ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

በኢትዮጵያ ለሚፈጸመው የዘር ማጥፋት ሂድተ በሕግ መጠየቅ የሚገባቸው አካላት

በኢትዮጵያ ሲካሄድ በነበረውና እየተካሄደ በሚገኘው ፖለቲካዊ፣ ሃይማኖታዊ ፣ ዘውጋዊ #የዘ*ር ማጥፋት ሂድት ለፍትሕ አደባባይ ቀርበው መጠየቅ የሚገባቸው አካላት ላይ ከወዲሁ በመወያየትና አቋም በመያዝ ለወደፊቱ ያዘጋጁትን የክፋ ጥቃት መከላከል ይቻላል።

ዘር አጥፊዎች በብዙኃን ጥላ ሥር የሚደበቁ ጥቂት አካላት በመሆናቸው ከጎሬአቸው አውጥተን ካጋለጥናቸው ሕዝብን እያታለሉ እርስ በርስ በማፋጀት ከደሙ ንጹሕ ነን ሊሉ አይችሉም. በመሆኑም እንደ እኔ ግምገማ የሚከተሉት በቀጥታ በመፈጸምና ሌሎች በተዘዋዋሪ በመተባበር ውይንን ተጽእኖ የማሳደር #ሃይማኖታዊ#ባህላዊ#ምሁራዊና #ዲፕሎማሳዊ አቅም እያላቸው በዝምታ በመተባበራቸው የወንጀሉ ተካፋዮች ናቸው ብዬ አምናለሁ። በዚህ ብያኔ መሠረት የሚከተሉትን ዘርዝሬዝለሁ። አናንተ ጨምሩበት ፦

የኢትዮጵያ እና የዓለም ሕዝብ ይወቀው!!


በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ለሚካሄደው፣ ምናልባትም ውደፊት ሊፈጠር ለሚችለው የሕዝብ መተላለቅ ተጠያቂዎቹ የሚከተሉት ኃይሎች በብቸኝነት እና በቅደም ተከተል ይሆናል፦
፩) አብይ አህመድ አሊ እና አማካሪዎቹ

፪) የሕወሃት መሥራቾችና እስከ መጨረሻው በአመራር፣ በትርክት ፈጠራና በወታደራዊ አመራር የሚገኙ

፫) የኦነግ መሥራቾችና እስከ መጨረሻው በአመራር፣ በትርክት ፈጠራና በወታደራዊ አመራር የሚገኙ

፬) የኦፒዲኦ ምሥራቾችና እስከ መጨረሻው በአመራር፣ በትርክት ፈጠራና በወታደራዊ አመራር የሚገኙ

፭) የኢሕአዴግ አባልና አጋር ፓርቲ አመራሮች

፮) የዉሀብያ ጽንፈኛ ዑስታዞች፣ የጥላቻ ትርክት አምራችና አከፋፋዮች

፯) የሕዝብን እልቂት በዝምታ ያስቀጠሉ ጳጳሳትና የመጅሊስ መሪዎች

፰) ዓለም ዐቀፍ ተሰሚነት ያላቸው በእልቁቱ ተቃውሞ ባለማሰማት
የተባበሩ ኢትዮጵያውያን ምሁራን እና የኪነ ጥበብ ሰዎች፣ ጋዜጥኞች

፱) ድምጽ በማሰማት ሕዝባቸውን ከጥፋት እንዲታቀብ ማድረግ የሚችሉ የተለያዩ ባህል መሪዎች፣ በተለይ የኦሮሞ አባ ገዳዎች፣ ሡልጣኖች፣ ዑጋዞችና ሌሎችም

፲) ባለፉት 50 ዓመታት በደኅንነት፣ በፍትሕና በጸጥታ መሥሪያቤቶች በኃላፊነት የነበሩ ባለሥልያናትና ከፍተኛ ባለሙያዎች የወንጀል እቅዶችን ባለማጋለጥ፣ ለፍትሕ ባለመቆምና በእልቂቱ በመተባበር
መጠየቅ አለባቸው።
ፍትሕ ሳይሰፍን፣ ጉዳተኞች ሳይካሱ፣ ጎጅዎች ሳይቀጡ ሰላም ወደ ኢትዮጵያ ሊመለስ አይችልም።

በምክክር ኮሚሽን፣ በድንብርና ማንነት ኮሚሽን፣ በሃይማኖት ትቋማት ጉባኤ እና በሌሎች የማታለያና ማደንዘዛ እንዘጭ እንቦጭ የአገዛዙ የሤራ መሸፈኛ ሰላምን አናገኝም።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

የሐሰት ትርክት ኦነጋውያንና የሕወሃታውያ የጋራ ስልት ከነግሥታት ወደ ተራ ግለሰቦች

✏️ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።  እርሱ ይመስገን። ምድራችንን #በደም #ያጨቀየው $ህሊና #የነሳን ፣ #ልቦናችንን #ያጨለመን ፣ #ሰብእናችንን ያዋረደው:- 👉 የሕወሐታውያንናንየኦነጋውያን የንዑስ ማንነት የጎሣ ፖለቲካ የደንቆሮ ርእዮትና፣ 👉 መርዛማን ጥላቻን ለ፶ ዘመናት ያከፋፈሉት የሐሰት ትርክት ናቸው። ✏️እንደ ዳግማዊ #ምንልክ ያሉ   ከዋክብት መሪዎች፣ እንደራሴቻቸው፣ ደጃዝማቾችና ቀኝና ግራ አዝማቾቻቸው  ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ብዙ ውለታ ውለውልናል:- 👉 በዘመነ ኦቶማንና አውሮፓ፣ በዘመነ መሳፍንት የተበታተነውን እና የተቆነጻጸለውን፣ ጎሠኛ የአርብቶ አደሮች  መሬት ፍለጋ  የደመሰሱትን ክርስቲያናዊ የግዕዝ/የነፃነት ሥልጣኔ አሻራ እንዲያገግም ደክመውልናል፤ 👉 የጥንት አገርን እና ሕዝቦችን   በከፊልም ቢሆን በመሰብሰብ  ጠንካራና ብቸኛ የነጭ ቅኝነትንና ባርነትን በመከላከል፣ ከኦቶማን ቱርክ ወር ትናንት ውስጥ ጥረኛ  አህመድ ግራኝ በመጋደል  ልዩ የነጻነት ማንነት ያላትን አገር ብበቸኝነት በዓለም ካርታንላይ አቆይተዋል፤ 👉 የሬማ ግዛት በጎሣ ተብልቶ ፲ ትንንሽ ሲሆን ከበበባውን ተቋቁማ በዝኃነታችን በተመጋጋቢ አንድነት ከ፹ በላይብቋንቋ፣ ከዓለም ትልልቅ እምነቶች ክትስትናን ፣ ይሁዲን፣ እስልምናን፣ የእረማውያንን ቅሪት የሆኑ የባህል እምነቶችን ሁሉን ይዛ በአውሮፓ በአርብ አምሳል ሳትሠራ ለእኛ አቀብዋል፤ 👉 ወያኔና ኦነግ፣ ገንጣዩ ሻዕብያ፣ ከሃዲው የማርክሲስት የአእምሮ  ባሪያን ስብስብ  እስኪፈትናት ድረስ ራሷን የቻለች አገር እንድንፈጥር ያስተባበሩን ነገስታት የተመሰገኑ ናቸው። አገር ሲያረጅ ጃርት ያብቅላል እንዱሉ: መል...