የህልውና ትግል ሃይማኖትን አይመለከትም ለምትሉ ጥያቄ እና ሤራችሁን የማጋልጥበት መለእክት አለኝ፦
👉 የህልውና ትግላችን ሌሎች ፍላጎቶችን አያስተናግድም ማለት ምን ማለት ነው?
👉 የሃይማኖት ነገር አይነሳ ማለት ምን ማለት ነው?
👉 ህልውናን መታደግ የማኅበረሰቡን ሥጋዊ አካል ብቻ ነው?
👉 ህልውና ሃይማኖት፣ ታሪክ፣ ርስት፣ ቅርሥ፣ ትውልዳዊ ተስፋ፣ ማኅበራዊ ትሥሥር፣ ዓለም አቀፋዊ ትሥሥር፣ ቀጠናዊ ሰላም አይጨምርም?
👉የህልውና ተጋድሎ በምእራባውያን ፍልስፍናና ይሁንታ ብቻ የሚትረጎም ነው?
ከእኔ ዐሳብ የትሻል የሙስሊሙና ክርስቲያኑ የሃይማኖትና የታሪክ ልሂቃን ይህን ሰውር ሤራ ማክሽፍ የጠበቅባችኋል።
============================================
በአንድን ክፍለ-ሕዝብ ላይ እየተሞከረ ያለው ድምሳሴ ከተሳካ የሚያጠፋው የማኅበረስቡን፡-
1) አባላት (ሰዎችን) እና የትውልድ ቀጣይነትን
2) ባህሉን
3) ሃይማኖቱን
4) ታሪኩን
5) የስነ-መንግሥትና የእምነት አሻራ የሆኑ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሦቹን
6) ማኅበረ-ሰበእ-ፈለቅ ዕውቀቶቹንና ጥበቦቹን
7) ቋንቋዎቹን
8) ርስቶቹንና ማኅበራዊ ትሥሮቹን ወዘት ሁሉ ነው።
የህልውና ተጋድሎ የሚታደገው 8ቱንም ለማዳን ነው።
ዛሬ ላይ ግን በአማራ የህልውና ጠላቶችን አጥፊ ፍልስፍናዎች የወረሱ ወይንም ባለማወቅ የጠላት ሤራ ሰለባ የሆኑ አንዳንድ የፋኖ ልሂቃንና መሪ ካልሆንን ሞተን እንገኛለን የሚሉ ሰዎች "የአማራ ህልውና በ1ኛው ተራ ቁጥር ላይ የተገለጸውን ብቻ የመለክታል---
--- የተቀረው ግን ያረጀ፣ ያፈጀ፣ የጃጀ ስለሆነ እኛ በምንበይነው ይተካልና ትግላችን ለሌሎች ፍላጎቶች ዝግ አድረገናል፣ አያስተናግድም፣ ጣልቃ አትግቡብን!" ማለት ጀምረዋል።
ሌሎች መሠሪዎች ደግሞ ትግሉ "እንዲ ካልሆነ፣ የእገሌ ሃይማኖት ስሙ ክተጥቀሰ፣ ፍላጎቱ ዕውቅና ካገኝ እኔ ሙስሊም ነኝና በህልውና ትግሉ አልሳተፍም" --- የሚል ፕሮፓጋንዳ መንዛት ተጀምሯል።
ይህን ሳይቃጠል በቅጠል በዬ ይህን ጽፌአለሁ። ይህን ስሑት አመለካከት የሚያመነጩት የድብቅ አጀንዳ አራማጆች እንጂ ከኦርቶዶክሳውያን ጋር 1400 ዘማናት የኖሩ ነባር ሙስሊሞች መልእክት አይደለም።
በመሆኑም ሊታርሙና ሊመክሩ እንጂ በእነዚህ አዳዲስ ሰርሣሪዎች ድምጽ የኦርቶዶክሳውያንን የህልውና አደጋ ከአማራ የህልውና አደጋ ፣ ከነባሩ ሙስልም የህልውና አደጋ ለመነጠል መሞከር ጥፋቱን ለማስቀጠል ከጽንፈኞቹ ዑስታዞች መንጭቶ የሚሠራጭ መሆኑን እገምታለሁ።
=====================
ሤራው ሲገለጥ
በእኔ ምልከታ --- መሠረት ለዚህ ድምዳሜዬ ረዥም መልስ ስጥቻለሁ። ሰሞኑን #ሞዐ #ተዋሕዶ የትግላችን ጠላት ነው የሚሉ ጥቁት የአማራ ትግል የውስጥ ነቀዞች " #ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በትግላችን ውስጥ ፍላጎት አይኑርሽ" ለማለት ሲዳዳቸው፣ --- የደርግና የጎሣ ነጻ አውጭዎችን ባህል ለማስቀጠል ሲሞክሩ በማየቴ ለመገላለጥ ሞክሪአለሁ።
በዚህ ሙከራ ሂደት ካገኛሁት መክረ ዐሳብ ብዙ ግንዛቤዎች አግኝቻለሁ። ከእነዚ መካከል አንዱ "ትግሉ አምላክ-የልሽ ይሁን" ከሚሉት ጀምሮ "ኦርቶዶክስን መጥቀስ ሙስሊም እና ሌሎች እምነቶች በትግሉ እንዳይሳተፍ ያደርጋል" እስከሚሉ አጭበራባሪ ጎጠኞችና ወይንም አደናጋሪ ዉሃቢያዎች ተመልክቻለሁ።
በጎጠኝነትና በራስ ወዳድነት (ናርሲሲስት ባህርይ) በሽታዎች ያደነቃቀፉትን የፋኖ አንድነት ሂደት ለማርም ራስን ከበሽታው መፈውስ ሲገባቸው በጣልቃ ገብነትና በሃይማኖት ማላከክ የሐወሃት/በሽዴንና የኦነገውያን የሤረኝነት ወርስ ሰለባ መሆናቸውን ከመግለጡ ተጨማሪ የደም አፍሳሽና አሸባሪ ቀፍቃፊዎ ዉሃብያ ሕዋስ መኖሩን ነው።
ስለዚህ በእኔ ምልከታ ይህ ዳርዳርታ ግቡ ሩቅ፣ መሠሪና አስመሳይነት የተጫነው የህልውና ትግሉ እንቅፋትና ፈተና መሆኑን እና በጊዜ ሳይገነግን ፈርጦ መፈወስ ያለበት አደገኛ መርስ መሆኑን አሳያለሁ፦.
የኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖችና ነባር ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ለማጋጨት የጽንፈኞች ዉሃብያ ሤራዎችን በንቃት መመከት የንቁ ታጋዮች ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የሙስሊምና ክርስቲያ ሊቃውንት ኃላፊነት ነው!!
የአማራን የህልውና ትግል የምሳተፍበት ኦርቶዶክስ ከርስትና ስሙ እስካልተጠራ ብቻ ነው የሚለ የሌላ እምነት ተክታይ እርሱ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ሳይሆን የጽንፈኞቹና አሸባሪዎቹ መፈልፈያ ማሕፀን የሆነው የዉሀብያ ሴል ነው!!
በተመሳሳይ ደርጃ ክርስቲያን ሆኖ ተመሳሳይ ፕሮፓጋንዳ የሚያራምድ እርሱ ደግሞ አገራችንን በማስወረር፣ በምከፋፈልና በማጋጨት የሚታወቀው የቫቲካን የአልፎንሶ ማንዴዝ ኩስ ላይ የበቀለ የዘረኛ አውሮጳ ቅኝ ገዥ ኑፋቄ የአእምሮ ባሪያ ነው። ሌላው ዘር ቆጣሪው በክርስትና ስም የሚነግደው ፕሮቴስታንት አይነት የሆነው የናዚ ጀርመን በሁለተኛው ዓለም ጦርነት መሸነፍን ተከትሎ ከተበተኑት መርዘኛ ሰባኪያን መካከል ወለጋ ግምቢ ሆስፒታል ውስጥ የናዚ ፓርቲ ፍጡር የሆነውን “የጀርመን ክርስትና” በመዝራት አራጁን ኦነግ የቀፈቀፈው፣ አሁን ኩሽና ሲሜቲክ ትርክት የሚዘራውና ጀርመን አገር ፕሮጀክት መሥርቶ "ኢትዮጵያን" ከመፍሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚፍቀው፣ የኦሮሞ ሕዝብን ከገዕዝ ፊደልና ስነ-ጽሑፍ ሀብታቱ ለመነጠል ላቲን ያላመደው ፕሮቴስታንት ነው።
ኦርቶዶክስ የሆኑ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የትግራይ፣ የደቡብ ሕዝቦች በሙሉ “ሃይማኖታችሁን ካልደበቃችሁ፣ ስለ ሃይማኖታችሁ ከተናገራችሁ በፋኖ ትግል አልሳተፍም፣ እኔ የምታገለው 'ለአማራነቴ' እንጂ ለእምነቴ አይደለም፣ --- ወዘተ” የሚል ፕሮፓጋንዳ የሚነዙ ሁሉ ----
----- ኢትዮጵያዊ መልካችንን ክደው እኛን በአረቡ፣ በአውሮፓና ሌሎች አገራት አስተሳሰብ ሊከፋፍሉንና ኦርቶዶክስን የማዳከም አጀንዳ ያዘሉ ብቻ ናቸው። እነዚህ ደግሞ የአብይ አህመድን ስንኩል ግብ ደግፈው ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሙስሊም አጀንዳ ብለው ያስገቧቸው ነጥቦች ሁሉ ለኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን፣ ለታሪኳና ለአገሪቱ ነባር ጽጋዎች አሉታዊነት ያላቸው በመሆናቸው የአጀንዳው ምንጭ የአብይ ፍጡር የሆነው የዉሃብያ መጅልስ ቡድን እንጂ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም እዳልሆነ ማሳበቁ ነው።
ለንዚህ አደናጋሪዎች የታሪክ ምስክርነት ለመጥቀስ፦
ምድሪቷ ሁሉ ክርስቲያን በነበርችበት፣ ቤተ መንግሥቱ ማጽሐፍ ቅዱስን እንድ ሕገ-መንግሥት፣ ካህንን እንደዳኛ በሚጠቀምበት፣ ኢትዮጵያ በአክሱም ሥልጣኔ የሮማን መንግሥት ሳይቀር የምታሰጋበትና ምንም ዓለም አቀፍ ሕግና ጫና በሌለበት ሌላውን እምነት ማለትም ነባሩን ይሁዲ፣ መጤውን ተሰዳጅ የሳውዲ እስላም ቤተሰን በፍትሕ፣ በፍቅር፣ በቤተስብነት ያኖረን ኦርቶዶክሳዊ እምነትና ኦርቶዶክሳዊ መንግሥት ውልታ በመካድ “ሃይማኖትህን ከጥቀስክ እኔን ልትገፋኝ ነው” የሚለው መክራከሪያ የኢትዮጵያውያን ነባር ሙስሊሞች ጥያቄ ሳይሆን በሽብር፣ በቡርቦራ፣ በኢኮኖሚ አሻጥር፣ በማሕፀን ጂሃድ፤ “በተጭቁነን ነበር” ዋይታ አገርን ቀምቶ ሌላውን ወድ እንግድነት ለመለወጥ ከሚሯሯጡ የዉህብያ ዑስታዞች የሚረጭ መርዝ እንጂ ከአማራ ሙስሊም አይመነጭም።
--- በዚህ ይሉኛታና ፕሮፓጋንዳ ለጥፋት ዒላማ የተደረገችዋን ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ከርስቲያንና ክርስቲያኖችን የህልውና አደጋ ሰውሮ ጥፋታችንን ለማስቀጥል የሚደርገውን ሤራ አንቀበልም። ይህ ለነባር ሙስሊሙም እኩል ይሠራል።
የሙስሊሙና ክርስቲያኑ የሃይማኖትና የታሪክ ልሂቃን
ይህን ሰውር ሤራ ማክሽፍ የጠበቅባችኋል። በሌላ በኩል በግልብና ጥራዝ ነጥቅነት “ሴኩላር፣ ንጹህ ትግል” የምትሉ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች፣ ከአማራ ህልውና የበለጠ የጎጣችሁና የግል ሥልጣናችሁ፣ ወይንም ከባእዳን የተቀበላችሁት ተለዕኮ የበለጠባችሁ ወገኖቻችን የመረጣችሁትን መንገድ ትርፍና ኪሣራ ከሚሞተው፣ ከሚሳደደው፣ በመክራ ውስጥ ከሚገኘው ሕዝብ አንጻር መዝኑና #ታረሙ!
አስተያየቶች