የገዳዩንስ አውቀን እድረናል። እረኛ ተሰኝቶ የአስገዳይ ሆኖ መገኘት ይባስ!! ብለን ከምንተኛ መፍትሄ እንጠቋቆም።
==============
ይህ እኮ እልቂት አይገርምም። እነርሱ የተስማሙበት ዘር የማጥፋት ፕሮጀክት ነው!!! እኛ ነን እንጂ "ሶፍት አቀብሏቸው" በሚሉን ነፍሰ ገዳይ መሪዎች ፰ ዓመት ሙሉ እያለቀስን "ድረስልን" የምንለው።
============
እስቲ የውጭውን አቆይተን የውስጡን እረኛ ተብዬ እንጠይቅ!!!
ዘወትር ከሞት የተረፍነውንና ወረፋ የምንጠብቀውን የጥምቀት ልጆች በከተማና በውጭ አገር ሰብስበው :+
! ምእመናንን! ወላችሁ፣ ድምጻችሁ አይሰማም፣ አመስግኑ!! እሪሪሪሪሪ!!!
! እልል በሉ
! አጨብጭቡ
! እንኳን ደስ ያላችሁ
! አባታችንን የሰጠን እርሱን አንዴ ሞቅ አድርጋችሁ አመስግኑ
! እጃችሁን ወደ ኪሳችሁ አግቡና ጣል ጣል
! በረከት ከቤት ይቆያችኋል ስጡ
! ዘምሩ ! ሞቅ ሞቅ !
!
ጳጳሱ መጡ! ጌታ እንዳስተማረን ዘምሩ ---
“ወኵሉ ዘዚኣየ ዚኣከ ውእቱ ወዘዚኣከኒ ዚኣየ ውእቱ ወተሰባሕኩ ቦሙ። ወኢይሄሉ እንከ ውስተ ዓለም ወእሙንቱሰ ውስተ ዓለም ይሄልዉ ወአንሰ ኀቤከ እመጽእ። #ኦ #አባ #ቅዱስ #ዕቀቦሙ በስምከ ለእለ ወሀብከኒ ከመ #ይኩኑ #አሐደ #ብነ #ከማነ።" (እኔና አንተ አንድ እንደሆን አንድ ይሁኑ)
(ዮሐ:፲፯:፲-፲፩
--- ያለውን የሰበኩንና የዘመርንለት ጳጳስ ዞር ብሎ ምነውሳ #በዘር እና #በጎጥ እየተካፈለን መበተኑን ለ፴ ዓመት አለማምዶን ይባስ ብሎ በዘመነ ብልጽግና ላይ #አስክሬናችን #እንዳይቆጠር አለ?
ይህ ነገር ገብቷችኋል?
=================
ነፍሳት በክህደት ነፍሳቸው ስትነጠቅ፣ የጥምቀት ልጅ ያለ እረፍት ከበደኖ እስከ ማይካድራና አክሱም በጎሣና ጽንፈኛ የጂሃድ አውሬ፣ በሕወሃት ሤራ፣ በኦነጋዊው ብልጽግና ትብብር በሥጋ ሞት ሲያልቅ ---- የበለጠ ቀጣይ የእልቂት ድግስ እንደአለ በብልጽግና ባለሥልጣናት ቅስቀሳ ሲካሄድና "የያዛችሁትን #ዱላ ወደ #በክላሽ ቀይረን ለጭፍጨፋ እናሠማራችኋለን" እያሉ በአደባባይ ሲሰበክ፤ አብይ በፓርላማው በወደብ ስም ክርስቲያኖችን ለማስጨረስ ሲያውጅ ----
ስለምን ----
በአንድም ተቋም ውስጥ የሰው መከራን ለማስቆም አጀንዳ የጠፋው?
ለምን "ባልታወቁ ታጣቂዎች" ብለው የሚዘግቡ የቤተ ክህነት ጋዜጠኞችና ትዕዛዝ ሰጭ አባቶች በረከቱ?
=======
ከሁሉ በላይ --- ለፈጣሪ ተገዝተን ፍትህን እንጠብቃለን ያሉ የሃይማኖት መሪዎችም እልቂቱን ለመከላከል ሳይሆን ፍጅት የሚፈጽመውን ሥርዓት ገጽታ ለመጠበቅ ሠራተኛ ሲሆኑ ፣
"ክፉውን ለማድረግ ብዙ ሰዎችን አትከተል፤ ፍርድንም ለማጥመም ከብዙ ሰዎች ጋር ተስማምተህ አትመስክር።" (ዘጸ ፳፫:፪) በተግባር ሲሽሩት ለምን ሁላችንም ፈዘዝን?
#የአርሲ፣ #የወለጋ የመላው #አማራ ክልል እልቂት እንዳይነገር አቡነ ያራድ፣ አቡነ ርሩፋኤል፣ አቡነ አብርሃም፣ አቡነ እንትና ወዘተ ለምን ይከላከላሉ?
በጭንቅ ከውጭ በሕገ ወጥ መንገድ ጋዜጠኛ እስገብተው የትግራይን ሕዝብ እልቂት ለዓለም የነገሩት #ፓትሪያሪክ #ማትያስ ለምን አሜሪካ ድረስ ተጉዘው የተወገዘውን መንበረ ህወሃትን/"ሰላማን" ሲባርኩ ጋዜጠኛ ጠርተው #እልቂቱን ለዓለም ለማጋለጥ #ለገሙ?
መልሱ:-
መስቀል የጨበጡ ካባ የደረቡ ይህን #የዘር #ማጥፋት ፖሊሲ ትግበራ ተጨባጭ እውነታ በዓይናቸው እያዩ #እንዳይነገር እንዲከላከሉ #በአብይ አህመድ ትዕዛዝ ተቀብለው እየትገበሩ ስለሄነ። ከክርስቶስ ድሎት ስለበለጠናቸው።
የደብረንኤልያስን እልቂት ያድበደበሰት አቡነ አብርሃም ምእመናንን ለማታለለል ተቀንጥሶ የማያልቀውን አንገታቸውን "ስለ ሃይማኖት አንገታን እሰጣለሁ" የምትል መዝሙራቸው "ሃይማኖት" ለእርሳቸው የሚያልቀው የጥምቀት ልጅ ሳይሆን "ፍሎታቸውን ላማስጠበቅ ከአብይና ከዳንኤልብክብረት ጋር መስማማት ነው"
አሁን ሁሉም መመራት የጀምሩት በቀኔና ሐርያት ሳይሆን በሌላ በመሆኑ ከሐዋርያት አንድነት ራሳቸው #እንደለዩ ማረጋገጥ ይቻላል።
ከሐርያት መንገድ #አልተለየንም የሚሉ ከሆነ በተግባር:-
፩) ቀኖናውን መልሰው፣
፪) በብርና በጎሣ የተሰበሰበውን ጳጳሳት ሽረው፣
፫) ያደለቡትን ሀብት ለቤተ ክርስቲያን አስረክበው
፬) በንፍስና በሥጋ ያስጠፉትን የጥምቀት ልጅ ቄጥረውና ተናዝዘው
፭) ከጎሰኝነትና ጎጠኝነት ተፋትተው
፮) የሰበሰቡትን ዘመድ አስማድ አሰናብተው እና አንዳንዶች የወለዱትን ልጅና ቅምጥ ተናዝዘውና ተለይተው
---- የተጠሩበትን የምንኩስና ሕይወት፣ ቃል የገቡበትን የእረኝነት ሥራቸውን ጀምረው ያሳዩ።
ይህን #እምቢኝ ብሎ ---- እንደተለመደው
በምንደኛ ሰባኪና የማኅበራዊ ሚዲያ አጽዳቂ ዘመቻ፣ እንዲሁም እያስገደለ አክብሩኝ እንደሚሉት አባቶች በመግለጫ እና በፕሮፓጋንዳ #የሐዋርያት #መንበር #ወራሽነትን ማጽናት አይቻልም። በብልጽግና መንግሥት ድጋፍ ሲፈልጉ #ወሊሶ ሳይመች አምስት ኪሎ እየመጡ #ብፁዕ መባባል ለረዥም ጊዜ በጥምቀት ልጆች ደምና የነፍስ ጉዳት ላይ መቀለድ የሚቀጥል አይመስለኝም።
ወይ ብፁዕ #ሆኖ #መገኘት ወይ ከገዳዮቹ ጋር ካራ ይዞ መሀዝገዝ!
ቀኖና ሐዋርያትን በአብይ ደብዳቤ ቀይረው እና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ሸቅጠው በእንድ የደሞዝ ሰንድ ላይ መገረም. ወይንም ነአንድ አዳሽ መሰብሰብ "ከቅዱስ" ሲኖዶስነትን አያሟላም።
ወድ ጎሣ ምክር ቤት የወረደ ድብሰባ በወሊሶም በአራት ኩሎም ተሀኝቶ በምእመናን ደም ላይ ቆሞ "እኛና መንገድ ቅዱስ ወስነናል" እያሉ በእግዚአብሔር ላይ ጽረፈት ማወጁ ማብቃት አለበት ።
እግዚአብሔርን በመዳፈር አሰገዳዩን "ብፁዕ"፣ ተሿሚውን የጎሣ የፓርቲ ወኪል በቅድስና ሕይወቱ መሆኑ ቀርቶ "ንፁህ ጎሣ" እያሉ በሚሾሙት ሰው ጉባኤ መንፈስ ቅዱስ ወሰነ ማለት እንዴት ይቻላል?
የተቀደሰውን የሐዋርያት መንበር በስሙ ቢጠሩበትም ይህ ገባኤ ከሚያስጨፈጭፈን፣ ክብረ-ሰብእና ፍትሕን ከማያውቁት ከዘረኞቹ ከጀዋር መሀመድ ተከታዮች፣ ከመረራ ጉዲና ፓርቲ፣ ከሽመልስ አብዲሳ ካቢኔ፣ ከአብይ አህመድ መንግሥታዊ መዋቅር የሚለዩበት ሚዛን ምንድነው?
ይለያል ወይንም።አይለይም ለማለት በማስረጃ እንሟገት። በሚከተሉት የምርመራ ነጥቦች እንፈትሽ ----- የሲኖዶሱ ከተጠሩትብተቋማት ጋር
፩) በአጀንዳቸው
፪) በቃለ ጉባኤአቸው
፫) ሞትና ስደትን በመከላከል
፬) ፍትህን እና እውነትን በመከላከል
፭) የተጎዱትን በማስካስና በማጽናናት
፮) ገዳዮችን በማውገዝ
፯) መናፍቃንን ከምእመናንን በመለየት ----- ሲመዘኑ:-
---- በምን እንደሚለዩ በትህትና የሚያስርዳኝ ሰው ፈልጋለሁ።
ማስመሰል፣ እውነትን ሸቅጦ፣ የተቀደሰ ቀኖና ትውፊትን ደፍጥጦ ለአድርባይነት መካካብ አያድነንም።
በፍቅር እውነትን እየተነጋገርንና ተጨካክነን የድኅነት መንገዳችንን እንሥራ!
ሐዋርያው በፊልጵስዩስ መልእክቱ 2:12 "ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤'
ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።። 1) ሻሸመኔ ከተማ I. የተገደሉ 1. አያሌው ተረፈ ● በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ● ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ● በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ● በ ጥር 30 2015 ዓ/ም ሰማዕትነትን ተቀብሏል 2. ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ● የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ● በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ● ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ● በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም ሰማዕትነትን ተቀብለዋል። 3. ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ● የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...
አስተያየቶች