮ የወረሱትን ቅርጽ እና ትርጉም በመስጠት ለማሥረጽ እየሞከሩ መሆኑን ልብ ማለት ይገባል እላለሁ፤ መልካም ንባብ፡፡ የኦሮሚያ መንግሥት በዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ፣ በሐመድ ሀሰን፣ በዓለማየሁ ኃይሌ እና በእነ ዶክተር ገመቹ መገርሳ የተተለመውን የኦሮሞ ታሪክ፣ ትውፊት፣ ባህል፣ እና ሃይማኖት መሬት ለማስያዝና ሕዝባዊ ለማድረግ ሲባል የኦሮሞ ባህልና እምነቶች ፖለቲካዊ መሣሪያነታቸው የጀርመን ናዚን መስመር ተከትሎ ወደ አሁናዊ እሬቻና ዋቂፈታ ጠባይን አስገኝቷል ። ‹‹የታሪክ ጥናት›› በሚል በየአካባቢው የሚገኙ አባ ገዳዎችን እና የሀገር ሽማግሌዎችን በመሰብሰብ ፖለቲካዊ ኦሮሙማንን መዋቅራዊ አድርገውታል። ይህንኑ መሠረተ ቢስ ናዚያዊ መንገድ ወደ ጽሑፍ የሚቀይሩ ተራኪዎችን በማደርጃት ተውልዱ ትርኩትንን እንደ እውነት እንዲወስደው፣ ፖልቲካው የሠራቸው አባገዳዎችም ይህንኑ እንዲያጠናክሩ ስምሪት ወስደዋል። ለዚህ ያልተመቹ አባገዳ በግድያ ተወግዷል። የኦሮሚያ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ የኦሮሞን ባህል፣ ታሪክ፣ ሃይማኖት እና እሴት በሚል የተፈጠረውን አዲስ የኦሮሙማ ፕሮጄክት በእቅድና በበጀት የሚያስፈጽም መዋቅር ነው። የዚህ መዋቅር መሠረታዊ ግብ የኦሮሞን ሕዝብ የአማራ፣ የኦርቶዶክስ ክርስትና፣ የኢትዮጵያዊነት ነባር ትርክት ጠላት አድርጎ መቅርጽና በዚያው ተግባራዊ እርምጃዎች ለሚወስደው የጸጥታ፣ የአስተዳደር፣ የንግድ፣ ይግብርናና የምነት ተቋማት አመቺ ሁኔታ መፍጠር ነው። አንዳንድ ግምገማዎች እንደሚያመለክቱት የፖለቲከኞቹ ዓላማ እና ግብ በአውሮፓ ሚሽነሪዎች (በተለይ በወለጋ እና አካባቢው የተሠሩ) እና በጀርመን አጥኚዎች በተሠራው መሠረት የአማራ ሕዝብ የኦሮሞ ጠላት፣ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ኦሮሞን የሰበረች ተቋም አድርጎ የማሳየት ጥረት በተወሰን ደርጃ በኦሮሞ ሽማግሌዎች እየከሸፈባቸው እንደ ልባቸው አላራምድ ብሎ መዘግይቱን እነድ ቁጭት በማንሳት አሁን ግን ፖልቲካዊ አባገዳዎችና አእምሮው የታጠበ ወጣት ለጥፋት መሰለፉ አካክሶታል ይላል። ግምገማውን ተከትሎ አዳዲስ የጥላቻ አቀጣጣይ ፕሮፓጋንዳ ሆኖ ተገኝቷል የሚሉተ፦ • ሚኒልክና ኦርቶዶክስ ያስቀሩብንን የኢሬቻ ቦታዎችን ማደስና መመሥረት በማለት አዳዲስ ቦታዎችንና ትርክቶችን መጨመር፣ ለምሳሌ ድኅረ ውድቀተ ደርግ ለመጀመሪያ ጊዜ በሆራ አርሰዲ (ቢሾፍቱ) በተከበረው የኢሬቻ በአል ላይ ንግግር ያደረጉት አባ ገዳ ‹‹ወደ ጥንቱ ሃይማኖታችን እንመለስ ካላችሁ እስልምናን ከመካከላችን አውጡ›› ብለው በመናገራቸው በአሉን ለማክበር የመጡ እንደነ ዋቆ ጉቱ እና ጃራ አባገዳ አኩርፈው መመለሳቸው ይታወቃል ፡፡ • እነርሱ የመጡት ‹‹ምኒልክ የጫነባቸው ሃይማኖት›› ኦርቶዶክስ ትጥፋ የሚል ቃል ለመስማት ቢሆንም ሽማግሌዎቹ ግን ‹‹ባህላችንን፣ ታሪካችንን፣ ማንነታችንን ያጠፋው እስልምና እንጂ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አይደለችም›› በሚለው አቋም በመምጣታቸው ከፖለቲከኞቹ ሐሳብ ተለይተዋል፡፡ • በአርሲ ውስጥ የ‹‹Harma Muraa›› fi ‹‹Harka Muraa›› (ጡት መቁረጥ እና እጅ መቁረጥ) ታሪክ ፈብርከው ሕዝቡ ውስጥ ለማሥረጽ ሕዝቡን በስታዲዮም ውስጥ ሰብስበው ሲሰብኩ አንድ በዕድሜ የገፉ እናት ‹‹እኔ ልናገር›› ብለው እጅ ሲያወጡ ፖለቲከኞቹ ሐሳባችንን ይደግፋሉ በማለት ዕድል በሰጧቸው ጊዜ አሮጊቷ ተነሥተው ‹‹ኧረ እየተናገራችሁ ያላችሁትን አስቡ! እኔ እዚሁ ተወልጄ አድጌ ያረጀሁ፤ የሁላችሁ እናት የምሆን አሮጊት ነኝ፡፡ አሁን እየተናገራችሁ ያላችሁት ታሪክ ውሸት ነው፡፡ ይኸው ጡቶቼም እጆቼም ደኅና ናቸው›› ብለው በመናገራቸው ዓላማቸውን አክሽፈውባቸዋል። የኦሮሚያ መንግሥት በየቦታው የሚሠሩት ሴራ በሽማግሌዎቹ እየከሸፈባቸው ስላስቸገራቸው ሽማግሌዎችን መቅረብ ያለበት በጥንቃቄ መሆን እንዳለበት ወሰነ፡፡ የኦሮሞን ‹‹ታሪክ›› አጥንቶ እንዲያቀርብ ኃላፊነት የተሰጠው የኦሮሚያ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ የታሪክ ጥናቱን ጨረስኩ ካለ በኋላ ግን ሽማግሌዎቹን እየፈሩ ከመኖር ‹‹የመጨረሻ መፍትሔ ነው›› ያለውን እርምጃ ወደ መውሰድ ተሸጋገረ፡፡ በየመድረኩ ሽማግሌዎች በተናገሩ ቁጥር ባለ ሥልጣናቱ እየተሸማቀቁ ከሚሄዱ ሽማግሌዎቹን ወደ ራሳቸው ሐሳብ ማምጣት የሚለውን ወጠነ፡፡ ከየወረዳው ታሪክ ያውቃሉ የተባሉትን ሽማግሌዎች ሰበሰበ፡፡ ለፖለቲከኞች ባደሩ አባ ገዳዎች ምክንያት ለሦስት ወራት ያህል እየቀለበ ‹‹የኦሮሞን ታሪክ ከሥር ከመሠረቱ›› አሠለጠነ፡፡ ታሪክ እንደዚህ አይልም ብለው የተከራከሩ ሽማግሌዎችን በሂስ እና ግለ ሂስ እያሸማቀቀ አንገት አስደፋቸው፡፡ በመጨረሻም የኦሮሞ ሽማግሌዎች ‹‹አንድ ታሪክ የሚናገሩ፤ አንድ ዋቃ የሚያመልኩ›› ሆኑ፡፡ ፖለቲከኞቹ ካስተማሯቸው ‹‹ታሪክ›› ውጪ ሌላ ታሪክ የሚናገር ሽማግሌ ከተገኘ ጸረ ኦሮሞ ተብሎ እንዲወገዝ ተበየነ፡፡ አባ ገዳ አመንሲሳን የገጠማቸው ይህ ነው፡፡ ከሦስት ወራት ‹‹ሥልጠና›› በኋላ የሚያውቁትን ሳይሆን የተነገራቸውን የሚናገሩ ሆኑ፡፡ ከዚህ ሥልጠና በፊት የሚናገሩት ታሪክ እና ከሥልጠናው በኋላ የሚናገሩት ‹‹ታሪክ›› የተለያየ ሆነ፡፡ የሚያውቃቸው ሰው ችግራቸውን ሳይረዳ ‹‹ኦቦ አመንሲሳ ነገር መርሳት ጀምረዋል›› ተባለባቸው፤ ጃጅተዋል ተባሉ፡፡ ይህ ኀዘን ላይ ጣላቸው፡፡ ስለዚህ ምንም ነገር ላለመናገር ወሰኑ፡፡ አገልግሎታቸውንም የተጣላውን በማስታረቅ ብቻ ላይ ገደቡት፡፡ ሕዝባዊ ስብሰባዎች እና መሰል ቦታዎች ላይ መገኘት አቆሙ፡፡ በዚህ ሁኔታ እያሉ ነበር ያገኘኋቸውና ይህንን ታሪክ የነገሩኝ፡፡ ጀርመኖች ቀድመው ‹‹ኦሮሞ ጥቁር ጀርመን ነው›› የሚል አቋም ይዘው ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሲሆን እነዚህ ሚሽነሪዎች ከኢትዮጵያ መንግሥት ፈቃድ ወስደው በምዕራቡ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ላይ እንቅስቃሴ ጀምረው ነበር፡፡ ትምህርት ቤት እና የጤና ተቋማትን በማቋቋም በትውልዱ ላይ ሥራ ጀምረው ትውልዱን ሊበክሉ ችለዋል፡፡ በፖለቲካዊ ኦሮሙማ መንግሥትነት መቆናጠጥ አምቺ ጊዜ ያግኘው ኦሮ-ዉሀቢዝም አንዳንድ ጽንፈኛ የሌሎች ማኅበረሰቦች ዑስታዞችን ከስልጤ፣ ከኦሮሞ፣ ከአማራ፣ እና ሌሎች በማቀናጀት ነባሩን እስልምና በተለይ ኦርቶዶክስ ክርስትናን፣ እንደ ማኅበረሰብ አማራን እና ሌሎች ነባርነት ያላቸው ባህሎችን ዒላማ በማድረግ በድብቅና ብኅቡዕ ሲያካሄድ የነበረውን ስውር ጥቃት አደባባይአውጥቶ በተቆጣጠራቸው የስልምና ምክር ቤቶችና መጅልስ በኩል ግልጽ አደረገው። ይህን ጥምርታቸውን ከፖልቲካዊ ኦሮሙማና የናዚ ፓርቲ ውልደትና እድገት ጋር በማያያዝ ሰፊ ጥናት ተደርጎ በመጠናቀቁ በምጽሐፍ መልክ በቅርቡ ሲታተም ሁሉም ለሕዝብ እና ምሁራን ክርክር ግልጽ ይሆናል። ከመጣው ጥፋት የምንድነው በፖልቲካዊ ትክክለኝነትና በአስመሳይነት ሳይሆን እውነቱን ስንጋፈጥና በፍቅር እውነቱን ስንነጋገር በቻ ነው። የኦሮ-ዉህቢዝም እና ተከታዩ በአማራ ማኅበረስብ፣ በስልጤ ማኅበረሰብ እና በሌሎች የጎሣ ፖልቲካ ተሰውሮ ለዓመታት ደም ሲያፈስ፣ ኢኪኖሚያዊ ግኑኝነት ሲያዛባ፣ ማኅበረ ስቦችን ሲከፋፍልና ጥርጣሬ ሲዘራ የኖረው ጽንፈኛው ዉሃብያ አሁን ተጋልጧል። የገዳን እና ፖልቲካዊ ኦሮሙማ ስትራተጂም በሚሠራው መንግሥታዊ ወንጀል ጭንብሉ ወልቋል። የሚቀረው የኢትዮጵያውያን ዜጎች በንቃት መተባበርና እነዚህ የጥፋት ተክሎች መንቀል ብቻ ነው። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ወደ ቀደመው መተማመን፣ ትብብር፣ ፍቅር፣ አንድነት ይምልስልን። ፋንታሁን ዋቄ/ መስከረም 26 ቀን 2018

አስተያየቶች

አካሄድ …ብሏል
ፀጋውን ይጨምርሎት መምህር፤ ስራዖት ፴ ፍሬ አፍርቷል ብዬ አምናለው። በመጪው ዘመን ፷ እና ፻ ፍሬ ያፈራል ብዬ አምናለው።

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

  ኦ ርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩ . ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡ በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያ...