ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

በትግል ስም ኑፋቄ ከክርስቲያኖች ይራቅ

ምን ነክቶን ነው በማኅበራዊ ሚዱያ ጀግናና እፕዋቂ የሆንን እኛ ግብዜቹ  ከማሰብ ወደ መከተል ሰውነት የወረድነው? አሁንስ ፈራሁ። በፓስታና ኮካ ውስጥ ሊቀበሩ በሚችሉ ማይክሮ ሺፕስ እናንተን/ዘረ-መል ለውጭ ቅንጣት ሮቦት ሆነን ይሆን?

ምነው ሰው ከመሬት ተነስቶ ፕሮግራምድ ሆኖ እንደተለቀቀ ድሬንንየተጫነውን ሁሉ የሚተኩሰው? ባለህሊና ሰው መሆናችን ሊቀር እንዳይሆን?

በእምነታችን ደረጃ ክርስቲያን ክልሆኑት በጋራ የምናመልከው አምላክብየለንም።

የእኛ አምላክ ራሱን በባሎን ግንብ፣ በአብርሃም ቤት  እንግድነት፣ በዳዊት ትንቢት፣ ኋላም በዮርዳኖስ በልጁ ጥምቀት፣ በታቦር በነብያትናን ሐዋሪያት ጉባዔ ምስክርነት የነገረን  ያለመቀላቀል አንድም ያለመለያየት ሶስትም መሆኑን ነው።  አንድ  አምላክ ቅድስት የሆነች ሦስትነቱን  (አብ ወልድ መንፈስ ቅደስ አንድ አምላክ) መሆኑን  ነው።

ሌሎች አንድ ቢሉ ምን እንድሆነ ሊገልጹት  የማይችሉት ወይ በፍልስፍና ወይ ወግ እንጠብቃለን ብለው የመገለጥ ትምህርትን በመቃወም፣ ወይንም ነብያት ያስተማሩትን፣ ወንጌላውያን በእግዚአብሔር በሥጋ በመገለጥ ያስተማራቸውን ትምህርት ሲያስተላልፉ  ባለመቀበል አዳዲስ አማልክት ለራሳቸው ፈጥረዋል። ስለዚህ  የጋራ አምላክ የለንም።

ነገር ግን በማመንና ባለማመን ደረጃ የጋራ አምላክ ባይኖረንም የጋራ ሰውነት፣ የጋራ ምድራዊ አገር ፣ የጋራ ምድራዊ መንግስት፣   የጋራ ዜጋዊ ክብር ግን አለን።

የጋራ ሰማያዊ ርስት ያለን በጋራ ቅርንጭፍ የሆንበትን ሕያው የወይን ግንድ የክርስቶስን የእግዚአብሔር ልጅነት የተቀብልን ከተጠመቅነው ጋር ሁሉ ብቻና ብቻ ነው። ሌሎች ከተቀበሉት ርስቱን አሁንም ቢሆን ይወርሳሉ።

ለክርስቲያን ማስመሰል ኃጢአት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ነው ብሎ አምኖ፣ በአፍ መስክሮ   መዳን ራሱ ያስተማረን እንደሆነ በእውደምህረት ጆሮአችን እስኪግል ይነግሩንና ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ከአሕዛቡም፣ ከመናፍቁም፣ ከፀረ ክርስቶስም ጋር ይጸልያሉ። አንድ ክርስቲያን  የሊብራል ኢአማንያን መንፈስ ተጋሪ  ካልሆነ በስተቀር እውነትን ደብቆ ውሸትን ዲፕሎማሲና አብሮነት ነው በሚል ግብዝነት ትውልድን ክህደት አያወርስም።

"ችግር የሚፈታው፣ ፖለቲካ የሚሠራው፣ ጦርነት የሚካሄደው፣ እውቀት የሚፈለገው እምነትን ጥሎ ነው" የሚል ክርስቲያን ክህነትን ከንግሥናብያስተባበሩትን ቅዱሳን ነገሥታት ከምልከ ጸዴቅ እስከ ዛሬ ያሉትን ሁሉ፣ በተለይ በቅርብ ዘመናት የተገለጡትን ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስን፣  ቅዱስ ላሊበላን፣ ቅዱስ ነአኲቶ ለአብን ቅዱስ አጼ ካሌብን  ወዘተ ያሚያነውር ከሀዲ ነው።  ታቦት ተሸክመው አድዋ ዘምተው ከሴኩላሪስቶቹ አራዊት የታደጉንን ማውገዝና መሳደብ ነው።  የቅዱሳን ሰማዕታት ጳጳሳትን የአቡነ ጴጥሮስን፣ የእቡነ ሚካኤን፣ ፰ሺ ከሀዲውን ሱሲንዮስ ተዋግተው የተሰዉትን የጎንደር ሰማዕታትን መሳደብ ነው።

የሚገርመኝ የፍቅር ትርጉም ጠፍቷቸው "፣መቻቻል፣ መብት ማስከበር፣ ጨቋኝ ተጨቋኝ፣ ነፃነት፣ ወዘተ" በተሰኙና ትርጉማቸው በአገሩ የባህል፣ የእምነትና የታሪክ አውድ ውስጥ ያልተነገሩ ፅንሰ ዐሳቦችን በማንገብ  ስለ ሰማይ ርስት የክርስቶስ ሰማዕታት በሚያስመስላቸው ትጋት በማኅበራዊ ሚዲያ ድንቁርናቸውን መተኪያንየሌለው ዕውቀት አስመስለው የሚወናጨፉ ወገኖቼን በታላቅ ትህትና ተረጋጉ ለማለት እወዳለሁ።

የፍቅር ሃይማኖት ውስጥ እየኖርን፣ ሰውን በእምነትና በሰው ሠራሽ ማንነቱ የእግዚአብሔር ክቡር ፍጡርነቱን እንደማንነሳ የውጭ ተላላኪ ያልሆነ ህሊና ያለው ሁሉ የሌላ እምነት ሰውብያውቃል። ይህ  እየታወቀና የ፫ ሺ ዘመን ታሪካችን እየመሰከረልን እንዴት ፍቅርን የማያውቁ መንገደኞች "በመቻቻል"  ስም እውነትን እንዳንመሰክር፣ ሃይማኖታችንን በሁሉም የሕይወት ዘርፎቻችን ማለትም በፖለቲካ፣ በጦርነት፣ በሰላም፣ በምጣኔ ሀብት በአስተዳደር፣ በትምህርት በሕግ፣ በፖሊሲ  ውስት እታካቱት የሚሉን ለዚያውም ተጠመቅን የሚሉ ሰዎች ተፈጠሩ? ነው ጥምቀቱ አልገባቸውም? የእግዚአብሔር ልጅ የመሆን ሥልጣን የሚያስከትለውን በሕይወት የመመስከር ኃላፊነት ችላ ለማለት አዲሲ ሃይማኖት-አከሉ የብሔር ፖለቲካ ነጠቃቸውን? እላለኩ።

እኔ ሰውንንየምወደው፣ የማከብረው፣ የምታገልለት በሃይማኖት አይደለም። በመጀምሪያ በመሆኑ ነው።  ሁለትኛ በመገፋቱና ዒላማ በመደረጉ ድምጽና ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ሳምን ነው።
ከዚህ ውጭ ብየ ማንም ጭፍን አገልጋይ፣ መገልገያና ማደሪያ አልሆንም።

" ስለ ኦርቶዶክስ መገፋት የማንናገረው አጠገባችን እነ እንትና ስላሉ ነው" የሚለው መከራከሪያ ራስን ትኩሶ እንደማቁሰል ያለ ጅልነት ብቻ ሳይሆን የጠላት ሤራ ሰለባ መሆን ነው። ፍቅር የማያውቁና በእምነት ካልመሰልከኝ በዚህ ዓለም በምድር መኖር አይገባህም የሚሉ የሰው ሰራሽ እምነቶችን ባህል አምጥቶ "ኦርቶዶክሳዊት ክርስትናን" በዚያው ልክ መመልከት ምን ለራስህ ብል ስምህ ፈራሃለሁ ማለት ስህተት ብቻ ሳይሆን የማይገባ የክፋት ብልጠት ነው።
ይህችም ቪዲዮ ታስተምራለች https://youtu.be/lNcskbugmLY?si=5rX8L_P7ngP64RUe

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

  ኦ ርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩ . ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡ በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያ...