በምንሞትለት አገር እንደ እንግዳ ሳይሆን እንደ ባለቤት ልንኖርበት ይገባል።
ደማችሁን ስጡን ነገር ግን መብታችሁን አትጥቀሱ የሚል የሴኩላሪስቶች የሃምሳ ዘመን ሤራ የሚያበቃው ለሁሉም የሚጠቅም እውነትን በፍቅር እና በአንድነት ስነጋገር ብቻ ነው።
ፖለቲካዊ ትክክለኝነት (political correctness) በቅዝቃዜ ጀምሮ በኑፋቄ አድጎ በክህደት የሚጠናቀቅ የሰይጣን ማታለያ በመሆኑ ኦርቶዶክሳውያን የሌሎችን ነጻ ፈቃድ ሳንጋፋ በአገራችን የሚገባንን መብት ሁሉ ሳናመነታና በሌሎች አጀንዳዎች ሥር ሳንወሸቅ በፍቅር ሁነን መወያየት መጠየቅና ማስከበር ይኖርብናል።
አንድ ሰው አንድ እስከ ሆነ ድረስ ሃይማኖት ከፖለቲካ ሲደባለቅ አደጋ አለው የሚለው ስብከት ሳይንሳዊም፣ አመክንዮአዊም፣ ተግባራዊ ምስክርነት የለውም።
እኛ የተሰቃየነው ከፖለቲካ ወጥተን በሴኩላሪዝም ወይንም በማርክሲዝም ስም ኦርቶዶክስ ጠል አካላት ሥልጣኑን ጠቅልለው እንዲይዙት እና ኦርቶዶክስ ጠል ሥርዓት ሕግ ሲሆን ዝም ማለታችን ነው።
ምንም እንኳ በሐሰት ተራኪዎችና የውጭ ጠላቶች ስብከት ቢጠለሽም የእኛ በትክክለኛው መርህ መገኘት እንደሚተረከው ስንኳንስ ሌሎች እምነቶችን ሊጎዳ ቀርቶ ለዛፎችና አራዊቶች የተረፈ ነበር።
እጄ ተቆርጦ ነበር ከሚለው እምነት ተጨቁኗል ከሚለው ሐስተኛ ዛሬ ነፍሰ ጡር ማኅፀን ከፍቶ ፅንስ እየሸለቀቀ ስለሃይማኖታችሁ አትሟገት ሲለን መቀበል "አጥፉን" ብሎ ፈቃድ የመስጠት አስሳስብ ነበር።
===============================
ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነት በዓለም ውስጥ በተጎታችነት ብቻ እየኖሩ የሚደበቁበት ሕይወት ሳይሆን ከግበበ ምድር እስከ ሮም ቤተ መንግሥት አሕዝባዊነትን ተዋግቶ የመቀደስ ጠቃሚ የንቃት ጉዞ ነው!!
================================
ይህን ማንነታችንን በመዘንጋታችን አሳዳጅ የፖለቲካ ባህል አድጎ ቤተ መንግሥታችን ውስጥ እና በየትውልዱ የፖለቲካ ንቅናቄ ደረጃ ጎልቶ መታየት ከጀመረ 60 ዓመታት አልፈዋል ሁል ጊዜ መሳሳት ግን ስንፍና ነው።
=====≠===========================
ዛሬን ስናስብ:-
ክርስቲያኖች ሁሉ ምናልባት በፕሮፓጋንዳ ብዛት ግራ ተጋብተው ፖለቲካን ለኢአማንያንና ለመናፍቃን ብቻ የተገባ የአገልግሎት ዘርፍ አድርጎ በማየት ራስን ማግለል ወይንም በማመንታት ወይንም በተጎታችነት በመሳተፍ በቤተ ክርስቲያን እና በልጆቿ ላይ ከውጭም ከውስጥም የተቃጣውን ጥቃት እንዲቀጥል ፈቅደናል ማለት ይሆናል።
በመርዛማ ትርክት ወለድ እየተገፋን ነው፣ እየተጨፈጨፍን ነው፣ እየተከፋፈልን ነው፣ እየተሰደድን ነው።
ይህ የስንፍና ጉዞ ለሁሉም በሚጠቅም ሁኔታ ማብቃት ወይም በእውነታው መርህ መቃኘት አለበት።
የሚያበቃውም በአገራችን ጉዳይ ሳንሽኮረመም እኩል ከሌሎች ወገኖቻችን ጋር ግልጽ በሆነ ዓላማ ያለ ድብብቆሽ በፍቅር ሁነን ስንሳተፍና ስንተማመን ብቻ ነው።
ዝም በሉ! ማንሾካሾክ ይበቃችኋል ማለት ግን ትክክለኛ አስተሳስብ አይደለም።
ከሌሎች ጋራ ሁነን የምንሞትለትን ነገር እንደ እንግዳ ሳይሆን እንደ ባለቤት ልንኖርበት ይገባል።
========================
የተለያዩ የንቅናቄ አካላት ሁሉ እየተነሱ የጥምቀት ልጆችን ዕውቀት፣ ሀለንተናዊ አቅም ፣ ላብ እና ደም እየተጠቀሙ በእኛ መስዋእትነት ለእምነታችንን ተፃራሪ የፖለቲካ፣ የአስተዳደር፣ የፖሊሲና የአጠቃላይ አኗኗር አውድ ሲፈጥሩ ኖረዋል።
የጥምቀት ልጆች መስዋእትነትና ደም ለክርስቲያኖች ተፃራሪ ለሆኑ ግቦች የጥፋት ተባባሪ ሁነው መዋል እንዳይችሉ በግልጽ አቅማችን የማንኛውም ትግል አካል አስተሳስባችን የተጠበቀ ሆኖ መገለጽ አለበት። በሴኩላሪዝምና ገለልተኝነት ስም በሚጠሉን ወይንም እውቅና በሚነሱን ቡድኖች እና ግለሰቦችን ያለ ማቅማማት ማስረዳት ክርስቲያናዊ ግዴታችን ነው።
==================
መታወቅ ያለበት
የዘለዓለም ሕይወታችን ብቸኛ መንገድ የሆነችዋን ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችንን የሚያሳንስ፣ በሕዝብ ሕይወት ውስጥ ሚና እንዳይኖራት የሚያስተምር፣ ታሪኳ እንዲጠለሽ የሚያደርግ ወይንም አይቶ የማይከላከል፣ አስተምሮዋ በአደባባይ ሳይሞገት ሰፈር ለሰፈርና በየካድሬ ማሠልጠኛው ሲጣጣል ዝምታን የሚመርጥ፣ "በአረጀና ባፈጀ" ስም የማናውቀውን አዲስነት የሚሰብክን አይቶ የማይቃወም ሁሉ ለክርስቶሳዊ አስተምህሮና ሕይወት የመመስከር ግዴታውን ያልተረዳ ብቻ ሳይሆን የጠላቶቻችን ሠራተኛ መሆኑ ነው።
የሕይወት ብቸኛ መሰላላችንን ኦርቶዶክስን ዒላማ የሚያደርግ አስተሳሰብ ብቻ ሳይሆን ክርስቲያኖችን ከእምነታቸው ለይቶ ለማይጠቅመን ሴኩላር ፖለቲካ ግብ ግብአትነት ብቻ የሚፈልገን፣ ነገር ግን ሁለንተናዊ ህልውና (መንፈሳዊና ሥጋዊውን አስተካክሎ) የማያረጋግጥ፣ ጀግንነታችንን ብቻ ለድብቅ ግቡ ብቻ ለማዋል የሚሞክር ማንኛውንም ቡድን ካለ ትክክል አይደለም።
አንድ አካል ምንም አይነት መስዋእትነት ቢከፍል የክርስቶስን የመስቀል ክፍያ ማሳነስም ሆነ መተካት አይችልም። መተካት ብቻ ሳይሆን ለማሳነስ መሞከር ከዘዓለም ሕይወት ህልውናችን የሚያስወጣን ነውና ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ሁሉ ሊቀበሉት የሚገባ እውነት አይደለም።
=============================
በዚህ ስሑት መንገድ የሄዱ የ፷ዎቹ ትውልድ እንዳደረጉት ሃይማኖታችንን ከሕዝብ ሕይወት
ለማሳሳት እና ለማስወገድ ጭምር የሚሞክር:-
👉 ከወጣት ተማሪ እስከ ፕሮፌሰር አስተማሪ፣
👉ከምንደኛ ቄስ እስከ ኢአማኒና ጎሠኛ ጳጳስ፣
👉 ከንዑስ ምንነት ፖለቲካ ታጋይ እስከ ምእራቡ ስግብግብ ተቋማት እና እስከ ሀገራችን ሤረኛ ተላላኪ ድርጅቶች
👉 ከእልቃይዳ እስከ ቦኩሃራም መፈልፈያ ዉሀብያ
👉 ከደርግ እስክ ብልጽግና
👉ከዑስታዝ እስከ ዑላማ ---- ማንም ይሁን ማን ፣ በምንም ቋንቋ ይናገር፣ ምንም አብረቅራቂ ግብ አለኝ ይበል -----
------- የዘላለም ሕይወታችን እንቅፋት መሆኑ ከታወቀ "የመስቀሉ" ጠላቶች ተብለው እስከ ሰማዕትነት ተቃውሞ ይገጥማቸዋል።
እንግባባ።
ለማንም አድልኦ በሌለው ፖለቲካዊ ትክክለኝነትና ቁማርተኝነት ሳይሆን እውነትን በፍቅር መናገር ሕይወትን ይሰጣል። በእርግጥ ጊዜአዊ ድሎችን ሊያመክን ይችላል እንጂ ለዘለቄታው ፍሬው ጣፋጭ፣ ዘለቄታዊነቱ አስተማማኝ ነው።
አስተያየቶች