ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

አጥፊዎቻችንና ቤታችን ውስጥ የሚኖሩ ረዳቶቻቸው

የውጭ #አጥፊ*ዎቻችንና ቤታችን ውስጥ የሚኖሩ ረዳቶቻቸው

በአገራችን የሚካሄደው መንግሥታዊ የሃይማኖትና የቋንቋ ዘውግን የተከተለ ሁለገብ ዘ*ር የማጥፋት ተግባር አቅም ያገኘው በሚከትሉት አካላት ነው፡-
1) ኃላፊነት የጎደላቸው፣ ፈሪሃ እግዚአብሔር የተለያቸው የእምነት፣ የባህል፣ የምሁርነት ከፍታ እና ተሰሚነት እያላቸው እረኝነታቸውን ለግል ጥቅማቸው ባዋሉ አድርባዮች ምክንያት አጥፊው በረታ፣ ጠፊው ተበታትኖና ፈዝዞ እስኪጠፋ ጥቃት ሥር ይቀጥላል፤

2) ክርስቲያን #ጨውና #ብርሃን የመሆን ግዴታ ያለበት የሰማዕትነት እና በምሥጢራት በኩል ክርስቶስን የመምሰል ሕይወት መሆኑ በመዘንጋት፤ በሰንበትና በበዓላት ከሥራ ድካም ማረፊያ መዝናኛ ወይንም ቴራፒ እንደሆነ የምንቆጥር፣ እንደ ቃየል "እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን" በሚል ትዕቢትና በኃጢአት የመጽናት መንፈስ ተጸናወትን እኛ ነጭ ለብሰን የወገኖቻችን መከራ መካከል እና በደማቸው ላይ ቆመን ምንም እንዳልተፈጠር የምንዘምር፣ ከንስሐ በመራቅ ለሰማእትነት ጀርባችንን የሰጠን አድርባይ ምእመናን መብዛታችን ለአጥፊዎች እንደ ልባቸው እንዲጋልቡ እድል ሰጠናቸው፤

3) በአዘናጊና አደንዛዥ አባቶች፣ ሰባኪያን፣ የመንፈሳዊ አገልግሎት ጸጋቸውን ወደ ገቢ ምንጭነት የቀይሩ አገልጋዮች፣ --- አዘናጊነት
--- ብዙኃን ሳለን አናሳ፣ እውነትኞችና ታሪካውያን ሳለን የምንነወር፣ አገር ሠርተን ከአጥፎዎቻችን የአምልኮ መፈጸሚያ ቦታ የምንለምን፣ ሕግን ለዓለም ሰጥተን ያለ ሕግ በየዕለቱ የምንገደል ሆነናል።

#መፍተሔ -መነሻ ሀሳብ

የቤተ ክርስቲያንና የአገርን #ትንሳኤ የሚሻ ሁሉ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድና እንደ አቅሙ ከቀላል ወደ ከባድ የሚያድግ አገልግሎት መጀመር፦

1) ክርስቲያናዊ ኃላፊነታችን ደምቆ እንዲታየን፣ እንድናፈቅረው እና ለመወጣት ኃይል ከአምላካችን ለመቀበል እንችል ዘንድ ንስሐ መግባት፣ በጾም በጸሎት መበርታት፤

2) እንደየጸጋችን በምንችለው ሁሉ ወጎኖቻችንን በሁሉም ዘርፍ መርዳት፣

3) እንደየ አቅማችን ከቤተ ስብ፣ ከቅርብ ወዳጆች ብሎም በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እና በምንሳተፍበት መንፈሳዊ ማኅበር ደረጃ የአገራዊ ፖለቲካው ነባር-ጠልነቱ የሚገልጽባቸውን ንግግሮች፣ ፖሊሲዎች፣ ትምህርቶች፣ ድርጊቶችና በአጠቃላይ ዘ*ር የማጥፋት የሚከተላቸውን ስልቶች፣ ሊመጣ ያለውን የከፋ ጥፋት በማስረዳት ግንዛቤ መፍጠር፤ መፍትሔዎቻቸው ላይ መወያይት፤

4) በቤታችን፣ በሠፈራችን፣ በቤተ ክርስቲያናች ውስጥ የተሰገሰገውን አባትና አገልጋይ መሳይ የአጥፊዎቻችን መሣሪያ በመሆን አንድነታችንን የሚከፋፍሉ፣ በአዘናጊ አጀንዳ ለሞትና ለስደት አሰልፈው በመፍዘዝ እንድንጠብቅ ተልእኮ ተቀብለው የሚሠሩ ህሊና ቢሶችን ከእውነተኞቹ አባቶችና አገልጋዮች በጥንቃቄ፣ በማስረጃና በቀኖና ሚዛን እየለዩ መገሰጽ፣ በሚሰጣቸው ጊዜ ገደብ የማይስተካከሉትን ማጋለጥ፣ ከዚያም በግልጽ መቃወም፤

5) ራስን ከጥፋት ለመከላከል የሚያስችሉ ዝግጅቶችን ሁሉ ማድረግ፣

6) የአጥፊዎቻችንን ሚዲያዎች፣ ፕሮፓጋንዳዎች በእውነተኛ ማስረጃ፣ በእውነተኛ ትርክት፣ በስብአዊ ክብርና በፍትሕ መሠረትነት በሚመራ ፖልቲካ ሙጉት ማጋለጥና ተከታይ ማሳጣት፣

7) በሐሰተኛ ትርክትና በስሑት ርእዮት ተመርዞ ጥፋት እየፈጸመ ያለውን የምንግሥት መዋቅር፣ ሠራዊት፣ ፖሊስ፣ የድኅንነትና የጸጥታ መዋቅር የዕለት ዕለት በደሎችና ድርጊቶችን እየመዘገቡ በየዕለቱ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በተለያዩ ቋንቋዎች ማስቀመጥ፣

8) የሐሰት ትርከትና የጥላቻ መልእክቶችን እግር በእግር እየተከተሉ መሚገት፣ ማጋለጥና ለምን ግብ እንደሚነገሩ፣ ዋና ባለቤቱ ማን እንደሆን በመጥቀስ በማህበራዎ ሚዲያ ማሰራጨት

9) --- ሌሎች ፈጠራ የታከለባቸው አጥፊዎቻችንን የሚገቱ እቅዶችን አቅዶ መተግበር።

ተኝቶ መዳን የለም!

ሁሉን ቻይ ቸር አምላክ እኢየሱስ ከርስቶስ እንኳ በፍርድ ቀን በጋራን ቀኝ የሚቆሙትን የሚለየው በሥራቸው ነው። ሠርቶ ለተቸገሩት መልካም ያደረጉትን የአባቴ ብሩካ ሲላቸው -- ሰንፎችን ከእኔ ወግዱ ይላቸዋል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

  ኦ ርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩ . ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡ በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያ...