ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ሰይጣንን ለማሸንፍ የሚያስፈልገው ቅዱስ መልዐክ መሆን እንጂ ሰይጣን መሆንን አይደለም!


ሰይጣንን ለማሸንፍ የሚያስፈልገው ቅዱስ መልዐክ መሆን እንጂ ሰይጣን መሆንን አይደለም!



በጎጥ፣ በደምና አጥንት ቆጣሪዎቸ  መንደር፣ በዘመናችን የአፍሪካ ናዚዎች ዕሳቤ የማልገኝ ፋንታሁን ዋቄ ነኝ ። ከሰውነት አደባባይ
        
ሰኔ ፴ ቀን ፳፻፲፯ ዓ•ም•

ትድረስ 
፩)  ለጸረ-ኢትዮጵያ፣ ለጸረ - ኦርቶዶክስ ክርስትና፣ ለጸረ-ነባርነት  "የአዲሱቷ ኢትዮጵያ" አቀንቃኝ የባእዳን ፈረሶች፣  ለጸረ-አማራ አካላት ላቀረባችሁ ነጋዴዎች ሁሉ፤
እንዱሁም 

፪) የሕዝብን ደምና መስዋእትነት እንደ ተራ ቁስ  ለግል ግብ መረማመጃ በማድረግ ለስግብግብ ስነ ልቦናችሁ ማስተታመሚያ ላደረጋችሁ፤ 
እና 

፫) የሕወሃት፣ የኦነግ፣ የኦፒዶኦ/ብልጽግና የቁማርና የሤራ ፖለቲካ የሚያስቀናችሁና የተቀደሰ የትግል ርእዮትና ስልት መቀመር ለተሳናችሁ፣  ከጠላት ዐስተሳሰብና ስልት ለምትቀላውጡ የሚዲያ አርበኞች
=================

የፓን አፍሩካ ዕሳቤ መነሻ የሆነውን ኢትዮጽያዊነትና እውነትኛ መሪዎቻችንን ሁሉ
እያደነ የሚቀስፈው  ምዕራቡ ዓለም በአፍሪካ የሚደግፋቸውና የሚያወድሳቸው ንቅናቄዎችና መሪዎች   ( ምሳሌ :- https://www.economist.com/middle-east-and-africa/2018/11/24/god-wants-ethiopians-to-prosper ) ከተገኙ እነዚያ ያለ ጥርጥር ጸረ አገርና አህጉር አጀንዳ ያላቸው ናቸው። የአድዋ ድል ቁስለኞች የዳርዊን ልጆች የሚደግፉት አፍሪካዊ ድርጅትና  መሪ እርሱ እቃቸው ነው!! (ለምሳሌ መለስ ዜናዊና ምእራባውያን:-( ለምሳሌ መለስ ዜናዊ እና ምእራባውያን:-  https://www.wsws.org/en/articles/2012/09/mena-s04.html )

ከዚህ ተጨባጭ ሁኔታ ተነስተን በአማራ ሕዝብ መካከል ሆነው በግላቸው ጠባብ ዐስተሳሰብ ልክ እያሰቡ ምእራባውያን  ለሥልጣን ያበቁናል ብለው የሚጠጓቸው ያለ ጥርጥር የሕዝብ ትግል ሻጮች ናቸው። ለዚህ አባባሌ ምእራቡ ዓለም  ያጠፋቸውን ባለ ራእይ አፍሪካውያን መሪዎችንንበዚህ ጽሑፍ እዘከራለሁ። 

======================

ጉዳዩ ሳታዩ እናያለን፣ ሳትሰሙ እንሰማለን፣ ሳት ዳስሱ ነክተናል ለምትሉ ውድ ወንድም እኅቶቼ ምናልባት "አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይነቃ". ካልሆነ በቀር ለመታረሚያ  ትሆናለች ብዬ ከእፍሪካ ባለ ራእይ መሪዎች ታድኖ መጥፋት አንጻር የጀመራችሁት ጉድኝት አደገኛ መሆኑን መጠቆም፤ እና   ዛሬ ለሥልጣን ያበቁናል ብላችሁ የምትወዳጁት ባዕድና ልትፀየፉት የምትሞክሩት ኦርቶዶክሳዊነትና ነባርነት ውጤቱ የከፋ እንደሚሆን ማሳሰብ ይሆናል።

ሁላችን፣ በተለይ ለእውነትኛ ድል ብለው በንጹሕ ልብ ለመሰዋት የተሰለፋችሁትን የአማራ ጀግና ልጆች ጠንቅቃችሁ እንደምታውቁት  እትግጠኛ ነኝ።  እጃችሁ  ላይ ያለው የተጋድሎ ኃላፊነት ትልቅ ነው። አማራን የሚያድነው አንድነቱ፣ ርቱዕነቱ፣ ከጠላት የዐስተሳሰብ ውራጅ  ራሱን ጠብቆ በነባር የእምነትና የባህል እሤቶቹ መጽናቱ፣ ፍትሐዊነትና ሰብአዊነቱ ነው። 

በተቃራኒው የአማራ  ትንሳኤ የሎለው ውድቀቱ  የሚፈጠረው ከሚዋጋቸው ጠላቶቹ ቁማርተኝነትን፣ ነባር-ጠልነትን፣ ከእግዚአብሔር ተለይቶ መታገልን፣ አፍሪካንናንበተለይ አገራችንን ሱቦርቡሩና ውክልና አማራንናንኦርቶዶልስ ክርስትናን ዒላማ አድርገው ሲወጉን ከኖሩትንጋር መዋዋል፣ ዘረኝነት፣ የሐሰት ተራኪነትን መዋስና መውርስ ይሄናል። 


 ጠላት የአንድን ታሪካዊ ክፍለ ሕዝብ እንደ ሕዝብና እንደ ሰው በምድር ላይ በክብር    የመኖርና ያለመኖር እድሉን ለመወሰን በሚፍጨረጨርበት  ጊዜ  ለሰብአዊነትና ለፍትሕ የቆማችሁ ናችሁ። ይሁምንና ይህን ክቡር ዓላማ በብልጠትና ግለኝነት ፣በታወሩ ናርሲሲስቶች (  https://youtu.be/n-VI93HgYIo?feature=shared ) እጅ መጣል አያዋጣም። 

ሁሉም በመስዋእትነት ደሙን እንድሚያዋጣ ሁሉ ጭንቅላቶችም ያለ ጥቂቶች ሞኖፖሊ ዐሳብ ማመንጨት አለባቸው። አመራርም በብዙኃን ተሳትፎና፣ በሕዝቡ ነባር እሤቶች፣ እምነቶችና ባህሎች መገራት ይኖርበታል። 

 የዚህ አማራ የተባለ ክፍለ ሕዝብ  ጠላቶች  ዝናብ ሲጥል እንደ ድንገት በፍግ ላይ እንደሚበቅል ሙጃ ብቅ ብለው፣ በወር ውስጥ በጸሓይ ሙቀትና በነፋስ የሚጠወልጉ ሥር-የለሽ አረሞች  አይደሉም። 

ዝጅታቸውና ጥቃታቸው በትንሹ ፪፻ ዘመናት  ተከታታይ ጥረት ተደርጎበት  በ፲፱፻፵፪ በትምህርት ሥርዓት ደረጃ  በጁሲቶች ሤራ፣ በንጉሥ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መታለል ተዋቅሮ በኢትዮጵያንላይ የተዘረጋ ነው። 
በዘመናዊነት ስም የተተከለው ትምህርት በተጀመረ  በ፲ ዓመት ውስጥ ጸረ ዘውድና ነባርብታሩክ የሆኑ አስተሳሰቦችን ያነገቡ መንግሥቱ እና  ወንድሙን ግርማሜ ንዋይን  ማፍራት ቻለ፣ በሁለተኛው አሥርት ዓመት  እነ ዋለልኝ መኮንን የመሰሉ ተላላኪዎችን ለአቅመ ፖለቲካ አበቃ። ይህን ሰውና መስሎቹን   በእንጭጭ አእምሮአቸው ውስጥ  ያደሩቱ  ባዕዳን የመርዝ አንደበት  አደረጓቸው። በድፍረት እና በድንቁርናቸው ጥልቀት ምን እንደሚያስከትል ሳያመዛዝኑ  "ኢትዮጵያ የብሔረሰቦች እሥር ቤት" በሚለው ፕሮፓጋንዳቸው  የሲዖልን በር ከፈቱት።   ውጭ ቆመው ሲያንኳኩ ብዙ ዘመን የደከሙት ጠላቶች የአእምሮ ባሪያ ልጆቻቸው ደርሰውላቸው  አገርና ሕዝብ የማፍረስ ተልዕኮአቸውን በውክልና የመፈጸም አቅም አገኙ።  መርዶ የሰማነው በ፲፱፻፷ዎቹ መጀመሪያ ላይ ነበር።  ይፕጥፋት እቅዱ ሕግ የሄነው በሕወሃትና በኦነግ ጥምረት ሲሆን ፣ አጠቃላይ የኢትዮጵያን ግብአተ መሬት ይፈጽማል ተብሎ የተወከለው እንደ ሰው ሠራሽ ሮቦት በሳምንታዊ የስልክ ክትትል ከምእራብ እየታዘዘ፣ ከእረብ እየትላከ የሚሠራ አብይና ጓዶቹን ተከሉ።

እነ አጼ ምንሊክና ብልህ አማካሪዎቹ ከፈረንሳይ፣ ከጣሊያን፣ ከእንግሊዝ፣ ከቱርክና ሌሎች ከበባ ባተረፉት ሉዓላዊ ሀገር ውስጥ ማበብ ችሎ እና  በአድዋን ተገልጾ የነበረውን ኢትዮጵያዊ አንድነትና ቤተሰብአዊ ተዋህዶ ተቃርነው ቅኝ ተገዝተናል፤ መገንጠል አለብን፤ ታላቋን እገሌ  ለጎሣችን ሀገር አርገን እናቆማለን፣ ምንልክ ጡትና እጄን ቆረጠኝ፣ አማራ ገዥነታችንና ታላቅነታችንን ቀማን፣ ኦርቶዶክስ የኋላ ቀርነታችን ምክንያት ናቸው፣ ወዘተ የሚሉ ውጭ ዘራሽ የባእዳን የአእምሮ ባሮች የአገሪቷን ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና የትምህርት አውዱን አቆሸሹት።  

በዚህ የጥፋት በር የገባው የጠላት ርእዮት ገንጣይ፣ አስገንጣይ፣ ከፋፋይና የሐሰት ትርክት ፋብሪካ መሥርቶ ሻዕብያን፣ ሕወሃትን፣ ኦነግን፣ ኦብነግን፣ ሲነንን፣ ወዘተ ፈለፈለ።  እንዚህ ሁሉ የእብሮነትና ተዋህዶ ጠላት ነበሩ። ናቸውም። ልክብእንደ አድዋ ድል ቁስለኞቹ በውንርሱ ፈንታ ተወክለው አንድነታችን፣ የመዋሀድ ሂደታችን ያሳማማቸዋል። መለያየትን "ነፃነት" ፣ መጠፋፋትን "ትግል"፣ ሐሰተኝነትን " ከነጠላ ትርክት ወደ ብዝኃ ትርክት መሻገር'፣ አማርንና ኦርቶዶክስ ማጥቃትን "የመብት ማስመለስ ህጋዊ  ተግባር" አድርገው ይኮሩበታል።

ለመንግሥትነት የተፋለሙ ኢሕአፓና ደርግን በዘረኝነት ባንከሳቸውም በጸረ-ኦርቶዶክስ ክትስትና እና በአንጻሩ በጸረ-አማራዊ እሴት ልዩነት የላቸውም። መነሻቸው ከነባር እሤቶችና መልክ ሁሉ የተቃረነች "አዱሲቷ" የምትባል ነገር ግን ምን እንደምትመስል ሕዝቡ የማያውቃት፣  በቅዠት መልክ መሪ ነን ባዮች ከሚስሉት ብዥታ ውጭ  በማንም ልትገለጽ ያልቻለች ሀገር መፍጠር ነበር።  

አዲሲቷ የምትባለዋን የሕዝብ ጠላት እና የፖለቱከኞቹ  አእምሮ እንኳ በትክክል የተሳለ ምስል ሳይኖር ብቻ  ያለውን የሚጨበጥ አጥፍቶና ደምስሶ መገኘት ግብ ሆነ። 
በዚህ ከሃምሳዎቹ መጨረሻ  በኢትዮጵያ ጠላቶች በምሁርነት ሽፋን የተፉጠሩት ዘመናውያን ከምን እንደሚጀመር የማይታወቅ ወደ "አዲሲቷ" ኢትዮጵያ የመጓዝ ጅማሮ አመፅ/አብዮት ነው። የቅዠቱ  ገዞ ፋናውና መዳረሻው አይታወቅም፣ ሁሉም ግን በአንድ ነገር ይስማማሉ። እርሱም ነባር የሆነውን እምነት፣ ባህል፣ ሥርዓተ መንግሥት፣ ሥርዓተ ማኅበር፣ ረዥም ታሪክና አሻራዎችን መደምሰስ ነው።  ይህ ጉዞ ተከታይ አመጽ ወለደ፣ እርሱም የቋንቋ ዘውጋችንን ከሌላው  ጠላት ከተባለ ወገንና እምነት ነፃ አውጥተን ወይንም ለይተን በምንፈጠረው አዳዲስ አገራት  ላይ እነግሣለን፤ የሚል ሆነ። 

ለዚህ አስተሳሰብ  ተከታይ ማበጀት፣ ትናንሽ ሀገር መፍጠር "ነጻነት" ወይንም "የራስን እድል በራስ መወሰን" ብለን እንጠራዋለን ብለው ተነሱ፤ እንደ ሕወሃት፣  ኦነግና ሻዕብያ አይነቶቹ ደግሞ ቅኝ ተገዝተናል እንበልና "የነጻነት ትግል" የተባለውን ግጭት እንጀምር በማለት ፶ ዓመት ዘልቆ የቀጠለውን በሐስት ትርክት ግጭቱን አቀጣጠሉት፤ ለጥፋት ትግላቸው  በተውሶ ርእዮት እየተመሩ ሰብአዊ ደም ማፍሰሱን፣ ሕዝብ ማፈናቀሉን፣ በእቅድ ማደኸየቱን፣ ታሪክ መበረዙን፣ ርስት መንጠቁን፣ ሃይማኖት ማፍለሱን፣ ከባእዳን ሙሉ ድጋፍ ለማግኘት  ሙሉ ባርነት መቀበሉን ቀጡለበት።

በዚህ ሁሉ ነጻ የሚወጣው ጭቁን የተባለው፣ ቅኝ ተይዟል የተባለው ወገን ሲሆን ቅኝ ገዥው፣ ወራሪውና ነጻነት ነፋጊው አማራ ኦርቶዶክ ቤተክርስቲያን  ተባለ።

 የአማራ ርእዮታዊ ምንጭ ደግሞ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ቤተክርስቲያኒቷ ሆኑ።  ከነባሩ የሺ ዘመናት ሀገር-ፈለቅ የአስተዳደርና የፍትህ ሥርዓት በየአካባቢው ሕዝብን አስተሳስሮና አከባብሮ የሚኖረውን ሽምግልና ሳይቀር ጠላት በማድረግ የአድዋ ቁስለኞችን የመረቀዘ ሕመም የሚበቀሉ የገዛ ወንድም እኅቶቻችን  ከውጭ ጠላት የከፉ የውስጥ ደዌ ሆነው ተከሰቱ።

"አዲሲቷ" ለሚሏትም ይሁን "ነጻ አውጥተን ሀገር እናደርጋለን" ለሚሉት መንደር እዉን መሆን የተውሶ ርእዮት ላይ የተመሠረተ ጸረ-አማራ፣ ጸረ-ኦርቶዶክስ፣  ጸረ-ነባር እሤቶች፣ ጸረ-ኢትዮጵያዊነት እና ፓን-አፍሪካንዝምን ዋና የማይነገር ነገር ግን በተግባር የሚታይ ሁለገብ (ፖለቲካ፣ ትምህርት፣ ትርክት፣ መዋቅር፣ ምጣኔ ሀብት፣ ፕሮፓጋንዳ፣ ዲፕሎማሲ፣ ክግና ፖሊሲ ሁሉ ለአጥፊው አዲስ አስተሳሰብ እንዲያገለግሉ ተደረገ)።

አፍሪካን በዘለቄታዊነት ጥገኛና ሰላም ዮሴፍየሌላት በማድረግ (፴፭ቱንም የአፍሪካን አንድነትንድርጅት ጠንሳሽና ጀማሪ ባለ ራእይ መሪዎች  የገድሉና ከሥልጣን ያስወገዱ አካላት ሥራቸውን የበለጠ አድርገው የሚሠሩላቸው  ሕወሃትን፣ ሻዕብያንና ኦነግን ፈጥረው አሳደጉ።

  እነዚህ  ነባር-ጠል የባእዳን የእእምሮ ፍጠራን የአገር ነቀርሳ ሆነው ለሃምሳ ዓመት ያዘለቋቸው ባዕዳን አገራት የስለላ ድርጅቶች ጥበቃና እዝ ሥር ይኖራሉ።  በእንጻሩ  ባለራእይ  መሪዎችን በገደሉበት የደም እጃቸው አዲስ የፈጠሯቸውን ነፃ አውጭ ነን ባይ ባሮቻቸውን እየደባበሱ ደም የማፍሰስ ብቻ ሳይሆን የገዛ አገራቸው ጠላት ሆነው ህሊና ያላቸው ብሔራውያን ሊቃውንትን፣ ቤተክርስቲያን መሪዎችን አስፈጁ። እያስፈጁም ነው። አሁን ያሉት አሬራዎች ሃይማኖታቸውንና የተቀደሰ ሕይወታቸውን አርክሰው ከመጣው ሁሉ ጋር እንፈ ሴትኛዳሪ የሚወዳጁ ካንተዎች ሆኑ። 

ይህን ለማያውቅ የፌስ ቡክ ትውልድ ለናሙና ያህል በባእዳን እጅ ያለቁትን ባለ ራእይ የአፍሪካ መሪዎች ልዘከር:-

በባእዳን ሤራ  የተገደሉና ከሥልጣን የተወገዱ መሪዎቻችንን ስንረዳ ዛሬ የሀገር መከራ ቀፍቃፊዎቹ በምትካቸው የተሰሩ  አገልጋዮች መሆናቸውን እናረጋግጣለን።
 በተለይ  የአገር ነባርነት ጠላት መንፈስ ያለው ማኒፌስቶ፣ የትግል ስልት፣ የፕሮፓጋንዳ ቀመር፣ የሀሰት ትርክት፣ የባእድ ወዳጅነት አበጅተው በሚችሉት ሁሉ ጸረ አማራ እና ጸረ ኦርቶዶክስ ክርስትና፣ ጸረ ኢትዮጵያዊነት  ትግል የሚያካሄዱት የዛሬዎቹ ቡድኖችና የብልጽግና መንግሥት  የማን መገልገያ እንደሆነ ለመረዳት በምንም መልኩ ልዩ ትምህርትና እውቀት አይጠይቅም። 

በአማራ የኮድ ስያሜ ነባርነት፣ ክርስትና እና ኢትዮጵያዊነትን በማጠቃለል  የኦሮሞና የትግራይ ሕዝብ  ልጆችን በማታለልና በሐሰት ትርክት በማደንዘዝ የራሳቸውን የጋራ ታሪክ፣ አገርና እምነት እንደሚወጋ እንዳያውቅ   ማደንዘዣው:-

" ነፃነት፣ መብት፣ ልዩ ማንነት፣ ቋ ንቋ፣ ፊደል፣ መማክዐ ምድራዊ አሰፋፈር ወዘተ" ጽንሰ ዐሳቦች በግርድፍና በአጓጊ ግን የማይጨበጥ ባዶ ምኞት ማብሰልሰል ስልታቸው ነው።  እነዚህን ቃላት ያለ አግባብ በመተርጎም እና አማራን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ኦርቶዶክሳዊ ክርስትናን ዒላማ  ያደረገ ሠራዊት አድርገው የቀረጿቸእን ከኢዳያስ አፈወርቅ፣ ሌንጮ ለታ፣ ስብሃት ነጋ፣ መለሰ ዜናዊና የክብረት ልጆች አብይ እና ዳንኤል ድረስ የእናት ጡት ነካሾችን ፈልፍለው አስለፉ።  በዚህም በአድዋ የተሸነፈውን እና በሞት አፋፍ ላይ የደረሰውን የምእራባውያን የዘረኝነት ርእዮት በታመመበት አገር በኢትዮጵያ ላይ ትንሳኤውን እንዲያገኝ እኛን ዜጎችን በውክልና የጠላትን ቂም  ማርኪያ አድርገው ለጥፋት ዳረጉን።  


 [ለታሪክ መታሰቢያነት ከሀገር አንድነት እልፈው ለአህጉር አንድነት በመታገላቸው እንድ ሕወሃትና የኦነግ ባሉ የባእዳን አገልጋዬችና ሰላዮች  ህልማቸውን ሳያሳኩ የተገና ከሥልጣን የተወገዱ የአፍሪካ መሪዎችን እጠቅሳለሁ:+

፩) ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ፣ በሄንሪ ኪሲንጀር ፖሊሲናንበአውሮፓውያን ሤራ ወደ ተራንየባዕዳን እቃነት በተለወጡ ምሁራን ተብዬዎቹና ወታደሮች ከሥልጣን ተወግደው የተገደሉ።

፪) ከዋሜ ንኩርማህ (ጋና) የፓንንአፍሪካንጽንሰ ሀሳብ ዋና አቀንቃኝ እና የአንዲት አፍሪካ ሀገርነት ህልመኛ በመሆኑ የበ፲፱፻፷፮ በሲአይኤ የተወገደ።

፫) ጁሊየስ ኔሬሬ (ታንዛኒያ) የአፍሪካን ሶሻሊዝም ለማስተዋወቅ በመሞከሩንየተወገደ።

፬) ጆሞ ኬንያታ (የኬንያ ነጻነት አባት) የአፍሪካን አንድነት መፈጠር በጽኑ በመደገፉ የተቀጣ።

፭)) ጋማል አብደል ናስር (ግብጽ) የአፍሪካ አንድነት አራማጅና ጸረ ኢምፔሪያልስትነቱንያስገደለው።

፮) አህመድ ቤን ቤላ (አልጄሪያ)_  ድህረ ቅኝ ግዛቶች ራሳቸውን እንዲችሉ በሰሜንብእፍሪካንንቅናቄ በመፍጠሩ በ፲፱፻፷፭ የተወገደ።

፯) ሊዮፖልድ ሴዳር ሴንጎሆር (ሴኔጋል)፣ ምሁርና መሪ የነብረ፣ የእፍሪካን ባህላዊ ውህደት በማራማዱ በጠላትነት ተፈርጆ የተወገደ፣ 

፰) ሚልቶን አቦቶ +ዩጋንዳ)  የአፍሪካ አህጉራዊ ዲፕሎማሲኔ እውነትኛና ሁለገብ ነጻነት ዙሪያ በማቀንቀኑ  በ፲፱፻፸፩ እና ፹፭ መፍንቅለ መንግሥት የተደረገበት። 

፱) ፓትሩስ ሉሙምባ (ኮንጎ) ፣ በአፍሪካ ላይ የጸናውን እጅ አዙር ቅኝ አገዛዙን  በመቃወሙ በ፲፱፷፩ የተገደለ። 

፲) ቶማስ ስንካራ (ቦርኪ ናፋሶ) የኦምፕሪያሊስትና የአብዮተኛ ብጥበጣ ለውጦችን በመቃወሙ በ፲፱፻፹፯ በመፈንቅለ መንግሥት የተገደል።

፲፩) ሙአማር ጋዳፊ (ሊቢያ) ፳፻፲፩ የእፍሪካን መተባበር፣ የጋራ ገንዘብ መፍጠርና ራስን መቻል እቅድ በመያዙ ኔቶን በማዝመት አሜሪካ ያስገደለችው።
   
፲፪) አሚልካር ካብራል (ጊኒዎ ቢሳው/ኬከ ቨርዴ) ለነጻነት በመታገሉ ከድሉ አስቀድሞ በ፲፱፻፸፫ የተገደለ።

 ፲፫) ሲልቫነስ ኦለንፑዮ (ቴጎ) አገሩቷ ከቅኝ ነጻ በሆነች በእፕጭር ጉዜ ውስጥ ከምእራባውያን ጎራብአልሰለፍም በማለቱ በ፲፱፻፮፫ የተገደለ።
፲፬) ፌሊክስ-ሮላንድ ሞኡሜ ምናልባት በፈረንሳይ ስለለላ አካላት ተመርዞ በ፲፱፻፷ የተገደለ።

፲፭) ሩቤን  ኡም ኖዮቤ (ካሞሩን) በ፲፱፻፶፰ የሀገሩን የነጻነት ንቅናቄ በመምራቱ በፈረንሳይ ሠራዊት የተገደል። 

፲፮) ኤድዋርዶ ሞንድላኔ (ሞዛንቢክ) : በየፊሮሊሞ ንቅናቄ መሪ በመሆኑ በፖስታ በተጠመደ ቤምብ ፲፱፻፷፱ የተገደለ።  

፲፯) ሳሞራ ማቼል (ሞዛምቢክ)፣ አውሬፕላኑ በአጠራጣሪሁኔታ  እንዲወድቅ ተድርጎ በአፓርታይዷ ደቡብ አፍሪካ ድንበር አክባቢ በ፲፱፻፹፮ የተገደለ።

፲፰) ስቱቭ ቢኮ (የደቡብ አፍሪካንአፓርታይድ ተቃዋሚ መሪ፦ በ፲፱፻፸፯ በፖሊስ በጭካኔ ተቀጽቅጦ የተገደለ።

ጥያቄ እንጠይቅ!!
ሀ) ለአገራቸውና ለሕዝባቸው፣ ለመላው አፍሪካ መልካም ርእይ ያላቸውን ታጋዮች የሚገድል የዳርዊን ልጅ ለምን የሻዕብያን፣ የወያኔን፣ የኦነግን፣ ኦፒዲኤ/ብልጽግናን ደገፈ?

ለ) እብይ አህመድን ለምን የሰላም ኖቬል ሽልማት ሰጠው?

፫) ታንዛኒያ ድረስ ተጉዘው ኦነግ/ኦሮሙማን ከወያኔ ያስተባበሩትና የሕወሃትን ህልውና ከመጥፋት በመታደግ ለዳግም ወረራ የሚያዘጋጁት  ለምንድ ነው?

፬) የአማራንናንየኦርቶዶክስን እልቂት ችላ ብለው፣ ፪፻ በላይ በአማራ ላይ የድሮን ጭፍጨፋ፣ በገዳማት ላይ እልቂት  ሲካሄድ ለምን ችላ ይላላሉ? በአንጻሩ በትግራይ ላይድሮን ድብደባ ሲፈጸም ለምን ከ፭ ጊዜ በላይ የጸጽታ ምክርቤት ስብሰባ ጠሩ?

፮) አንዳንድ የፋኖ መሪዎችን ከሌሎች ለይተው ለምን ያነጋግራሉ?

መልሱ ቀላል ነው፦ ንግግራቸውና ፍቅራቸው ከጸረ-ኢትዮጵያ፣ ጸረ-አማራና ኦርቶዶክስ ክርስትና መንፈስ ካላቸው እካላትብጋር ነው።

ከአማራ ትግል ውጭ የነበሩት ባለ ማኒፌስቶዎቹ 
የትግላቸው ዋና ምሰሶዎች ሀሰት፣ ሤራ፣ ክህደት፣ ግድያ፣ ዘረፋ፣ ተላላኪነት፣ የሀገርን ጥቅም ሳይሆን ሥልጣን ላይ አውጥቶ ያቆየናል የሚሉትን የውጭ ኃይል ማገልገል ነው።  

ሻዕብያ፣ ሕወሃት፣ ኦነግ እና የጎሣ ነጻንአውጭ ነን ባዮች ሁሉ በአንድ አይነት ጸረ-አማራ፣ ጸረ-ኦርቶዶክሳዊት ቤተንክርስቲያንና ኢትዮጵያዊነት ዐስተሳሰብ  ላይ የተዋቀሩ ነበሩ።  አንዳቸውም የኢትዮጵያን መልካም እሤቶች፣ ታሪካዊ ሀብታት፣ ማኅበራዊ መዋቅራት፣ ጥበቦችና ሀገር-ፈለቅ ዕውቀቶች አይታዩአቸውም ነበር። 

እናም ለትግል ሲነሳሱ መነሻቸው ኢትዮጵያዊ ነባር ማንነታችንና አንድነታችን በአድዋ የሰበረው የዳርዊን ዘረኛ ልጆች  የሰውን ልጅ የሚከፋፍልና በክብር የሚያበላልጥ የቅኝና ባሪያ ገዥዎችን ፋልስፍና እንደ እናት የጡት ወተት ተግተው ያደጉ በሥጋ ውልደትብኢትዮጵያዊ ግን በአእምሮ ባዕድና የነባር ማንነቶቻችን መሠረታዊ አስተምህሮና ርእይንጠላቶች ናቸው።

አፈጣጠራቸው ከስኳላ ፊደል ቆጠራ፣ ከሚሽነሪዎች ጸሎት ቤት፣ ከአብዱል ዉሀብ መርዛማ መድረሳ፣ ከውጭ ስኮላርሺፕ፣ ከማርክስ አምላክ የለሽ ርእዮት፣ ከጣሊያን ባንዳ ቤተሰብ ወዘተ የተበላሸ ሁኔታ ውስጥ ነው። 

የአማራ ሕዝብ የህልውና ይግል መንሻ ከእነዚ ባዕድ-ድቅል ተላላኪዎች ራሱን ለመከላከል የተከሰተ ተፈጥሮአዊ የአደጋ ምላሽ ነው። ስለሆነም ሤራ፣ ሀሰት መፈብረክ፣ የባእድ ርእዮት መቃረም፣ የጎሣ ጠላት መሰየም፣ የባእድ ድጋፍና ምክር መሻት፣ የጎጥና የቋቋን ዘውግ ማቀንቀን፣ በጅቡዕ የትውልድ አእምሮ በመርዛማ ትርክትና በቅዠታዊ ርእይ ማታለል አላስፈለገዉም።

ተነስቶ "ሰው ነኝ፣ ሰው ናችሁ፣ ህልው ነኝ አልጠፋም" የምትል መጽሐፍና ፍልስፍና የማትሻ ተፈጥሮአዊ የሰብአዊነትና የፍትህ ንቅናቄ ነው።

የሚያስደነግጠውና ከፍተኛ ትኩረት የሚሻው ይህን ተፈጥሮአዊ፣ ስብአዊ፣ ፍትሐዊ ንቅናቄ ጠልፈው ለግል የሀብት፣ የሥልጣንናን የዝና ማጋበሻ፣ የጎጥ ስነ ልቦና መታሻ ለማድረግ ለአገርና ለአህጉር አንደነትና ውህደት የሠሩ መሪዎችን እያደነ ከሚያጠፋው ሼተላይ ጋር አጋርነት መጀመራቸው ሱሰማ ነው።  ተላላኪ ድውያንን ወደ አፍሪካ አገራት ሥልጣን እያወጣ፣ እንዳዉም ከተጠየቀው በላይ ለሚሠራላቸው ኖቤል እየሚሸለመ፣ ወይንም ዝናውን በፕሮፓጋንዳ እያጎነ  የገዛ አገሩን የሚያስጠፋውን ባዕድ አለመረዳት ምንኛ መቀሰፍ ይሆን? እነዚህ አፍሪካን በተለይ ኢትዮጵያን ለመቅበር የሚደክሙ አካላት  ጸረ-እኩልነት መሆናቸውን ከ፬፻ ዘመን በላይ በፈጸሙት ታሪካቸው ይታወቃል።

 ዛሬን ከእንዚህ ጋር ተባብረን ችግር እንፍታለን፣ "አማራ ለህልውናው ከሰይጣንም ጋር ይሠራል" የሚሉ ከስይጣን ጋር ሰርቶ  ውድቀት እንጂ ድል እንደማይገኝ ያልዞረላቸው ከርሞ ጽጃዎች ብቻ ናቸው። 

በጎሣና በእምነት ከፋፍለን ኢትዮጵያን ለማጥፋት የጎሣ ነጻ አውጭ ፈልፍለው ለዚህ የዳረጉንን አካላት ከሕዝብ ጀርባ እየተገናኙ የሚርመጠመጡ ድንኮች በአማራ መካከል መብቀላቸው  በእውነት የአማራን ህልውና ለማረጋገጥ ወይስ በገዛ ልጆቹ ደም ወደ ዘለቆ
ቄታዌ ጥፋት መንዳት ይሆን? ማሰብ የቻልነው ይህን ያህል ብቻ ነው? መካሪ ሲገኝ መከራከርና ዐሳብን ማስፋፋትብሲገባ ተሳዳቢ ገዝቶ እንደ ሙሾ አውራጅ ዐሳብ ዐልቦ ዘፈን ማዜም ማንን ይጠቅማል? 
ይታሰብበት።

የህልውና ትግልን ቅዱስ የሚያስፕኘው ሤራ፣ ጌጠኝነት፣ ሀሰተኝነት፣ መግደል መቻል አይደለም። ቅዱስነቱ የሚመነጨው እውነተኝነቱ፣ ፍትሐዊነቱ፣ ክቡር የሰው ልጅን ያዋረዱትን አስተሳሰቦችና ድርጊቶችን ለማሸነፍ መነሳቱ፣ ከጎሣ አጥንትና ደም ቆጠራ በላይ ሰውነቱና፣ የከበረ ሰው የሚኖርባት የተከበረች ሀገርን ማለሙ እና ለዚህ መሰዋቱ ነው።

ይህን ቅዱስ ነገር ውሾች እንዳይጫወቱበት ባለቤቱ የሆነው የአማራ ሕዝብ ከፕሮፓጋንዳና አጭበርባሪ ባንዳ ልጆቹ የጠላትን ያህል መጠበቅ ይኖርበታል። ካልሆነ ግን ደሙን አፍስሶ፣ አጥንቱን ከስክሶ የሚያገኘው ውጤት ከክወሃትና ኦነግ ዲቃላ ከብልጽግና ወንጌሉን ነፍሰ ገዳይ  ገዥ  ማሸነፍን፣ በምትኩ  ከአማራንአብራክብየተከፈሉ ነገርብግን በአማራ ስም እየማሉ በሥልጣን ላይ ወጥተው ለባእዳን አማራን እየቸረቸሩ ለዘላለም ነጻ ሕዝብ እንዳይሆን በሚያደርጉት አማርኛ ተናጋሪና  በ"አዱስነት" ስም እሤቶቹንና እምነቱን  ደምስሰው ወደባሰ አዘቅት የሚከቱት እጅ ይወድቃል።

አማራ ሆይ አማርኛ ተናጋሪ አብይዎች፣ ስብሓቶዥ መለሶች፣ ሌንጮዎች፣ እዳይጋልቡህ የማይመስሉህን ለይ። በጫጫታና በአፈቀላጤነት ሳይሆን የሚፈሰውን ደም የሚመጥን እና  የሚያስከብር በእርጋታ የታሰበበት፣ ግልጽ አማራነትን የሚተረጉም መሪ ዐሳብ ይወለድ።   ከጫጫታውና ባዶ የጥቂት ጠባብ ፍላጎታቸው ያሳወራቸው ቡድንተኞች ፕሮፓጋንዳ ከመወዛወዝ ቀነስ!!!

ይህ ዐሳቤ ነው። ዐሳቡን ሞግቱት፣ የተሻለ ጠቃሚ እይታ ይፈጠራል። ዐሳብ የሌላችሁ ስድብ፣ ደምና አጥንት መቁጠሩን፣ ያልተጻፈ አንብባችሁ መተንተኑን ቀጥሉበት። ይነጋና ሁሉም ሁሉን ያያል። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...

ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች; በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጽዋዕ ማህበራትና ሰንበቴ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ የተገዳደሯትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች የተከላከለችባቸው፣ የተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ያስከበረችባቸው እሴቶች  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  nigatuasteraye@gmail.com  ሚያዚያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.  (April 28, 2025)  መግቢያ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል  ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡   ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡   የጽዋ ማኅበር መነሻ...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

  ኦ ርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩ . ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡ በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያ...