እንደማንኛውም ማኅበረስብ ስለ አማራ ማኅበረሰበ ያገባኛል!!
ነገር ግን ስሞኑን የምትንጫጩ ጥቂት የሤራ ቡድኖች የግል እቃችሁ ስለሆነው አማራ በእርግጥ አያገባኝምና አልናገርም። ስለ ነጻ ሕዝብ አማራ ግን ያገባኛል።
በዚህ ጽሑፌ አቋሜን ግልጽ ላድርግላችሁ እና በግምት ከምትፈጥሩት የሀሰት ትርክት ላሳርፋችሁ።
አማራ በእግዚአእብሔር የሚያምን ሕዝብ ነው፤ ነጻ የሚወጣውም እግዚአብሔርን ይዞና መከታው አድርጎ እንጂ እናንተ እንደምትሉት እምነቱን እንደ ትርፍ ነገር ወዲቅያ በል ብሎ ትቶት አይደልም‼️
===========================================
መታወቅ ያለበት ፦
አማራ ሕዝብ እንጂ ከሕወሃትና ኦነጋውያን እንደቀሰማችሁት ጥቂት ግለሰቦች በአምሳላቸው የሚፈጥሯቸው ቡድኖች የፈቀዱትን የሚፈጽሙበት የእጅ መሣሪያቸው እና ባሪያቸው አይደለም።
በሌላ አነጋገር ፦
👉አማራ በእግዚአብሔር የሚያምን እግዚአብሔር በነጻ ፍቃድና በግዕዛን የፈጠራቸው ሰዎች አንድነት ያስገኘው ታሪካዊ ሕዝብ ነው እንጂ ዛሬ የሚነሱ ልሂቃን በአእምሮአቸው ስፋትና አመለካከት ለክተው የሚፈጥሩት ፖለቲካዊ ማንነት አይደለም!
👉 አማራ ለሰው ልጅ ሁሉ በሀገሩ የሚገባው ማኅበራዊ፣ መንግሥታዊና መንፈሳዊ ክብርን የነሱትን መዋቅራትና ፖልቲካዊ ርዮቶችን እንጂ የጎሣም ሆነ የእምነት ጠላቶች አላበጀም! እናንተም አታብጁለት፣ ሌላውን ማንነቶች "እንትን" እያላችሁ በአማራ ስም አትስደቡ፤
👉አማራ በሀገሩ መንግሥታዊ ሥራዓት ውስጥ እንደ ሕዝብ ከሰው ሁሉ እኩል ሆኖ የሚመራበትና የሚመ'ራበትን ሁኔታ ልፍጠር አለ እንጂ ማንንም ላሳንስ ወይን ባሪያ ላድርግ፣ ላፈናቅል ወይንም ላምክን፣ ከተወሰን አካባቢ ላጽዳ ወይንም ሁለገብ አድልዎ ልፈጽምበት አላለም! እናንተም እንድ አማራ በሉ፤
👉አማራ በፖለቲካዊ ረዮትና በመንግሥታዊ ሥራዓት ተግፋውን ሕዝብ ልዕልና ላስመልስ፣ የሀገርና የርስት ባለቤትነቱን ላረጋግጥ አለ እንጂ የናርሲሲስትና ሤረኛ የግለስቦችን ንግሥና ላርጋግጥ፤ ከዚያም እነርሱ መልሰው ሲያጠፉት ከኖሩት አካላት መሸነፍ በኋላ ከአብራኬ ለሚከፈሉት ባርያ ልሁን አላለም! ---
---- ይህ እንግዲህ እኔ እስከምረዳው ድረስ ማለት ነው። --- ደግሞ ግልገል ፋሽቶች ብቅ በሉና "በአማራ ትግል ምን አገባህ" ብላችሁ ተንጫጩ አሉ። ነግሬአችኋለሁ --- ስለ ሰው ያገባኛል ( ከሁልተ ዓመታት አስቀድሞ ነግሬአችሁ ነበር 👉 https://youtu.be/j1PeK_LWfKc )። በእርግጥ የናንተ የግል እቃ የሆነ አማራ ከአለ አያገባኝም
===================
#ሲጠቃለል
የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል የመጨረሻ ግብ ሕዝብን ከህልውና አደጋው በዘለቄታዊነት መታደግ ወይስ የትግራይና የኦሮሞን ሕዝብ በነጻነት ስም አሰልፈውና አድምተው፣ በመጨረሻ በትግሉ ተሳትፈው ለሞቱት የድንጋይ ሐውልት አቁመው፣ "ታራራን ያንቀጠቀጠ ትውልድ" የመሰለ ድርሰት ደርሰውለት፣ ሤርኞቹ የትግሉ መሪዎች ግን በትግሉ ከሞትና ከስደት የተረፈውን ሕዝብ #1ለ5 አየጠርነፉ የአእምሮና የአካል ባሪያ አድርገው፣ ባዘጋጁት የንዑስ ማንነት የክልል ጎርኖ ውስጥ አሥርው፣ ለ30 ዓመታት በዘርፋ ሲከብሩ እና የተከተላቸውን ሕዝብ ሀገር የሚያማስሉበትና የሚያፈርሱበት ሠራዊት እንዳደርጉት እንደ ሕወሃትና እንደ ኦነግ/ኦሮሙማ አይነት ሌላ ዙር #የዘረኞች #ሥርዓት ለመትከል ነውን? ነ የሚለውን ጥያቄ መመለስ ወቅቱ አሁን ነው።
እኔ አይደለም የምለው ሕየወቴ ሙሉ ከገበሬው ጋር ከሶማሌ ክልል በስተቀር ከሁሉም ማኅበረሰብ ጋር ቤት ለቤት በደረሰ ደረጃ በመሥራትና በማጥናት፣ በመማርና በማስትማር ስላሳለፍኩ ነው።
የሕዝቡን ተጋድሎ ለግል ፍተወታቸው ለመጥለፍ የሚጋጋጡ እንደአሉ ለማወቅ ብዙም የሚያደክም ምርምር አያሻም። አሁን ላይ ተደራጅተው በሚያሠራጩት መርዛማ፣ ከፋፋይና አጠልሺ፣ ኦርቶዶክስ-ጠል፣ ፋሽታዊ የሐሰት መርጃ ብቻ ከመገመት ያለፈ ብያኔ ላይ መድረስ ይቻላል።
ሌላው ምልክታቸው
👉 "አማራ" የእኔ ንብረት ስለሆነ እኔ እና እኔን ብቻ ማዳመጥ አለበት፣ ሌላ አማራጭ ዐስተሳስብ አታሰሙት፣ እ
👉 እናንተ የእንትን ጎሣ አባል ስለሆናችሁ ዐሳባችሁ ሁሉ ለአማራ አሉታዊ ነው፣
👉 የደም ጥራታችሁ የተበከለ ስለሆነና እኛ በደምና አጥንት እንጂ በእሤት፣ በባህል፣ በእምነትና በታሪካዊ ማንነት አናምንም እና ጣልቃ አትግቡብን፣ ወዘተ ማለታቸው እና እንዲሁም
👉 ከአማራነት በወርደ ነውረኝነት ለጥቂት ሰዎች ቡድናዊ ሤራ የሚያገለግሉ ገለሰቦችን በመረብ በማደራጀት በመላው ዓለም የሚገኙ የአማራ ተጋድሎ ድጋፍ ሰጭ ስብስቦች መካከል በማሰማራት መጠምዘዝ፣ ማወክ፣ ማፍረስና መልሶ በልካቸው ለማደራጀት መጣራቸው፣
👉 በፈጠሩት ሀገርና ዓለም ዐቀፍ የሤራዎቻቸው ተጋሪ ወይንም የተታለለ የዋህ ወገን በኩል ዒላማ ያደረጉትን ግለስብም ይሁን ለትግሉ አማራዊ አንድነት የሚጠቅመውን ሁሉ ስም ማጠልሸት --- ወዘት በቂ ማስርጃ ነው።
--- ለሚያቀርቡት ክስና ሐሰት አንድም ማስርጃ አቅርበው መሟገት አይችሉም።
እንደ እኔ ከሆን (#"ምን አገባህ" ለምትሉ ፋሽስቶችና ድውያን ቦታ የለኝም፣ የምናገረው ህሊና፣ ፈሪሃ እግዚአብሔር ላላቸው፣ ለክብር-ሰበእ እና ለፍትፍ ለቆሙት ሰዎች እንጅ ለሤርኛ ቡድን የአእምሮ ባርነት ለሚያገለግሉት ተላላኪዎች አይደለምና) የአማራ ወጣትና ገበሬ ደም እየፈሰሰ የሚገኘው የህልውና አደጋ የደቀኑትን ፦
(1) የዘር መዋቅራትና መንግሥታዊ ሥራዓታትን፣
(2) ዘረኝነትን ወደ ፖለቲካዊ ርእዮተ ዓለም ያሳደገውን የአስተሳስብ መሠረትና ትርክት፣
(3)ከዚያም ሰዎችን በንዑስ ማንነታቸው ወደ ሚታሠሩበትና "ሌላ" ከተባለው (በተለይ ከአማሮችና ኦርቶዶክስ ክርሰቲያኖች) ሥፍራ/ክልል የሚጸዱበትን መንግሥታዊ ፖሊሲና አሠራር፣ -----
---- በማሸነፍ እና ሥልጣንን በዘልቄታዊነት ዳግም በእኩያን እጅ እናዳይገባ ለመቆጣጠር የሚያስችል አስተማማኝ ሀገራዊ ሁኔታ መፍጠር ነው!!‼️ --- ለተፈጸሙት የዘመናት ግፎች ፍትሕ ማስገኘት፣ ተገፊዎችን ማስካስ፣ ከፊዎችን በሕግ ፊት ማቅረብ እና የትውልድን የወደፊት ተስፋና አስተማማኝ ሰላም ማረጋገጥ ናቸው።
--- ከዚህ ያነስ ሁሉ ከንቱ መድማት ነው‼️
በአጭሩ፦
የህልውና አደጋ የተደቀነበት፣ ላልፉት 50 ዓመታት መንግሥታዊ ሥልጣንን በተቆጣጠሩ የአሉታዊ ብሔርተኞች(ዘረኞች)ሲፈናቀል፣ ሲዋረድ፣ ሲገደል፣ ሲመክን፣ ሲደኸይ የኖረውን፣ አሁን እየተጨፈጨፈ ያለውን አማራንና በአማራ ምሥጢራዊ "ኮድነት"የ የሚደመሰሰውን ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ፍትሕና ሰብአዊ ክብር፣ የሀገር ባለቤትነት እና ከሌሎች ወገኖቹ በንዑስ ማንነቱ ሳይለይ ዋስትና ባለው ሀገር ውስጥ እንዲኖር ማስቻል ነው።
ከዚያ ያለፈም፣ ያነሰም ድብቅ አጀንዳ አንግቦ፣ ከባእዳንና ለመክራው መከስት ምክንያት ከሆኑ አካላትም ሆነ ከአስተሳሰቦቻቸው እይተዋሱ የሕዝብን የደምና አጥንት ዋጋ በማርከስ ለጥቂት ግለሰቦችና ቡድኖች የፍተወት እርካታ ለማዋል መሞከር ወንጀልም፣ ኃጢአትም ነው።
በዚያ ላይ አማራንም ሆነ ሌሎችን የቋንቋና የእምነት ንዑስ ማንነቶች የህልውና አደጋ ላይ የጣሉ አካላትን ትፋት መልሶ መላስ ያህል ክህደት መዋስ ያሳፍራል። የእነርሱን የትግል መርህና ስልት በተለይ የሐሰት ትርክት መፈብርክ፣ ሤረኝነት፣ ቁማርተኝነት፣ ፋሽታዊ ዘርኝነት፣ ነባር-ጠልነት፣ ጸረ ኦርቶዶክሳዊነትን ለአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል እንደ መሣሪያ መጠቀም አማራን መልሶ እንደምውጋት የሚቆጠር የውስጥ እሾኽነት ነው።
--- በዚህ መንገድ እየተገለጣችሁ ያላችሁ ግለሰቦችና ተከታዮቻቸው ሁልት ጊዚ አስቡበት። ከእውነት ጋር ስትጋጩ፣ ቤተ ክርስቲያንን ስታፈርሱ እንዳትገኙ። ቤተ ክርስቲያ የጥምቀት ለጆች ሁሉ አንድነት ነው እና ለትግላችሁ አእምሮአችሁን አስፍታችሁና ተጨንቃችሁ እርሷን ሳትነኩ አንድ ጠንካራ ኃይል ሁኑ። የለም ከርሷ ተነጥለን እና ተነጣጥለን፣ በአምላክ-የለሽነት መርህ (ፈረንጆቹ ሴኩላር/ሊብራል (ዶግማ አለባ)) እንድሚሉት) ፋሽስታዊ የደምና የአጥንት ቀምርን ተጠቅመን ብቻ ነው የሚያዋጣን ካላችሁ የምታጡት አማራን ነው።
አማራ በእግዚአእብሒር የሚያምን ሕዝብ ነው፤ ነጻ የሚወጣውም እግዚአብሔርን ይዞና መከታው አድርጎ እንጂ እናንተ እንደምትሉት ትቶት አይደልም‼️
https://youtu.be/j1PeK_LWfKc?si=84-B0j09I708VP45
አስተያየቶች