ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ቅዱስ ሲኖዶሱ ከአጣብቂኝ የሚወጣው ወደ ሓዋሪያቱ ቀኖናና ቀዳሚያን አበው ውሳኔዎችን በማገናዘብ ተመልሶ ስሕተቶቹን ሲያርም፥ ኢቀኖናዊያን ሹመኞችን ሲሽር ብቻ ነው

በትግራይ ቤተክርስቲያን ዙሪያ አያገባህም አርፈህ ዝም በል የሚል አስተያየት ተሰጠኝ። 

ይህ ቤተክርስቲያን አንዲት ናት የሚለውን የዶግማ ትምህርት የሚቃረን አባባል ነው። እንኳንስ ትግራይ ውስጥ ባለችዋ ቤተክርስቲያን ግብፅ፣ አርመን፣ ሶርያ፣ ህንድ፣ ኤርትራ ባለችዋ ቤተክርስቲያን እኩል ባለጉዳይ መሆኔን ማሳወቅ እፈልጋለሁ። ዘረኝነት በቤተክርስቲያን ውስጥ ቦታ የለውም። ቅዱስ ሲኖዶስም ራሱን ቢያጠራ ደስ ይለኛል። እኔን አትናገሩኝ እነ አባ ኢሳይያስን ብቻ ተናገሩልኝ አይባልም። ነውር ነው። ለሻረው ቀኖና ይቅርታ ይጠይቅ። ሲኖዶስ ራሱ ቀኖና ነው የሚሉ አንዳንድ የዋሃንን እየተመለከትኩ ነው። 

መጽሐፈ ሲኖዶስን ከሆነ ጥሩ ብላችኋል። የአምስት ኪሎውን ስብስብ ከሆነ ግን ተሳስታችኋል። ሲኖዶስ ራሱ ቀኖና ነው የሚለው አባባል የፈለገውን ዓይነት ውሳኔ ቢወስን ቀኖና አድርገህ ተቀበል እንደማለት ነው። ለምሳሌ ባለፈው ንጹሕ ኦሮሞ ሹመናል ብሎናል ሲኖዶስ። ስለዚህ ሲኖዶስ ቀኖና ስለሆነ ንጹሕ ኦሮሞ (የሌላ ዘር ያልተቀላቀለበት) መሾምን እንደ ቀኖና እንቁጠረው ይሆን?? 

ባለፈው እነ አባ ሳዊሮስ የኦሮሞና የብሔርብሔረሰቦች ሲኖዶስ ብለው 26 ሰዎችን ሹመው ነበር። ከዚያ ቅዱስ ሲኖዶስ አወገዛቸው። እንደገና በዐቢይ አማካኝነት ተደራደሩ። ሐምሌ ፱ ቀን ቅዱስ ሲኖዶስ ንጹሕ ኦሮሞ ሹመንላችኋል እንኳን ደስ አላችሁ አለን። ከዚያ አሁን ደግሞ እነ አባ ኢሳይያስ መንበረ ሰላማ ብለው 6 ሰዎችን ሾሙ። ቅዱስ ሲኖዶስ ባለፈው እንዳደረገው ተደራድሮ ንጹሕ ትግሬዎችን (የሌላ ዘር ያልተቀላቀለባቸውን) ይሾምልን ይሆን ይሆንን??? አባ ሰረቀ ያለው ልክ ነው ማለት ነው? 

ቅዱስ ሲኖዶስ የሾማቸው ንጹሕ ኦሮሞዎች ወደፊት እነርሱም የሚሾሙት ንጹሕ ኦሮሞ ነው የሚሆነው ወይስ እንዴት ነው? በእናቱ አማራ በአባቱ ኦሮሞ፣ በአባቱ ኦሮሞ በእናቱ ትግሬ የሆነ ሰውስ አይሾሙም ማለት ነው?! ትላንትና የሆነ ትግሬ መነኩሴ አቡነ ተክለሃይማኖትን አማራ ናቸው ብሎ ሲያብጠለጥላቸው ሰማሁ። ብዙ አልገረመኝም። ወደፊት ንጹሕ አማራ ናቸው ተብለው የሚታሰቡ ቅዱሳንን የመጥላት ዘመቻ ይሠራል። ይኽው ትላንት ተጀመረ። በእርግጥ ቅዱስ ሲኖዶስምኮ ሲሾም ባለፈው ንጹሕ ኦሮሞ ብሎ ነው የሾመው። ጉዳዩ የሃይማኖት አይደለም። ጉዳዩ የዘረኝነት ነው። ዘረኝነትን ደግሞ ቤተክርስቲያን ትጸየፋለች። ቅዱስ ሲኖዶስ ብቃትን መሠረት ያደረገ ሰው ቢሾም መልካም ነበር። ችግር ችግርን እየወለደ ይኽው እስካሁን አለን። ውሸትን በሌላ ውሸት ማሸነፍ አይቻልም። ውሸትን ማሸነፍ የሚቻለው በእውነት ነው። 

መውጫ:- ቅዱስ ሲኖዶስም፣ መንበረ ሰላማ ነን ባዮችም ሁላችሁም ይመራናል የምትሉትን እግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ብታከብሩ መፍትሔው ቀላል ነው። እግዚአብሔር መንፈስቅዱስ በቅዱሳን ሊቃውንት አድሮ በቅዱሳት መጻሕፍት ምን አለን የሚለውን አይታችሁ እንድትወስኑ ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ ባለፈው ቀኖና ሽሮ በዘር የሾማቸውን ስለእግዚአብሔር ብሎ ሹመታቸውን ቢተወው፣ "መንበረ ሰላማ" ነን ብለው በራሳቸው ጉልበት አጰጵሰናል የሚሉትም ከእልህ ወጥተው ክርስቶስን ቢፈሩና ስለክርስቶስ ብለው ሕገወጥነታቸውን ቢተውት መልካም ነው። ብልጽግናንና ሕወሀትን ፈርታችሁ ከምትወስኑ መንፈስ ቅዱስን ፈርታችሁ ብትወስኑ መልካም ነው።

 ቤተክርስቲያንን ለመገንጠል ምናምን ምናምን የሚለው ከቅዱስ ሲኖዶስም ከመንበረ ሰላማም የሚነገረው ንግግር አስቂኝ ነው። ብፁዓን አባቶቼ ቤተክርስቲያን ትገነጠላለች እንዴ? ራሳችሁ ልትገነጣጠሉ ትችላላችሁ እንጂ ቤተክርስቲያን እንኳ ተገንጥላ አታውቅም። በጣም የሚገርመው ወደፊትም ለዘለዓለሙ አትገነጠልም።

አንድ ነገር ግን አለ። ይኽውም አንድ ሰው ወይም ጉባኤ ከቀኖና እና ከዶግማ ውጭ ከወሰነ አለሁ ቢል እንኳ የተገነጠለ መሆኑን መረዳት አለበት። 

© በትረማርያም አበባው

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

የሐሰት ትርክት ኦነጋውያንና የሕወሃታውያ የጋራ ስልት ከነግሥታት ወደ ተራ ግለሰቦች

✏️ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።  እርሱ ይመስገን። ምድራችንን #በደም #ያጨቀየው $ህሊና #የነሳን ፣ #ልቦናችንን #ያጨለመን ፣ #ሰብእናችንን ያዋረደው:- 👉 የሕወሐታውያንናንየኦነጋውያን የንዑስ ማንነት የጎሣ ፖለቲካ የደንቆሮ ርእዮትና፣ 👉 መርዛማን ጥላቻን ለ፶ ዘመናት ያከፋፈሉት የሐሰት ትርክት ናቸው። ✏️እንደ ዳግማዊ #ምንልክ ያሉ   ከዋክብት መሪዎች፣ እንደራሴቻቸው፣ ደጃዝማቾችና ቀኝና ግራ አዝማቾቻቸው  ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ብዙ ውለታ ውለውልናል:- 👉 በዘመነ ኦቶማንና አውሮፓ፣ በዘመነ መሳፍንት የተበታተነውን እና የተቆነጻጸለውን፣ ጎሠኛ የአርብቶ አደሮች  መሬት ፍለጋ  የደመሰሱትን ክርስቲያናዊ የግዕዝ/የነፃነት ሥልጣኔ አሻራ እንዲያገግም ደክመውልናል፤ 👉 የጥንት አገርን እና ሕዝቦችን   በከፊልም ቢሆን በመሰብሰብ  ጠንካራና ብቸኛ የነጭ ቅኝነትንና ባርነትን በመከላከል፣ ከኦቶማን ቱርክ ወር ትናንት ውስጥ ጥረኛ  አህመድ ግራኝ በመጋደል  ልዩ የነጻነት ማንነት ያላትን አገር ብበቸኝነት በዓለም ካርታንላይ አቆይተዋል፤ 👉 የሬማ ግዛት በጎሣ ተብልቶ ፲ ትንንሽ ሲሆን ከበበባውን ተቋቁማ በዝኃነታችን በተመጋጋቢ አንድነት ከ፹ በላይብቋንቋ፣ ከዓለም ትልልቅ እምነቶች ክትስትናን ፣ ይሁዲን፣ እስልምናን፣ የእረማውያንን ቅሪት የሆኑ የባህል እምነቶችን ሁሉን ይዛ በአውሮፓ በአርብ አምሳል ሳትሠራ ለእኛ አቀብዋል፤ 👉 ወያኔና ኦነግ፣ ገንጣዩ ሻዕብያ፣ ከሃዲው የማርክሲስት የአእምሮ  ባሪያን ስብስብ  እስኪፈትናት ድረስ ራሷን የቻለች አገር እንድንፈጥር ያስተባበሩን ነገስታት የተመሰገኑ ናቸው። አገር ሲያረጅ ጃርት ያብቅላል እንዱሉ: መል...

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እና ቋንቋና ማንነት ተኮር እንቅስቃሴዎች   ፩. ቋንቋን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ትውፊት ከሰው ልጅ መበደል በፊት ፍጥረት ሁሉ የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር፡፡ “ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” እንዲል፡፡ ዘፍ. 11፡1 በኃጢአት ምክንያት ግን ሰውና መላው ፍጥረት በአንድ ቋንቋ መግባባታቸው ቀረ፡፡ ኃጢአት እየበዛ ሲሄድ የሰው ልጅ ቋንቋም በባቢሎን ተደበላለቀ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የማይግባቡ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎችም ተፈጠሩ፡፡  በበደል የመጣውን ሁሉ ሊያስተካክልና ሊያድን በመጣው በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ያ የቀደመው ጸጋ ስለ ተመለሰልን በበዐለ ሃምሳ ሰዎች በልዩ ልዩ ቋንቋ አንድ ዐይነት የእግዚአብሔርን መልእክት ሰሙ፡፡ በዚህ ጸጋ የተጠቀሙና የበቁ ቅዱሳን የእንስሳትን ቋንቋ እስከ ማወቅ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡   የክርስትና ጉዞ ወደ ቀደመው በአንድ ቋንቋ መግባባት መመለስ ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ደግሞ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚሰማው ቋንቋ መማር አለበት፡፡ በበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቋንቋ የገለጠላቸው ሰውን ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጸጋ በሚሰማው ቋንቋ እንዲያስተምሩት ነው፡፡ ሆኖም ቋንቋ መልእክት ማድረሻና መግባቢያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ሰዎችን በሆነ መደብ ለመመደብና የልዩነት አጥር ለመሥራት እንደ መሳሪያ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ ከክርስትና ዐላማ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡  ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ዐለም ሁሉ ሲልካቸው ሰዎች የሚቀበሏቸው በሚያስተምሩት ትምህርት መሠረት ነበር እንጂ በትውልድ፣ በብሔርና በመሳሰለው መስፈርት የእኛ ናቸው/አይደሉም በሚል አልነበረም፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በቋንቋ መ...

ገድሎና አስገድሎ ብፁዕ እየተባሉ መኖር የተፈቀደላቸው ጳጳሳትና ቆሞሳት እንዳይረሱ

ከጥር 27 ጀምሮ በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ የተሾሞና በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ አካላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን እናስገባለን ባሉ የመንግስት የጽጥታ አካላት በተትኮሰ ጥይትና ሕገ ወጡ ቡድን ባደራጃቸው ወጣቶች ተደብድበው የተገደሉና የቆሰሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን።።   1)  ሻሸመኔ ከተማ   I.   የተገደሉ 1.  አያሌው ተረፈ ●   በሻሸመኔ የደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ማህደረ ፃድቃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ●  ጥር 27 ዓ/ም በሻሸመኔ ከተማ በጸጥታ ሃይሉ በሚመራ የጨፍጫፊ ቡድን በደረሰበት ከፍተኛ ደብደባ ወደ ሆስፒታል ገባ ●  በአላቲዮን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ●  በ ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብሏል       2.  ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ሐረገወይን ●  የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ●  በሻሸመኔ በሕገወጦች በጸጥታ አካላት  በበግፍ በዱላ ተቀጥቅጠው በጭንቅላታቸው በእጅና በእግራቸው ላይ በደረሰባቸው ድብደባ በሀዋሳ ሕክምና እያሉ አርፈዋል። ●  ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው  በያኔት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ●  በዛሬው ዕለት ጥር 30 2015 ዓ/ም  ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።     3.  ዘማሪ ፍቃዱ ደጉ ●  የቅዱስ ሚካኤል ከሣቴ ብርሃን ሰ/ትቤት አገል...