ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ብርሃን ሲለግም ጨለማ ይነግሣል፦ አልቦነት፣ ፖልቲካዊና መንፈሳዊ ውድቀት (ለሲኖዶስ የተጻፈ ነበር፣ ዛሬ ለፋኖ የውስጥ ችግር መንሻ የሆነ የአስተሳሰብ መዛባትን መንስዔም ጠቋሚ ነው ብዬ ለጠፍኩት)

ብርሃን ሲለግም ጨለማ ይነግሣል!
የሲኖዶስ አባላት መሠዘም(being secularized) ለፖለቲካ ሲታዘዙ ሰይጣን ከእሥሩ ይፈታል!

ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ/ም

 © ፋንታሁን ዋቄ

የዘሬውን ዓለም ያጨለመው አልቦነት (Nihilism) ወደ ኦርቶዶክሳዊት ቅድሰት ቤተክርስቲየዓን ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ገብቷል!

አገራችን ኢትዮጵያ  ተማርን በሚሉ ጥቂት አእምሮአቸው በተቀሰፉ የፖለቲካ ልሂቃን ምክኒያት እጃችን ላይ ከሟሟች ቆይታለች።  ዘሬ ደግሞ ሲኖዶሱ ከጎሠኛና ዘረኛ መንግሥት ትዕዛዝ ተቀብሎ በሐዋሪያት አምሳል ሳይሆን በብሔር ፖለቲካ የፌደራል ምክር ቤት አርአያነት  የቤተክርስቲያን መሪዎና እረኞች ጳጳሳትን ለመሾም ተወስኗል።  ውሳኔውን የሚያከፋው፦

✝️ የመንግሥት ትዕዛዝ መሆኑ፥ 

✝ ጥቆማውን ተቀብለው መርጠው ለሲኖዶስ እንዲያቀርቡ ከተመለመሉት መካከል  በክፋታቸውና በኢቀኖናዊነታቸው የሚታወቁ ሰዎች መኖራቸው፥ 

✝️ እነዚህ ሰዎች የቅዱስ ሲኖዶስን ውግዘት ባለመቀበል መልሰው የሚኣወግዙና በሐዋሪያት የክህነት ሥልጣን አንደማያምኑ በተግባራቸው የገለጡ ሰዎች መሆናቸው ነው። 

✝️ ተጨማሪውና አስቃቂው የሆደት ተፋልሶ የቆሞሳት ምርጫ ሕግና የማጽደቅ ሂደት  ከተጻፈ ሕግ ያፈነገጠና ከምእመናን የተደበቀና በፖለቲከኞች የሚመራ መሆኑ፤ 

✝️ በዚያ ላይ ሰኔ 30ቀን 2015  የተመረጡት ታውቀው፥ ምእመኑ አስተያየት ሳይሰጥ፥ ገደማት ሳያውቁ፥ የሰ/ት/ቤትና ሌሎች ማኅበራት ስለ ቅድስናቸው ምስክርነት ሳይሰጡ በሳምነት ሐምሌ 9 ቀን  ለሲመት እንዲቀርቡ መታቀዱ፤

ይህ የሚያሳየን አልቦአዊነት ባጨለማት ዓለም በርሃን መሆን የሚገባትን ቤተክርስቲያን የሴኩላር ዲሞክራሲና የዘረኞችን ፖለቲካ ትዕዛዝና ፍላጎት የተቀበለ ሲኖዶስ በኢትዮጵያ እየተፈጠረ ለመሆኑ ግልጽ ተግባራዊ መገለጫ ነው። በጨለማ ላይ ገደል ተጨመረ፥ ሰይጣን ተፈትቶ ተለቀቀ ማለት ይቻላል። ይህን  አሳዛኝ ሁኔታ ይዘን የሰው ልጅ እንዴት ከታለቅ ሰማያዊነት ወርዶ ከዚህ የወደቀ ደረጃ ላይ ደረሰ የሚል ጥያቄ አንስተን  እንወያይ። ለውይይቱ መነሻ ለእኔ ዋና መንስዔ የምለው ምእራባዊያንን መንፈስ-አልባ ቁሳዊያን፥ ሰዶማዊያን፥ ጦርነት አምራች፥ ስግብግብ፥ ወራሪና ባሪያ ፈንጋይ፥ ስግብግብና አልጠግብ ባይ ያደረጋቸው የአእምሮና የስነልቦና ሁኔታን ያስከተልን “አልቦነት” (NISILISM)   መረዳቱ ለመፍትሔው ግማሽና ለእርምጃችን ቁልፍ ጉዳይ በመሆኑን በርዕሱ  ላይ  ከወቅቱ የቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የኤጲስቆጶሳት ምርጫ አንፃር ስለ አልቦነት፥ ስለአጋጠመን የውሳኔ ስሕተትና መፍትሔ ሀሳቤን እሰጣለሁ።  ይህ ሀሳብ አባቶችን የማክበርና ያለማክበር ጉዳይ ሳይሆን በቤተክርስቲያን ላይ የውስጥ የፖለቲካ ሠራተኞች የሶኖዶሱ አባላትና የዘረኛ መንግሥት ባለሥልጣነት ጥምረት አከርካሪ ያሳጣቸውን አባቶች መልካሞቹን ለማበረታታት፥ ክፉዎቹን ደግሞ ምእመናን አውቀው ስለ ቤተክርስቲያናችን ብለው አንዲቃወሙአቸው ጥሪ ለማቅረብ ነው። ክብር ለሚገባው ክብር መስጠት ክርስትና ነው፤ በዚያው ልክ “ሂድ አንተ ሰይጣን ከወደ ኋላዬ” ማለትም ክርስትና ነው። አይጣሉም።  


አልቦአዊነት ምንድነው? በቤተክርስቲያን አገልጋዮች መካከል አንዴት ታየ?

አልቦአዊነት ወደ ሰው ልጆች እምሮ ገብቶ ልቦናን ተቋጥሮ እውነትና ሐሰት፥ ሕይወትና ሞት፥ ብርሃንና ጨለማ፥ ፍትሕን ግፍ፥ አማኝነትና ክህደት፥ በሙት ጣዖትና በሕያው እግዚአብሔር መ መካከል ያለውን ድንበር በማጥፋት  ቤተክርስቲያንና ከኢአማኒኣን የፖለቲካ ተቋማት ጋር ያስተካክላል፥ ሰዎችን የመኖር ትርጉማቸውን ያዛባል፤ ዛሬ በኢትዮጵያ እንደሚታየው አይነት በደምና ዕንባ ግብር ውሎ የሚያድር የመፖሊካ ሥርዓትን ይተክላል፥ ቤተክርስቲያንና መስጊድ እየደመሰሰ መናፈሻ የሚገነባ፥ ሚሊዮኖችን እያሳደደ፥ ሴቶችን ለአረብ ባርነት እየሸጠ ስንዴ ወደ ውጭ ልካለው የሚል መሪ አዝሎ የሚኖር ግብዝ ተውልድ ይፈጥራል።

አልቦአዊነት ሁሉንም በሃይማኖት፣ በባህል፣ በማኅበረሰብ ታሪካዊ መስተጋብር የሚታወቁ የእምነት፣ የስነ ምግባር፣ መርህ፣ የመኖር ትርጉምን ሙሉ በሚሉ በመሻር ተርጉም-የለሽነትን የሕይወት ማዕከል የሚያደርግ ፍልስፍናዊ ዕሳቤ ነው።  

አልቦአዊነት የሰው ልጅ ሕይወትን በባዶነት ዕሳቤ ላይ በመመሥረት አሉታዊነት፣ ጥርጣሬና እርግጠኝነት ማጣት፣ ተስፋቢስነት፣ ነባር-ጠልነት/ተቃውሞ፣ ማራከስ/ማዋረድ፣ ክህደትና ቅልበሳ፣ አብዮት፣ ኢአማኒነት፣ ታጋላጭነት፣ ለምንም አለመኖር፣ ተለዋዋጭነት፣ የስነ ምግባር እሴት ማጣት፣  ሃይማኖተኛ/ምንፈሳዊ አለመሆን፣ የተጨባጭነትንና የእውነት መኖርን መካድ --- ይገልጹታል። 

አልቦነት ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ እምነታዊ ማኅበረሰብንና ተቋማት የሚመሰረቱበትን አምነቶች፣ እሴቶች፣ የሞራልና የፍልስፍና አስተምህሮዎችን ሁሉ በመቃወም አዲስ ነገር ግን ምንም ቋም አስተምህሮና ግብ በሌለው መንገድ የማመስ ዝንባሌ ያለው አስተምህሮ ነው ብሎ መደምደም ይቻላል።


የዓለማችን ሰለማዊ ሁኔታና የሰው ልጅ ደኅንነት ወይንም አለመግባባት፣ ጥላቻ፣ ጦርነት፣ ግጭትና አውዳሚ አብዮቶች መነሻቸው አስተሳሰብ ነው። “እውነተኛ” እና “ትክክለኛ” አስተሳሰብ ሰላምን፣ ፍቅር፣ ፍትሕን፣ ሰብአዊ ፍቅርን፣ ትብብርና ሕብረትን ከቤተሰብ እስከ አገር፣ ከአህጉር እስከ ዓለም ያሰፍናል። በተቃራኒው “ሐሰት”፣ “ስሑት ርዕዮተ ዓለም”፣ “ስህተት” (በተለይ ለንስሓና ለመታረም የራቀውን በስሑት ርዕዮት የሚመራ ስህተትና ሐሰት) እና “አልቦነት”  አጠቃላይ የሰው ልጆችን ፍቅር ማጣት፣ ጥላቻ፣ መለያየት፣ ስስት፣ ግራ መጋባት እና ውጥንቅጥነትን ከቤተሰብ ጀምሮ እስከ ዓለም ደረጃ የሚያመነጭ መንገድ ነው።

ዛሬ በኢትዮጵያ አገራችን በቤተሰብ፣ በማሕበረሰብ፣ በጎሣ ቡድን፣ በፖለቲካ ደርጅቶች መካከል የሚካሄደው የማያቋርጥ ጦርነት ምክኒያቱ ወደ አልቦነት ደረጃ ያደገው ስሁት ነፅሮተ ዓለም፤ በስሑት ነፅሮተ ዓለም ምክኒያት የሚመሠረት ፖለቲካዊ ተቋምና አስተዳደር፣ ሕጎችና ደንቦች ናቸው፤ ሁሉም በሚባሉ ደረጃ በሐሰተኝነት፣ ሆነ ተብሎ በፖለቲካ ቁማርተኝነት በሚፈጸም ትክክል ያልሆነ ውሳኔና ድርጊት፣  የሚሊዮኖች ዜጎች ሞትና ስደት ተከትሏል፤ የወዲፈት ትውልድ ሳይቀር በሰላምና በስምምነት የሚኖርበትን እድሉን የሚበላሽ ሥርዓት ከላይ እስከ ታችኛው የመንግሥት አስተዳደር መዋቅርና ማኅበራዊ መሰረቶች ድረስ ደርሷል።  ሰውነት፣ ዜግንት፣ ሰብእና፣ ፍትሕና ሕግ ትርጉም አልባ ሆነው የፖለቲካ ልሂቃንና ሥልጣንን በቁማርተኝነት የጨበጡ አካላት የሚሊዮኖችን ዜጎች ሕይወት ከአንድ ጽ/ቤት ውስጥ ተቀምጠው የሚያውኩበት፤ የሺ ዘመናት የሕዝቦች መስተጋብር፣ ሃይማኖትና ባህል ያወረሰን እሴት በአፈቀላጤ ተሽሮ አዳዲስ በግልሰቦች አእምሮ ልክ የሚፈጠሩ አስተሳሰቦች የሕዝብ ሥርዓትን የሚመሩበት፤ ትምህርት፣ መገኗኛ ብዙኃን፣ ኪነጥበብና ሕግ ሙሉ በሙሉ ከሕዝብ እሴት መመንጨታቸው ቀርቶ የጥቂት ልሂቃን አስተሳሰብ ውጤት የሆኑበት ደረጃ ላይ ደርሰናል። በአገራችን የሚታየው ሁኔታ እጅግ የከፋ ከመሆኑ የተነሳ ባሕር ተሻግሮ፣ ድንበር ጥሶ የሚመጣ ጠላት ሳይኖር ልሂቃን ከባዕዳን ምሪት እያገኙ፣ በብድር መገዳደያ ማሽን እየሸመቱ የገዛ አገራቸውን ዜጎች የሚያፋጁበት፣ በአነዲት ታሪካዊ አገር ውስጥ ሌሎች ትናንሽ አገራትን በየጎሣው የፖለቲካ ልሂቃን የአእምሮ ስፋትና ግንዛቤ ልክ ለመሥራት ሚሊዮኖችን የሚያፈናቅሉበትና የሚያገዳድሉበት መሆኑ ነው።  

ለዚህ ጥፋት መሠረት የሆነው የአልቦነት ዕሳቤ ውልደቱ ውጭ አገራት ቢሆኑም በተገኘበት አገራት የግልሰቦችን ሰብእና ከማዋረድ አልፎ አንደ ኢትዮጵያ በአንድ አገር ውስጥ አገራትንና ልሂቃን በሚገባቸው ልክ የሚባዙት ብዝኃ እሴትና አዳዲስ አደገር ወይን አዲስ አገር ለመፍጠር መንግሥታት ዜጎቻቸውን ሲያፋጁ አልታየም።  አባ ሴራፊም ሮዝ ለአመጽና ለጥፋት ሁሉ ምንጭ ሆኖ ዘመናዊውን ዓለም የሚፈታተነው “አልቦነት” እንደሆነ በጠንካራ አመክንዮአዊ ተጠየቅ፣ በነገረ መለኮት፣ በታሪካዊ መረጃ፣ በአሁናዊ የማኅበረሰብ ሁኔታ ምልከታና በግል ሕይወታችን ሁሉ ያለአንዳች ጥርጣሬ መመስከር እንችላለን።  “ሥዝም ሰብአዊነት(secular humanism:- ‘የልማታዊ’ ወንጀሎች ምንጭ” በሚል ርዕስ አንድ   ዳጎስ ያለ መጽሐፍ አሳትሜ ነበር። ያንን መጽሐፍ ለማዘጋጀት በማደርገው ጥናት የሥዝም ሰብአዊነት ማኒፌስቶ የተባለን “እውነትን” በመካድ በኢአማኒያን (አቴይስቶች) ልሂቃን ቁንጽል አእምሮ ልክ ተዘጋጅታ ለሥዝም የዓለም ፖለቲካ ሁሉ (በተባበሩት መንግሥታት ተቋማት መሣሪያነትና በኃያላን አገራት ፍላጎት) ሳይገባው ሚመራበት የሥዝም ሰብአዊያን ማኒፌስቶ ቁጥር 1 እና ቁጥር 2ን (Humanist Manifesto II and III) በሰፊው በመሞገት “አልቦ ትርጉም” መሆኑን ለማሳየት ሞክሬ ነበር። 

ዛሬ በአገራችን መንግሥትና የፖለቲካ ልሂቃን የሚፈጸመውን ሳጤን፥ በተለይ አልቦነት ያጠቃቸው ሰዎች የኦርቶዶክሳዊት ቅድሰት ቤተክርስቲያናችን ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት መሆን ማቻላቸውን ሳጤን ከፍተኛ ሀዘን አግኝቶኛል። የምድሩን ሁሉ አበላሽተው የመኖር ትርጉማችንን አዛብተው፥ እንደ ማኅበረሰብ ቁርኝታችንን በዘረኛ ፖለቲካ በጣጥሰው፥ በአንዲት አገር ውስጥ ትናንሽ አገር ለመፍጠር በቋንቋ ዘውግ ዜጎችን ተካፍለው በአንድ ጦርነት አንድ ሚሊዮን ወጣጥ የሚያስገድሉ መሪዎችን አዝለን መኖራችን ሲገርመኝ ዛሬ ላይ የፍጽምት እውነት ጠባቂዎች፥ የሞራል መሠረቶች፥ የፍጥሕ ሚዛኖች፥ የቅድስና አርአያዎች ያልናቸው አባቶች ከአገር አጥፊ ኢአማኒያንና አልቦአዊያን መመሪያ ተቀብለው ጵጵስናን በጎሣ ለመሾም መበየናቸውን መመልከት “ጌታ ሆይ ቶላ ና!” ያሰኛል። 

መፍትሔው በሁለት አካላት እጅ ላይ ነው፦ 

(1) ከምእመናንና (2) አሁንም የሐዋሪያትን ቀኖና የቤተክርስቲያንን ዶግማ ለመጠበቅና ለማስጠበቅ ቁርጠኛ የሆኑ አባቶች 

✝️  አልቦነት የሚሰብከውን አንፃራዊ፥ ሴኩላር-ዲሞክራሳዊ፥ የብልጽግና መንግሥት የሚያዘውን ዘረኝነት ፊት ለፊት በመቃወም በቀነኖና ሐዋሪያት መፅናታችን ሳይውል ሳያድር መግለፅ

✝️  በቤተክርስቲያን ውስጥ በአባትነት ስም የተሰገሰጉትን ኢአማኒያን፥ መናፍቃን፥ የፖለቲካ ቅጥረኞች ለምእመናን ማጋለጥ

✝ ️ ሐሰተኞችን ማውገዝ

✝ ️እውነተኛ ገዳማዊያን፥ የወንበር መምህራን፥ ሊቃውንት በአስቸኳይ የተፈጠረውን ስሕተት በፍትሐ ነገሽቱ፥ በቀኖናውና በሐዋሪያት ትውፊት፥ በጥንታዊቷ የመንበረ ማርቆስ ቤተክርስቲያን የነበሩ ቅዱሳን ጳጳሳት ሕይወትን ለምእመናን መግለጥ

✝️ ቤተክርስቲያንን ብቻ ሳይሆን ቤተክርስቲያን የምትገለጥበትን አገር በማጥፋት የተጠመደውን የዘረኝነት ፖለቲካ ፊት ለፊት ጥፋቱንና የሚያመጣውን ምድራዊና ሰማያዊ መከራ በግለጥ ለምእመናን ማስተማር፥ 

✝️ ዘረኛ ልሂቃን የጥምቀት ልጆችን በቦታና በቋንቋ ዘውግ ተካፍለው  አሁን የተጠመዱበትን ማጠፋፋት አንዳይቀጥሉበት ዘረኞችን የሚከተሉ የጥምቀት ልጆች አንዲመለሱ ማስተማር፥ በእንቢታ የፀኑትን ማውገዝ

✝️ ከከፋፋይ፥ ጥላቻን ከሚያሰተምር፥ ጦርነትና መጠፋፋት ከሚያስከትል ፖለቲካ ራሳቸውን በማግለል የራሳቸው በሰብአዊነት፥ በዜግነት፥ በፍትሕና በእውነተኝነት ላይ የተመሠረተ የራሳቸው የፖለቲካ ሥርዓት ለመመሥረት በፍጥነት እንዲሰባሰቡ በመስበክና በማስተማር በጥላቻና በማገዳደል ነፍስና ሥጋን ከሚጎዳ ከዚህ ዘመን ፖለቲካ መለየት።  


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

  ኦ ርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩ . ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡ በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያ...