ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

የምመኛት ኢትዮጵያና ሕዝቧ

Let's dialogue about the Orthodox

ምን አይነት ኢትዮጵያ ትመኛለህ?

እኔ፦

1.       የሰው ልጅ ሰው በመሆኑ ብቻ የምከበርባት አገርና ይህን የሚያስከብር መንግሥት የሚመራት አገር፤  

2.      ሃይማኖት፥ ባህል፥ ጾታ፥ ቋንቋ፥ ያለፈ ታሪክ፥ አሠፋፈርና የኑሮ ዘይቤ ሁሉ የሰውነትና የዜግነት ማንነቴ ላይ ምንም ተጽእኖ የማያሳድሩብተ ሥርዓተ መንግሥትና ሥርዓተ ማኅበር የሚገለጽባት አገር፤

3.      የአገር አስተዳደር አከላለል ከቋንቋና ከፖለቲካ ነጻ ሆነው በልማት ቅልጥፍና፥ በንዑስ ማንነት መዋሃድ መሳለጥ ሚዛን ብቻ የሆነባት አገር፤

4.      ፖለቲካ መንግሥት ከሃይማኖት፥ ከጎሣ ቡድን፥ ከቋንቋ፥ ከፖለቲካ ሠራሽ ማንነትና አግላይ ትርክቶች ነጻ ሆኖ ለሰው ክብር፥ ለፍትሕና ለሕዝብ ሰላምና መዋሀድ የሚሠራ የሆነባት አገር፤

5.      ወታደር ትጥቅ ይዞ አገር ውስጥ የማይታይባት፥ ድንበር ብቻ በወታደር የሚጠበቅባት አገር፤

6.      ፖሊስ ሀብታምና መንግሥት ዱላ ሆኖ ከማገልገል ወጥቶ  ሕዝብ የሚጠብቅባት  አገር፤

7.      ፍትሕ በማሥበራዊ፥ በምንግሥታዊ፥ በሃይማኖታዊና ባህላዊ መዋቅራት ውስጥ ሁሉ እውቅና አግኝቶ የሚተበርበት አገር፤

8.      አገርና ሕዝብ ለምግብ፥ ለመድኃኒት፥ አገርን ከውጭ ወረራ ለመከላከል በሚያስችላቸው ግብአቶችና እውቀቶች ሁሉ ከጥገኝነት ነጻ የሆኑባት የሉዓላዊ ሕዝብ አገር

9.      ከባእዳን ጋር ተመሳጥረው አገራቸውን የሚወጉ፥ ሕዝባቸውን በሐሰተኛ ትርክትና በተውሶ የፖለቲካ ርእዮት የሚያምሱ አገር-ጠል እና ውጭ ናፋቂ “ምሁራን” ተብዬ የጠላት አገልጋዮች በአገር ክህደት የሚቀጡባት አገር

10.    የሐሰት ትርክት ከፍተኛ የአገር ወንጀል የሚደረግባት፥ የፖለቲካ ቁማርና ማጭበርበር በሚት የሚያስቀጣባት አገር።

ይህን አይነት አገር

ü  የብሔር ፖለቲካና ብሔርተኝነት አይሰጠነም።

ü  ብልጽግና ሕወሃት፥ ኦነግ አይሰጡንም።

ü  ከውጭ የምንዋሰው የፖለቲካ ርእዮትና ውጭ ናፋቂ ምሁራን አይሰጡንም

የዚህን አይነት አገር የምናገኘው፦ ሁላችንም ተነስተን

ü  ለክብረ-ሰብእ ስንቆም

ü  ከዘረኛ የቡድን ዕሳቤ ባርነት ራሳችንን ነጻ ስናወጣ

ü  ለፍትሕ ስንሟገትና እኛም በአቅማችን ፍትሓዊ ስንሆን

ü  ከስስት፥ ከቅሚያ፥ ከልዩ ማንነት የፋሽት ፖለቲካ መለየት ብቻ ሳይሆን ጠላታችን ነው ብለን ስነዋጋው

ü  አገራችንን በመስዋዕትነታችን እንደምንጠብቃት ከፋፋዮችን ጠላቶቻችን ናቸው ብለን ስንስማማ

ü  ዐመሓራነትን ከደምና አጥንት ስሌትና ቀመር አስወጥተን ለሁሉም የሰው ልጆች የሚመጥን እሤት ነው ብለን የራሳችን ስናደርገውና አብረን ስንቆም፥

ü  አንዲሁም ዐመሓራነትን  ከሕወሃትና ኦነጋዊነት ከብሔርተኝነት  መርዝ ስንጠብቀው

 

YOUTUBE:- https://www.youtube.com/@Orthodox_Secular_FantahunWakie/videos

ትዊተር፦ @fwakie
FB:- https://www.facebook.com/fwakie

Blog:- https://ethiopiaorthodoxchristian.blogspot.com

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

የሐሰት ትርክት ኦነጋውያንና የሕወሃታውያ የጋራ ስልት ከነግሥታት ወደ ተራ ግለሰቦች

✏️ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።  እርሱ ይመስገን። ምድራችንን #በደም #ያጨቀየው $ህሊና #የነሳን ፣ #ልቦናችንን #ያጨለመን ፣ #ሰብእናችንን ያዋረደው:- 👉 የሕወሐታውያንናንየኦነጋውያን የንዑስ ማንነት የጎሣ ፖለቲካ የደንቆሮ ርእዮትና፣ 👉 መርዛማን ጥላቻን ለ፶ ዘመናት ያከፋፈሉት የሐሰት ትርክት ናቸው። ✏️እንደ ዳግማዊ #ምንልክ ያሉ   ከዋክብት መሪዎች፣ እንደራሴቻቸው፣ ደጃዝማቾችና ቀኝና ግራ አዝማቾቻቸው  ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ብዙ ውለታ ውለውልናል:- 👉 በዘመነ ኦቶማንና አውሮፓ፣ በዘመነ መሳፍንት የተበታተነውን እና የተቆነጻጸለውን፣ ጎሠኛ የአርብቶ አደሮች  መሬት ፍለጋ  የደመሰሱትን ክርስቲያናዊ የግዕዝ/የነፃነት ሥልጣኔ አሻራ እንዲያገግም ደክመውልናል፤ 👉 የጥንት አገርን እና ሕዝቦችን   በከፊልም ቢሆን በመሰብሰብ  ጠንካራና ብቸኛ የነጭ ቅኝነትንና ባርነትን በመከላከል፣ ከኦቶማን ቱርክ ወር ትናንት ውስጥ ጥረኛ  አህመድ ግራኝ በመጋደል  ልዩ የነጻነት ማንነት ያላትን አገር ብበቸኝነት በዓለም ካርታንላይ አቆይተዋል፤ 👉 የሬማ ግዛት በጎሣ ተብልቶ ፲ ትንንሽ ሲሆን ከበበባውን ተቋቁማ በዝኃነታችን በተመጋጋቢ አንድነት ከ፹ በላይብቋንቋ፣ ከዓለም ትልልቅ እምነቶች ክትስትናን ፣ ይሁዲን፣ እስልምናን፣ የእረማውያንን ቅሪት የሆኑ የባህል እምነቶችን ሁሉን ይዛ በአውሮፓ በአርብ አምሳል ሳትሠራ ለእኛ አቀብዋል፤ 👉 ወያኔና ኦነግ፣ ገንጣዩ ሻዕብያ፣ ከሃዲው የማርክሲስት የአእምሮ  ባሪያን ስብስብ  እስኪፈትናት ድረስ ራሷን የቻለች አገር እንድንፈጥር ያስተባበሩን ነገስታት የተመሰገኑ ናቸው። አገር ሲያረጅ ጃርት ያብቅላል እንዱሉ: መል...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩. ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡  በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡  ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በቋንቋ መ...

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...