#ፋኖነትን ከሽፍጠኝነትና ከሤራ ጋር ማን አጋባው?
የዚህ በሽታ ተጠቂዎች በአመራር፣ በማኅበራዊ ሚዲያ፣ በማካሪነት እንዴት ተሰለፉ? ማንስ ላካቸው?
---- የታጋዮች መስዋዕትነትን ከሚያረክሱ ተላላኪዎች ትግሉን ጠብቁ!በጭፍን ተከታይነትና በጎጠኝነት፣ በምላስ መውለብለብ አትታለሉ!!!
ፋኖነትን ወድ ተራ ሽፍትነት የሚያወርዱ አእምሮዎች ከጎንደር መብቀላቸው አማራም፣ ኢትዮጵያም ገና ብዙ መከራ እንደሚጠብቃቸው ይጠቁማል።
ራሱን ደብቆ #Amanuel Z Gonder እያለ ቆሻሻውን ዕውቀትና መርጃ አስመስሎ እንዲያቀርብ ቡድን የተደራጀለትን አንድ ድውይ ሰው መንሻ አድርጌ መናገር ፈለጉሁ። ይህን እና መሳዩን ሰውና የኼ ነው የብሻሌ ራሱን የሚባሉ ሰዎችን ኑና በአደባባይ ሕዝብ እየሰማን እንከራክር ብላቸው አሻፈረኝ ብለው በሥርቻ ውስጥ ተወሽቀው የአማራን ሕዝብ የህልውና ትግል ብቻ ሳይሆን መሠረታዊ የእውነተኝነት፣ የሰባዊ ክብር፣ የካህንና የእምነት አባቶችን ማክበር፣ ወንድማማቾች መካክለ ጥል አለመዝራት፣ ዋሽቶ ማስታርቅ እንጂ ሐሰት አምርቶ አለማጋጨት የመሳሰሉትን ሁሉ የሚጎዱ መልእክቶችን በጭፍን ለሚከተላቸው፣ ከማገናዝብ ይልቅ ማዳነቅ ብቻ ለለመደው የኳስ ተመልካች ዘመን መንጋ ይመግቡታል። ምግቡ የመረዛቸው እንደ እቃ እየታዘዙ ከትግሉ ዓላማ በተቃራቂ እርስብርስ ይጠፋፋሉ።
የአማራን ሕዝብ የህልውና አደጋ ላይ የጣለው የኼው #ሕወሃትና #ኦነግ በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ተላላኪነት ሲደርሱትና ሲረጩት የኖሩት የሐሰት ትርክት፣ ቁማርተኝነትና ሕዝብን አሳስቶ የማፋጀት አባዜ ነው።
#አማኗኤል ዘ ጎንደርና መሳዮቹ የዚሁ እንዋጋዋለን የሚሉት ቡድን ቀጥትኛ ነጸብራቅ ናቸው።
በፋኖ መካከል #ፋኖነትን ወደ #ሽፍትነት የሚዘቅጥ መንገድ በመያዝ የትግል መነሻቸውን ሕስት፣ ሤራና ማጋጨት መዳርሻዊን መለያየትና ሕዝብ መካክለ ጠላትነት መፍጠር እንዳደረጉት መቅሰፍቶች እንደ ሕወሃትና ኦነግ በሐሰት ፍብረካና ግጭት ፋኖን ከፋሎና በትኖ ለመምራት የሚሞክሩ ሰዎች አሉ። እንዲህ አይነት ድውያን "ፋኖ" በሚለው ታላቅ የልዕለ ሰብእ ማንጸሪያና የነጻነት ጎዳና ላይ እንድ ጭለማ ውስጥ እንቅፋት መገኘታቸው እጅግ እጅግ አሳፋሪ ነው።
ፋኖ ተኳሽ ብቻ ሳይሆን "ቀዳሽ" ነው የሚባልበትን መሠረታዊ ፍልስፍናና እሤት የደፈጠጡ ሰበናዎች ናቸው። እነዚህ ርካሽ እና በተቀሰፉ አእምሮዎች የሚረጩት መርዝና እያለማመዱ የሚገኙት ክፉ ባህል የህልውና ተጋድሎው ተጻራሪ በቻ ሳይሆን ለወደፊቱ ተውልድ ቅድስናም፣ ለመኀበረስቦች መተማመንም እንቅፋት የሚሆን ባህል ማንበር ስለሚሆን በማንኛዉም ጽኑ ቋንቋ መወግዝ ያለበት ርኩስ ነግር ነው።
#ፋኖ #ቀዳሽ ነው ማለት ቄስ ውይንም ቅዳሴ የሚቀድስ ማለት አይደለም። ምሥጢሩ ያለው ፋኖ መመሪያው ፈሪሃ እግዚአብሔርና ክብር-ሰብእ በመሆኑ በጦርነት መካከል እንኳ #ጠላት የሚለው የሰውን ፍጥረት በቁሙ ሳይሆን የሰውን ፍጥረት አእምሮ አጥበውና አደንቁረው፣ በትርክትና በስሑት ርእዮት አጨለመው የሚያዘምቱ ተቋማትና አስተሳሰቦቻቸውን ነው። ፊት ለፊቱ ስይፍ ይዞ የመጣውን ገዳይ እጁን ባይሰነዝር ማርኮ እንደ ሰው አክብሮ ወደ መጣበት የመልሰዋል፤ ነገርግን ሰይፍ ከሰነዘረ እጁን፣ እምቢኝ ካል አንገቱን ይቆርጠዋል። ከሞተ በኃላ እያለቀስ ይቀብረዋል። ሬሳ ስይጎትትም፣ ስየስልብም፣ ሞራውን አውጥቶ አይጠንቁልበትም፣ አንገት ገዝግዞ ምርኮኛ አያርደም፣ መኪና አይነዳበትም፣ ገድል አይጨምርም፣ በሣት አያቃጥለዉም።
#ቀዳሽ ነው ማለት በትጋድሎ ውስጥ ርኩሰትን፣ ኃጢአትንም ውሸትን፣ ክህደትን፣ ዝሙትን፣ ዘርፋን፣ አፈናን፣ ማንገላታትን አይቀላቅልም እና የተቀደሰ ተጋድሎ በመፈጸም ሕዝብን እና ትውልድን እሤቶቻቸው ሳይረክሱ እንዲቀጥሉ መስዋዕት ይሆናል ማለት ነው።
ግና እነዚህ ከጎንደርና ከጎጃም እንደተግኙ አድርገው የሚጽፉና እድፎች የመፈጠራቸው ዋና ምክንያት (እንደ እኔ አስተሳስብ) በሚከትሉት ምክንያቶች ይመሰለኛል፦
1) ናርሲሲስት (የበዛ ራስ ወዳድነት፣ ማን እኽሎኝነት፣ ስግብግብነት፣ ቁማረተኝነትና አጭበራባሪነት) ግለሰቦች በመሆናቸው በዙሪያቸው የሚገኙ በዕውቀት፣ በሕዝብ ተቀባይነት፣ በእምነት ጽናት፣ በርእይና ዓላማ ግለጸኝነት #ኃያላን የሚመስሏቸውን ታጋዮች በማሳነስ ራሳቸውን ደማቅ ኮከብ አድርጎ በሌላቸው ወይንም ከአላቸው የብርሃን ጸጋ በላይ በቁማርና በፕሮፓጋንዳ #ለማብልጭለጭ ሲሹ በሚያደርጉት መውራጭት በእውነትኞች ወገኖቻቸው ላይ የሚረጩት ጭቃ ነው።
2) ከህልውና ትግሉ ዋና ዓላማ ውጭ የጥቂት ቡድኖች ድብቅ ፍላጎት እንዲሣካ ተለእኮ በመቀበል ለትግሉ መሳካት ወሳኝ ሚና ይኖራቸዋል ብለው የሚያምኑትን ቡድን ወይንም ግለ-ስብእ የስብእና-ገደላ (character assassinarion) የሚፈጽሙ የህሊና ሙታን፣ ፈሪሃ እግዚአብሔር የተለያቸውና በጭንቅላት አስልተው ሲያበቁ ልቦናን ደፍጥጠው ሆድ ላይ የሚያበቁ ውዱቃን ናቸው፡፡
3) ሕዝብ ያወቀው፣ ንስሐ ያልገቡበት ወንጀል፣ ረኩስት፣ ነውር፣ ሌብነት የሚያስጨንቃቸው፣ ነገር ግን ለመተለቅና ለመክበር ሲሹ ክፍ ብሎ የሚታያቸውን ሁሉ በሕሰተኛ ምላሳቸው አቆሽሸው ከእነርሱ በታች በማውርድ በመታይት የፋኖ ታጋዩና ያማራ ሕዝብ እንደ አምራጭ እንዲቆጥራቸው የሚጋጋጡ ውዱቃን ናቸው፡፡
4) የሚያውቁ የሚመስላቸው፣ አለማወቃቸውን ከትህትና ደርጃ አድርሶ አለማወቃቸውን የሚያሳውቃቸእው የእውቀት እርሾ ያጡ ደናቁርት፣ ነገር ግን በዘምናዊም ይሁን በቤተ ክህነት ትምህርት እንደ ኮምፒዩተር የቅዱባቸውን እያስታወሱ የትምህርት ክፍተኛ ድርጃ ማዕረግ የተቆናጠጡ፣ ዕውቅትን እንደ ማገናዘቢያ ሳይሆን እንደ እምነት የዘው ቆመው የቀሩ ተዕቢተኞች ወደ ሤረኝነት ሲያዘቅጡ የሚሠሩት ሥራ ነው።
5) እጅግ ጭካኝ፣ ምህረት የሊላቸው፣ ለላካቸውና ላለሙት ግል-ተኮር ግባቸው መላው የአማራ ሕዝብ፣ የፋኖ ሠራዊት፣ ኢትዮጵያ፣ ቤተ ክርስቲያን ሁሉ ቢሰዉ ግድ የሌለው ግለኝነት ያሳወራቸው።
ፋኖነት ተኳሽነቱን ብቻ ከያዘ ነፍሰ ግዳይ አራዊት ይሆናል። ቀዳሽነቱን ብቻ ከያዘ የአረመኔዎች መጫውቻ እንጂ እውነትን የሚመስክርበት ሀገር ያጣል፣ አራሽ ብቻም ከሆነ የሆድ ባሪያ እንስሳ፣ አገር አልባ ባሪያ ይሆናል።
የፋኖነት ሚዛኑ በቅደም ተከተል #ቀዳሽ፣ #አራሽ፣ #ተኳሽ ነው።
#በቀዳሽነቱ በቅድስና፣ በስብአዊነት፣ በእውነትና በፍትሕ ይቆማል፣ ዕውቀት፣ ጠበብ፣ ተውልዳዊ ርእይና ወድፊትን የተነብያል፣ እግዚአብሒረን በሕይውቱ በምግባር ይገልጻል፤
#በአራሽነቱ የሠራል፣ ያመርታል፣ ይረዳል፣ ከጥገኝነት ነጻ ሆኖ ይኖራል፣ ርስት ያስከብራል፤
#በተኳሽ ነቱ ቀዳሽነቱንና አራሽነቱን የሚግልጽበትን ርስት፣ ሀገር፣ ማኅበራዊ ሥሪት፣ ስነ መንግሥትና ተቋማትን እስከን አስተምህሮዎቻቸውና ታሪኮቻቸው ለማጥፋት የሚንቀሳቀስን የውስጥና የውጭ ጠላት የቀጣል።
#Amanuel Z Gondar እና #ይኼነው #የብሻሌው የመሳሰሉት ሰዎች እና የላኪዎቻቸው ስበና የፋኖነት መገልጫ መሠርቶችን የናደ፣ የዳኔል ክብረትና የአብይ አህመድ፣ የሕወሃትና የኦነግ የሽፍጥና የክህደት መንፈስ ምርኮኞች ናቸው። እነዚህ የአማራ ሕዝብ የህልውና እንቅፋቶችን ጭፍን መንጋ ተከታዮቻቸው ሊገንዘቡና ሊገስጿቸው በተገባ ነበር። ምን ያደርጋል ማጨብጭብ እንጂ መመርመር ርቆናል።
እኔ ግን የበኩሌን መወጣቱን እቀጥላለው።
ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።። 1) ሻሸመኔ ከተማ I. የተገደሉ 1. አያሌው ተረፈ ● በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ● ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ● በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ● በ ጥር 30 2015 ዓ/ም ሰማዕትነትን ተቀብሏል 2. ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ● የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ● በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ● ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ● በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም ሰማዕትነትን ተቀብለዋል። 3. ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ● የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...
አስተያየቶች