ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

የወደ ፊቷ ኢትይጵያ መሪዎች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

የወደ ፊቷ ኢትይጵያ  መሪዎች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች 

ሕዳር ፲፫ ቀን ፳፻፲፮ ዓ/ም


መግቢያ 


የውደ ፊቷ ኢትይጵያ የግድ የፍትሐዊት፥ ሰብአዊትና ታሪካዊት ሉዓላዊት   የፖለቲካ  ርእዮት፣ አስተዳደርና አመራር ያሟላቸ መሆን ይኖርባታል።  የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚህ ያነስ ሌላ አይነት ሀገር እንዲኖረው መፍቀድ አይኖርበትም።  በባእዳን ፖልቲካው ፍልስፍና ላይ የተመሠረቱ የጎሣ ማንነት ፖልቲካ፣ የቂምና የጥላቻ ትርክት፣ የምለያየትና ሕዝብን በአካባቢ ባሪያ አድርጎ የመንገሥ ጥባብ የሊሂቃን ፍላጎት በሚያስከትለው ግጭት፣ ስደት፣ ሞት፣ ድኽነት የደከመ ሕዝብ የተርጋጋና ሰላማዊ፣ ትስፋ ስጭና ለተውልድ የሚተርፍ ሁለገብ እድገት ጎዳና ውስጥ የሚያራምደው ጎዳና ምርጫው እንደሆን በሚያደረግው ተጋድሎ አሳይቷል። 


አገራችን ምንን አንኳ ከዓለም ሁሉ ተለይታ ያልተቆራረጠና ፈሪሃ እግዚአብሔር፥ ከሰብአዊ ክብር፥ ከፍትሐዊነትና ከአገር ልጆች እኩልነት የተለየ በተቃራኒው በጣዖት፥ በሰብአዊ ፍልስፍና እና ሐሰት ላይ የተመሠረተ የሰው ልጆችን የሚያበላልጥ፥ እልቂትና ወረራዎችን የሚፈጽም የፖለቲካ አስተዳደር አንደ ፋርስ ባቢሎን፥ እንደ ግሪክ፥ እንደሮምና የሩቅ ምሥራቅ፥ ወይንም በ18ኛ መቶ ክፍለዘመን አንደተወለደው ሰውን ዝንጀሮ አድርጎ ዓለምን የወረረው የአውሮፓ አስታሰብ ግራ ሳትጋባ ከኖኅ መርከብ ወርደው የሸው ልጆች ርስትን ከተከፋፈሉበት ዘመን አንስቶ ለ6000 ተውፊታዊ እና ለ3000 የተጻፈ ታሪክ መኖር የቻለች ብቸኛ አገር ናት።  የባቡሎን፥ የግሪክና የሮም ሥልጣኔዎች ረዥሙ መቆየት የቻለው 600 ዓመታት ብቻ ነበር።


ይሁን እንጂ አገራችን በዓለም ውስጥ አንደ መገኘቷ  ከውጭ በመጣባት ተጽእኖ የተለያዩ ባህሎችን፥ እምነቶችን፥ ሥርዓተ ፖለቲካንና በቀጥታ በኃይል በሚደረጉ ወረራዎች፥ ከ1940ዎቹ ወዲህ በትምህርት ስም በሚመጣ የአእምሮ አጠባ ናበር ማንነቷን በማሥበራዊ፥ በፖለቲካዊ፥ በስነ መንግሥትና በፍልስፍና ደረጃ እያጣች መጥታ በመጨረሻም በአምላክ የለሽ የማርክሲስት አስተምህሮ በውጭ-ገብ የባእዳን ትምህርት በሠለጠኑ ልጆቿ ማምነቷን ሙሉ በሙሉ ተነጥቃለች።


የኢትያጵያ ረዥም ታሪካዊ ሂደቷን ያገናዘበ፥ በፈሪሃ እግዚአብሔርና በትወፊት ላይ የተመሠረተ ሥርዓተ  መንግሥት እና ሥርዓተ ማኅበር፥  የሰው ልጆች ፍጹም እኩልነትና የአገር ሙሉ ባለቤትነት ወደ ሊመለስ የሚችለው አገሪቷን ለመምራት ወደ ሥልጣን እና የፖለቲካዊ አስተዳደር ኃላፊነት የሚወስዱ ዜጎች ስነ ልቦናዊ ውቅር፥ ነፅሮተ ዓለም፥ እምነትና ባህል ተጠቃሎ በውጭ-ገብነት የአገር ሥርዓተ ትምህርት ይዘት አካል በመሆን ልሂቅ ወይንም ምሁር በሚያሰኝ ደረጃ ከሚያስገኘው በላይና ዳኛ እንደሆነ የሚያምን፥ እንደተለመደው “ሳይማር ያስተማረን ሕዝባችን” እያለ ራሱን በመኮፈስ ነባር እና አገር-ፈለቅ አውቀቶችን፥ ማሥበራዊና መንፈሳዊ መዋቅራትን፥ የሕዝብ አሠፋፈርና አኗኗርን፥ የአስተዳደርና የፍትሕ ሥርዓትን ሁሉ አንድ ሕንፃ ውስጥና በየዩኒቨርሲቲው ተሰብስቦ በመቀየር ወይንም በመዋስ በሕዝቡ ላይ ለማጫን የማይሞክር መሆን ይኖርበታል። 


ወደ ፖለቲካ ሥልጣን የሚመጣ ማንኛውም ዜጋ የአካባቢንና የአገርን አጠቃላይ ነባር ባህሎች፥ እምነቶች፥ ማኅበራዊና መንፈሰዊ መዋቅራት፥ የአስተዳደርና የፍትሕ ሥርዓቶች አክብሮ ለማጎልበት፥ ከውጭ የተማረውን እንደተጨማሪ እንጂ አሁን ለጥፋት እንዳበቁን ፖለቲከኞች ሕዝብን በአፈና ይዞና የራሱን ብቻ የሚጭን ነቅሎ-ተከል መሆንን የሚያወግዝ መሆን ይኖርበታል። ወደ ፖለቲካው ሥልጣን የሚመጡ ዜጎቻችን ፀረ አምልኮተ-እግዚአብሔር፥ ፀረ-ታሪክ፥ ፀረ-ነባርነትና ፀረ-ኢትዮጵያ አቋም ሲያራምዱ ከኖሩ ወይንም ከሚገኙ ስብስቦችና የፖለቲካ ተቋማት ጋር ምንም አይነት ተሳትፎና ወዳጅነት የሌለው፥ የእነዚህንም አካላት ማንነትና ምንነት ጠንቅቆ የሚያውቅ መሆን ይገበዋል።


በአጠቃላይ አሁን የምንገኝበት በቅድሚያ አማራን በዋናነት ህልውናውን ማረጋገጥ፥ ቀጥሎ የብዙኃን ባህል፥ ቋንቋ፥ እመነት፥ ማኅበራዊ አደረጃጀት፥ የአካበቢ ንዑስ ታሪክና ማንነት ያላቸው የአንድ ቤተሰብ የኢትዮጵያ ልጆች መኖሩያ የሆነችዋን ታሪካዊት አገር ከጠባብ፥ ሤረኛና ዘረኛ የጎሣ ሥርዓት በማዳን ሉዓላዊነቷ የተከበረ፥ ታላቅና አንዲት፥ ለሁሉም እኩል እናት የሆነች አገርን ከአደጋ ለማዳን  የሚከተሉትን መሥፈርቶች ከግምት ውስጥ በማስገባት የፖለቲካ መሪዎችን በመለየት መቀበል ወይንም ከተሳትፎ ማገድ አስፈላጊ ነው። ይህም መሥፈርት በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ወጣት ዘንድ የታወቀ፥ የተረዳና እንደ ማጣሪያ የሚገለገሉበት መሣሪያ እንዲሆን በሰፊው ማስተዋወቅ አግባብነት ይኖረዋል።


መሥፈርት

ለፖለቲካዊ የሥልጣን የሚያሳጭ ጠቅላላ መሥፍርት

ፈጽሞ በሚመጣው የፖለቲካ ሕይወት ውስጥ

  1. በሕወሐት፥ በኦነግ፥ በብአዴን እና በዘረኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ተሳትፎ ያልነበረው

  1. የዘረኝነትና የቆጠኝነት ዝንባሌ ያለውና ሰፊውን የአማራም ሆነ የሌሎች ማኅበረሰቦች እኩልነትና ባለአገርነት አሳንሶ የሚመለከት

  1. ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው፥ በአገራችን ሥርዓት መሠረት የባህልና የሃይማኖት፥ የእድሜና የአገር-ፈለቅ ዕውቀት ያከበራቸውን በተግባር የሚያከብርና ለአገር አስተዳደርና የየፍትሕ ሥርዓት ያላቸውን ፋይዳ የሚቀበል

  1. በአምላክ የለሽ የማርክሲስትና የዘረኛ ነፃአውጭዎች ፖለተሊካ ተሳትፎ የነበረው

  1. በኢትዮጵያ የግዛት አንድነት ጽኑ እምነት ያለው፥ በንግግርና በድርጊትም በጽሑፍም ይሁን በውይይት ይህን የሚያንፀባርቁ

  1. አገርን ከአካባቢ አሳንሶ መለያየትን የሚዘራ፥ የሰው ልጅ መበላለጥና መለያየትን የሚሰብክ

  1. ሁሉም ኢትዮጵያውያን እኩልነት የሚያምን

  1. የሁሉም ኢትዮጵያዊ በአገሩ ሙሉ ባለቤትነት፥ የኢትዮጵያዊነቱን ታሪክ ከብዝኃ ትርክቶች ጋር በእውነተኛ ምንጭና ከዘር ፖለቲካ ውጭ  አስታርቆ ለመኖር ቁርጠኛ የሆነ

  1. እውነተኛ ታሪኮችን ለወገንተኛ ፖለቲካዊ ግብ ሲባል በሐሰት ትርክት የሚበክል ወይንም ተበከለውን የሚያሰራጭ፥ ስለ እውነት የማይሟገት

  1. የብሔር ክልል፥ የእሔረሰብ ድንበር፥ የብሔረሰብ የፖለቲካ ሥልጣንን  ፈጽሞ  የሚጸየፍና ጎሣዎች ከፖለቲካ ውጭ ሁሉንም ልዩ ጸጋዎቻቸውን ማልማትና መጠበቅ ይችላሉ ብሎ የሚያምን 

  1. በብሔር ፖለቲካ፥ በብሔር ክልል፥ በብሔር አሰላለፍ ሥልጣን የመከፋፈል ልማድ ለሕዝብና ለአገር አንድንት ጠንቅ ነው ብሎ ያማያምንና የማይታገለው

  1. በአገር ውስጥ የፖለቲካ ሹመትም ይሁን የሕዝብ መሪነት በእውቀት መደራጀት እንዳለበት የሚያመንና እውቀት ውጭ-ገብና በድግሪ ብቻ የሚደረስበት አለመሆኑን የተረዳ 

  1. እውቀት ከውጭ ብቻ የሚገኝና በኢትዮጵያ ውስጥ በቅሎ የማያውቅ አድርጎ ዘመናውያን ምሁራንን በጭፍን የሚከተል

  1. በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁሉ ልዩነታቸው ከ1-7 ያለውን አክብረው ሌሎች ልዩነቶቻቸውን ይዘው በመፋጨት አመራጭ የሚያቀርቡ እንደሆነ የሚያምንና የሚሠራ

  1. በኢትዮጵያዊነት፥ በሰብአዊነት፥ በፍትህ፥ በአገር ሉዓላዊነት፥ በሕዝብ አንድነትና እኩልነት ላይ ጥያቄ የሚያነሳ 

  1. እምነቶችና ባህሎች በአገራቸው እኩል የሆኑ ማንነቶች ሲሆኑ በአገር ደረጃ በቦታና በሁኔታ ምንም አይነት ጫና ሳይኖርባቸው መኖር ይችላሉ።  

  1. ሰዎችን በማንኛውም ንዑስ ማነነት የሚፈርጅ


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

  ኦ ርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩ . ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡ በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያ...