ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ስውር ትዕዛዝ በኦርቶዶክስ ክርስትና ላይ

ስውር ትእዛዝ!!
የኦርቶዶክስን እልቂት ከተቻለ አትዘግቡ፣ ከዘገባችሁ ግን  በቋንቋ ዘውግ ብቻ እና  በግጭት ስም ከመዘገብ አትለፉ!
 =========
ይህን ትእዛዝ የተቀበሉ አንዳንድ የፋኖ መሪዎችናንየፕሮፓጋንዳ ተከፋዮቻቸው  የኦርቶዶክስ ጥቃትን በሚመለከት በሚናገሩ ንቅናቄዎችና ግለሰቦች ላይ ዘመቻ ጀምረዋል።
እስቲ የዛሬውን የብቻ የቤ ክህንቱንንየቴሌቢዥን ዜናና የተጨባጩን ውሎ እናወዳድር።

ዛሬ አርሲ፣ ጅማ፣ ቤኒሻንጉል፣ ትግራይ አማራ ስንት ክርትስቲያን ሞተ? ተፈናቀለ፣ ከእምነት ፈለሰ? የሚሉትን ማየት አትችሉም። 

የክርስቲያኖች መጠቃት ፋጽሞ እንዳይነገር አንዳች ታላቅ ሤራ መኖሩን ለመጠጠር ለታወራችሁ  ዓይን መግለጫ ይሁን:-

፩) ቤተ ክህነት የኦርቶዶክሳውያንን እልቂት እንዳይዘግብ ከብልጽግና ጋር ስምምነት አለው፣ 

፪) በየሀገረረ ስብክቱ የሚገኙ ጳጳሳት በአካባቢያቸው በክርድቲያኖች ላይንየሚፈጸመውን ግድያ፣ ማፈናቀል፣ ማግለልና ማሳደድ ፈጽመው በሚዲያ እንዳይናገሩ ስምምነት አላቸው፣

፫) አንድ የምእራብ ሀገር ኤምባሲ በሚሰጠው ቅድመንሜ ሁኔታ መሠረት አንዳንድ የፋኖ መሪዎች ትግሉ ለኦርቶዶክስ መጠቃት እውቅና እንዳይሰጥ፣ እንዲሁም ወልቃይትና  ራያ በብልጽግናና ሕወሃት ስምምነት፣ በሕወሃት የዘር ክልል ሕገ መንግሥት መሠረት ብቻ እንዲፈጸም ዩምናደርገውን ጥረትብም በግልጽ መደገፍ ባትችሉ እንኳ ዝም በሉ  በሚል ስምምነት ላይ ደርሰዋል

፭) ሰባኪያንና መዘምራን ጥቅስ ከማሽሞንሞንና የዜማ ቅላጼ ከማሳመር አልፈው ዘመኑን የዋጀ፣ ግፍና እልቂትን ለመቃወም ኦርቶዶክሳውያንን የሚያነቃና አንድም አይነት ስብከትም ሆነ ዝማሬ እንዳያቀርቡ ያልተጻፈ ስምምነት አለ፣  በውክልና እልቂት በሚያስፈጽሙት የቤተክህነቱ ምንደኞች በኩል አቅጣጫ ትፕቀምጧል።  በዚህ መሰረት ነው ደብረ ሊባኖስ ሰብራችሁ ግቡ የሚል ዘረኛ ሁሉ "ዐቃቤ ሃይማኖት" ብሎ የሚሾመው።

፮)/የምእራቡ ሚዲያና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች  የአማራንና የኦርቶዶክስን ስም እንዳይጠሩና ዘገባቸው ሁሉ "ግጭት" እየተባለ እንዲነገር አንድ አውራ ሀገር ትዕዛዝ ሰጥቷል።

በዚህ መሠረት የዛሬን አንድ የግል ጋዜጠኛና የኦርቶዶክስ ሚዲያ አዘጋገብን ለናሙና መርምሩ። ምስሉን አንብቡት፣ አስቡ፣ ሤራውን ተረዱ፣ ጭፍን መንጋነትን አቁሙ።

"እልቂት ሲፈጸም ክርስቲያኖች ከሆኑ 
በቋንቋ ማነታቸው እንጂ በእምነታቸው አታንሷቸው" የሚሉ ሤረኞች ይህን አስክሬን አማራ ብቻ በሉት፣ ሃይማኖቱን አትናገሩ፣ ከተናገራችሁ አማራ ዘመድ ይበዛለታል ብለው ይቆጣሉ። 
አብይብአህመድ የመጀመሪያ ዙር የሻሽመኔ ጭፍጨፋውን  ውጤት ሲገልጽ  በቋንቋ ዘውጋቸው ዘርዝሮ ነበር፤ ቀጥሎም  "ኦሮሞም ሞቷል" ብሎ በሚዲያ አሰራጨ።  የተገደሉት አማሮች ጉራጌዎች፣ ወላይታዎች፣ ኦሮሞዎች፣ ትግሬዎች ወዘተ በሙሉ ኦርቶዶክሶች መሆናቸው ከተነገረ ክርስቲያን ሁሉ በወንድነትንይቆማል፣  ብልጽግናና ወላጆቹ ሕወሃትና ኦነግ የለመዱትን ከፋፍሎ የማጠፋፋት ሤራ ማስቀጠል አይችልም ፣ ስለዚህ በዚያው በተሠመረለት በቋንቋ ዘውጋችሁ እንጂ በእምነት አታስቡ አለን።  

በወለጋ በአንድ ወቅት የወሎ ሰፋሪ ወገኖቻችን በአብይ ሤራ ሱጨፈጨፉ የቱርክ፣ እናንሌሎች ሀገራት ኤምባሲዎች ሃይማኖቱን ጠቅሰው አውዘዋል። ይህ ለኦርቶዶስ እንኳንስ ሌሎች ሀገራት ጳጳሳትም አላደረጉትም። 

ዛሬ አብይ በአማራ ክልል የጨፈጨፋቸው አስክሬኖች በምስሉ እንደሚታየው ክርስቲያኖች ናቸው። ግን የፋኖ ዘጋቢዎችም ይሁኑ ማንም በክርስትና እምነታቸው እንዲነሱ አልፈቀዱም። የቤተ ክርስትያን ካህን ምልክት መታየቱ ሳያስከፋቸውም አይቀርም።  አስክሬን ሃይማኖት የሌላቸውን ከቤተ ክርስቲያንና ከመስጊድ ርቀው ጫካ በጅምላ ቢቀበሩ የሚመርጥ ሴኩላር ፋኖ እንዳለ ገምታለሁ። ቤተንክህነቱማ ብልጭልጭ ደስታ እና ገዳዮችን በመሸለምናንፎቶ እብሮ በመነሳት ላይ ነው። 

ግን ማንነት ስንት ዘርፍ አለው? የቋንቋው ብቻ ለምን እንዲጎላ ተፈለገ? 

የማን ሤራ ነው? 

በሕወሃትና በኦነግ ቀመር ብቻ ነው የምናስበው የሚሉ አንዳንድ ጸረ ኦርቶዶክስ አቋም እንዲይዙ በምእራባውያን የተመከሩ የፋኖ ፕሮፓጋንዳ አፎች ለምን ኦርቶዶክስ ላይ ዘመቱ?

እንደተላክን ብቻ እንድናስብ ማን ፈረደብን?

 ለምንኛውም ተላላኪና፣ጭፍንገልባጭ በመሆናችን  የሚጀምረው የማንነት መነሻው  ሰው በመሆን ከእንስሳትና መላዕክት ልዩ በመሆን  እንደሆነ ሀሉ የዘነጋን ይመስለኛል።

 በዚህ ደረጃ ሁላችንም ሰው ነን እና አንድ የሚያደርገን ማንነት ነው። ቀጥሎ ያሉትን እንዘርዝርና የወያኔና የኦነግ ለምን ቋንቋ ብቻ ሆነ ስለሚለው እንመራመር።

የማንነት ዘርፎች እንጥቀስ:-
👉 ሰውነት (ሰው ከእንሳት የሚለየው ማንነት)
👉 ዜግነት፣ (ኡትዮጵያዊ፣ ኬኑያዊ ወዘተ የሚለይበት፣ ሰውን ግን ግን አይ ስው እም አያሳንስም)
👉 ሃይማኖት (ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት፣ ኡሰላም ሱኑ፣ ውሃቡያ፣ ከዋሩጃ ወዘተ ሁሉ በፍጥረት ሰው መሆንን አያስቀርም፣ ነገር ግን ጠባይና ምግባር ይቀይራል።)
👉 አሠፋፈርና ባህል (ቆላና ቆለኛ፣ ደጋና ደገኛ፣ ከተሜና ገጠሬ፣ )
👉 ታሪክና ትርክት (አመለካከትና ርእይን ን የተለያየ ያድርግልን)
👉 ቋንቋ  ( መግባቢያ ብቻ ነውና ሰውነት፣ ጠባይ፣ እምነት፣ አይቀርም) 
👉 ሙያዊ (ገብሬ፣ ወታደር፣ ሀኪም፣ መሀንዲስ ወዘተ)
👉 ጾታ. (ወንድ ሴት)
👉 ዕድሜ  (ሕፃን፣ ወጣት፣ ብማግሌ)
👉 ጤና (ሙሉና የተሳነው)
👉 ቀለም (ነጭ፣ ጥቁር፣ ቢጫ)
👉 ትምህርት ( ዐዋቂ የተማረ፣ አላዋቂ ያልተማረ)
👉 ማህበራዊ፣ መንፈሳዊ፣ ፖለቲካዊ ድርሻ (ካህን-ምእመን፣ መሪ-ተመሪ)።

 ከዚህ ሁሉ ቋንቋና አሰፋፈር ብቻ ለምን ጎልቶ ይነገራል?

 ፲ሚሊዮን በላይ ኤርቶዶክሳውያን በአስግዳጅ ሁኔታ ከእምነት ፍለሰዋል፣ ከፖለቲካናን ኢኮኖሚ ተገልለዋል፣ እልቁት እየተፈጸመባቸው ነው።  አንድ እንዳይሆኑ በአማራና ነፍጠኛ ስያሜ ኮድ ተደርገዋል፤ የአማራ ታጋይ ነኝ እያለ ሥራው እንዳይበጣጠስ የሚከራከር እርሱ በእውነት ለአማራ ቆሟል ማለት ይቻላል?

ከዚህ ሁሉ  የማንነት ዘርፎች ሁሉ መካከል ተለይቶ እንዳይነገር የሚፈለገው  "ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብና ሰው" ለምን ሆነ?

የአማራ ሕዝብ  ከ፺% ኦርቴዶክሳዊ ሆኖ እያለና  ለህልውናው እየሞቱለት ያሉትም ልጆቹ ኦርቶዶክሳውያን ሆነው እያሉ አንዳንድ የፋኖ መሪዎች ሥራዬ ብለው የፕሮፓጋንዳ ሠራዊት በመመሥረት ለምን ኦርቶዶክስዊ ጥቃት በስሙ እንዳይጠራ ብቻ ሳይሆን የሚጠሩትን ለማውገዝ የሚተጋው?

ይህን ሤራ ፍቱት እስቲ።

ይህ መልእክት ለጭፍን መንጋ ሰው አይስማማም። እምነት ላለው፣ በእግዚአብሔር አምሳል መፈጠሩ በማመኑ በጭፍን የማንም ቡድን ግዑዝ መንጋና ወንጭፍ ለመሆን ፈቃደኛ ያልሆነ፣ ነጻ ሰው ብቻ ይሳተፍበት። መንጎች በጎሬአችሁ።

"ሃይማኖት ከጠቀስን ይላኩን ምእራባውያን ጽንፈኞች ብለው ጠላቶቻችንን ይደግፋሉ" ብሎ መከራከር የሕፃናት ትንታኔ ይመስላል። ማንም የሃይማኖት ጦርነት ያበረታታ የለም። ይህች አባባል ምንጯ ይታወቃል። ነገር ግን ምላሽና ስልት አላት። 
ምን ያደርጋል ወንጭፉን የያዘው ሤረኛ ጠላት ሁሉ ጠጠር መንጎቹን በሐሰት ትርክት ወዝውዞ ሲያስወነጭፍ መምዘግዘግ እንጂ መደማመጥና ማሰብ የለም። 

ለማንኛውም የሚመለከታችሁና የማሰብ ነፃነት ያላችሁ አስቡበት።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

  ኦ ርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩ . ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡ በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያ...