ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ
ማን ገደላቸው? ለምን? ለሚለው ጥያቄ ፬ መላምቶች እናስቀምጥ:-
፩) አማራን እና ኦርቶዶክስን ከኢትዮጵያ ለማጽዳት የሚንቀሳቀሰው የብልጽግና ወንጌል መንግሥት ሠራዊት ሉሆን ይችላል ፣
፪) "ከሃይማኖት የጸዳ" ትግል እናካሄዳለን የሚሉ አምላክ-የለሽ አንዳንድ ሤረኛ የታጋዮቻችን አመራር ደረጃ ላይ ተቀምጠው ኢአማኒ ወይንም መናፍቅ፣ ወይንም ሃይማኖትን መጥቀስ ትግል የሚጎዳ ነው ብለው የሚያምኑ፣ ወይንም ምእራባውያን ጽንፈኛ ይሉናል ብለው አስበው ድጋፍ ለማግኘት የተላላኪነት ሚናንየወሰዱ አመራሮች አጋጣሚውን በመጠቀም መምህራንና ተማሪዎችን የሚያጸዱ፣
፫) ምናልባት የተገደሉት መምህር እጅግ ዐዋቂ መሆናቸው እና እውነትን፣ ርቱዕነትን ለሕዝቡ ስለሚያስተምሩ፣ ጎጠኛ የዘር ብሔር አምልኮን በማቆም ራሳቸውን ብቸኛ ዐዋቂና የወደፊት አብን ተክቶ አማርኛ ተናጋሪ አዲስ አብይ ንጉሥ ለመሆን ሲንቀሳቀስ መምህሩን እንደ እንቅፋት የሚመለከቱ ከአሉ፣
፬) ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን ለማዳከም ከዘመነ ሱሲኒዮስ እና አልፉንሶ ማንዴዝ እና ይፕዛሬዎቹ የደብረ ኤልፓስ መናፍቃን ቅባት፣ ፕሮቴስታንት፣ ዉሃቢያ እስላም፣ ኢአማኒ ከፋፋይ ፖለቲከኞች የፋኖን አመራር ጠልፈው የተዋሕዶ መምህራንን በስንት እያስጠፉ ሊሆን ይችላሉ።
ከእነዚህ መላ ምቶች ውጭም ሉታሰብ ስለሚችል ጨምሩበትና ለህልውና ትግል የወጣው አምላክ ያላቸው ታጋዮች በሚጠላቸው አስመሳይ መሪዎች ሥር ተሰልፈው ደማቸውን ከንቱ እንዳያደርጉ አንቁአቸው።
እስቲ ከመንጋነት ተላቅቀን በሚጠቅምና ወደ መፍትሄ በሚያመላክት ዓላም እንወያይ።
=============
ይህ በሽታ ወደ አንዳንድ ናርሲሲስት የፋኖ ጎጠኛ መሪዎች እና ጭፍን የማኅበራዊ ሚዲያ እንጀራ ጋጋሪዎች የተጋባ ይመስላል።
አይ ሽሜ? እንዲህ የጥቀር ናዚ ፖሊሲያችሁን ንገርና።
==========
በእነዚህ ማስፈንጠሪያዎች ሁሉ ለመወያየት አለሁ።
ከሰው አንባ ወደ ጎሣ ቡድን ዕሳቤ እሥረኝነት ያልወረዳችሁ ባለነጻ አእምሮ ወዳጆቼን ብቻ ነው የጋበዝኩት። ዘረኞችና ተላላኪዎች በነዚህ ገጾች ላይ ብትገኙ የእናንተ ድምጽ ዋጋ ስለማያወጣ እንዳትጎዱ ራሳችሁን አርቁ።
ትዊተር https://x.com/fwakie
ቴሌግራም @Fantahun_Wakie



አስተያየቶች

Mekonnen Birhanu …ብሏል
ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ መመስረት ላይ ትኩረት ይደረግ እያንዳንዱ ተገድሉ ሳያልቅ።

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

  ኦ ርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩ . ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡ በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያ...