ጭፍን መንጋነት ክፉዎችን ያነግሣል!!
ከእነዚያ ከኦነግና ሕወሃት የሐሰት ትርክት የማመንጨትና የማከፋፈል፣ ማጠልሸትና ሰብእና የመግደል ባህል የተወለዱ ከጎጠኝነት ልክፍት ልምሾዎች በሚመነጭ ፕሮፓጋንዳ የተጎዳ አንድ የዋህ እና ደግ ወዳጄ የሚከተለውን ጥያቄ በቴሌግራም ማወያያዬ ላይ ላከልኝ።
" ለመምህር. ፍታሁን ዋቄ ያድርሱልኝ !
ሞዓ ተዋህዶ ! ፍኖዎችን ቀብቶ ለማንገስ !
የሚሰራ ነው ። በማለት በተደጋጋሚ ይሔ
ጉዳይ እየተነሳ ነው ። መምህር ከቻሉ በዚህ
ጉዳይ. መልስ ቢሰጡበት እና ! ግራ የተጋቡ
አካላት እውነቱን እንዲረዱ ።
እንቅስቃሴው እና አላማው ምን ላይ እንደተመሰረተ ግልጽ ቢያደርጉት ! ጥሩ
መስሎ ስለታየኝ ነው ።" ይላል
ለወንድሜ መልስ ለመስጠት ስጀምር እንደ ጠያቂዬ ያሉ መልካም ልብ ያላቸው ሰዎችን ወደ ግል የክፋት መሣሪያቸው የሚቀይሩትን በማሰብ ለእነርሱ ሳይሆን በእነርሱ ለሚታለሉትም እንድትሆን ብዬ የሚከተለውን መልስ ሰጠሁ:-
"ወዳጄ የኢትዮጵያ ትልቁ መቅሰፍት ማሰብ አቁመው የተጫነባቸውን በጭፍን መንጋነት የሚሰለፉትን እና በቀላሉ ወደ ሤረኞች ወንጭፍና ጠጠር በመቀየር ለጮሌዎች አድርገው የሕዝብን ትግል ሁሉ ፍሬ ዐልቦ ለሚያደርጉት ማንቂያ ትሁን ብዬ ነው።
ጭፍን ተከታዮች በጎጥ ቡድን አድሎአዊነት ፣ ወይንም ባለማወቅ፣ ወይንም ከትግል የድል ፍሬ ከሚገባቸው በላይ ለማግኘት የሆነን ወገን ያለ አምክንዮ የመደገፍ እና በግል ሊገኝ የሚችል ፍርፋሪ እያሰቡ፣ ወይንም ዘረኝነትና ሐሰተኛ ትርክት እንደ ትግሬ እና ኦሮሞ ነጻ አውጭ ነን ባይ አእምሮ አጣቢ እንዶዶች የሐሰት አመንጭና አከፋፋይ የሠፈራቸውን አውራ ሀሳብ ሁሉ እንደ አእምሮአቸው ምትክ የሚያምኑና የሚከተሉ ሰዎች መብዛት ክፉኛ ስለጎዳን ከፕሮፓጋንዳ እረፍት ወስደን እግዚአብሔር የሰጠንን እእምሮና ህሊና እንድንጠቀም ለመጎትጎት ነው።
ለጠይቀኸው ጥያቄ መልስ ከእኔ ወይንም ከሌላ ለማግኘት መጀመሪያ "አሉ" ያልከውን "ማን አለ?" ብለህ በመጠየቅ ከላይ ያልኩትን መከራከራዬን ባታረጋግጥ ለክስ አቅርበኝና ይቅርታ ጠይቃለሁ። ሐሰትን፣ ግምትን፣ ቅዠትን ሁሉ ሳናረጋግጥ ማሰራጨት በሰብአዊ ሕግ ወንጀል፣ በእግዚአብሔር ሚዛን ኃጢአት ነው።
አጥርተን እያየን እውነቱን ለማግኘት አንድ የሳትነው ቁልፍ ጉዳይ አለ። እርሱም እኛ ማን ነን? ለምን እንኖራለን? ለምን እንቆማለን? ለምንስ እንሰዋለን? በምንስ መስፈርት ጠላትና ወዳጅ ስንል ወገኖችን እንፈርጃለን? ለምን? የሚሉትን እነዚህን ጥያቄዎች እንደሚገባ ባለመመለሳችን የተውለበለበ ምላስ ሁሉ ያንሳፈናል።
መሬት እንርገጥ። እንቁም፣ ራሳችንን እንወቅና ለሌሎች መድኅኒት፣ ብርሃንና ጨው ለመሆን እንጋደል። ክርስቶስን የማይመስል ወቅታዊ ገበያ ያሳፈፈው አርፋና አሬራ ሁሉ ከፍታ እንዳልሆነ በቀላሉ እናያለን። ቀዳዳው ከማፍሰሰሱ በፊት በእውነት ወስፌ እየወጋን እንሰፋዋለን። ሳይወጉ መስፋት አይገኝማ። እንቀባባ!
ለአንተ የምለው:-
ከቡድን እዕሳቤ እስረኝነት አምልጥ (ምናልባት ተጠልፈህ እንደሆነ) ፣ መንጋነትህን ለእውነት ክርስቶስ ብቻ አድርግ፤ ያን ጊዜ ነጻ ትወጣለህ፣ አጥርተህም ታያለህ!!
እያየሁ ነው ካልክ "የአማራ ትግል ሞኖፖሊ" የወሰደ ማነው? አማራን የተረጎመ ማነው? ስለ እማራ መናገርና መሥራት ለእዚያ ሰው እና ቡድን ብቻ ሥልጣን ማን ሰጠው?
"ከህልውና አደጋ ወገኔን ውታደጋለሁ" ብሎ ከቤቱ ከወጣና አንዴት ውድ ነፍሱን ለመስጠት ቃል የገባለትን ሕዝብ፣ ሊያድነው የሚዋጋለትን ሕዝብ መልሶ እንዴት "እቃዬ ነው እና አትንኩብኝ" በሚል ስነ ልቦና የማሰብና አማራጭ የማየት መብቱን ስንኳ ሊገስስ ይደፋፈራል።
ትልጋይ እውነትኛ የትግለን ግብ ለማሳካት ከሆነ እና ሊሰዋለት ከትሰለፈለት ሕዝብ ሌላ ወዳጅም፣ እምነትም፣ እውነትም አይገባውም ብሎ ይበልጣል?
ነው ወይስ ራሱን በስውር ለሥልጣንና ለዘረፋ ሊያዘጋጅ እና ነውሩን ጸሐይ እንዳይመታው በአመክንዮ ሳይሆን በስሜትና በፕሮፓጋንዳ አርብ መልእክት የነጠፈ እንደ ወያኔና ኦነግ መንጋ መፍጠር ፈለግ? ማን ነው ሞዐን የመክሰስ ሞራል ያለው?
የአማራ ሕዝብ ብዙ እያለ እንደ አናሳ ተበታትኖ በአናሳዎች ለዘመናት የተጠቃን ሕዝብን አንድ አድርጎ መምራት ተስኖት በመንደር የሐሰት ትርክት የተጠመደ፤ የድውያን ፖለቲካ ርእዮት እያመነጨ የማኅበረሰቡን ስቃይ የሚያራዝም ህሊና ቢሶችን (ባለ ህሊናዎቹ ለወገን ልቅደም ብለው ይሰዋሉ፣ ቀማርተኞችና ህሊና ቢሶች እየ ሰው ይከተላሉ፣ በወንድም እኅቶቻቸው ደም እነርሱ ይደምቃሉ) ከእውነተኞቹ ለይቶ መቃወም ማሰብን፣ የነጻነት ስነልቦና ባለቦትነትን፣ እፕርቄና ከግል ፍተወት ባላይ ማሰብን ይጥይቃል።
በነገራችን ላይ ይህ ሁሉ ነገሬ ለአንተ ብቻ አይደለም፣ መነሻ ሆነህ ተናገርኩ እንጂ ፤ እግረ መንገዴን ብዙ የሳቱ ወገኖቻችንን ምልከታዬን ለማጋራት ነው። ቅር አትሰኝብኝ።
በፍቅር እውነትን ለመናገር ስንጨካከን ከብዙ ጥፋት እንተርፋለን።
እግዚአብሔር ያክብርልኝ። አገራችንን የምናድንበት ዓይነ ልቡና ያድለን።
አስተያየቶች