የአማራ የህልውና ተጋድሎ ያገባኛል ስላልኩ --- እንዴት እና ለምን እንደሚያገባኝ እነሆ ጻፍኩ፦-
አደራ አደራ፦ ያልተጻፈ የምታነቡ፣ ያልተነግረ የምትተነትኑ፣ ፈሪሃ እግዚአብሔር የሌላችሁ፣ እውነት የማያስጨንቃችሁ፣ አማራ ወገናችሁ ሌላ አማራጭ ዐሳብ ባለመስማት እናንተን እንዲያመልካችሁ የምትሹ የህልውና ትግሉ ጠላፊዎች ከዚህ ገጽ ራቁ።
=======================
ወደ ጽሑፉ ----
ግልጽ እንነጋገር። የእውነተኛ ፋኖነትና በፋኖነት ሥር የተደበቀ የጎጥ ሽፍትነት ይለያያል።
ለትግሉ ውጤታማነት ስለሚጠቅም በማለባበስ በሽታን ታቅፎ መንፏቀቅ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከሚናፈቀው በጎሣ ፖልቲካ ከመጣው አጥፊ ማዕበል ታድጎ ከእርፍት ወደብ አያደርስም። ካደረሰም አያዘልቅም። ከዘለቀም ቀጣይ መጠፋፋትን ይተክላል እንጂ በፍትሕ፣ በእውነት፣ በክብረ-ስበ፣ በፍቅርና መተማመን ላይ የተመሠረተ የአንድ ቤተ ሰብእ የሚያኖር ሰላምን ማንበርና ዋስትና መስጠት አያስችልም።
አማራን ከአማራነት እሤቶቹ በሚቃረነው በጠላቶቹ ነጽሮተ ዓለም እና የፖለቲካ-ሠራሽ ማንነት ለመተካት አማራን ለህልውና አደጋ ከዳርጉት አካላት ዐስተሳስብ በመዋስና ስልታቸውን በመከተል አማራን ከአጥፊዎቹ ለመታደግ የሚመኝ ቡድን ፈጽሞ ከአማራነትና ከታሪካዊ “ፋኖነት” ጋር እጅግ የተለያየ አስተሳሰብ ነው። ፋኖነት ተውሶ፣ ቁማር፣ ወደ ዶግማነት ያደገ አግላይ ጎጠኝነት፣ ሤራ፣ ወገንን በሐሰት ፕሮፓጋንዳና በገንዘብ ኃይል፣ ሌላውን በመግደል፣ ታሪክና እምነትና በመካድ፣ ከባእዳን ተዋውሎ የሕዝቡን መስዋእትነት የሚከፈልለት ግብ በግለሰቦችና ቡድኖች ፍላጎት ማርኪያ አንጻር ቀርጸው የሚትክሉት ባዕድ ረእዮት አይደለም። ፋኖነት በሰባዊነት፣ ፍትህ፣ እውነት፣ ግልጸኝነት፣ ነባርነት፣ መተማመን፣ ቃል ኪዳን አክባሪነት፣ መስዋእትነት መሶሶዎች ላይ የሚቆም የሕዝብ እሴት ነው።
አማራ በእውነት ከህልውና አደጋ ለመዳን የሚያደርገውን ተጋድሎና መስዋእትነት ውጤታማ ለማድርግ ከፈለገ እንዲህ የበል፦ “እኔን አማራውን የሚያጠፋኝን አካል አጥፊ አድርጎ ያቆመው የእኔ የአማራነት እሤቶቼ መጠላት ነው። ዒላማ የመደርጌ ምክንያትም ይኼው ከደሜና አጥንቴ ልዩነት ሳይሆን ከሰባዊነት፣ ከባለታሪክነት፣ ከአትንኩኝ ባይነት፣ ከአገር አፍቃሪነት፣ ከእግዚአብሔር ሕዝብነት የተገኘ ማንነቴ እንደሆን አውቃልሁ፤ ይኽን እያወቅሁ ራሴን ለማዳን አጥፊዎቼን መምሰል የግድ ነው” ብዬ ልነሳ ብሞክር የአጥፍቶ መጥፋት መርኅን እንጂ የአማራነትን የአሸናፊነት ምሥጢር መሶሶዎች፦ የፍትሕ፣ የእውነት፣ የሰባዊነት፣ የታሪካዊነት፣ የሕዝበ-እግዚአብሔርነትን ነቅዬ በተሸናፊዎቹ ጠላቶቼ ልክ ራሴን ማሳነስ እንድሚሆንብኝ አእውቃለሁ። ይህንን ዕውቀቴን፣ እውነቴን፣ የህልውና ዋስትና ማረጋገጫ የኃይል ምንጬን ለማድረቅ አትሞክሩ። የምትሞክሩ ካላችሁ ወዳጅ መሳይ የውስጥና የውጭ ጠላቶቼ እንደሆናችሁ ዐውቃለሁ።’
ፋኖነትን ጠምዝዘው “የማራ የህለውና አደጋ ምክንያት የሆኑ እንደ ሕወሃትና ኦነጋውያን አይነት ዘረኝነት ካላሰብኩ፣ ፋሽስታዊ ርእዮት ካልጋትኩትና ጭፍና መንጋ አድርጌ ካልጋለብኩት፣ እና የአማራ ጠላቶች ነጻ እናውጣህ ብለው ነጻውን ክፍለ-ሕዝቦች የባርነት ስነ-ልቦና ውስጥ በማስገባት፣ በስሜት ነጻነትን ባርነት፣ ባርነትን ነጻነት ብሎ እንዲያምንና በጭፍን መንጋነት የፖልቲካ ልሂቃን ሤራ ማስፈጸሚያ አድርገው ለመከራ እንደ ዳረጉት፣ አማራንም በጠላትነት እንዳስፈርጁት አይነት ስልት በምቅዳት አማራን ከነባር ማንነቱ፣ እምነቱ፣ ባህሉና ታሪኩ ነጥዬ ዕቃ ካላደረግሁ አላሽንፍም” የሚሉ ቡድኖች ሁለት ጊዜ ማሰብ ይጠበቅባቸዋል።
ጠላቶቻችንን ለማሸነፍ ጠላቶቻችንን እንምሰል ማለት አመክንዮአዊና አዋጭ ከሆነ ይህን የሚያምኑ ሰዎች ለምን ጦር ሜዳ ወረዱ? ለምን ሕዝቡን መስዋእትነት ያስክፍሉታል? ለምን አንደኛቸውን ወስነው ታሪካቸውን፣ እምነታቸውን፣ አገራቸውን፣ ባህላቸውን፣ ሰብአዊ ክብራቸውን ሁሉ ሊመስሏቸው ከሚጓጉላቸው የሕውሃትና ኦነግ ተቋማት ጋር ተስማምተው አማራ አገር ዐልባ፣ እምነትና ታሪክ-የለሽ፣ ስደተኛ የአፍሪካ ጅብሲ እንዲሆን ፈቅደው ውይንም ሕውሃት ሁሉንም የትግራይ ክልል በሚለው ድንበር ውስጥ የሚኖሩ ንዑሳን-ማንነቶች ሁሉ ጨፍልቆ ትግራዋይ፣ ኦነግ/ብልፅግና ኦሮምያ ውስጥና ዙሪያ የሚገኙትን ማንነቶች ሁሉ ጭፍልቆ የኦሮሙማ እምነትና ማንነት ልብስ ሊያለበሰው እንደሚጥርው ሁሉ አማራ ለሁለት ተከፍሎ እንደየቅርበቱ ክፊሉ የፖለቲካ-ሥር ትግራዋይ፣ ሌላው ደግሞ ፖልቲካ-ሥር ኦሮሞ በመሆን ራሱን አያክስምም? አማራ ነባር አማራነትን የህልውና ትግሉ አካል ለማድርግ በማይፈልጉ የፖልቲካና የትግሉ ልሂቃን አየር-ወለድ አዲስ ማንነት ዙሪያ ተሰልፎ መስዋእትነት መክፈሉ ሃይማኖቱን፣ ባህሉን፣ ታሪኩን፣ ኢትዮጵያ ርስቱን ሁሉ የሚተው ከሆን የሚዋጋው “አማራ” የሚባል ከሰው እሤትና ታሪክ፣ ሰብአዊ ክብርና ፍትሕ ጋር ቁርኝት የሌለው የማይጨበጥ መንፈስ ነው ወድሚል ድምዳሜ ያደርሳል። የትምታታ እና ትርጉም የሌልው ርእዮትም ነው። ፋኖን እንምራ የሚል ሰው ሕዝቡን እየማገድና መክራውን እያራዘመ የሚያልመው የአማራ አይነት ምን እንደሆን ወጥቶ በግልጽ፣ በትጻፈና በትሰነድ መንገድ ግልጽማድረግ ይጠበቅበታል። ከዚህ ውጭ ራሱን ከአጥፊዎች ለመታደግ የወጣውን ሕዝብ እየሰዉ ከዓላማው ውጭ ስለ ግለሰቦች አራት ኪሎ መንገሥ ብቻ እያወሱ ውይንም ወደማይታወቅ ግብና ሁኔታ ማድረስ ወንጀል ይሆናል። ይህ ግልጽ ያልሆን በፕሮፓጋንዳ ላይ የተንጠለጠለ ሞቅታ ሌላ የከፋ የህልውና አደጋ የሚጋብዝና በእርጋታ ማሰብን፣ ምክክርን፣ ከግለኝነት መላቀቅን፣ በባዕዳን ምክርና ድጋፍ መዋዠቅ ማቆምን ይጠይቀናል።
የአማራ ልጆች የሚዋጉት፣ የሚሞቱትና የሚገድሉት “አማራ” ለሚባል “ሃይማኖት፣ ታሪክ፣ ትውፊት፣ ፍትህ፣ ባህል፣ እሤት፣ ርስት፣ ሰብአዊ ክብር” ለማያስፈልገው ሆድና ሥጋን ብቻ ከሥልጣን ጋር ለሚያልም ግዕዛኑን ተነስቶ ለመሪዎቹ ባርያ ለሚሆን መንጋ ማንነት ዐልቦ ሕዝብ ለመፍጥር እናድልሆን ሳይታለም የተፈታ ነው። ጥያቄው፦ የአማራ “ህልውና” “አማራ” ለተባለ ስያሜ፣ ለአማርኛ ቋንቋ እና የየጎጡን ራስ-ነገሦች ለአራት ኪሎ ለማብቃት በቻ ነው ወይስ ሙሉ ሰባዊ ክብርን እስከነ ርስቱ፣ እምነቱ፣ ባህሉ፣ ትውፊቱና የርዥም ታሪኩ ትርክት ጭምር ነውን?
ወይስ አማራን በባዕዳን ፍላጎት፣ በዘረኞች ሕገ መንግሥትና ላልፉት ብዙ አሥርት ዓመታት በመሬት ላይ በትውልድ አእምሮ በተቀጹት ስሑት ርእዮቶችና ሐሰተኛ ትርክቶች አንጻር በተፈጠረ አደገኛ አውድ ውስጥ አማራን ከርክሞና አሳንሶ በተፈቀደለት ልክ ፖልቲካ-ሥር አዲስ ማንነት አልብሶ ማስቀመጥ? ይኽ ክሆን መስዋዕትነት ሳይሆን የሚያስፈልገው፦
1) የብልጽግና መንግሥት ወንጅሎቹንና አገር የማፍረስ ፕሮጄክቱን ሕጋዊ የሚያደርግበትን ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን ዕውቅና መስጠትና ብያኔውን መቀበል፣
2) ኦነግ/ብልጽግና እና ሕወሃት ከፈጣሪዎቻቸውና ከደጋፊዎቻቸው ጋር አማራን በማግለል የተፈራረሙትን ለታላቋ ኦሮምያና የትግራይ ሪፐብሎክ ምሥረታዎች ዝግጅት የመጀመሪያ እርምጃ ተደርጎ የትቀመጠውን የፕሪቶሪያ ስምምነት መቀበል
3) በምሥራቅ አፍሪካ ክሚያሰጋው የኦርቶዶኦክስ ክርስቲያን ጽንፈኝነት ያሰጋናል እና ራሳችሁን የኦሮቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንና በክርስቲያን ላይ የሚፈጸመውን የማጽዳይም ሆን ትውልዱን ከእምነት የማስወጣት ሂድት ፈጽማችሁ እናዳላያችሁ በማለፍና “ትግላችን ከእምነት የነጻ ሴኩላር ነው በሉ” በተባላችሁት መሠረት መታዘዝ
4) የአብይ አህመድን ዘር አጥፊ ወንጀለኛ ሠራዊት ከክልሉ እንድናስወጣላችሁ እናንተም ሕወሃት ካሠመራቸው ድንበሮች ውጭ ያሉትን የአማራ እና የኦርቶዶክስ ማስጽዳት ፕሮጄክት ይመለከተናል እንዳትሉ በተባላችሁት መሠረት በምስማማት ካዕላይ ባዴን ሆናችሁ የጎሣ ውያን ፌዴሬሽን እንደ አዲስ በሽግግር መንግሥት ስም እንዲመሠርት መቀበል
----- የአማራን ኢትይጵያዊነት መሠረዝ እና ክልላዊነት መቀበል፣ አምራነት እምነት፣ ባህል፣ እሤት፣ እውነትና ፍትሕ የማያስፈልገው የዘር ማጥፋት የ50 ዘማናት ትራፊና ለወደፊቱም የህልውና ዋስትናና ሀገር የማይኖረው በሚያደርግ ብያኔ የምትስማሙ ከሆን እየተካሄድ ያለው “የህልውና ትግል” እንድ ስያሜው የአንድ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ክፍለ-ሕዝብ በክብር የምኖር ዋስትና ማረጋገጭ ሳይሆን የጥቂት ሰዎች የፖልቲካ ሥልጣን መቆናጠጫና የሃብትና ክብር ማግኛ መሣሪያ ብቻ ነው።
ይህ ካልሆነ እና የአማራ ማኅበረስብ ሁለገብ መስዋእትነት ከንቱ እናዳይሆ የአማራን ህልውና እስከን ነባር አማራነቱና ዋስትና ሰጭ አውድን በምሥራቅ አፍሪቃ በሚፈጥር ርእይ፣ ግብ፣ ስልት፣ መርኅ፣ ሂደት፣ ግልጸኝነት ያለው አቋም የሚመራ ከግለስቦችና ቡድኖች ያልተገልጹና የተነግሩ ፍላጎቶች ነጻ ማድረግ ያስፈልጋል።
በመጨርሻ ለፋኖ መሪዎች መለእክት፦
ሕይወታችሁን ለሕዝባችሁ ለመስጠት ቆርጣችሁ ከወጣችሁት መካከል የተወሰኑት ተሰውተዋል፣ የተወሰኑት በቂ ሕክምና በማያገኙበት ሁኔታ ውስጥ ቁስላቸው እያመረቀዝ በክፍተኛ ህመም ውስጥ ይገኛሉ። ሁላችሁንም አለማክበር ከሰውነት ያሳንሳል። እናም ሰው ለመሆን የምሞክር ክርስቲያን ስለሆንኩ አከብራችኋለሁ። የምቸለው አገልግሎት ከተገኘም እታዘዛችኋለሁ።
እኔ የማልደራደርባቸውና የምቃወማቸው ነግሮች በጣም ጥቂቶች ናቸው፦ ክብረ-ስብእ፣ እውነት ራሷን ሰው ሆና በገለጠችበት መንገድ፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንና የክርስቲያኖች ህልውና፣ ፍትሕ፣ ኢትዮጵያ፣ ሰውን ሰው የሚያደርጉና ከጭፍን መንጋነት ነጻ የሚያደርጉት ቋሚ የሰው ልጆች ነባር እሤቶችን የሚሸረሽሩ ሢራዎችን፣ አስተምህሮዎችን፣ የትግል ስልቶችንና ከጠላት ጋር የሚደረጉ ጉድኝቶችን ብቻ ነው።
ዙሪያችሁ ያለው ሁሉ ቅዱስ፣ ሁሉም ተጠርጣሪ ሊሆን አይችልም። ነገር በእናነተ መልካም ስንዴዎች መካክለ ግን በጠላት የተዘራ እንክርዳድ አይጠፋም። ስለሆነም ለህልውና ትግሉ ውጤታማነትና የውጤቱ ዘለቄታዊነትን በሚመለከት በሚቀርቡ የፈቃድ ምክር ለጋሾች አሳሳችነት፣ በገንዘብ ደጋፊዎች ጫና፣ በፕሮፓጋንዳ ግራ አጋቢነት ስሕተቶችን ብትሠሩ የሚጠበቅ ነው። ከእናንተ የማይጠበቀው ከየመንደሩና ከየማኅበሩ ወሬ ለቃቅማችሁ ሳታረጋግጡ "እገሌ የተባለው ግለሰብና ቡድን የማራ ትግላ ጠላት ናቸው" ወደሚለው ሰሚኑና በአንድ የውጭ ኔትዎርክ አንቀሳቃሽ የፋኖ አመራር አባል (የበዕር ስሙ ዖዝያን) በተርጨ የሐስት መለእክት መሠረት ሚዲያ ማዝመት ይቅርባችሁ።
እኔን ፋንታሁን ዋቄ በሚመልከት ከዖዝያንና መንጋዎቹ ውጭ ያላችሁ አመራሮች በሙሉ "ለአማራነት" (ደምና አጥንት ብቻ ሆኖ ወድ ፋሽስት ርእዮተ-ዓለምና ስነ ልቦና ያለትገፋውን ማለቴ ነው) ታማኞች እንደሆናችሁ አምናለሁ። አቅም የለኝም እንጂ በምችለው ሁሉ ድጋፌን መሥጠት ፈቃዴ ነው።
እንደ አንድ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያንም እና የኦርቶዶክሳውያን በሥራአቱና በዘር ፖለቲካ ዒላማ መደረግ እንደሚያንገበግበው ዜጋ ስንኳንስ የጥምቀጥ ልጆችን ቀርቶ ከጽንፈኛው የአይሲስ፣ የአልቃይዳ፣ የቦኩሃራም፣ የአልሻባብ ቀፍቃፊ ኢንኩቤተር ዉሃብያ ውጭ ያሉቱ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች (ኢትዮጵያዊ የሚባል እስልምና የለም ከሚሉት እንደ አንዳንድ ዑስታዞች ጽንፈኛ አስተምህሮ ሳይሆን) ለቤተ ክርስቲያን ጠላት ናቸው ብዬ አስቤም ተናግሬም አላውቅም። በሐሰት ትርክት አጠገባችሁ ሆነው የሚያሳስቷችሁና "ትግሉን ከሃይማኖት ነጻ ነው" የሚል ያልተባራራ ዐረፍተ ነገር በመወርወር እና ከሞዐ ተዋህዶ ግብር ኃይል ጋር ሊያጠራጥሯችሁ የሚሠሩትን እንደ ዖዝያን ያሉ ሤርኞችን እወቁባቸው።
======================================
ለበለጠ ግብረ መልስ በእነዚህ ማስፈንጠሪያዎች ሁሉ ለመወያየት አለሁ።
ከሰው አንባ ወደ ጎሣ ቡድን ዕሳቤ እሥረኝነት ያልወረዳችሁ ባለነጻ አእምሮ ወዳጆቼን ብቻ ነው የጋበዝኩት። ዘረኞችና ተላላኪዎች በነዚህ ገጾች ላይ ብትገኙ የእናንተ ድምጽ ዋጋ ስለማያወጣ እንዳትጎዱ ራሳችሁን አርቁ።
ትዊተር https://x.com/fwakie
ቴሌግራም @Fantahun_Wakie
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/@Orthodoxy-VS-Secularism
https://www.youtube.com/@finoteretuan-2
ፌስ ቡክ. https://www.facebook.com/profile.php?id=61576051634449
https://www.facebook.com/fwakie
ቲክቶክ፡ https://www.tiktok.com/@fantahunwk?_t=8qLqoSRV9Ta&_r=1
ብሎግ፡ https://ethiopiaorthodoxchristian.blogspot.com/
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
አስተያየቶች