የበዛ ራስ ወዳድነትና (የናርሲሲት ባሕርይ) የመሪነት ፈተናዎች በኢትዮጵያ
1) የኢትዮጵያ ሕዝብ የመስዋዕትነት የስነ-ለቦና፣ የነጽሮተ ዓለም (ስለ ራሳቸው፣ ስለ ሀገር፣ ስለ ዓለም፣ ስለ ትውልድ፣ ስለ አመራር) ጤንነታቸው ለብዙኋን ዜጎች በሚጎዳ ሰዎች እየተነጠቀ ከመከራ ወደ መከራ ተሻግሯል
2) መሪዎች በተፈጥሮ፣ በሀገር-ፈለቅ ትምህርት፣ በማኅበረሰብ ነባር ባህል፣ በተቀደስ ትውፊት የተገኙ ማያዎችን፣ እሤቶችን እና መዋቅራትን ዋጋ በማሳጣት የእነዚህ ሀብታት ጠላት በሆኑ የባእዳን ፍላጎትና አስተሳሰብ በመመራት ሀገራችንና ትውልዱን ክፍተኛ ግራ መጋባትና የህልውና አደጋ ላይ ጥሎታ
3) አሁንም ሀገራችን ከጥልቅ ወደ በለጠ መቀመቅ ወይንም ወደ ትንሳኤ የመሻገር መስቀለኛ ጎዳና ላይ ቆማለች። ሁለቱም መንገድ የሚወሰነው በተለያዩ ውስጣዊና ውጫዊ ሁኔታዎች ይኖራሉ። ነገር ግን ወሳኙ አዎንታዊ ተጋድሎአቸውን በሚመሩት ሰዎች ጤንነት ይወሰናል።
መሪዎች፦ ከቤተሰብ እስከ ሀገርና ዓለም ዐቀፍ የሕዝብን መስዋእትነት ለመልካም ወይንም ለጥፋት ያደርጉታል፦ ከደርግ እስከ ዛሬ ሕዝብ ይሞታል፣ ጠቂቶች ግን በደሙ ይነግዳሉ
በፖለቲካ፦ በሀገራችን ከቅርቡ ብንነሳ መንግሥቱ ንዋይ፣ መንግሥቱ ኃ/ማሪያም፣ የኢሐፓ መሪዎች፣ የሕወሃት መሪዎች፣ የኦነግ መሪዎች፣ የኢሕዴግ መሪዎች፣ የብልጽግና መሪዎች፣ የፋኖ መሪዎች፣
ወዘተ ጤንነት እና ውጤቱን ከታሪክ እውቀታችንና ምርምሮች በመነሳት አሁን እየተካሄዱ ያሉ የልዩ ልዩ አካላት ተጋድሎ አዎንታዊ ውጤት እንዲያስገኝልን የመሪዎቻችንን ጤንነት እየገመገምን ወደፊታችንን ማስተካከል እንድንችል ይህን ዝግጅት በተከታታይ ለማቅረብ ወድጄአለሁ።
መግቢያ
ይህ ዳሰሳዊ ጽሑፍ ዓላማዉ የበዛ ራስ ወዳድነትና አመራር(Narcissistic personalities & leadership) በአብይ አህመድና ጓዶቹ ፤ የሕወሃትና የአንዳንድ እየታዩ ያሉ የአማራ ፋኖ መሪዎች ሰብእና መገለጫዎችን በአጭሩ በመዳሰስ የኢተዮጵያ ሕዘብ በአጠቃላይ እና ለህልውና ተጋድሎ ራሱን የሰጠው የአማራ ሠራዊት ከታግድሎው ዋና ግብ የበለትጠ ስለራሳቸው በሚጨነቁ መሪዎች እየተመራ ሕይወቱን፣ የሚታገልለትን ሕዝብ ህልውና፣ የኢትዮጵያን መቀጥል ከንቱ እናዳያደርግ የንቃ! ደወል ማሰማት ነው።
የጥናቱ ዘዴ
1) በተግባር በሕወሃት፣ በብልጽግናና የፋኖ አደረጃጀቶች አምራር ውስጥ በተወሰኑ መሪዎች ላይ የሚታየውን ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያውቃቸውን እውነታ ማገናዘብ
2) በመሥመር ላይ (ኢንተርኔት ላይ) ተአማኒነት ያላቸው ሳይንሳዊ ጥናቶችን መሠረት ያደርጉ ጽሑፎችን ማገናዘብ
3) በቀጥታ (ከአብይ አህመድ በስተቀር) ግለሰቦችን ስም ባለማንሳት፣ ነገር ግን በተግባር እየሆነ ያለውን በምሳሌነት በማገናዝብና ከሳይንሳዊ ጥናቶች ጋር በማገናዝብ --- ተዳሷል።
የዳሰሳ ጥናቶቹ ጥቆማ
ናርሲስቲ ወይንም የበዛ ራስ ወዳድነት በኤ የትርጎምኩት የስነ-ልቦና በሽታ ያለባቸው ሰዎች የቤተሰብ፣ የአንድ ተቋም፣ ማኅበረሰብና ሀገር መሪ ሆነው ሲገኙ በየደርጃው ለመምራት ሥልጣን ባገኙባቸው ተመሪዎ ወይንም ትግዥዎች ላይ ከፍተኛ እና ሁለ-ግብ አደጋ ያደርሳሉ።
በሽታ ከሚገለጥባቸው ዋና ዋና ምልክቶች መካክለ ፦
1. ራስን አይተኬና ብቸኛ አድርጎ መመልከትና ማቀርብ ከሁሉ የሚበልጥበት፤
2. በማያቋርጥ ቋሚነት ባለው መልክ ትኩረት ለመሳብና ለመደነቅ ቅድሚያ ብመሥጠት የተጠመድ
3. የሌሎች ህመም፣ ስሜት፣ ህልውና፣ ፍላጎት እና ማንነት ፈጽሞ ትርጉም የማይሰጠው
እነዚህን 3 ባሕርያት የሚያንጸባርቁ ሰዎች መሪ ሲሆኑ፡
• ልዩ የታላቅነት ስሜት(Grandiosity) ፦ ያሰቡትና የተመኙት ሁሉ ያለ ጥያቄና ተቀናቃኝ ለእነርሱ ብቻ የሚገባቸው ይመስላቸዋል፣ ተዕቢተኞችና ብቸኛ የሆነ ልዩ ክብርና መብት እንደሚገባቸው ራሳቸውን ያሳምናሉ፣ አይተኬነት ይሰማቸዋል እና ይህንንም ለማሳመን የማያውቁትን እንደማያውቁ፣ የሠሩት ሁሉ በሌላ በማንም ሊሠራ እንደማይችል ለማሳመን ይደክማሉ፤
• ይገባኛል-አባዜ ( Entitlement)፦ በዚህ አባዜ ስነ ልቦና የተለከፉ ሰዎች አቅማቸው የላቀና ከሁሉ እንደተሻለ ስለሚያምኑ ያምናሉ፣ በዚህ ምክንያት ሌሎች ሰዎች ለእነርሱ ፍላጎትና ዓላማ መሳካት የማገልገል ግዴታ እንዳለባቸው ለማሳመን ይደክማሉ፣ ድካማቸውን ውድቅ የሚያደርግ ማንኛውንም ሰው ጠላት ያደርጉታል፣ እንዲህ አይነቱ ስነ-ልቦና ግኑኝነቶችን ያውካል፣ ግለሰቦቹንም የአእምሮ መታውክ ውስጥ ያስገባቸዋል ፤
• ልዩ ታላቅነት እና ይገባኛል አባዜ የተጠናወታቸው ሰዎች ወይንም ናርሲስት ሰዎች መሪ ሲሆኑ ከሁሉ የተሻለ አመራር የመስጠት ችሎታ ያላቸውና እስከ አሁን የተገኝ ድል ወይንም ውጤታማነት ሁሉ ያለ እነርሱ አመራር የማይታሰብ አድርገው ስለሚያምኑ ለዚህ አስተዋጻኦአቸው ልዩ ክብር፣ ጥበቃ፣ አንቱታና ጭብጭባ፣ ምስጋናና የዝና መናኛትን ይጠብቃሉ። ይህ ካልሆን ሤረኞች እንደ ከበቧቸውና ዋጋቸው እንዲረክስ እንድሚሠሩባቸው ስለሚያስቡ በጥርጣሬና በአንጻራዊ የሤረኝነት አዙሪት ውስጥ ይገባሉ፤
• በሌሎች ትከሻ ለግል ማትረፍ (Exploitation of Others) – የሌሎች ጓዶችን የድካም ውጤት ለራስ ማስመዝገብ፣ ባልደርቦችን የተለያዩ መርጃዎችና ዐሳቦች በማቅረብ ማምታት፣ እና ከጋራ ድልና ውጤት በላይ ለግል ትርፍ ቅድሚያ መስጠትን ሥራዬ ብለው ይከውኑታል ፤
• ሂስን መመከት (Resistance to Criticism) – አሉታዊ ተግባራቸው ላይ የሚሰነዘር ማንኛዉም ግብረ መልስ አይዋጥላቸውም፤ ትችት ሲያጋጥማቸው አድምጠው ከመማርና ከመለወጥ በተቃራኒ ራሳቸውን በማንኛውም መንገድ በመከላክል፣ አንዳንዴ ወድ ኃይል አምራጭም በማዘንበል ማንም እንዳይገዳደራቸው ዙሪያቸውን ያመቻቻሉ ፤
• የማይገባ ግብታዊ አካሄዶችን መሞከር (Risk-Taking & Impulsivity) – ናርሲሲት ስነ ልቦና ያላቸው መሪዎች በቅጡ ያልተጠና፣ ሌሎች ያልመከሩበት፣ በዘለቄታዊነት ከፍተኛ ኪሣራ ሊያስከትል የሚችል ውሳኔና እርምጃ ይወስዳሉ፤ የውሳኔአቸው ውጤት ለራሳቸው ሥልጣን፣ ዝናና ሌሎች ጥቅሞች ያመጣል ብለው እስከ ገመቱ ድርሰ በጓዶች፣ በማኅበረስብ፣ በሀገርና በዓለማ ላይ የሚያስከትለውን ችግር ለማጤን ፈቃደኛ አይሆኑም፤
• ሳቢና አጭብርባሪ (Charm & Manipulation) – ስነ ልቦናዊ ማንነታቸው መርዛማና አፍራሽ ቢሆንም ደጋፊ ለማብዛትና የግል ፍተወታቸውን ለማርካት ሲሉ አሳሳችና ብዙዎች የሚወዱትን በጊዜአዊነት በመናገርና በማድረግ፣ ወይንም በገንዘብና በስውር ደጋፊዎቻቸው በኩል የተክለ ሰውነት ግንባታ በማሳለጥ ተከታዮቻቸውን ይቆጣጠራሉ።
ናርሲሲት መሪዎች ባላቸው ራሳቸውን ብቸኛ ታላቅ፣ ዐዋቂ፣ አይተኬና ክብር እንደሚገባቸው ለማረጋገጥ ብለው በሚወስዱት ደፋርና ግብታዊ ውሳኔዎችና ድርጊቶች በአጋጣሚ ለአጭር ጊዜ ጠቃሚ ለውጦችና ውጤቶ ሊያስገኙ ቢችሉም፣ የሞራል ለክት፣ በሌላው የሰው ልጅ ቦታ(ጫማ) ሆነው እርምጃቸውን ስለማያሰሉ ለጓዶቻቸው፣ ለማኅበረስበእ እና ለሀገር ዘለቄታዊነት ያለው የማይቀለበስ አደጋ ሊያስከትሉ ይችላሉ።
ፋንታሁን ዋቄ፣ ግንቦት 2017 ዓ.ም.
ናርሲሲስት መሪዎች በሀገርና ማኅበረስብ ላይ ስላደረሱት አደጋ ከታሪክ ጥቂት ምሳያዎች
የዓለም ታሪክ በናርሲሲስት መሪዎች ምክንያት በተፈጠሩ አስቀያሚና አሰቃቂ ኩነቶችና ውጤቶቻቸው እንደተሞላ ለማሳየት ጥቂት ታዋቆ መሪዎችን በማንሳት ግንዛቤአችንን ማስፋት ጠቃሚ ነው። ሀገራችን ኢትዮጵያን ከሚያማቀቋት አያሌ መንሴዎች መካክል ዋንኛው የሀግሪቷን ውስብስብ ሁኔታዎችና ዐለም ዐቀፍ ግኑኝነቶች ማገናዝብ የማይችሉና በብዛ ራስወዳድነታቸው የታወሩ፣ ትችትና ምክር፣ ሞራልና ሃይማኖት፣ ታሪክና ተግባራዊ ተጨባች ሁኔታዎች ከጀመሩት የጥፋት መንገድ የማይመልሳቸው መሪዎች በሀገር፣ በጎሣ ንቅናቄዎች፣ በእምነቶች ቤት ሁሉ መፈጠራቸው አንዱ ነው። ብዚህ ሁኔታ ውስጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ “በሕግ አክባሪነትና ታዛዥነት” ስም ለአጥፊዎቹ አገልጋይ ሆኖ መገኘት፣ መብቱን ሌሎች ሰዎች ተሰውተው እንዲመልሱለት ነጻ አውጭ የመጠበቅ ሽባነት አዙሪት ውስጥ መግባት ነው።
በዓለም ታሪክ ከላይ የተገለጹ 3 የናርሲሲስት ምልክቶች የታዩባቸውና በዘመናቸው ለሀገራቸው እና ለዓለም መከራን ካተርፉ እና በሀገራችን ከምንመልከታቸው ናርስስቲክ ሰብእና ካላቸው መሪዎች መካክል፦
1) ናፖሊዮን ቦናፓርት – የዚህ ሰው የልዩ ታላቅነትና የይገባኛል አባዜ፣ ለራሱ የሰጠው የተጋነነ ሰበእናና ምኞት አጠቃላይ አውሮፓን በዘላቂነት የለወጠ ነበር። ምክር ባለመስማት ተዕቢተኝነትና ማን አህሎኝነት በክረምት ሩሲያን በመውረር የራሱን ፍጻሜ ብቻ ሳይሆን የአውሮፓንም ሁኔታ ወስኖታል።
2) ጁሊየስ ቄሳር፡ ይህ መሪ ራሱን “የዘላለም ግዥ” ብሎ የሰየመ ነው፤ ለሀገሩና ለዓለም አስፈላጊና የራሱን አይተኬነት፣ ልዩ ታላቅነት ለማሳየት ባደረጋቸው አዳዲስ እና ግብታዊ፣ ተቀባይነት የሌላቸው ውሳኔዎች ብዙ ጠላት ማፍራት ችሏል። በመጨረሻም በሰው እጅ ሞቷል።
3) ክልዮፓትራ – በምታበጃቸው ስትራተጂካዊ ጉድኝቶች፣ በልዩና ጥበበኛ ስልቶቿ ከፍተኛ የሥልጣን አቅም ደርጃ ላይ የደረስች መሪ ሆና ነበር። ይሁን እንጂ ሁሉንም የሥልጣን ምንጭና ዘርፍ ለመቆጣጠር በነበራት ከፍተኛና ያልተገደበ ፍላጎት ለውድቀት ተዳረገች ።
4) አዶልፍ ሂትለር– በሥልጣን ፍቅርና ሁሉን በመቆጣጠር ፍተወት በመታወሩ እና እንደ ማንኛውም ናርሲሲስት ሰው በሌሎች የሰው ልጆችና ሀገራት ቦታ (ጫማ ውስጥ) ሆኖ ማሰብ የማይችል ሰው መሆኑ በሰው ልጅ ታሪክ የጨለማ ዘመን፣ የደም ዘመን፣ የዕልቂት ዘመን፣ የፍጹም ዘረኝነት ዘመን ሊሰኝ የሚገባውን ክስተት በዓለም አምጥቶ በመጨረሻ ራሱን አጠፋ፤ ከራሱም አልፎ የርሱ የሥጋ ተወላጆቹ በመዋለድ እንዳይቀጥሉ አደረጋቸው።
5) ጆሴፍ ስታሊን – በፈጠረው ግለሰባዊ ከልት (አምልኮ መሰል ዕይታ) እና በፍጹም ጭካኔ ላይ የትመሠረተ ሁለ-ገብ አብዮት (በነባርነት ላይ ማመጽ) ወስን የሌለው መከራና ስቃይን በሩሲያና የቀድሞ ሶቮየት ሕብርት ሀግራት ሕቦች ላይ ጭኖ አለፍ።
6) ሄንሪ 8ኛ፦ ይህ ሰው ኢንግሊዝን 1509–47 የመራ ነው። ይህ ሰው ፍጹም አምባገነንነትና ሁሉን የመቆጣጠር ሉጋም የለሽ የሥልጣን ፍተወቱ እስከ ዛሬ ድርስ ዓለምን ለሚያውክ ከፍተኛ ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ቀውስ ምክኒያት ሆኗል። ናርሲሲስት ከመሆኑ የተነሳ በክርስትና ባህል የማይፈቀድውና የነግሥታት ሚስት ፈትቶ ማግባት ሃይማኖታዊ ቀኖና ዶግማ ለማድረግ ከካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አንድነት በመውጣት አንግሊካል የሚባል የንጉሥ ፈቃን ፈጻሚ የሐሰት ቤተ ክርስቲያን ፈጥሯል።
ከላይ ልናሙና ያነሳናቸው ናርሲሲስቲክ መሪዎች ግርማ ሞገስ፣ ሳቢና ተጸኖ አሳዳሪ ሆነው ቢከሰቱም የአመራራቸው ውጤት ዘለቄታዊ የዓለም እዳና መከራ እየወለድ ለትውልድ አሸክሟል።
የአብይ አህመድ ናርሲሲስታዊ ሰብእና መገለጫዎች የትኞቹ ናቸው?
አብይ አህመድ አሊ ከላይ ለናሙና ያነሳናቸው የ6ቱን ናርሲሲስት መሪዎች ማንነት ጠቅልሎ የያዘ ሲሆን፣ ከስድስቱም ልዩ የሚያደርገው ተለዋዋጭ፣ በራሱ ዜጎች ጥፋት የሚርካ፣ አዲስ ልማት ሳይሆን ነባሩን ነቅሎ የማያውቀውንና የማይዘልቅውን የሚተክል መሆኑ ነው።
ናፖሊዮን ቦናፓርት – ታላቅነትና የይገባኛል በሚል አባዜ የተለከፈና ለራሱ የተጋነነ የሰበእና ምስል የሚሰጥ ነብር፣ አብይ አህመድም እንደዚሁ በምሆኑ የጦር ጄኔራሎችን፣ አርቲስቶችን፣ ሚኒስቴሮችን፣ የሃይማኖት ሊቃውንትን፣ ፓስተሮችን፣ ዑስታዞችን፣ ጳጳሳትን ሁሉ ከበታቹ አስቀምጦ ለማስተማርና ለማሳነስ የሚደክም ሰው ነው። ናፖሊዮን ምክር ባለመስማቱና በራሱ ቅዠት በመመራቱ ሩሲያን በመውረር የገነባውን አውሮፓ ዐቀፍ ጠንካራ ሠራዊ አስጠፋ። አብይ አህመድም የማንንም ምክር ባለመቀብል መላውን ሀገር ወደ ጦርነት አስገብቶ መከላክያውን አስፈጅ፣ ዜጎችን አስጨረሰ፣ ኢኮኖሚውን አደቀቀ፣ የአንድ ሃይማኖት እና አንድ ክፍለ ሕዝብ አማራንና ትግሬን ለማፋጅትና በማጥፋት ተጠመደ።
ጁሊየስ ቄሳር፡ ራሱን “የዘላለም ግዥ” አድርጎ እንደሰየመ ሁሉ አብይ አህመድም ለዘላለም በቸኛ ንጉሥ ለመሆን ባለው ነዲድ የሥልጣን ፍተወት የመቶ ሺዎችን መኖሪያ በማፍርስና ወገንና ለስቃይ በመዳርግ በብድር ሁሉም እየመጣ ለእርሱ የሚሰግድበት ቤተ መንግሥት በመሥራት ማንነቱን ገለጠ።
ጁሊየስ ቄሳር:- የራሱን አይተኬነት ለማጽናት ባደረግው ጥረት ብዙ ጠላቶች አፍርቶ ለሞት እንደብቃው ሁሉ አብይ አህመድም ብዚህ ናርሲሲስት ዝንባሌው በ7 ዓመት ውስጥ በሁሉም የኢትዮጵያ ማኅበርሰቦችና ነባር ኢትዮጵያዊ እምነቶች ሁሉ ዘንድ ጠላት አፈራ፡፡ አብይን ከልብ በወዳጅነት የሚቀርበው አንድች ሰው የለም፣ የሚያጨብጭቡለት ለሆድ ያደሩና የርሱን ዘር የማጥፋት እኩይ ፕሮጄክት የሚደግፉ ጥቂት የውጭ-ግብ እምነቶች፣ የሐሰት ተርክትና ስሑት ርእዮት ያጨለማቸው ለጋ በጥቅም የተግዙ ወጣቶች ብቻ ናቸው።
ክልዮፓትራ : – ባበጅቻቸው ስትራተጂካዊ ጉድኝቶች፣ በልዩና ጥበበኛ ስልቶቿ ከፍተኛ የሥልጣን አቅም ደርጃ ላይ የደረስች መሪ ሆና እንድነበር ሁሉ አብይ አህመድ ጥበብ በጎደለውና አድሮ በሚጋለጥ የማታለያ ንግግሮቹ ጊዜአዊ ድጋፍ የሰበሰብ፣ ሰዎች በርሱ ፈንታ የተወረወረበትን ቦንብ በመቀለብ እስኪሰዉለት የወደዱት፤ እንዲሁም ተቃዋሚዎችን ሁሉ በማታለል ሰብስቦ ያከሸፍ ሰው ነው። ይህ ማንነቱ እንደጤዛ ረግፎና ተጋልጦ ሲገኝ በማሠር፣ በመግደል፣ በጦርነት ሥልጣኑን የሚከላከል ሆኗል።
ክልዮፓትራ ሁሉንም የሥልጣን ምንጭና ዘርፍ ለመቆጣጠር በነበራት ከፍተኛና ያልተገደበ ፍላጎት ለውድቀት እንደተዳርገች ሁሉ አብይ አህመድ በብኩሉ ፖሊስን፣ ሚሊታሪን፣ ደኅንነትን፣ የፋይናንስ መዋቀርን፣ ሚዲያን እና እምነቶችንና የባህል መዋቅራትን ጠቅልሎ ለመቆጣጠር ሲል የፈጠርው የኦርቶዶክስ ቤተ ከርስቲያንን ሲኖዶስና ምእመናን ሳይቀር ከፋፍሎ በማዳክም ተጠምዷል።
አዶልፍ ሂትለር:– በሥልጣን ፍቅርና ሁሉን በመቆጣጠር ፍተወት በመታወሩ እና በሌሎች የሰው ልጆች ተገብቶ ማሰብ ባለመቻሉ ምክንያት በሰው ልጅ ታሪክ የጨለማ ዘመን፣ የደም ዘመን፣ የዕልቂት ዘመን፣ የፍጹም ዘረኝነት ዘመን ሊሰኝ የሚገባውን ክስተት በዓለም ላይ አመጣ። ሂተለር በመጨረሻም በገዛ እጁ ራሱን እንዳጠፋ ሁሉ አብይ አህመድ ከልጀነቱ ጀምሮ እናቴ 7ኛ ንጉሥ ነህ ብላኛለች በሚል የንግርት እሥረኝነት በተፈጠረ ናርሲሲስት ስነልቦ እሥረኝነት ውስጥ ያለ ይመስላል።
አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ሕወሃትና ኦነግ-ኦሮሙማ ባሠመሩለት ኦርቶዶክስንና አማራን አጽድቶ፣ ኢትዮጵያን በትኖ እና ትናንሽ የጎሣ ሀገራትን ለመፍጠር በተቀመጠው ፍኖተ ካርታ መሠረት በእነዚህ ተመሳሳይ ግብ በአላቸው በሁለቱ ተቋማት ርእዮትና ትርክት ውስጥ ባደገበት የአስተሳሰብ ማኅቀፍ መሠረት ኢሕአዴግ በጀመረው መሠረት ኢትዮጵያን የጨለማ፣ የደም፣ የመክራ፣ የስደት፣ የሰቆቃና የመለያየት አገር አድርጓት ቀጥሎበታል።
ጆሴፍ ስታሊን: – በፈጠረው ግለሰባዊ ከልት (አምልኮ መሰል ዕይታ) እና በፍጹም ጭካኔ ላይ የተመሠረተ ሁለ-ገብ አብዮት (በነባርነት ላይ ማመጽ) ወስን የሌለው መከራና ስቃይን በሩሲያና የቀድሞ ሶቮየት ሕብርት ሀገራት ሕዝቦች እንደጫነው ሁሉ አብይ አህመድም “ብልጽግና፣ ኦሮሙማ፣ ኩሽ፣ ግራንድ ናሬሽን (ታላቁ ትርክት)፣ መደመር” በተሰኙ ባእድና ለሥልጣን ማዝለቂያ ይጠቅሙኛል ብሎ በፈጠራቸው ተለዋዋችና ተደጋጋፊ ከልቶች/እምነቶች ፍጹም ልብ አልባ ጨካኝ፣ ያለ ደም ውሎ የማያድር መሪ ሆኖ ተከስቷል።
ሄንሪ 8ኛ፦ ክፍጹም አምባገነንነቱና ሁሉን የመቆጣጠር ሉጋም የለሽ የሥልጣን ፍተወቱ ሃይማኖትን ሳይቀር ከፋፍሎ አዲስ መንግድ እንደከፈተ ሁሉ አብይ አህመድ ለሥልጣኔ መዝለቅ ተገዳዳሪ ይሆናሉ የሚላቸው እምነቶች፣ ባህሎች፣ ነባር መዋቅራትን በመከፋፍልና ጽናት ያሳዩትን በመፍጀት ሄንሪ 8ኛን አሥር እጥፍ በልጦታል። ሃይማኖታዊ ቀኖና ዶግማን በደብዳቤ በመሻርና ሐወሃት ሸርሽራ ወድ ጎሣ አገልጋይነት ያዋርደቻቸውን ጳጳሳት በመጠቅም ቀኖና ሐዋርያትን አስሽሮ የጎሣ የሆኑ ኢክርስቲያናዊ የሐሰት ጳጳሳትን መፍጠር ችሏል።
ግን ናርሲሲት ስነ ልቦና ያላቸውን ሰዎች የሚያፈራ ቤተሰባዊና ማኅበረሰባዊ ሁኔታዎች የትኞቹ ናቸው?
ለናርሲሲስት ሰብእና መፈጠር ብዙዉን ጊዜ ምክንያት ተደርገው የስነ ልቡና ጉዳይ ተመራማሪዎች የሚጠቀሰው በሕጻንነት ዘመን ተጋላጭ የሆኑበት ሁኔታዎች ናቸው። የተጸኖ አውዶች ማኅበራዊ፣ ትምህርታዊ እና የወላጅ ቤተሰብ ሁኔታዎች ተጸኖዎች ናቸው። እነዚሁ ሁኔታዎች በምን አይነት ሂደትና መንገድ ተጽእኖ እንደሚያሳርፉ ያሳያሉ፦
ሀ) ቤተሰባዊ ተጽእኖ
1) ከሚገባ በላይ የሆነና ያልተመጠነ ሙገሳ ውይንም ወቀሳ የሚያቀርብ ቤተሰብ– ከሚገባ በላይ የሚካቡ ወይንም የሚወቀሱ ልጆች ራስን በመከላከል ሂደት ውስጥም ሆነ ሙገሳውን እውነትና ከሌሎች የተሻሉ አድርጎ በመሳል ሂድት ናርሲሲስቲክ ሰብእናን ያዳብራሉ።
2) ትኩርት ማጣት፣ የክብካቤ ጉድለትና የስነ-ልቦና ጥቃት፦ የስነ-ልቦና ድጋፍ አጥተው ውይንም በተለዋዋጭና ቋሚነት በሌለው የወላጆች ጠባይና ሁኔታ ውስጥ የሚያድጉ ልጆች የማያቋረጥ ራስን ከሌሎች በሚያገኙት ግብረ-መልስ ማንነታቸውን ለማረጋግጥ ወደ መጣር አዙሪታዊ ዑደት ውስጥ ይገባሉ፤
3) ናርሲሲስት በሆኑ ወላጅ ቤተሰብ ውስጥ ማደግ፦ በዚህ ኑኔታ ውስጥ ልጆች ማጭበርበር፣ ራስን ማስቀደም፣ ሽሚያ፣ ነውርን አለማወቅ፣ የይገባኛል እና እሻላለሁ ባሕረይ ያዳብራሉ፤ እንደየኃላፊነት ደረጃቸው ሁሉን ጠቅለሎ የመቆጣጠር ጠባይ ያዳብራሉ፤
4) ከተግባራዊነት የራቀ ቅድመ-ግምትና ምኞት – ልጆቻቸው ልዩ ታላቅነትን ለመጨበጥ እንዲጥሩ የሚገፋፉ ወላጆች ልጆቻቸው በሚያደርጉት ነገር ሁሉ ጎዶሎነትና የሚጠበቅባቸውን፣ ወይንም እንዲመኙት በተደርጉበት የሕይወት አይነት ወይንም ሊኖራቸው ይሚገባቸው የስበና አይነት ውይንም በዚህ ዓለም ላይ ስለሚኖራቸው የበላይነት ቅድመ ግምት ልክ አለመገኘት ውስጥ ይወድቃሉ። ይህ ሁኔታ ትህትናን፣ ከሌላ ጋር እኩል መሆንን እንዲፈሩት፤ የእነርሱ ከማንም ያለመብለጥ ተጨባጩን እውነታ ላለመቀብል ለራሳቸው ሐሰተኛ ምስል በመፍጠር ናርሲሲስት እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። በአእምሮ ስለ ራሳቸው የሳሉትን ምስል እዉን ተደርጎ በሌሎች ተቀባይነት እንዳያገኝ ምክንያት የሚሆኑ አስተሳስቦችን፣ ሰዎችን፣ ተቋማትን፣ ባህሎችን፣ እምነቶችን፣ ትውፊትና ነባር ትርክቶችን እንደ ጠላት ይመልከቷቸዋል፤ አምቺ ጊዜና አቅም ሲያገኙ ያጠፏቸዋል።
ለ) ማኅበራዊ ተጸእኖ
1) ግለኝነትን የሚያጠናክር ማኅበራዊ ባህል (Culture of Individualism) – ከማኅበራዊ የጋራ ድልና ጥቅም የበለጠ ግላዊ አሸናፊነትን የሚያበረታታ ባህል ናርሲሲስት ባህርያትን በአባላቱ ላይ የመፍጠር እድሉ ሰፊ ነው፤ ከዚህ አንጻር ኦርቶዶክሳዊነትን፣ ሮማ ካቶሊክን፣ ፕሮቴስታንትን፣ እስልምናን፣ ሴኩላር አስተምህሮዎችን ሁሉ በመርመር የትኞቹ ግለኝነትን ወይንም ህብረታዊ አንድነትን እንዲሚያበረታቱ መገንዝብ የቻላል፡፡
2) ማኅበራዊ ሚዲያና የሌሎችን እውቅናና ተቀባይነት የማግኘት ዝንንባሌ: – በዚህ ዘመን የማኅበራዊ ሚዲያ መስፋፋት ሰዎች በግላቸው የመታውቅና ተቀባይነት የማግኘት ዝንባሌያቸው እንዲያድግ ወድ ናርሲሲስት ሰብእና እንዲሻገሩ አስተዋጻኦ አድርጓል፤
3) ጠንካራ የውድድር ከባቢዎች ውስጥ መገኘት :– በአካዳሚ ፣ በሙያ እና በገበያ ተወዳዳሪነት ውስጥ አሸናፊ ሆኖ ለመገኘት በሚደርግ የሀብት፣ የዝና፣ የክብር ሽሚያ ሂደት ናርሲሲስቲክ ሰበናዎች ይፈጠራሉ፤
ሐ) የቤተስበ መስተጋብር
1) በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሠረት ፍቅር/መውደድ (Conditional Love) :– ከእውነትኛና በሁኔታዎች የማይለዋወጥ የቤተ ሰበ ፍቅር ቀርቶ ጎሽታ መስጠትና ፍቅርን ሁኔታዊ አድርጎ መግለጽ ወይንም አዎንታዊ የቤተሰብ ግኑኝነት በልጆች አንድን ነገር መቻልና አለመቻል ላይ የተመሠረተ ሆኖ ሲገኝ ልጆች ናርሲሲስት ዝንባሌ ያዳብራሉ፤
2) ልጆችን የማወደዳርና የማበላለጥ ልማድ :– በልጆች መካከል የውድድር ስሜይ እንዲፈጠር ማድርግ ልጆች በራሳቸው መተማመን እንዲያጡ፣ ዘወትር እና በሁሉ ሁኔታ ውስጥ ራሳቸውን አሸናፊና የበላይ ለማድረግ በሚያደርጉት ጥረት የበላይነት ስነ-ልቦና ይፈጥርባቸዋል።
3) ተዋረዳዊ የመከባበር ግኑኝነት የተበላሸበት ሁኔታ፦ በአባትና እናት፣ በልጅና ወላጅ፣ በታላቅና ታናሽ መካከል መኖር የሚገባቸው ድንበሮች መፋለስ፦ በቤተሰብ መካከል የሚኖር ሚና፣ የክብር ተዋራዳዊ ደረጃ ሲደበዝዝ የቤተስቡ አባላት የመብት እና የይገባኛል ስነ-ልቦና ያዳብራሉ፤ አንዱ ሌላውን ወደማታለል ያዘነብላል።
በዓለም ዙሪያ በናርሲስት ባሕርያቸው ሀገራትን፣ ዓለምን ፈተና ላይ የጣሉ መሪዎች የወላጆቻቸው ወይንም የአሳዳጊዎቻቸው እና ያደጉበት ማኅበረሰብ ሁኔታ ተጸኖ ትልቅ ነው።
1. ናፖሊዮን ቦናፓርት – የተወለደው በዘመኑ መካከለኛ የሚባል ቤተሰብ በሚዲተራንያን ባህር ወስጥ ከደቡብ ፈርንሳይ ድንበር 170 እና ከሰሜን መራብ ጣሊያን 83 ኪሎ ሜትር ላይ በምትገኝ የፈርንሳይ ግዛት አካል በሆነች ደሴት በኮርሲካ ነው። ወላጆቹ ናፖሊዮንን ወደ ፈረንሳይ የሚሊታሪ ትምህርት ቤት አስገቡት፤ እርሱም በትምህርት ቤቱ አያል የጦር ስልትና ስትራተጂውን የቀመርው፣ለውደፊት ለማድርግ የሚሻውን ጸንሶ ተዘጋጅ። ተወልዶ ያደገበት ዘመን አገሪቷ ከፍተኛ የፖለቲካ አለመረጋጋት ያለበት በመሆኑ ለወደፊቱ የአመራሩ አይነትና ለማንነቱ አስተዋጾ እንዳደረገ ይታመናል።
1. አዶልፍ ሂትለር፦ የተወለደው እጅግ ወግ አጥባቂና ቁጥጥራቸው የጽና ቤተስብ በኦስትርያ ተወለደ። ከአባቱ ጋር የነበረው መግባባት አሉታዊና ሰላም የተለየው ነው። በልጅነቱ ከቤተሰቡና ከአካባቢው የተነፈግው ተቀባይነት በስነ-ልቦናው ጥልቅ ከሌሎች በላይ ሆኖ የመቆጣጠርና የመግዛት ዝንባሌና ፍላጎት አሳደረብት። አባቱ ፍጹማዊ ሥርዓት የማስጠበቅ ባህል የነበረው፣ እናቱ ተፈጥሮን የማድነቅ ትወዳልች፤ ሂትለር ላይ የሁለቱም ወላጆቹ ዝንባሌ አሳድሮበታል። በትምህርቱ ደካማ የነበረና ለሚበልጡት ሁሉ ድብቅ ጥላቻ በልቡ የሚፈለፍል ሆነ።
በቤተሰብና ትምህርት ቤት በኩል ከሚጫንበት ትርክትና ባህል በትጨማሪ በግል የስነ ልቦና ብልሽቱ ላይ ሂትለር ጸረ-ሴማዊ ርእዮተዓለም እንዲያዳብር ያደረጉት የዘመኑ ሁኔታዎች አሉ ፡-
1. ግላዊና ማኅበራዊ ተጸኖዎች፦ አንዳንድ ታሪክ ጸሐፊዎች እንድሚጽፉ በቬይና ውስጥ ጸረ ሴማዊ ትርክቶች ይሰራጩ ነበር እና ሂትለር ከወጣተነቱ ጀምሮ በእነዚህ ተጽኖዎች ሥር ወድቋል።
[ Madeleine M. Neiman: In her research paper, An Education in Hate: The “Granite Foundation” of Adolf Hitler’s Antisemitism in Vienna, Neiman examines how Hitler's exposure to Viennese culture, political figures like Georg Ritter von Schönerer and Karl Lueger, and anti-Semitic newspapers shaped his ideology. ሂትለር በዘመኑ የቬይና ፖለቲካ ወስጥ ተክለ ቁመናቸው ክፍ ያሉ እንደ ጆርጅ ሪትተር ቮን ስቾነረር እና ካርል ሉኤንገ/ጀር ኋላ ለተገለጠው ማንነቱ አስተዋጾ አድርጓል። ]
Guido von List and Lanz von Liebenfels: እነዚህ የታውቁ የዝመኑ ግዙፍ ተክለ ሰውነቶች በስዊዘርላንድ ቬይና ውስጥ የቬና አራያን ታላቅነት የሚያቀነቅን ንቅናቄ ነበራቸው። ይህ ሂትለርን የዘር ጥላቻ ዶግማ እንዲያበቅል አድርጎታል።]
2. Political Opportunism ፖልቲካዊ ስግብግብነት: ሂትለር ጽረ ሴማዊነትን ብዙም ማሰብና መፈላሰፍ ሳይጠበቅበት ተከታዮችን ለማፍራት እና ለማስተባበር አንድ የጋራ ጠላት እንድሚያስፈልግ በማመኑ እንደ ሥልጣን መወጣጫና መግዣ ዕድል አድርጎ ወስዶት ነበር። በማኅበረሰቡ ዘንድ የንበሩ ማንኛዉም ችግሮችና እርካታ ማጣት መንሴዎቹ አይሁዶች ናቸው የሚል ትርክትን ማቅረብ የምታኔ ሃብት፣ የማኅበራዎ ስነ-ለቦና መዛባት፣ ሳይሠሩ መበልጸግ ለሚመኙ ሰነፎች፣ አንዱ ሲጠፋ ለሌላው ያልፋል ብለው የተመኙና የተታለሉ ሁሉ ከኋላው እንዲሰልፉ ማድርገ ችሏል።
o ሐሰተኛ ሳይንሳዊ-መሰል ዘረኝነት፡- (Pseudo-Scientific Racism): በሂትለር የስነ-ለቦና ብሽታ አንጻር የተፈጠረውን ዘረኝነት፣ የሕሰት ትርክትና አይሁድ በፍጥረታቸው ከሰው የሚያንሱ ነገር ግን ለተውለድና ሀገር አደግኛ እንድሆኑ በፖልቲክኞችና ቡድኖች ሲዝዋወር የኖረውን ትርክት ሳይንሳዊ ለማስመሰል ሐልዎቶች ተፈጥሩ፣ ምርምሮች ተደርግው የአራያን ታላቅነት የሌልቹ ታናሽነት ተርጋገጠ የሚሉ እንድ ሕወሃይና ኦነግ አይነት ምሁራን ተነሱ። በሽተኛው መሪ ራሱን እንዳያይ ስህተቱን እንዳያርም በዚያው አባሱበት።
o የጀርመን በ1ኛው የዓለም ጦርነት መሸነፍና የቨርሳኢሌ ውል ፦ ለመሸነፏና በኢኮኖሚ መዳከሟ አይሁዶች እጅ እንዳለበት በመተረክ ጥላቻ ማቀጣጠል፤ (አባ ሰርቀ የትግራይ ችግር ከአማራ መዳቀላችን ነው እንደሚለው) World June 28, 1919 ይህ ስምምነት ጀርመን ግዛቶቿ እንዲቆነጻጸሉ፣ (ለማሳሌ Alsace-Lorraine ለ France, Eupen-Malmédy ለBelgium, እና ሰፊ የድንበር ክልል ለ Poland)፤ ከ100 ሺ በላይ ሠራዊት እናዳታደራጅ፣ ለጦርነቱ መንሴዋ ሙሉ በሙሉ እርሷ እንደሆነች፣ ለጦርነቱ ኪሣራ ክፍያ እንድትፈጽም፣ ሊግ ኦፍ ኔሽን ሲመሠርት ለጊዜው መገለሏ --- ለሂትለር የስነ-ልቦማ በሽታ መታከሚያ ፖልቲካዊ እድል ፈጥረለት፤--- ይህን ተጠቅሞ ጀርመኖች እንዲከተሉትና ለ2ኛው ዓለም ጦርነት እንዲዘጋጅ ተመቸው።.
3. ፕሮፓጋንዳና የቡድን ዕሳቤ ስነ-ልቦና ባርነት፦ የናዚ ፕሮፓጋንዳ ጸረ-ሴማዊነትን ከማጠናከሩም በላይ አይሁድን የተለየ ምልክትና ማንነት ማስጠት፣ ማጠልሸትና ከሰውነት ማሳነስ የፖልቲካዊ ማእከላዊ ሞተር ሆኖ የጀርመንን ዝርያ ጥራትና ከፍታ ማንጸሪያ ሆነ። ናዚ ሊፈጥረው ፈለግው የጀርመን ብሔርተኝነትና ልዩ ማነንት የፍልስፍና መንሻ ተደርገ። በኛ ሀገር ትግራዋይና ኦሮሞን ለመተርጎም የግድ ንፍጠኛ፣ ኢትዮጵያ፣ ኦርቶዶክስ የግድ መንሻ እንደተደርጉት ማለት ነው።
እነዚህን የተጠቀሱትን ጉዳዮች በመጠቀም ሕዝብን አሳውሮ ማስከተል በመቻሉ ሂትለር በተክታዮቹ በጀርመኖች፣ ዒላማ በትድርጉት አይሁዶች፣ በሁለተኛው ጦርነት በተፈጠርው ሁለግብ ጥፋት አሰቃቂና ለዓለም ሁሉ የትርፈ ጥፋት ተከሰተ። በእኛ ሀገርም የኤርትራ፣ የትግራይና የኦሮሞ ነጻ አውጭዎች በፈጠሩት የሐሰት ትርክት፣ በረጩት ስሑት የትውሶ ርእዮት የስነ-ልቦና ቀውስ ያላቸውን የጎሣ ነጻ አውጭ የተከተሉ ጎሣዎች፣ ዒላላማ ያደርጉት ኦርቶዶክስ ክርስቲያንና አማራ እስከዛሬ መፍትሄ ያልተገኝለትና መቋጫ በሌለው መከራ ውስጥ ተገኝቷል።
4. ጆሴፍ ስታሊን፦ በድኽነት ውስጥ ተውልዶ ያደግ፣ እጅግ አስክፊ የፖልቲካ ሂድት ባልበት ዘመንና ማኅበረሰብ ውስጥ ማደጉ ጭካኝና ምህረት የለሽ ስነ-ልቦና ቀርጸውለታል። የአመራር ዝይቤዉም ከዚህ ከልጅነቱ ካጋጠመው ሁኔታ የመነጭ ነበር። በአመራሩ ላሳየው ኢሰባዊና አፍራሽ ጠባዩ መፈጠር አስተዋጾ አደረጉ ከሚባሉት መካከል፦
o በልጅነቱ ባልተርጋጋ ቤተስብእ ውስጥ ማደጉ፦ ጎሪ በተባልች የጆርጀያ ከተማ ያደገው ስታሊን አባቱ ጠጭ ሰካራም፣ እናቱንና እርሱን ዘወትር የሚደበድብ ሰላም የሌለው ቤተሰብ ነው። ይህ ሁኔታ ያለ በቂ ምክንያት መጠራጠርን እና ጭካኔን ይዞ ለመገኘቱ አስተዋጾ አድርጓል።
o ትምህርትና አብዮታዊ ዕሳቤዎች፦ ስታሊን በምጀምሪያ ትምህርቱ በሴሜናሪ ገብቶ ያጠናው ነገር-መለኮት ነበር፣ ግን ወድ ኋላ ወድ ማርክሳዊ ርእዮት እና አብዮተኝነት ንቀናቄዎች ተሳብ። ብዚህ ጽንፈኛ የፖልቲካ ረእዮት ውስጥ መሳተፉም ወድ ኋላ ላይ ላሳየው አምባገነናዊ አምራርና ማኅቀፈ ዕሳቤ መያዝ አስተዋጾ አድርጓል።
o ሳይኮፓቲክ ባሕርይ ( Psychopathic Traits) : አንዳንድ የታሪክ ጸሓፊዎች እና የስነልቡና ባለሙያዎች ጆሴፍ ስታሊን ሳይኮፓቲክ ለምሆኑ የሚያቀርቡት ማሳያ፦ በሌላ ሰው ጫማ ሆኖ አለማሰቡ፣ አታላይነቱ፣ እጅግ የበዛና መንሻ የሌልው መጠራጠርን የመሳሰሉ የበሽታው ምልክቶችን ነው። በትግባር ይህ ሰው ተቀናቃኞቼ ናቸው ወይንም ሊሆኑ ይችላሉ የሚላቸውን የቀርብ ጓዶቹን ሳይቀር ለሥልጣኑ መጽናትና ሙሉ የምቆጣጠር አቅም ለማረጋገጥ በጭካኔ ይገድላል፣ ያሥራል፣ ያሳድዳል።
o ፖለቲካዊ ውጥንቅጥና የሥልጣን ሽኩቻ፦ የስታሊን ወደ ሥልጣን መምጣት ሂደት ፖለቲካዊ አለመርጋጋትና ግራ መጋባት ባለበት ሁኔታ ውስጥ፣ መካካድ፣ አንዱ ሌላውን የማባረር፣ የተሰላና በጭካኔ የሚፈጸሙ መጠፋፋቶች በነበረበት ሂደት ውስጥ በመሆኑ፣ በቮልሼቪክ አብዮትና በሶቮየት አስተዳደር ውስጥ ያያቸው ፖለቲካዊ ክህደቶችና ጭካኔዎች በውስጡ የነበረውን ሁሉን የመቆጣጠር ስነ-ልቡና አጠናከረለት ።
o በጥርጣሬና በፍርሃት ላይ የተመሠረተ አመራር፦ የስታሊን አጠቃላይ አመራር ይታወው የነበረው ፖልቲከኞችን በገፍ በማባረር፣ ሰዎችን ወደ አሰግዳጅ የሥራ ካምፖች በማጋዝ፣ በማሠር እና ብዙኃኑን በመሰለል ላይ የተመሠረተ ነበር።
ናርሲሲስት አእምሮዎች በብዛት የሚፈጠሩባቸው ባህሎች
ክርስትና የሰውን አኗኗር እግዚአብሔርን የሚያስደስት እንዲሆን ያስተምራል። በዚህ ትምህርት ውስጥ የሚፈጠር ቤተሰብ፣ ማኅበረሰብ፣ እና በዚህ ውስጥ የሚፈጠር ሰብእና ግቡ ሰው የሆነውን እግዚአብሔር እኢየሱስ ክርስቶስን መምሰል ነው። ራስን ለሌሎች መስጠት። ኃያል ሆነው እያሉ በደካሞች እጅ በፈቃድ መሰጠት የስሑታንን ልብ በአራያነት አቅንቶ ወደ እግዚአብሔር ማመልከት ባህልን፣ የቤተሰብ አኗኗርና ልጆች አስተዳደግን፣ የማኅበረሰብእ ገዥ ባህል እና እምነት ወሳኝ ሚና አላቸው። ኦርቶዶክሳዊ ከርስትና እና ከዚህ እምነት አስተምህሮ የሚመነጭ ባህል ቅድስና፣ ንጽህና፣ ድንግልና በአካልና በህሊና መከታተል፣ በልክ መኖር፣ ልሌላ መትረፍና መሰዋት፣ ሀገርና ሕዝብን፣ ትውልድና ዓለምን በፍቅር ለማገልግልና መልካም አራያነትን የሚያሳስብ ስነልቦና ያበረታታል። ትህትና እና አገልጋይነት ከፍተኛ ዋጋ አላቸው።
በሌላ በኩል ብዙ እምነቶችና ባህሎች፣ በመላምታዊ ሀልዎቶችና ፍልስፍናዎች ግለኝነትን፣ ራስን ለማስደሰት ባካንባ መዝናናትን፣ ቅድሚያ መውሰድን ታሳቢ አድርጎ በሚኖር ሕይወት ውስጥ እያንዳንዱ ሰው በውድድር፣ ራስን ከፍከፍ በማድርግ፣ ታይታና ዝና፣ መወደድና መፈራትን፣ መከበርና መገልገልን ዒላማ ያደረጉ አኗኗር ላይ ስለሚያትኩሩ ናርሲሲስት ባህርያት እንዲፈጠሩ እድል ያሰፋል።
• ቅጥ የልሽ መዝናኛ (Extravagant Rituals): የበዓላት አከባበርን ቦርቶዶክስ ክርስትና ስንመልከት እጀግ የብዛ ፈንጥዝያ የላቸውም፣ ትኩርታቸው በጋራ ምስጋና አምልኮ ነው። ቀላል፣ በመንፈሳዊ ጥልቀት ማደግና ትምህርታዊ ዓላማ፣ በታውቀና በተውሰነ ሥራዓት የሚመራ ነው። ሌሎቹን ስንመልከት የያንዳነዱ ሰው ስሜት እርካታ፣ ታይታ፣ የስን ልቡና ጭንቀት ማስወግጃ መዝናኛ ላይ ያተኩራሉ። ስሜትን፣ የግል ትርጉምን፣ ውድድርን የሚያበረታቱ ናቸው።
• ንጽህናና ድንግልና: የሥጋ ድንግልና፣ ሀሳብንም ለማንጻት፣ ልብን ለማቅናት የሚደርግ የቃልከዳን ሕይወት ነው። በገዳማዊ ሕይወት ውሰጥ ድንግልናና ንጽሕና የሥጋ ፍላጎትን በመግደል ራስን የክርሰቶሰ ሙሽራ አድርጎ ሕይወት ሙሉ በሙሉ በስቅል ፍቅሩን ለግልጸ አምላክ የፍቅር ምላሽ መስጠት ነው። ትኩርቱ በምንፈሳዊ እድገትና ምጥቀት ላይ ነው። በዓለም ያሉ ኦርቶዶክሳውያንም በአቅማቸው የገዳማውያን ቤተሰቦቻቸውን አራያ በቅናት የሚመልከቱና በሚቻላቸው ሁሉ መነኮሳትን በሕይወት ለመምሰል የሚጓጉ በመሆናቸው ሂዶኖስቲክ ደስታን ፍለጋ ወድ ናርሲሲስት ዝንባሌ ሊያጋድሉ አይችሉም።
• ገዳማዊ የትርህምት ሕይወት፡ ገዳማዊ ሕይውት ራስን የመካድ ሥራዓት ነው። መነኮሳትና መነኮሳይት ራሳቸውን በሁለንተናው ለመወስን ቃል ገብተው ከዓለም ሁካታና ቤተ ሰብእ ረቀው የሚጋደሉብት ነው። ተጋድሎው ከሌላው በዓለም ከሚኖር ክርስቲያን በተየ እግዚአብሔርን በጥልቀት ለመዋሀድ በጸሎት፣ ጾምና እና ባለተወሳሰብ የአገልግሎት ሕይወት ነው። በዚህ ሕይወት ውስጥ ትኩርቱ ትህትናና ሌላውን ማገልግል፣ ጽሎትና ጾም ላይ ተጥምዶ እግዚአብሔርን ማየት ስለሆን ራስን ከሌላው አግዝፎ ወድሚያሳይ ይናርሲሲስት ስነ ልቦና የሚወስደው መንገድ ሁሉ ዝግ ነው። በሌሎች እምነቶች፣ ፍልሰፍናዎችና የፖልቲካ ረእዮቶች አንጻር የሚፈጠር አኗኗር ሰዎች ራሳቸውን ከሌላው የተሻለ አድርገው እንዲቀርቡ የሚገፋፋ አውድ ይፈጥራል።
እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እና ታላቁ ቅዱስ ባስሊዮስ ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አባቶች ስል ትርህምት ሕይወት አስፈላጊነት በስፋት አስተምረዋል ጽፈዋል። ክርስቲያን በልኬታ የተገደበ የታወቀ ስነ-ሥራዓት በመጠን መኖር ነው ሲሉ አስተምርዋል። የዚህ አይነት ሕይወት ናርሲሲስት ባሕርያትን አያበቅልም፤ ሽሚያና ስስት፣ ቁማርና ብልጠት አይፈጠርባቸውም።
አስተያየቶች