ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ 
ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች 
ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ 

nigatuasteraye@gmail.com 
ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም. 
(April 28, 2025) 

መግቢያ 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡  

ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡  

የጽዋ ማኅበር መነሻዋና አመሠራረቷ


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋግዶ ቤተ ክርስቲያን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት ዘመናዊት ከሚያደርጓት ከብዙ እሴቶቿ መካከል አንዷ የጽዋ ማህበር ናት፡፡ የጽዋ ማሕበር መነሻውና የሚጠቁመው ከመሪር አገዛዝ ነጻ መውጣትን የምታሳይ ቀስት ናት፡፡ እንደ ስንበቴው ስርአት በቀጥታ ከእግዚአብሔር ወደ ሙሴ ባትደርስም በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰች የእግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ 

“እግዚአብሔር የእስራኤልን ጩኸት ሰማ፡፡ ለአብርሃም ለይስሐቅና ለያዕቆብ የገባውን ቃል ኪዳን አስቦ ጎበኛቸው ”(ዘጸ 2፡ 24) ብሎ ሙሴ እንደጻፈው በመከራ በጭቆናና በመሪር አገዛዝ ላይ ለወደቀ ሕዝብ ጮኸት ከእግዚአብሔር ወደ ሰው የመጣች ናት፡፡ ሙሴ ለነጻነት አመራር የተላከባት እግዚአብሔር ለአብርሃም ለገባው ቃል ኪዳን ጉብኝት ማስፈጸሚያ ናት፡፡ በመሪር አገዛዝ የወደቀውን ማኅበረሰብ ነጻ አውጥቶ ወደተስፋው ምድር ለማድረስ ሙሴ የተጠቀመባት የነጻነትና የክብር እንቅስቃሴ መነሻና መድረሻ ናት፡፡  

የጽዋውን ማህበር አደርጃጀት ሙሴ የመጀመሪያው ሆኖ ስለተጠቀመባት አባቶቻችን የጽዋ ማሕበራቱን መሪወች በሙሴ እንዲሰየሙ አድርገዋል፡፡ ሐሳቡ የፈለቀው ግን ከሙሴ ሳይሆን በምድያም ይኖር ከነበረው ዮቶር ከሚባለው ኢትዮጵያዊ እንደሆነ ሙሴ በመጽሐፉ ገልጾታል፡፡ እስጢፋኖስ “ሙሴ ጥበብን እውቀትን ሁሉ የሀሳብ መመዘኛ (ጽድቅን)ተማረ በቃሉ በተማረው የተማረውን ትምህርት በተግባር ለማዋል በረታ (የሐዋ 7፡22) ብሎ እንደተረከው የሙሴን ሕሊና መጀመሪያ ያነቃለት በፈሮን ቤተ መንግሥት ባደገባቸው አመታት ነው፡፡ ትምህርቱ በዚያ ዘመን በግሪክና ባጎራባች አገሮች ተስፋፍቶ ከነበረው ጋራ የተያያዘ በግብጹ ፈሮናዊው ቤተመንግስት ዳብሮ የነበረው ከአርዮስፋጎስ ቅኔና ተመሳሳይ ፍልስፍናዎች ጋራ የተያያዘ ነበር፡፡ ይህን እየሰማና እየተማረ በማደጉ የፖለቲካውን ጥንቅርና ውስብስብ በሚገባ ተገንዝቧል፡፡  

የድሀ ልጅነቱ፡ ወድቆ መገኘቱ የቤተ መንግሥት ልጅነቱና የናቱ በመግዚትነት ወደ ቤተ ምንግሥት መግባቷ ለሙሴ መሪነት ቅድመ ዝግጅት መለኮታዊ ኪነጥበብ ነው (ዘጽ 7_10)፡፡ ሙሴ ከናቱ በሰማውና በቤተ ምንግሥት ሲያደግ ያገኘው ትምህርት እግዚአብሔር ለጠራለት ለነጻነት ተልእኮ ድርብርብ ጸጋ ነበር፡: 
1  
የሙሴ እናት ተክትላ በሞግዚትነት ወደ ቤተ መንግሥት መግባቷ፦ ሙሴ በቤተ መንግሥቱ ቅንጦት በወገኑ ላይ የሚደርሰውን መከራ ዐይኑ ከማያት ጆሮው ከመስማት እንደይሸፈኑ እንድትረዳው ነበር፡፡ 
 
ከባርነት አገዛዝ ነጻ ሊያወጣው የተዘጋጀለት ሕዝብ ተባብሮ የተጠመደበትን የባርነት ቀንበር ለመስበር ከመታገል ይልቅ ከፈሮን መንግሥት ጋራ ተባብረው የራሳቸውን ወገን የሚጎዱ ዛሬ በአገራችን የሚታዩትን የሚመስሉ የወገን ጠላቶች ነበሩ፡፡ ከወገን ጠላቶች አንዱ የራሱን ወንድም ሲደበደብ ሙሴ አየው፡፡ ሙሴም “በተመሳሳይ ጭቆና ውስጥ ያለውን ወንድምህን ለምን ትደበድባለህ?  ብሎ ወቀሰው፡፡ ራሱን ለግል ጥቅም የሸጠው ከሐዲ የሙሴን ምክር ተቀብሎ የደበደበውን ወንድሙን ይቅርታ ጠይቆ ለጋራ ነጻነቱ ከሙሴ ጋራ ከመሰለፍ ይልቅ “ትላንት ግብጻዊ ግለህ ዛሬ ደግሞ እኔን ልትገለኝ ነው? በኛ ላይ አንተን አለቃ ወይስ ዳኛ ማን አደረገህ?  (ዘጸ 2፡13)፡፡ አለው፡፡ ሙሴን የተገዳደረው ሰውም ይሁን ሌላ ከሐዲ ለፈሮን ጠቁሞ ኖሮ የሙሴ ሕይወት አደጋ ላይ ወደቀ፡፡ በፈሮን አገዛዝና በንቃተሕሊና ጎዶሎወች ወገኖቹ መካከል ተጣበቀ፡፡ የሚስቱን አባት ዮቶርን ወደአገኘበት ወደ ምድያም ለመሰደድ ተገደደ (ዘጸ 2፡11_15 )፡፡ 

ማህበሩን መርቶ ከነጻነት ወደብ ለማድረስ ሙሴ ከፈሮን ትምህርት ቤትና ከናቱ እየተማረ ያገኘው እውቀት ብቻ ለበቂ ዝግጅት የሚያበቃው አልነበረም፡፡ ህዝብን መመራት ይቅርና ራስንም ለመመራት የራስን አቅም መረዳት ትልቁ ተቀዳሚ ጸጋ ነውና ሙሴ ያጠራቀመው ጸጋ ተናግሮ የማሳመን ሙሉነት እንዳልነበረው ተረዳ፡፡ ሙሴ እኔ አሻግራችኋለሁ ብሎ በራሱ ትቢት በመወጠር  በትልቅ ሕዝብ ፊት እራሱን ከመጣድ የመቆጠብ ጸጋ ነበረው፡፡ “እኔ አፈኮልታፋ ምላሴም ጸያፍ ነው” በማለት ከግዚአብሔር ተጨማሪ ርዳታ ለማግኝት ድካሙን ገለጸ፡፡ የሰውን አንደበት የፈጠረ እግዚአብሔር ከሱ ጋራ እንደሆነ በመንገር እንዲጠነክ መክሮ አሮንን አዘጋጀለት (ዘጸ 4፡10_)፡፡ ይህም ሁሉ ሆኖ የሕዝባዊ አደረጃጀትና አመራር ስልት ስለሚጎለው ሕዝባዊ አመራር ወደ እሚማርበት ወደ ምድያም እግዚአብሔር መራው፡፡ በዘመኑ ጥበብ የበሰለውን ዮቶር የሚባለውን ኢትዮጵያዊ የጥበብ ሰው በጋብቻ ተጠግቶ ተማረ፡  እንዲወድቅ በፈሮን ቤተ መንግሥት እየተማረ እንዲያድግና እናቱ ተከትላው ወደ ቤተ መንግሥት ገብታ እንድታሳድገው ያደረገ አግዚአብሔር፡ ወደ ምድያም ተሰዶ እንዲሄድ፡ በረዥም ጉዞው የሚገጥመውን መከራና ስቃይ ታግሶ ከግቡ ለማድረስ የሚያስችል የድርጅታዊ አመራር ጥበበ እንዲማር ወደ ዮቶር እንዲሄድ መራው (ዘጸ 18፡13_27)፡፡  

ኢትዮጵያዊው አማቱ ዮቶር ከሙሴ የጎደለበትን ጸጋ ባየ ጊዜ “ምን እያደረክ ነው? ይህን ሁሉ ህዝብ ከጧት እስከማታ  በዙሪያህ አቁመህ ብቻህን በፍርድ ወንበር ላይ ለምን ትቀመጣለህ? አመራርህ ልክ አይደለም፡፡ራሳህንም ሰውንም እያደከምክ ነው፡፡  ብቻህን ልትወጣው አትችልም፡፡ የኔን ምክርና ጥበብ ስማ፡፡ እግዚ የሚፈሩ ታማኞችን በማታለል የሚገኘውን ጥቅም የሚጸየፉ የመቶ  የአምሳ የአስር አለቃ አድርገህ ሹምላቸው” ብሎ የአመራር ጥበብ ለገሰው፡፡ ሙሴ የዮቶርን ምክር ተቀብሎ የሚያስቸግራቸውን ወደሱ እንዲያቀርቡለት አድርጎ በማደራጀት አመራሩን ቀጠለ፡፡ (ዘጸ 18፡25_27)፡፡ ዮቶር ከሙሴ ጋራ መቀጠሉን አቁሞ ወደ አገሩ ሲመልስ ሙሴን ብቻውን አልተወውም ፡፡ ሙሴን እንዲረዳው አባብ የሚባለውን ልጁን ማለትም የሙሴን አምቻ ትቶለት ዮቶር ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡  

ከአባብ ጋራ አንድ ቦታ ላይ ሲደርሱ አባብ ጥሎት ወደ አገሩ ለመመለስ ወሰነ፡፡ “ዐይናችን ትሆናለህና እባክህ አትለየን፡፡  በስደት በመከራው ዘመን በበርሀ አብረን መከራውን በመካፈል አይናችን ነህ፡፡ በመጨረሻው ዘመን እግዚአብሔር የሚሰጠንን የሰላምና የተረጋጋ ዘመን አብረን እንኖራለንና አትልየን” (ዘኁ 10፡29_32)፡፡ ብሎ አባብን ለመነው፡፡ ያም ሆነ ይህ ሙሴ  እስራኤልውያንን የመራበት ድርጅታዊ ጥበቡ የእግዚአብሔር ቢሆንም አባቶቻችን እንደሚነግሩን ሙሴ ይህን ማሕበራዊ አደረጃጀት  የተማረው ዮቶር ከሚባለው ኢትዮጵያዊው አማቱ ነው፡፡ “ሙሴ ህዝቡን የመራባት ይህች አደረጃጀት በዮቶር በኩል ያገኛት፡ ከእግዚአብሄር የፈለቀች ኢትዮጵያውያን ለነጻነታቸው ለረዥም ዘመናት የተጠቀሙባት ልዩ ጸጋችን ናት” እያሉ ሊቃውንት አባቶቻችን አስተምረውናል፡፡  

ከላይ በተገለጹት ድርብርብ ጸጋወች ያላንዳች እንከን በመምራት ላይ ሳለ ሙሴ በዘረኛዋ እኅቱና በአሮን ሙሴን ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው፡፡ ይህች ሴት ሙሴ ያገባትን ኢትዮጵያዊት የተቃወመች ዘረኛ “ከእናቱ ሆድ በወጣ ጊዜ ግማሽ ሥጋው ተበልቶ እንደሞተ” ጭንጋፍ ጉደኛ እንዳትሆን እንዲጸልይላት አሮን ሙሴን የለመነላት የተረገመች ሴት ናት፡፡ (ዘኁ 12፡12)፡፡ 

ከግብጽ ትምህርት ቤት፡ ከናቱና ከዮቶር ባገኘው እውቀት ባንደበተኛው አሮን አጋዥነት ህዝቡን በ12 ሽ ከፍሎ በ144ሽ አደራጅቶ እንቅቃሴ ቢጀምርም የፈሮንን አሳዳጅነት የሚከላከል ተጨማሪ ረድኤት አስፈለገው፡፡ እምነቱንና ቆራጥነቱን የሚደግፉ በሱ አመራር የሚመራው ሕብረተሰብ አንዳች ጉዳት ሳይይደርስበት ቀን ካሳዳጅ ጠላት የሚጋርድ ሌሊት ሙቀትና ብርሃን የተወሀደው የደመና አምድ ተሰጠው (ዘጸ 13፡21_22)፡፡ ሙሴ በዚህ አምደ ብርሃን በታጀበ ድርብርብ ጸጋ እስራኤላውያንን እርስበርሳቸው እየተረዳዱና እየተደጋገፉ በርሐውን እንዲያቋርጡበት ባሕረኤርትራን እንዲሻገሩበት መራቸው፡፡  
 
2  
ከላይ እንዳልኩት ይህች አመራር እግዚአብሔር ቀደም ብሎ ለአብራሃም ለይስሐቅና ለያዕቆብ ለገባው ቃል ኪዳን የምድራዊና  የጊዜአዊ ነጻነት ፍጻሜ ትሁን እንጅ፡ በክርስትና እምነት ለሚወረሰው ለሰማያዊና ዘላለማዊ ሕይወት ማሳያ ቀስት ሆኖ በእመቤታችን  በቅድስት ድንግል ማርያም አንደበት ተገለጸች፡፡  

“በርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖር እንጅ እናዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከመስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ” (ዮሐ 3፡16) በመውደዱ እግዚአብሔር የላከው የግዚአብሔር ቃል ማለትም የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ በማሕጸኗ ሥጋ ሲሆን “እግዚአብሔር ለአብርሃም ለአባቶቻችን ለዘሩ የገባውን ቃል ኪዳን አሰበ ” (ሉቃ 1፡55) ብላ ሙሴ ለነጻነት እንቅስቃሴው መነሻ ያደረጋትን ስለጠቀሰችው የጽዋው ማህበር ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር በጠበቀ ግንኙነት ተያያዘ፡፡ ጽዋ ሁለት ትርጉሞች አሏት፡፡ ከእኅተ ሙሴ ማርያም ጋራ ሲገናኝ “ከእናቱ ሆድ በወጣ ጊዜ ግማሽ ሥጋው ተብልቶ እንደሞተ”  የመረገም እድል ፈንታ ይሆናል፡፡ ከእመቤታችን ጋራ ሲይያዝ የበረከትና የነጻነት ዕድል ፈንታ ይሆናል፡፡  

ቃል በማሕጸኗ ሥጋ በሆነበት ቅጽበት የጸጋ ሁሉ ምንጭ የሆነው እግዚአብሔር ከጸሐይ ብርሃን በላይ በሆነው በጽድቁ ብርሃን በታጀበው መዋግደጸጋ በተጥለቀለቀችባት ወቅት፡ “አዕበዮም ለትኁታን ወፈነዎሙ ራቆሙ ለብዑላን ወተዘከረ ሣሕሎ ለአብርሃም ወለዘርዑ እስከ ለዓለም ” (ሉቃ 1፡55) ብላ ደስታዋን ገለጠች፡፡ የገለጠችበትን አዋጅ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ለጽዋ ማኅበራቸው መነሻና መድረሻ አድርገውታል፡፡ በሐዲስ ኪዳን ከክርስቶስ ጋራ የነበሩትን 72 አርድዕት 36 ቅዱሳት አንስትና 12  ሐዋርያት በጥቅሉ 120 ቤተሰብ የተካፈሉትም ማሕበር ከሙሴ ማህበራዊ ሕብረት ጋራ የተያያዘ ነው፡፡በሙሴ የተመራው ምድራዊና ጊዜአዊ ነጻነት በክርስቶስ ለተፈጸመልን ዘላለማው ነጻነት ተጠቃሽ ማረጋገጭ ሆኗል፡  

የጽዋ ማሕበራትና የሰንበቴ ሥርአተ ጸሎት  


የጽዋ ማሕበራትና የሰንበቴው ሥርአተ ጸሎት በቅዱስ መጽሐፍ ላይ የተመሠረተ የሚያሰደንቅ ወግና ስርአት አለው፡፡ የጽዋ  ማኅበር ሥርአት በክርስትና እምነት ለሚወረሰው ለሰማያዊና ዘላለማዊ ሕይወት ማሳያ ቀስት ይሁን እንጅ፦ በእመቤታችን በቅድስት  ድንግል ማርያም አንደበት እንደተገለጸው እግዚአብሔር ቀደም ብሎ ለአብራሃም ለይስሐቅና ለያዕቆብ ገገባው ቃል ኪዳን ሰው በምድር  ላይ ሲኖር ስለሚገባው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡ ኩለንተናዊት ቀዳማዊትና ደኀአርዊት የምትባለው ቤተ ክርስቲያናችን የጽዋ ማሕበራትን የመሠረተችው ለምድራዊውና ለሰማያዊው ነጻነት ለሁሉም እንዲጠቅም በማድረግ ነው፡፡  

የጽዋ ማህበር የተመሰረተው ከላይ ተሰናስለው በተገለጹት ሐሳቦች ላይ ሲሆን በሐዲስ ኪዳን መጨረሻ በራእየ ዮሐንስ ም 7  ላይ እንደተገለጸው ሙሴ በ12 ከፋሎ በ144ሽ ቁጥር ደምሮ ማህበረ እስራኤልን የመራበትን ምሳሌ በማድረግ ነው፡፡ ስርአቱ “ከታላቅ መከራ አምልጠው ከሕዝብ ከነገድ ከቋንቋ የመጡ ነጭ ልብስ ለብሰው የዘንባባ ዝንጣፊ በእጃቸው ይዘው በታላቅ ድምጽ ማዳን በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው የአምላካችንና የበጉ ነው እያሉ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማምለክ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡(9_10) ፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ያጠመቀቻቸው ልጆቿ በየዘመናቱ በወራሪወች የገጠሟትን መከራወች እያመለጠች ከትውልድ መድረሷንና ቀጣዩ ትውልድ ጽዋውን በመቀባበል ኢትዮጵያ ያለፍችበትን እንዳይረሳና ለሚገጥመውም ፈተና እንዲዘጋጅ የሚያደርግ ነው፡፡  

“በሚቀጥሉት ትውልዶች ሁሉ በልብሳቸው ጭፍ ላይ ዘርፍ አድርጉ እያንዳንዱ ዘርፍ ሰማያዊ ጥለት አድርጉ እነዚህ ዘርፎች በማየት የእግዚአብሔርን ትእዛዛት በማስታወስ እንድትታዘዙ ማስታወሻ ይሁናችሁ”(ዘኁ 15፡38_40) በሚለው መሠረት፦ የጽዋውማህበር ተረኛ ልዩ ክብርና ሞገስ ያለውን ባለ ጥለት ሸማ ለብሶ፡ በሆሣዕና እለት የዛፍ ቅጠል እየዘነጠሉ እንደጎዘጎዙ ቤቱን ቄጠማ ጎዝጉዞ ጸጋና ሞገስ በተሞላ ፍቅር ይጠብቃል፡፡ አባላቱም ዮሐንስ በራእዩ ያያቸውን “ከታላቁ መከራ የመጡትን ልብሳቸውንም በበጉ ደም አጥበው ያነጹትን ”(ራእይ 7፡9_14) መስለው ነጫጭ ልቦሶቻቸውን ተጎናጽፈው ተዘጋጅቶ ወደሚጠብቃቸው ቤት ይገባሉ፡፡  
ባብነት ትምህርት ቤቶች በማታ ጸሎታቸውና በማሕሌትም በሚደረጉ የማሕበር ጸሎቶች ሁሉ “ማህበረነ ዮም ድንግል ባርኪ” ሳይባል የሚጀመር ጉባዔ እንደሌለ በጽዋ ማኀበርም “ድንግል ሆይ ጉባዔያችንን ባርኪልን ይባላል፡፡ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላገኘነው ዘላለማዊ ነጻነታችን ምልክት ከሆነችው ከቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም ጋራ ጥብቅ ትስሥር አለው፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በዓለም የሉት ሁሉ ክርስቲያኖች ለቅድስት ድንግል ማርያም ከሚሰጧት ክብር እጅግ ከፍ ያለ  ምልዕተ ጸጋ በማለት የምንሰጣት ክብር በአምላክ እናትነቷ ብቻ ሳይሆን የነጻነታችን ምሳሌ በመሆኗ በድርብርብ ጸጋዋ ነው፡፡ 

ዘላለማዊ ነጻነትና እረፍት ያገኘንበት ቃል የተባለው አማኑኤል በማሕጸና ሥጋ ሲሆን ከኪሩቤል በላይ ባደረጋት ጸጋ በተጥለቀለቅችበት ጸጋ ለሙሴ ከተሰጠው ድርብርብ ጸጋ እጅግ የሰፋ የመጠቅና የጠለቀ ጸጋ ነው፡፡ በቅዳሴአችን “ወንጌልን ለዓለም ያስተምሩ ዘንድ መስፈርት መጠን ከሌለው ከማይመረመርና ከማይተረጎም ጸጋህ ከፍለፍ ጸጋ ለሐዋርያት ሰጥተህ የላካቸው ” (ሥ ር ቅ ገጽ 58) እያልን የምንገልጸው ለሰው ልጅ ያልተሰጠ ለሷ ብቻ የተሰጠ ከኪሩቤል በላይ ያደረጋት ጸጋ ነው፡፡ ትምህርቱን ለማድረስ ለሐዋርያት የተሰጣቸውን ጸጋ መጠን መስፈርት መተርጉም የማይቻል ብለን የምንገልጸው ጸጋ በዚህ ክብደት ከተገለጸ ራሱን መጠን
3  
የሌለውን ጸጋ ለሚስተማሩ ከሰጠ የጸጋ ባለቤትና ጸጋ የሚያድለውን በማሕጸኗ ዘጠኝ ወር ለተሸከመችው ለድንግል ቅድስት የተሰጣት ጸጋ ከኪሩቤል በላይ አድርጓታል፡ 
ክርስቶስን በጸነሰችባት ቅጽበት እስራኤል ነጻ ለማውጣት ለሙሴ ከተሰጠው ጸጋ ፡ትንቢቱን እንዲናገሩ ለነብያት ከተሰጣቸው ጸጋ ቃሉን ለዓለም ለማድረስ ለሐዋርያት ከተሰጣቸው ጸጋ በላይ ሲያጥለቀልቃት “ነፍሴ ጌታን ከክፍ ታደርገዋለች መንፈሴም በምድኃኒቴ በእግዚአብሔር ደስ ትሰኛለች በክንዱ ብርቱ ሥራ ሠርቷል በልባቸው ሐሳብ የሚታበዩትን በትኗቸዋል፡፡ገዥወችን ከዙፋናቸው አውርዷቸዋል ትሑታንን አድርጓቸል የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቧቸዋል፡፡ ሀብታሞችን ባዷቸውን ሰዷቸዋል፡፡

ምሕረቱን  በማስታወስ ባሪያውን እስራኤልን ረድቷል፡፡ ይህም ለአባቶቻችን ለአብርሃምና ለዘሩ እንደ ተናገረ ምሕረቱን ለዘላለም ለመጠበቅ ነው፡ (ሉቃ 1፡46_55) ብላ ያሰማቸው የደስታ መፈክር ሰማያዊውን ዘላለማው ነጻነት ብቻ የሚያሳይ ሳይሆን ምድራዊውን ነጻነትንም የሚያሳይ ነው፡፡ 

እመቤታችን ጌታችን በማሕጸና ሲያድር ያሰማቸው መግለጫ ሙሴ ማሕበረ ሰቡን ከመሪር አገዛዝ ነጻ እንዲያወጣ ከተላከበት ጸጋ እጅግ የላቀ ነው፡፡ ማህበረ ሰቡን በየነገዳቸው አደራጅቶ በመምራት ነጻ ካወጣበት እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለዘሩ ከገባላቸው ቃል ኪዳን በላይ ነው፡፡ ወደሷ የጎረፈው ጸጋ እግዚአብሔር ከዚህ ቀደም ለተለያዩ አገልጋዮቹ በየመጠናቸው ከሰጣቸው ጸጋ በላይ እጅግ የመጠቀ ጸጋ ነው፡፡  

የጽዋ ማህበር እመቤታችን “በክንዱ ብርቱ ሥራ ሠርቷል በልባቸው ሐሳብ የሚታበዩትን በትኗቸዋል፡፡ገዥወችን ከዙፋናቸው አውርዷቸዋል ትሑታንን ከፍ አድርጓቸል የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቧቸዋል፡፡ ሀብታሞችን ባዷቸውን ሰዷቸዋል” (ሉቃ 1፡46_55)  ብላ ደስታዋን ባሰማችበት መፍክር የታተመ ነው ፡፡ ቀጥለን ከጽዋው ማሕበር ጋራ ተፈጻጻሚ የሆነውን ሰንበቴን እንመልከት፡፡ 
 


    


የሰንበቴ ማህበር በገጠሪቱ ኢትዮጵያ 



ሰንበቴ የጽዋ ማኅበራት ስብስብ ነው፡፡ 

እግዚአብሔር “ሁሉን ከፈጠረ በኋል በሰባተኛው ቀን አረፈ፡፡ ሰባተኛዋን ቀን ባረካት አከበራት (ዘፍ 2፡2_3) ሰውም ማንም እንዳይሰራባት አዘዘ፡፡ የሻራትን ሰው “ማሕበሩ ሁሉ ከሰፈሩ ወደ ውጭ አውጥተው እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ወግረው እንዲገሉት እግዚአብሔር አዘዘ”፡፡ ተገደለባትም(ዘኁ 15፡)፡፡ “ኢያሱ ዕረፍትን ሰጥቷቸው ቢሆን ኑሮ እግዚአብሔር ሌላ ቀን ባልተናገረም ነበር፡፡ የሰንበት ዕረፍት ለእግዚአብሔር ሕዝብ ቀሮላቸዋል፡፡ ወደ እረፍቱ የገባ እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ እርሱም ከሥራው አርፏል፡፡ እንግዲያ እንደዚያ አለመታዘዘ ምሳሌ ማንም እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንትጋ” (ዕብ 4፡8_11) ብሎ ዕብራዊው ክርስቲያን እንዳስተማረ ሰንበት በኢያሱ ነጻ አውጭነት በተገኘው ነጻነት ላይ ያለቀና የቆመ አይደለም፡፡  

በክርስቶስ መሪነት በምትገኘውን ዘላለማዊት ዕረፍት የምትጠቁም ናት፡፡ ይህች ዘላለማዊት ነጻነት በክርስቶ ባለማመን እንዳናጣት እንትጋ በማለት ቤተ ክርስቲያናችን በቅኔ ማሕሌቷ፡ “ቀደሳ ወዐልዐላ እምኩሎን መዋዕል” እያለች፡ በቤተ መቅደሷ “ኩሉ ዘገብራ ለጽድቅ ጻድቅ ውእቱ ወዘያከብር ሰንበተ:: ኢይበል ፈላሲ ዘገብአ ኀበ ቤተ እግዚአብሔር ይፈልጠኒኑ እምሕዝቡ” ብሎ (ኢሳ 56፡1_7)፡፡ ብሎ እግዚአብሔር በነቢዩ በኢሳይያስ የተናገረውን እየጠቀሰች ሕዝቧ ለሥጋውም ለነፍሱም ነጻነት እኒዲጠቀምበት በማስታወስ ላይ ትገኛለች፡፡ 

እመቤታችን “ነፍሴ ጌታን ከፍ ከፍ ታደገዋለች፡መንፈሴም በመድኃኒቴ በእግዚአብሔር ደስ ትሰኛለች” ብላ ያሰማችው  የፍጹም ደስታ መፈክር (ሉቃ 1፡46_55) በሥጋም በንፍስም የተገኘውን ዘላለማዊ ነጻነት አጉልቶ የሚያሳይ ነው፡፡ ልጇ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ ኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከኔም ተማሩ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና” ብሎ ሰውን ወደ ራሱ ከጋበዘ በኋላ፡ (ማቴ 11፡28_30)  ከሰንበት በታች ወድቆ የነበረውን ሰው ከወደቀበት አንስቶ ወደ ቀደም ክብሩ ለመመለስ የሰንበትን ክብር ለሰው ልጅ ክብር እንድትለቅ አደረጋት፡፡ በሰው ላይ የነበራትን ኃይል ሽሮ ለሰው ልጅ በሚደረግ መልካም ሥራ ተካት፡፡ (ማቴ 12፡7_8) ፡፡  

ከሐዋርያት ቀጥለው የተነሱት ሰለስቱ ምዕት በቅድማና የነበራትን የሰንበትን ክብር ጨርሰው ሳይሽሩ ጌታችን ያስተማረውን መሠረት አድርገው እመቤታችን የገለጸችውን ሰባዊ ክብር ሚዛን በማድረግ “ሰንበትን በኦሪቱ ተንጠልጥለው እንደቀሩት እስራኤላውያን እንዳታከብሩ፡፡ የቀደመ ትሪኳን ምልክትነቷን እንደማያውቁ በጣኦት በዐላቸው አከባበር ባህል እንደ አሕዛብ በዓላት አከባበር እንዳታከብሯት ” (ሰለስቱ ምዕት 20፡13)፡፡ ብለው አዘዙ፡፡ እንደ አይሁድ እንደ ሕዛብም አከባበር እንዳናከብራት አድርገው በሰበነክ አገልግሎት የሰውን ክብር ከፍ ለማድረግ በሚያስችል አከባበር እንድትከበር ስርአት ሠሩ፡፡  

ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን ሙሴ ነጻ ያወጣበትን ክርስቶስ የሰራውን ስርአት እመቤታችን የተናገረችውን ሰለስቱ ምዕት የሠሩትን አሰናስለው፦ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች በስላሴ በመድኃኔዐለም በእመቤታችን በጻድቃን በሰማእታት በመላእክት ስም ተደራጅተው ደጀ ሰላም በሚባለው አዳራሽና በየአውራ ጎዳና የወደቀውን በማንሳት የተራበውን በመመገብ የተጣላውን በማስታረቅ ለሰው ክብር በመስጠት ስንበትን እንዲያከብሯት አድርገዋል፡፡ “እናነተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፡፡እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል፡፡ነቢይን በነቢይ ስም ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የነቢይን የጻድቅን ዋጋ ይቀበላል፡፡ ማንም ከእንዚህ ከታናናሾች ላንዱ ቀዝቃዛ ወሀ የሚያጠጣ እውነት እላችኋለሁ ዋጋው አይጠፋበትም”(10፡40_42)፡፡ ብሎ የተናገረውን ለሰንበቴው ሥርአት አድርገው አገናዝበውታል፡፡ ተጠቅመውበታል፡፡  

በተለያዩ ስሞች የተደራጁትን የጽዋ ማሕበራት በሰንበቴ አጠቃለው አደርራጁት፡፡ የማሕበራቱን ሙሴወች በማሕበረ በኩርነት አደራጅተው፡ ጥቅላላ ማሕበረ ሰቡን አስተባባረው በሰንበት ቀን የተጎዳውን አቅም ያጠረው መርጃ፡ ቤታቸው አጥራቸው የፈረሰባቸውን መስሪያ፡ የተራቆቱትን ማልበሻ ፡ ጠዋሪ ቀባሪ የሌላቸውን መፍቀጃ፡ ባሏ የሞተባትን የልጆች አናት ማጽናኛ፡ ሚስቱ የሞተችበትን የልጆች አባት መደገፊያ፡ እናት አባት የሌላቸውን እጓለ ማውታወች መሰብሰቢያ፡ ድንበር ጥሶ ወራሪ ሲመጣ ለመከላከል ለሚደረግ ሀገራዊ ጥሪ አዋጅ (ቃለዓዋዲ) ማሰሚያ አድርገውታል፡፡ 

የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴው ትሩፋታቸው ምንድ ነው?  


ኢትዮጵያን ኩለንታዊት ቀዳማዊት፡ ደኀራዊት ዘመናዊት የሚያደርጓትና ከጎረቤቶቿ አገሮች ልዩ የሚያደርጓት እሴቶቿ ናቸው፡ ፡ ከእሴቶቿ መካከል አንዱ ከጽዋ ማህበር ጋራ ተደምሮ የሰንበቴው ትሩፋት ነው፡፡ የሰንበቴው ትሩፋት ሕዝቡን እርስ በርሱ ከማስተሳሰርና እንዲረዳዳ ከማድረጉ ባሻገር አገር ሲወረር እንደ አጼ ምንይልክ የመሳሰሉ መሪወች ለሀገራዊ ጥሪ ተጠቅመውበታል፡፡ 

ይህንንም በዙ የውጭ ሰወች ምስክረዋል፡፡ Iris Habib el Masri የሚባል ግብጻው የታሪክ ሰው “The sheep of Ethiopia  have been delivered from the hyena of the west by the doctrine of st Ciril the great pillar of the Holy Orthodox  Church of Egypt” (the history of the Copts 1982 pp 262) ሲል የሰጠው ምስክርነት ኢትዮጵያ ከጽዋው ማሕበራትና ከሰንበቴወች ያገኘቻቸውን ትሩፋቶች የሚያረጋግጠው ነው፡፡ 
  
“እኛ ኢትዮጵያውያን ነጻነታችንን ያስከበርነው ግብጻዊው ጸሐፊ እንዳለው በቅዱስ ቄርሎስ ዶክትሪን ብቻ ሳይሆን ሙሴ ከዮቶር የተማረውን ማኅበራዊ ሥርአትና የቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምን መፈክር ከስነ ሕሊናችን ጋራ በማዘመዳችን ነው፡፡  ነጻነታችንን የጠበቅነው በየቅዱስ ቄርሎስ ዶክትሪን ብቻ ቢሆን ኖሮ የቅዱስ ቄርሎስን መጽሐፍ የሚጠቀሙ ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ  በተለይም ግብጽ ራሷ በተለያዩ ወራሪወች ከመቀጥቀጥ በዳነች ነበር” ይላሉ፡፡ ኢትዮጵያዊት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሕዝቧን አንቅታ አደራጅታ ነጻነቱን እንዲጠብቅ ያደረግችው በቅዱስ ቄርሎስ ዶክትሪን ብቻ አይደለም፡፡ሙሴ ከዮቶር በተማረው በስሙ በተዋቀረው የጽዋ ማሕበር ባህልና ከእመቤታችን መፈክር ጋራ ደምረው ሕዝቡን ባደራጁበት እንደሆነ Hggai Erlich የተባሉት ጸሐፊ ራሳቸው ግብጻውያን የተናገሩትን ጠቅሰው ጽፈዋል፡፡ 

“The majlis, perhaps the first manifestation of modern Coptic life, was the embodiment of the  educated youth’s desire to be accepted by modern Egyptian society. In time this modern waing of the Coptic  community would develop its own Ethiopian idias, quite different from those of the patriarchate, the Holy Synod,  and the Coptic Church establishment” (The Cross and the Riverpage page 68). 

Erlich የተባሉት ከዚህ በላይ የተጠቀሰውን እንዳሰፈሩት፦ ባንድ ወቅት በሲኖዶስ የሚመሩት ኦርቶዶክሶች በነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ላይ የነበረው ጸጋ ጎደለባቸው፡፡ ህዝቦቻቸው ቅኝ ገዝወች ተፈራረቁባቸው፡፡ ያለ ሲኖዶስ በጽዋና በሰንበቴ ማህበራት የተደራጀችው ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የተከላከለችበትን አመራር ተመኙት፡፡  

ከውጭም ሆነ አገር በቀል ጠላቶች ኢትዮጵያን ህዝቡን በቋንቋ በክልልና በሃይማኖት ከፋፍለው በኢትዮጵያ ላይ የሚዘምቱት በጽዋና በሰንበቴ ሕዝቡን ባዋቀረችው በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንና በተከታይቿ ላይ ነው፡፡ በደርግም በወያኔም ዘመን የተፈጸመው ይህ ነው፡፡ ሰማእቱ ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ቴወፍሎስ የሰንበቴንና የጽዋ ማህበራት አቀናጅተው ያደራጁበትን ቃለዓዋዲውን አፈራርሶ በከተማ በገጠር ያለውን ሕዝብ ወደ ቤተ ክርስቲያን በማይደርስበት ዘዴ አሰረው ፡፡ በነ ዶክተር ክነፈርግብ ዘለቀ አቡነ ቴወፍሎስ ተወገዱ ተገደሉ፡፡ በአቡነ ቴወፍሎስና በንጉሡ ፈቃድ ተመስርቶ የነበረው ሃይማኖተ አበው የተባለው ድርጅት ፈረሰ፡፡ ደርግ ቤተ ክርስቲያን ላይ የፈጸማቸውን የጥፋት ዘመቻወች ለመረዳት በቀዱስ ወብጹዕ ፓትርያርክ ቴዎፍሎስ ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግድያ መመልከት በቂ ማስረጃች ይሆናል፡፡  

ሰማእቱ ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ቴወፍሎስ ኮምኒስቶችን ተከትለው ያስገደሏቸውን የገደሏችን 
ብቻ ሳይሆን ዛሬም የመጣውን መንግስት በመከተል እርስ በርስ በመጠላለፍና ለምእመመናን 
እንቅፋት የሆነውን ሁሉ “ኢትሑር ወኢትንግድ ፍኖተ ባዕድ ከመ ኢትትዐቀፍ በዕብነ መንሱት” (ሲራ 35፡20) በማለት እያስጠነቀቁን ነው፡ 


በደርግ ዘመን የተደረገ የጥፋት ዘመቻ 


በ50 አመታት በቤተ ክርስቲያን ላይ የተፈጸመውን ዘመቻ እንመልከት፡፡ታሕሳስ 10 1953 ዓ/ም ብቅ ያለው ማሕበራዊ ቡድን የንጉሣዊውን አመራር ሕልውና እጥያቄ ላይ ከጣለbእት ጊዜ ጀምሮ እስከ 1966 ዓ/ም የ“መሬት ላራሹ” ታውጆ የመሳፍንቱ ሥርአት እስኪወገድ ድረስ ቤተ ክርስቲያናችን በግንባር ቀደም ከሚወቀሱት ድርጅቶች አንዷ ሆነች፡፡  

በ1953 ዓመተ ምሕረት በነ መንግሥቱ ንዋይ የተከሰተው የለውጥ እንቅስቃሴ የመሳፍንቱን ስርአት መጋረጃ ቀደደው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የአስኳላ ተማሪወች በመሳፍንቱ ስራት ላይ በሚያሰሙት የተቃውሞ ድምጽ ቤተ ክርስቲያኒቱንም ደምረው መውቀስ ጀመሩ፡፡ በተማሪው የተጀመረው እንቅስቃሴ እየቀጠለ መሄዱን ብሩህ ጭንቅላት የነበራቸው ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ቴዎፍሎስ በጥንቃቄ አጤኑት፡፡ ፓትርያርክ ቴወፍሎስ ከራስ እምሩ ጋራ በመሆን ንጉሡን ለተማሪወችን ድምጽ ትኩረት እንዲሰጡት ደጋግመው ጠይቀውም መክረውም እንደነበረ ይነገራል፡፡ 


ንጉሡ ትኩረት ሳይሰጠበት የተማሪው ድምጽ በህዝብ እየታጀበ እስከ 1964 ዓ/ም ሲቀጥል ብጹዕ ወዱስ ፓትርያርክ ቴዎፍሎስ በ1964 ዓ/ም ቃለዓዋዲ የሚል መመሪያ አዘጋጅተው ቤተ ክርስቲይናቸውን በሰበካ ጉባኤ በማዋቀር ከመሳፍንቱ ስርአት ለዩአት፡፡ ሰማእቱ ፓትርያርክ “ኢትሑር ወኢትንግድ ፍኖተ ባዕድ ከመ ኢትትዐቀፍ በዕብነ መንሱት” (ሲራ 35፡320) የሚለውን ከቀደምት መምህሮቻቸው የተማሩት ለፓትርያርክነት ለቀረበላቸው ጥሪ በቁና ዝግጁ ያደረጋቸው ነበሩ፡፡ ቅድመ ዝግጁነታቸውና የተቀበሉት ፓትርያርካዊ ጥሪ የተስማማላቸው ስለነበሩ መመሪያውን ቃለዓዋዲ፡ አደረጃጀቱን ሰበካ ጉባዔ ብለው የዘረጉት እቀድ ከባእድ የተዋሱት ሐሳብ ወይም ከራሳቸው የፈለቀ አልነበረም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ያጠመቀቸው ሕዝቧ ራሱን ከመበታተን ኢትዮጵያን ከወራሪ ስታስጠብቅባቸው ከነበሩት ከሰንበቴውና ከጽዋ ማሕበሩ የሠርጹ ናቸው፡፡  

በ1966 ዓመተ ምህረት የፈነዳው ለውጥ በ1967 የመሬትን መሳፍንታዊ ትስስር ከማወጁ በፊት ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ቴወፍሎስ ቤተ ቤተ ክርስቲያንን ከመሬቱ ስራት አስቀድማ እንድትላቀቅ ያደረጋትን ቃለዓዋዲውን ከደርግ በፊት በ1965 አወጁት፡፡ ሰማእቱ ቅዱስ አባታችን ፓትርያርክ “እንድታይ ዓይኖችህን የምትኩለውን ኩል ከኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሀለሁ”(ራእይ 3፡18) ብሎ ክርስቶስ የተናገረውን መንፈሳዊ ኩል የተኳሉ ነበሩ፡፡ አቡነ ቴወፍሎስ በዚህ መንፈሳዊ ኩል በደርግ የሚመጣባትን መከራና ስቃይ አስቀድመው አይተውበታል፡፡ 

የውጭና የውስጥ አስተዋይ የሆነ ሁሉ ቅዱስ ፓትርያርክ ቴወፍሎስን በዚህ እይታቸው ቢያደንቃቸውም በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ብዙ ጋሻ መሬት በነበሯቸው ወገኖች ጥርስ ውስጥ ከቷቸዋል፡፡ የብዙ ጋሻ መሬት ተጠቃሚወች ለንጉሡ ክብር መቀነስ የተቆረቆሩ መስለው ከንጉሥ ይኩኖ አምላክ ጀምሮ የነበረውን የሲሶ መንግሥት ስርአት በእርሰዎ ዘመነመንግሥት በሕይወት እያሉ ፓትርያርኩ አፈረሱት እያሉ ለንጉሡ ከሰው አቅርበዋቸው ነበር፡፡ ንጉሡ ግን “እኛም ተስማምተን የፈቅደነው ነው” በማለት ክሱን ሳይቀበሉ ከሳሾችን እንደመለሷቸ በወቅቱ በሰፊው ሲወራ ተስምቷል፡፡ቤተ ክርስቲያናችን ፓትርያርክ ቴወፍሎስን በሰሩት በጎ ተግባርና በተፈጸመባቸው ግድያ ሰማእት ስትላቸው፡ ንጉሥ ኃይለ ሥላሴ ቃለ ዓዋዲውና ሰበካ ጉባዔው በነጋሪት ጋዜጣ እንዲታወጅና ተቃዋሚወችን ሳይሰሙ በሥራ ላይ እንዲውል በመፍቀዳቸው በስንክሳር ሊጻፍላቸው በተገባ ነበር፡፡ 
 
አብዮቱ የነበረውን ስርአት እያፈራረሰ ሲቀጥል ይካሄድ የነበረውን ሕዝባዊ አለመረጋጋትና መናወጥ በመጠቀም በፓትርያርኩ ላይ የግል ጥላቻ የነበራቸው እምነተጎደሎወች? በፓትርያርኩ ላይ የሀሰት ውዥንብር ፈጥረው የዋሁን ህዝብ ቀሰቀሱባቸው፡፡ በሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ተወስዶ ጣሊያን አገር እየተማረ ያደገ ዶክተር ክነፈ ርግብ ዘለቀ የሚባል ሰው መሰሎቹን አሰባስቦ “ጊዜአዊ የተሐድሶ ጉባዔ” በሚል ስም በደርግ የሚታገዝ ድርጅት ፈጠረ፡፡ አጠቃላይ ጉባዔ በሚል ስያሜ በየደብሩ ያሉትን የሰንበት ተማሪወችንና በመጨረሻ ወደ ካዴሬነት የተቀየሩትን እነ ብህታዊ ቀለመ ካሣሁን የሚባሉትን ሁሉ አንደበተኞች አሰለፈባቸው፡፡ ጳጳሳቱንም ግማሾችን አቡነ ቴወፍሎስ እንዲወርዱ ባትስማሙ ትገደላላችሁ ብሎ በማስፈራራት እንዲወርዱ ባዘጋጀው ሰነድ አስፈረማቸወ፡፡ በወቅቱ የሲዳሞ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ከነበሩት ከአቡነ ጢሞቴዎስ በቀር ሁሉም ጳጳሳት ተስማምተናል ብለው ፈረሙ፡፡  

ቋንጃ ቆርጠዋል በአገር ላይም በደል ፈጽመዋል ተብለው የተመስክረባቸው ወንጅለኞች ከሚቀጡበት ቅጣት እጅግ በከፋ በዘግናኝ አገዳደል ደጃዝማች ወልደ ሰማእት በገለጹት አሰቃቂ ግድያ፡ ያለፍርድ አስገደሏቸው፡፡ በነገራችን ላይ ዶክተር ክነፈርግብ የሚባለው ሰው “ከወላይታ አባ መላኩን እንዳመጣለት ደጃዝማች ወልደሰማእት ከተደበቁበት ፈልጎ ላከኝ” የሚሉት ሰው ነው፡፡ 

ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ለመያዝ ይሞክሩ የነበሩት ለሀገር ቤዛነት ስትታገል የኖረችውን ቤተ ክርስቲያንን ጨርሰው ማጥፈት ባይችሉም ዶክተር ክነፈርግብን የወገን ጠላት መሳሪያ አድርገው ተግተው ይሰሩ የነበሩ ፡ የተከሰተውን የለውጥ ግርግር በመጠቀም “ሲጠበቅ የኖረ ፍርድ“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ የሐሰት ክስ ለህዝብ አንብበው በአሰቃቂ ግድያ አስገደሏቸው፡፡ “ሲጠበቅ የኖረ ፍርድ“ በሚል ተዘጋጅቶ በሞታቸው ላይ የተነበበው የሐሰት ፍርድ በዚህ አሰቃቂ ግድያ እንዲገደሉለት በፍቆትና በጉጉት ሲጠብቅ የነበረ ማነው? የዶክተር ክነፈርግብ ዘለቀ ተልእኮ ምን ነበር? ለምን ደጃዝማች ወልደ ሰማእት በመሳሪያነት ገቡበት? እያሉ ሊቃውንቱ በወቅቱ ይነጋገሩበት ነበር፡፡  

“ፓትርያርክ ቴወፍሎስ በቃለ ዓዋዲ ያዋቀሩት የሰበካ ጉባኤውም በሁለት አድሕሪወች በንጉሡና ፓትርያርኩ የተጀመረ ለአብዮቱ እንቅፋት ነው፡፡ መዘጋት አለበት” ብለው ፓትርያርኩን ያስገዱሉ ሰወች ፓትርያርክ ሆነው የተትኩትን ፓትርያርክ ተክለ ሃይማኖትን በማስተባበር ሰበካ ጉባዔው እንዲገታ አደረጉ፡፡ በዚያን ጊዜ አቶ በኋላ ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ አቡነ ቴወፍሎስ አቀደውት የነበረውን “ከፍጻሜ ለማድረስ ጥሪ (እራይ) አለኝ” ብለው የንቨርሲቲውን ጥለው ወደ ቤተ ክህነት እስኪ መጡ ድረስ ጨርሶ ተረሳ፡፡ 

ሊቀ ጉባዔ አበራ በቃለ ዓዋዲው የተዘረጋውን የአቡነ ቴወፍሎስን እቅድ በተግባር ለማዋል ቤተ ክህነቱ ቢሮ ብቻ ፈቀደላቸው እንጅ ስራውን የሚያካሂዱበት የጽፈት መሳሪያ በማቀበል እንኳ አልተባበራቸውም፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ ያለችበትን ሁኔታ ገልጸው “ቤተ ክርስትያኒቱን ማትረፍ የምንችለው አቡነ ቴዎፍሎስ ያቀዱት ተገባራዊ ማደረግ ብቻ ነው፡፡ እቅዱን ለምእመናን ለማድረስ የገንዘብ እጥረት ስለገጠመን እርዱን” ብለው ለዐለም አብያተ ክርስቲያናት ጻፉ፡፡ የዓለም አብያተ ክርስቲያንት የተወሰነ ገንዘብ ላከላቸው፡፡ 

እንቅስቃሴው በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በባህታውያን ተጀምሮ በየደረጃው ሲካሄድ ሊቀ ጉባዔ አባ አበራን የገጠማቸውን ፈተናና መንገላታት ሳስበው፡ በሚዘገንን ግድያ በተገደሉት በአቡነ ቴወፍሎስ ላይ የደረሰው ግፍ ይተካከለዋል ባይባልም በልዩ ጥሪ የመጡ በመሆናቸው እግዚአብሔር አስቻላቸው እንጅ ማንም ሰው የሚችለው አልነበረም፡፡  

ሊቀ ጉባ አባ አበራ እንደ ፓትርያርክ ቴወፍሎስ በሰው እጅ ባይሞቱም በደረሰባቸው ሕመመ ሲሰቃዩ በኮታና በዘር ቆቡን እያጠለቀ ለገባው ሁሉ መንገደኛ የሚደረገው እንክብካቤ እንዳልተደረገላቸው ስሰማ እጅግ አዘንኩ፡፡ የበለጠ እንዳዝን የደረገኝ በ20011  ዓ/ም ኢትዮጵያ በሄድኩበት ወቅት እስካሁን በገለጽኳቸው ትዝታወች ተገፋፍቸ መምሪያውን እምን ላይ እንዳለ ጎበኘሁት፡፡ 
በዚያን ጊዜ የሰበካ ጉባዔው መመርያ ኃላፊ አሁን በስደት ላይ ያሉት ፈንታሁን ሙ
ጨ ነበሩ፡፡ ከቢሮው ስገባ ከአቡነ ማትያስና ከአቡነ ጳውሎስ ፎቶግራፍ በቀር ቃለዓዋዲውን ቀርጸው ሰበካ ጉባዓኤውን የመሠረቱት ፓትርያርክ ቴወፍሎስንና ከፍጻሜ ያደረሱት ሊቀ ጉባዔ አባ አበራን የሚያስታውስ ነገር ባለማየቴ እጅግ በጣም ደነገጥኩ፡፡ 

የመምሪያ ኃላፊውን መምህር ፈንታሁን ሙጬን “ለቤተ ክርስቲያን የተሰው ፓትርያርክ ቴወፍሎስና ሊቀ ጉባዔ አባ አበራ ናቸው፡፡ እንዴት በዚህ ቢሮ እነሱን ይረሳሉ? የሚታወሱበት ስእላቸው እንኳ እንዴት ይጠፋል? ብየ ጠየኳቸው፡፡ እሳቸውም “ሰላቸውን ማግኘት አልቻልኩም” አሉኝ”” እንዳጋጣሚ የሊቀ ጉባዔ አበራ የቅርብ ቤተ ሰባቸው ዲያቆን ማንያዝዘዋልን እዚያው አካባቢ አገኘሁትና “የሊቀ ጉባዔ የአባ አበራን ፎቶ ግራፍ ማግኝት ትችላለህ? ብየ ጥየኩት፡፡ እሱም ፎቷቸውን ወዲያው አመጣና ለመምሪያው ሐላፊ አቀበላቸው፡፡
 
ፓትርያርክ ቴወፍሎስ በሞቱላት ሊቀ ጉባዔ አባ አበራ በተሰቃዩላት ቤተ ክርስቲያን ሁለቱም ይህን ያህል መረሳታቸው በግቢው የሚተራመሰው ሁሉ ባእድ መስሎ ታየኝ፡፡ በፈረንጅ አቆጣጠር 2004 ታሕሳስ 4 ቀን New Jersey ላይ የገጠመኝ ትዝ አለኝና በቤተ ክህነቱ የተሰገሰገው ሁሉ ከባእድነትም ወራሪ መስሎ ታየኝ፡፡ New Jersey የሄድኩበት ምክንያት በሚቀጥለው ጦምር እገልጽዋለሁ፡፡  

New Jersey ያለችው የአርመን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሁሉም የአኀት አብያተ ክርስቲያን ጳጳሳት ካህነትና ህዝበ ክርስቲያን የሚሳተፍበት ጉባዔ አዘጋጅታ ነበር፡፡ ያ ወቅት የከንሳስ ምእመናን ከሁሉም በመስማት እምነታቸው ለማወቅ የጓጉበት ወቅት ነበር፡፡ በአኀት አብያተ ክርስቲያናትና በኛ ያለውን ልዩነት ከሁሉም ለመረዳት የፕሌን ትኬት ገዝተው ላኩኝ፡፡  

በስብሰባው ላይ ቄስ ዘውድነህና ቄስ ግሪን የሚባሉ ጃማይካውያን ተወካዮች በማድረግ ልከው በስብሰባው ላይ አቡነ ማትያስ አልተገኙም፡፡ በተከናወነው ቅዳሴ ላይ ቀኖናው በሚያዝዘው መሠረት ዋናው ቀዳሽ ቄስ ለመንፈሳዊያን አባቶች በሚያቀርበው ተማኅጽና “O Lord our God, grant love stability and desirable peace to the world, to the holy Church and to all  Oreintal Orthodix Bishops and to our Chief bishops and venerable patriarchs; Catholikos Karekin 11; Pope  Shenouda 111, patriarch Abuna Theophilus, patriarch Zakka 1 and patriarch_Catholicos Mar Baselius Augen 1, (page  28) እያለ ቀደሰ፡፡ በሕይወት የሌሉትን አቡነ ቴወፍሎስን በህይወት ካሉት ከአኀት አብያተ ክርስቲያናት ፓትርያርኮች ጋራ ስማቸውን በማንሳታቸው ገረመኝ፡፡  

አቡነ ቴወፍሎስ ከሞቱ ከ28 አመታት በኋላ የተካኩትን ሶስቱን ፓትርያርኮች ትተው ለምን አቡነ ቴወፍሎስን ስም በሕወት ካሉት ከኦሬንታል ፓትርያርኮች ጋራ አነሷቸው ብየ ቅዳሴው አልቆ እስክ ጠይቅ ቸኮልኩ፡፡ ቅዳሴው አልቆ ጉባዓኤው በመካሔድ ሳለ ጠየኩ፡፡ የተሰጠኝ መልስ “አሁን በመተካካት ያሉት ፓትርያርካቸውን ከኮምንስቱ መንግሥት ጋራ በመተባበር በግፍ እንዲወርዱ  ተባብረው ያስገደሉ ናቸው፡፡ ስለ አቡነ ቴወፍሎስም በሰማእትነት መገደል የመሰከሩት ነገር ስለሌለ ለፓትርያርክነት የሚመጥኑ  ባለመሆናቸው ስማቸውን ለማንሳት ቀኖናችን ስለማፈይቅድ እንጅ እንደተተካኩ እናውቃለን” የሚል መልስ ነው ያገኘሁት፡፡ ይህ መልስ ፓትርያርክ ቴወፍሎስ በውጭ ተመልካች ያላቸው ክብርና በዚህ ከፍታ አለመረሳት፡ በተቃራኒው በራሳቸው ቤት በራሳቸው ሕዝብ መረሳታቸው ከራሴ ጀምሮ አረመኔነታችን ታየኝ፡፡  

አሁን በቀርቡ ደጃዝማች ወልደ ሰማእት ባንድ ሚድያ ስለ አቡነ ቴወፍሎስ አገዳደል የተናገሩትን የውጭ ክርስቲያኖች ቢሰሟቸው ንግግራቸውና አቀራረባቸው በፓትርያርኩ ላይ የነበራቸውን የራሳቸውንም የጥላቻ ስሜት በግልጽ የሚያሳይ ስለሆነ ራሳቸውን ደጃዝማቹን ከገዳዮቻቸው አረመኔወች አንዱ አድርገው እንደሚያወግዟቸው እርግጠኛ ነኝ፡፡ 
የደጃዝማቹ ንግግር ፓትርያርክ ቴዎፍሎስ በመያዛቸውና በመገደላቸው የራሳቸውን ተባባሪነት የሚያሳይ ሲሆን፦እየታነቁ እየተገረፉ በእሳት እየተጠበሱ በጦር እየተወጉና እየተሰየፉ ይህችን ዓለም ከለቀቁት ሰማእታት በከፋ አገዳደል እንደተገደሉ የቅዱስ ፓትርያርኩን ሰማእትነት አድርጎ አንጸባርቆታል፡፡ 

ፓትርያርክ ቴወፍሎስ በዚህ አይነት አሰቃቂ ግድያ የሚያስገድል በደል ሊኖርባቸው ቀርቶ፡ ደርግ መሬት ላራሹ ብሎ ከማወጁ በፊት ቀድመው ቤተ ክርስቲያንን ያላቀቋትን ፓትርያርክ መግደል ቀርቶ በአባትነታቸው ላይ ጥያቄ የሚያስነሳ አንዳች በደል አልነበረባቸውም፡፡ 

የጽዋና የሰንበቴ ማኅበራትን አጠቃለው ቃለዓዋዲውን ባዋቀሩበት ብሩህ ጭንቅላታቸው ቢቀጥሉ የቤተ ክርስቲያናቸውን እሴቶች ለመሳሪያነት አሳልፈው እንደማይሰጡና ከሕዝባቸው በፊት እንደሚሰለፉ ስላወቀ ደርግ የቤተ ክርስቲያኒቱን ኃይል ለመስበር ሲል ገደላቸው፡፡ ደርግ የቤተ ክርስቲያኒቱን ኃይል ለመስበር የጀመረውን ሂደት ወያኔወች ተቀብለው እንዴት እንደፈጸሙት ከዚህ ቀጥለን እንመልከት፡፡ 

  
ወያኔወች በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ የፈጸሙት ሰበራ 

ሻብያና ወያኔወች ኢትዮጵያን ለመበታተን ሕዝቡን ለመከፋፈል የዘረጉትን እቅዳቸውን ተግባራዊ ለማድረግ እንቅፋት የሆኑባቸው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያኒቱ የዘረጋቻቸው እሴቶቿ ነበሩ፡፡ ለዘረጓቸው የጥፋት አይነቶች እንቅፋት የሚሆኑባቸው እሴቶቿ ስለሆኑ አስቀድመው ቤተ ክርስቲያንንና ተከታዮቿን መምታት ነበር፡፡  

ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ለመመረቂያቸው ባዘጋጁት መጽሐፋቸው እንደገለጹት ወያኔወች አስቀድመው ካፈራረሷቸው ብዙ እሴቶች ዋናውቹ የጽዋማሕበርና የሰንበቴ ድርጅቶች ነበሩ፡፡ዶክተር አረጋዊ በርሔ “A Political History of the Tigray people’s  Liberation Front (1975-1991)” በሚል ርእስ ለDoctoral dissertation (page 302-3030) ባሳተሙት መጽሀፋቸው (page 246)  ላይ እንደገለጹት በደርግ የተጀመረው የማፍረሱ ተግባር በወያኔወች ተፈጸመ ፡፡ ከዚህ በታች ከመጽሐፋቸው የተወሰደውን እንመልከት፡፡   

“Thirdly, the TPLF launched a series of conferences or ‘seminars’ for selected parish priests in 1979 to win  them over The underling motive of the seminars was to isolate the church in Tigrai from the wider Ethiopian  church in order to foster Tigrian nationalism along the line of the TPLF’s strategic objective. Suppressed Tigrian  nationalism was invoked to challenge the dominant Ethiopian Orthodox Church. The initial woreda seminars for  priests were conducted by an eloquent TPLF fighter, Gebre Kidan Desta., a graduate of The Theological College at  Addis Ababa University The themes of the seminar were to replace the Ethiopian Church’s authority by a TPLF minded church and the language in the church with Tigrigna and, ultimately to further Tigrian nationalism and  identity. This process involved the mobilization of parish priests and ordinary Christians to isolate them from the  church’s national hierarchy. To weaken church authority, an intelligence group was formed under Sibhat Nega to  infiltrate the well-established monasteries in Tigrai such as Debre Damo, by planting TPLF members camouflaged  as monks and influencing church activities in the interests of the TPLF. . In 1987 and 1989, regional and national  conferences for priests were organized by the TPLF in the liberated territories to reshape the Tigrai church in line  with the TPLF programme.” A separate secretariat of the Orthodox Church was formed in the liberated areas of  Tigrai and was supposed to operate under the TPLF guidelines. Practically, the Ethiopian Church was divided in to  two separate secretariats, one under the regime and the other under TPLF. Both worked in Tigrai until 1990, when  the TPLF overran Meqele, the capital of Tigrai. The regime’s secretariat fled Meqele for Dessie and the secretariat in  the liberated territories entered Meqele and operated until the TPLF seized power in1991.” 

ወደ አማርኛ ሲተረጎም  

የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ግንባር በፈረንጅ አቆጣጠር በ1979 አመተ ምህረት አስተሳሰብ ለዋጭ የፕሮፓጋንዳ መርሀ ግብር ለሚመለምላቸው ቀሳውስት ዘረጋ። የማሰልጠኑ ዓላማ ቤተ ክርስቲያኗን ከህዝብ ለይቶ በመምታት ስፋቷን ማጥበብና በትግሬአዊነት ላይ ብቻ የተመሰረተ ስሜት በትግራይ ተወላጆች ጭንቅላት መክተት ነው። 

ቤተክርስቲያኗ ለረዥም ዘመናት በህዝቡ አዕምሮ ላይ ስትቀርጸው የኖረችውን ብሄራዊ የኢትዮጵያነትን ስሜት ከትግራይ ህዝብ አዕምሮ ጠራርጎ በጠባቡ ትግሬአዊነት ስሜት በመተካት የቤተ ክርስቲያኒቱን ይዘት እያጠበቡ ራሷን ቤተ ክርስቲያኒቱን መምታት ነው። 

የወረዳ ስልጠና የተጀመረው በጠንካራ ትግሉ የታወቀው ካዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በነገረ መለኮት ትምህርት የተመረቀው ገብረ ኪዳን ደስታ ነው። የስልጠናውም ይዘት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጠቅላላ መዋቅራዊ አስተዳደር በትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት ባለሟሎች መተካትና በቤተ ክርስቲያኒቱ አካባቢ የትግርኛ ቋንቋ እንዲሰፍን ማድረግ ነው። 

በዚህ መንፈስ ተቀረጾ የተዘረጋው እቅድ በየሰበካውና አጥቢያው ያሉትን ቄሶችና ምእመናኑን ቤተ ክርስቲያኒቱ ጠብቃ ካቆየችው ታሪክና ብሄራዊ መዋቅር እየገነጠሉ በማስኮብለል ወደ ነጻ አውጭው አምባ መሰብሰብ ነው። መነኮሳት በመምሰል ደብረ ዳሞ ወደ መሳሰሉት ገዳማት ሰርጎ በመግባት የድርጅቱን እቅድ በማስተጋባት የሚያዳክም አጥኝ ኃይል በስብሀት ነጋ መሪነት ተመሰረተ። የማሰልጠኑ ተግባር ከተፈጸመ በኋላ፤ የሰለጠኑት አስመሳይ መነኮሳት በትግራይ ምድር ዙሪያ ያሉት አብያተ ክርስቲያናት ከዋናው ጽፈት ቤት መገንጠልን በ1987 እና በ1989ተግባራዊ እንዲያደርጉት አደረገ። 

ከሁሉም እነ አቶ ስብሀት ነጋን እጅግ የከፉ ጠላቶች የሚያሰርጋቸው “The underling motive of the seminars was to  isolate the church in Tigrai from the wider Ethiopian church in order to foster Tigrian nationalism along the line of  the TPLF’s strategic objective.” ብለው በቤተ ክርስቲያን ላይ የዘመቱበት አዋጅ በድሮው አባ ሠረቀ በዛሬው አቡነ ሰላማ መፈጸሙ እጅግ የሚያሰደንቅ ነው፡፡ ከአማራው ጀምሮ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ከተጠመቀው ሁሉ ኦርቶዶክሳዊ ሕዝበ ክርስቲያን ይልቅ የትግራይ ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን የአቡነ ሰላማን አካሄድ ቢያወግዙት አማራጭ የሌለው ጥበብ ይመስለኛል፡፡ እንኳን የትግራይ ሕዝበ ክርስቲያን የኤርትራ ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን የአቶ ኢሳይያስን ፖለቲካ ተከትለው መከፈላቸው በሥጋና በመንፈስ ከመጎዳት በቀር የፈየደላቸው አንዳች ነገር የለም፡፡  

ደርግ በኮምኒስት ፍልስፍና የቤተ ክርስቲያኗን እምነትና እሴቶችን አፍርሶ ፓትርያርኩን በመግደል የጥፋት ሩጫዉን ጨረሰ፡፡  ወያኔወች ሕዝቧን በታትነው፣ አገሪቷን ከፋፍለው፣ የጥፉታቸውን ስልት ለብልጽግና አስረከቡ፡፡ ብልጽግና በተራው ከወያኔ የተቀበለውን የጥፋት ስልት በራሱ ቀይሮ ሕዝበ ክርስቲያኑን ከያለበት አሳዶ በመግደል፣ ከቤቱ በማፈናቀል አብያተ ክርስቲያናንና ገዳማትን በማቃጠል ከቻለ መደምሰስ ካልቻለ ለማዳከም በሩጫ ላይ ነው፡፡ 


መደምደሚያ 

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ሁሉም የዘመተባት ከኦሪቱ ጀምሮ እስከ ራእየ ዮሐንስ በተጻፈው ዘመናትን እያቋረጠች እስከ ዐለም ፍጻሜ ድረስ የሚከናወኑትን አሰናስላ በማያዟ ነው፡፡  
በአፍሪካ ቀንድ ባሉት አገሮች መካክል የክርስትና ደሴት ሆና በመቆዩቷና ለሀገር ሉዐላዊነት ተከላካይ፡ ለሰባዊ ክብር ቤዛ ሆና መቆየቷ፡ ዛሬ አገሪቱን በመምራት ላይ ያሉ ልጆቿ ስትታገላቸው በነበሩት ሰወች እየተጠመቁ፡ አጥማቂወቻቸው የሚናገሩትን በሚመስል ንግግር ያጠመቀቻቸውን ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እየከሰሱ ናቸው፡፡ ያጠመቀቻቸው ልጆቿንምም በጠላትነት ፈርጀው እያደኑ በመግደል ላይ ናቸው፡፡  
“እግዚአብሔር ለአብርሃም ለይስሐቅ ለያዕቆብ የገባውን ቃል ኪዳን አሰቦ ጩኸታቸውን ሰምቶ ሙሴ እስራኤላውያንን ነጻ ያወጣበትን”(ዘጸ 2፡24) የጽዋና የሰንበቴ ማሕበር ዘርግታ ቀጥላም በቃለ ዓዋዲው አዋቅራ ሕዝቧን ለሀገራዊ ክብርና ነጻነት እንዲሰለፍ ማድረጓም እንደጥፋተኛ እያስከሰሳት ነው፡፡  

እመቤታችን ክርስቶስን ስትጸንሰው “በክንዱ ብርቱ ሥራ ሠርቷል፡፡ በልባቸው ሓሳብ የሚታበዩትን በትኗቸዋል፡፡ ገዥወችን ከዙፋናቸው አውርዷቸዋል፡፡ ትሑታንን ከፍ ከፍ አድርጓቸውል፡፡ የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቧቸዋል፡፡ ሀብታሞችን ባዷቸውን ሰዷቸውል” (ሉቃ 1፡46_55)፡፡ብላ ያሰማቸውን የነጻነት መፈክር ኢትዮጵያውያን ላርበኝነታቸው ለነጻነታቸው መመሪያ በማድረጋቸው በእመቤታችንም ላይ የተዘመተበት ዘመን ነው፡፡ 

ኢትዮጵያውያን አርበኞች አሸናፊነቱንና ድሉን ለግዚአብሔር በመስጠት የቅድስት ድንግል ማርያምን የደስታና የድል መፈክር መመሪያ አድርገው በከፈሉት መስዋዕትነት ቅኝ ገዥወችን በኢትዮጵያ ላይ የዘረጉትን ዙፋናቸው አውርደውበታል፡ እየታበዩ የመጡትን በትነውበታል፡፡ በቅኝ ግዛት ውርደት ላይ ለነበሩት ጎረቤቶቿ በምሳሌነቷ ቅኝ ገዥወችን እንዳይመቿቸው አርገውባቸዋል፡፡  

ክርስቶስ “ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ ኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከኔም ተማሩ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና” ብሎ ሰውን ወደ ራሱ ከጋበዘ በኋላ፡ በሰው ላይ የነበረውን የሰንበትን ሸክም ዝቅ እንዳደረገና ሰውን ከወደቀበት ለማንሳት በመልካም ሥራ ተክቶ የሰውን ልጅ የሰንበት ጌታ ማደረጉን ተክትላ ሕዝቧን በሰንበቴ ማደራጀቷ (ማቴ 12፡7_8) በዐለም መድረክ ላይ ለነጻነት ትግል ደሐራዊትም ቀዳማዊትም አድርጓታል፡፡  

“በኦሪቱ ተንጠልጥለው እንደቀሩት እስራኤላውያን ሰንበትን እንዳታከብሩ፡፡ የቀደመ ትሪኳን ምልክትነቷን እንደማያውቁ አሕዛብ በዓላት አከባበር እንዳታከብሯት ” (ሰለስቱ ምዕት 20፡13)፡፡ ብለው ሰለስቱ ምዕት ያስተማሩትን አሰናስላ በመያዟ ቤተ ክርስቲያን ኩለንታዊት እንድትሆን አድርጓታል፡፡ 

ዕብራዊው ጸሐፊ “እያንዳንዱ ቤት በአንድ ሰው ተዘጋጅቷል፡፡ ሁሉን ያዘጋጀ ግን እግዚአብሔር ነው፡፡
 ሙሴስ በኋላ ስለሚነገረው ነገር ምስክር ሊሆን በቤቱ እንደ ሎሌ የታመነ ነበረ፡፡ ክርስቶስ ግን እንደ ልጅ በቤቱ የታመነ ነው፡፡ እኛም የምንደፍርበትን የምንመካበትን ተስፋ እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ ቤቱ ነን”(ዕብ 3፡1_6)፡፡ እንዳለው፦ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን በኦርቶዶክስ ክርስትና የተጠመቀ ሁሉ እንደ ሙሴ በሎሌነት ሳይሆን በክርስቶስ ያገኙት የልጅነት ጸጋ እስከ መጨረሻ አጽንተው ለመጠበቅ እንዲሰለፉ የቤተ ክርስቲያን ስርአት አድርገውታል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በተጓዘችባቸው ዘመናት ለኢትዮጵያ ያከናወነቻቸው ታሪኮቿ በውስጥና በውጭ ያሉትን አስተዋዮች ያስደንቃል፡፡ እኔን ለመሰሉትን ልጆቿን እጅግ ያኮራል፡፡ ጎረቤት አገሮችን ያስቀናል፡፡ ለመውረር ሞክረው ያቃታቸውን ያሳፍራል፡፡ ዛሬ በሚቀኑባትና ባሳፈረቻቸው ባእዳን ወኪሎች ተወራለች፡፡ በዮዲት በግራኝ መሀመድና በጣሊያን ወረራ ጊዜ ከገጠሟት ተግዳሮቶች እጅግ በከፋ ፈተና ላይ ወድቃለች፡፡ 

ይህ ዘመን ዕብራዊው ጽሐፊ ለዕብራውያን ክርስቲያን “የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ ባንዳንዶች ዘንድ ልማድ እንደሆነ መሰብሰባችንን አንተው እርስበርሳችን እንመካከር እንጅ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ”(ዕብ 10፡23_25) ብሎ የተናገረውን ሐዋርያዊ ትውፊት ቤተ ክርስቲያናችን ከመቼውም በበለጠና በላቀ ስሜት በተግባር እንድታውለው የምትገደድበት ዘመን ነው፡፡ ዛሬ ከሰማእቱ ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ቴወፍሎስ ብሩህ አዕምሮና ታማኝነት የላቀ እውቀትና ታማኝነት ያለው መንፈሳዊ መሪ ቤተ ክርስቲያናች አጥብቃ የፈለገችበት ዘመን ነው፡፡ ነገር ግን ከሰማእቱ ፓትርያርክ ከብጹዕ አቡነ ቴወፍሎስ የተሻለ ማግኘት ቀርቶ የእሳቸውን ምሳሌነት ይዞ የተገኘ መንፈሳዊ መሪ ያጣችበት ዘመነ መንሱት ነው፡፡ 

በዝርወት ያለችው የዋሸንግተን ቅድስት ድንግል እመቤታን ማርያም ምእመናን ሙሴ ከዮቶር የተማረውን ማኅበራዊ ሥርአትና የቅድስት ድንግል እመቤታችንን መፈክር ከስነ ሕሊናቸው ጋራ አዛምደው ራሳቸውን በማደራጀት ተቀዳሚ ምሳሌወች ሆነዋል፡፡ የጽዋ ማህበሩን ሰንበቴውንና በቃለ ዓዋዲው የተቀረጸውን የሰበካ ጉባኤውን መዋቅር ሳይለቁ በ12 ወራትና በ12 ሐዋርያት ተደራጅቶ የነበረውን የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴውን በየተወለዱበት ወራት ራሳቸውን አዘጋጅተውበታል፡፡ 

ቦታው ጌዜው በሚጠይቀንና በሚያስችለን መንገድ ከመቼውም አብልጠን ተስፋችንን እንድንመሰክር እንደንመካከር እንድንዋደድ እንድንነቃቃ መሠረታችንን ሳንለቅ ሰማእቱ ፓትርያርክ ካቀዱት ከጽዋው ከሰንበቴውና ከቃለ ዓዋዲው ሳንርቅ ያለንበት ቦታና የደረስንበት ዘመን በሚጠይቀን በተሻለ ብልሀትና ጥበብ ብንደራጅ፡ ራሳችንንም እናድናለን፡፡ ልጆቻችንን እናተርፋለን እንሻግራለን ላካባቢያችንም እኛነታችንን እንመሰክርበታለን፡፡ 

ይህን ተልእኮ ለመፈጸም በዝርወት ላይ ያለችው በሊቀ ማእምራን አማረ ካሣየ የምትመራው የዋሸንግተን ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም በተግባር አውለዋለች፡፡ ማሕበረ ምእመናኑ “እግዚ የሚፈሩ ታማኞችን በማታለል የሚገኘውን ጥቅም የሚጸየፉ  የመቶ የአምሳ የአስር አለቃ አድርገህ ሹምላቸው”” ብሎ ኢትዮጵያዊው ዮቶር ለሙሴ የነገረውን ጥበብ ተግባራዊ ለማድረግ ዐቢዩን ጉዳይ ማለትም መንፈሳዊ ምክርና ጥበብ ለሊቀ ማእምራን ትተው ከጧፍ ኩስታሪ እስከ ቤተክርስቲያን ቅጽር ያለውን ነዋየ ቅድሳት እየጠበቁ ለማስተዳደር እያንዳንዱ አባል ወደዚህ ዐለም በመጣበት ወር ተሰልፏል፡፡ “እኛም የምንደፍርበትን የምንመካበትን ተስፋ እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ ቤቱ ነን”(ዕብ 3፡1_6) የሚለውን ሐዋርያዊ ትውፊት መሠረት በማድረግ ከልሂቅ እስከ ደቂቅ ያሉት ምእመናን እምነታቸውንና ኅብረታቸውን አጽንተው ለመጠብቅ ለእግዚአብሔር ቤትነት ራሳቸውን ሠሩ፡፡ “ንሴብህ ጸጋኪ”  እያሉ የቅድስት ድንግል ማርያምን የደስታ መግለጫ መመሪያቸው አድርገው “ብጽዕት ሆይ ደስ ይበልሽ” በሚለው ምስጋና በታጀበ ዓቢይ ቃል “ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም” (ራዕይ 5፡12_13) እያሉ ልጇን ክርስቶስን እያመለኩ ናቸው፡፡ 
ይቆየን::

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

  ኦ ርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩ . ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡ በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያ...