ከተኩላ የከፉ እረኞች፦ ከሊቢያው አይሲስ እስከ አብይ አህመድና የጎሣ ጳጳሳት
ዛሬ በሊቢያ የተሰዉ የግብጽ ሰማዕታትን የሚመለከት መጽሐፍ አግኝቼ ቅናትና ቁጣ መጣብኝ። ቁጣዬ የሩቁን ጠላት የሚያስረሳኝ ሆነ፤ እርሱም የቤት ውስጥ ጠላትና ተባባሪ እረኛ በጥመቱ መቀጠሉ ነው።
እንደሚታወቀው Islamic State in Iraq and al-Sham (or
Islamic State in Iraq and Syria) (ISIS) አይሲስ የተባለው ድርጅት የጽንፈኛ የሱኒ ኢስላም ፍልፍሎች መካከል አንዱ ነው። የዚህ
ንቅናቄ ዓላማ ኢስላማዊ የከሊፋ መንግሥታትን መመለስና ዓለምን ኢስላም ማድረግ ነው።
የመጀመሪያ ትኩረቱ ከኢስላሞች ነብይ ከመሐመድ ጂሃድ
የወረሱት ሰይፈኛ ወራሽ ተከታዮቻቸው ወይንም ከሊፋዎች ከሳውድ አረብያ
ጀምሮ ሶሪያን፥ ሊባኖስን፥ ሊቢያን ግብጽን፥ እስራኤል፥ ዮርዳኖስ፥ ፍልስጤም፥ ደቡብ ቱርክን አጠቃሎ አንድ ኢስላማዊ አገር አድርገው እንደገዙትና በገዙበት መንግድ ታሪኩን መድገም ነው።
ቀጥሎ የሀበሻ ምድር የሚሉትን
ሱዳንን፥ ሶማሌን፥ ኤርትራን፥ አንዲሁም ኦቶማን ቱርክ በአህመድ ግራኝ
በኩል ፉት-አል-ሐበሽ ብሎ ያደናቀፈችውን ኢትዮጵያ መበቀልና የኢህ የሐበሻ ከሊፋ ምድር ብሎ መመሕረት ሌላ ሁለተኛው ኢስላማዊ መንግሥቱ ግብ ነው። ቀጥሎ ህንድ ውቅያኖስን፥ ሜድትራንያንና ቀይባህርን
ስትራተጂካዊ ቦታዎችን ይዞ ከተደላደለ በኋላ ወደ መላው ዓለም መዝመት
ነው።
በዚህ እቅድ ውስጥ ዘወትር ዒላማ
የሆነችዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንና ረዥሙ የተቀደሰ ታሪኳ እስከነ ቅርሦቿ ማውደም ነው። ለዚህ ደግሞ ምዕራቡም ከጂሃዲስቱ
ባልተናነሰ መንገድ በትምህርትና በሥልጣኔ ስም ሲያወድማት ኖሯል። አሁን በግልጽ በአካል እያጠፋት ነው።
የዚህ ኦርቶዶክስንና ነባር ኢትዮጵያውነትን
የማጥፋት ፕሮጄክት ሠራተኞች ብዙ ናቸው። ነገር ግን ጎላ ብለው አደጋ እያደረሱ የሚገኙት
ü በብሔር ፖለቲካ ሥር ተደብቀው “አጤዎቹ፥ አህምድ ግራኝ የናፈቀን ንጉሥ ነው፥ ጭቆና ተካሄዶብናል፥ ዓመተ ምህረት የሚለው
አቆጣጠርና የሰንበት ቀን መከበር ለስነ ልቦቻቸን ጫና ፈጥሯል፥ ባንዲራው የክርስቲያን ነው፥ ሚኒሊክ ቅኝ አድርጎናል፥ ዮሐንስ ጨፍጭፎናል የሚል መዝሙር በማሰማት፥ ነገር ግን ከሥር ደግሞ ግጭት እየፈጠሩና ቤተ መንግሥት ከመሸገው ባለድብቅ
አጀንዳው ኦሮሙማ/ብልጽግና ጋር ተባብረው ከጎዴ እስከ አጣዬ፥ ከጅማ
እስከ ቤኒሻንጉል፥ ከባሌ እስከ ሐረርጌ ከሊቢያው ጭፍጨፋ የከፋ ጥፋቱን
አጧጡፈዋል።
ü እነዚህ ኣከላት በሰሜኑ ክፍለ-ሕዝብ መካከል ግጭት ለመቀስቀስ
የእምነት ቦታ እያቃጠሉ “ተቃጠለብን” በሚል የሃይማኖት
ጦርነት ለመፍጠር ደክመዋል፥ በባሌ የኢስላማዊ መንግሥት ሴል ፈጥረው ከአልሻባብ ጋር ይሠራሉ፥ በጎንደር ከግብጽ ጋር የተሳሰረ ሤራ
ሲያካሄዱ ተደርሶባቸው ወደ ድበቅ ጉድጓዳቸው ገብተዋል ---- ይህን ሁሉ ስናስብ -----
ü ሁለተኛው አጥቂ የአገሩን ባህል፥ ትውፊት፥ ጥበብ በምንም ደረጃ ሳይቀስም በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ልሂቅ ተሰኝቶ በምንም
መልኩ ለአገር ፋይዳ ያለው ነገር የማይችል ሽባ ምሁር የፈጠረው የ50 ዓመታት አገር-ጠል ውጭ ናፋቂ የፖለቲካ ተቋማት ናቸው። እነዚህ
አካላት ለአገር ልማት የሚጠቅም ምንም አይነት አስተዋጽኦ የሌላቸው
ሆነው ነገር ግን በለውጥ ስም ቀዳማውያን ጸጋዎችን በመቃወም የተጠመደ፥ ኦርቶዶክሳዊነትንና ኢትዮያውነትን ጠላት ያደረገው ንቅናቄ
እና ትምህርቱን ለጥፋት ያቀበሉት የውጭ አካላት አማካሪና የጥቃቶቹን ደጋፊ ሆነው አብረው ቆመዋል።
ü መተባበር ሳይገባው የሚተባበረው ቤተ ክህነት።
ቤተ ክህነቱን የሚመሩ አካላት
ጠቅላላ የፈታነውን ክብደት ለመረዳት ፈቃደኛ ካለመሆን ጀምሮ፥ ልጆቻቸውን
የሚያልቁ ልጆቻቸው ድምጽ እንደሚገባ እንዳይሰማ የሚሸፍኑ የተለያዩ የበዓላት ድምቀት፥ ምንም አይነት እልቂትን የማያስቆም፥ ስልታዊና
መሠረታዊ ለውጥ የማያወጣ በዓመት ፪ እና ከዚያም ያለፈ ጉባኤ በማድረግ፥ ከችግራችን ጋር የማይገናኝ ዋጋ ቢስ
ሥልጣናዎችን በመሥጥ፥ የሕንጻ ግንባታ እንደ ድል በማቅረብ እየጠፋች
ለምትገኘዋ ቤተክርስቲያን መፍትሔ የሚሰጥ ጎዳና ላይ ከመቆም ይልቅ በተቃራኒ ጎዳነውን የሚያሳዩትን በማራቅና በጠላት ጉያ በመሸጎጥ
የጥፋት አካል ሆኗል።
የቤተ መንግሥቱ አፈጣጠር የዘር ፖለቲካን ከነባር ኢትዮጵያዊነት ጋር በተቃርኖ ያቆመ በመሆኑ ተግባሩ
ነባርነትን ማጥፋት ነውና ቢያጠቃን አይደነቅም። ጥያቄው ቤተ ክህነቱና
ቤተ መንግሥቱ እንዴት ሊተባበርብን ቻሉ?
ለማስታወስ ያህል፦ በሊቢያ በረሃ እኛ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ታርደን ዜናውን ከዓለም ሚዲያ
ሰምተን ስናለቅስ በሐዘናችን መካከል እኛን እየመሩን የሚጠሉንና የሚያስጠቁን እነ ሬድዋን ሁሴን ወጥተው “ኢትዮጵያኖች መሆናቸውን
እንጣራን” ብለውን ነበር። እንደቀለደብን እናስታውሳለን።
በመንግሥትና በቤተ ክህነት የተካደው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያንና መከራ የሚያበቃው ምእመናን እና ሊቃውንት እንደ
በድን ተኝተው መንጋውን ቀስ በቀስ እያዘናጋ የሚየፈጅና የሚያስፈጅ ልግምተኛና የጠላት ተባባሪ እረኛ ከመጠበቅ ለውጥ ወደ ማምጣት
ሲሸጋገሩ ብቻ ነው።
የግብጽ የሊቢያ ሰማዕታት ታላቅ ክብር በእውነተኛ እረኞቻቸው ታላቅ የቅዱሳን ሰማዕታት መዝገብ ውስጥ ሠፍረዋል። በስማቸው ቅዱሳት ምሥሎች
ተሰርተው በሲኖዶሱ በመላው ክርስቲያን እጅ እንዲገኝ፥ በየቤተክረስቲያኑና ምእመናን እንዲሰቀል፥ ቤተ መቅደስ እንዲሰየምላቸው ሆኗል።
ዛሬ መጽሐፉን እያነበብኩ ቅናት አነሳስቶች ስለ ራሳችን ለመናገር ተነሳሳሁ።
በግብጽ የቀናሁበትን ልንገራችሁ፦
ü የአልሲሲ መንግሥት ለበቀል ብሎ በጦር አውሮፕላኖች የአይሲስን ካምፖች በቦምብ ደብድቧል።
ü የግብፅ መንግሥትና ቤተክህነቱ የሰማዕታቱን አጽም አውጥተው ወደ ግብጽ አፍልሰዋል፥
ü የግብፅ ቤተክርስቲያን ለሰማዕታቱ በቀኖና የቅድስና ሰጥታለች፥
ü ሲኖዶሱ ለሰማዕታቱ ልዩ የሆነ ምስል በማሠራትና በማጽደቅ በየቤተክርስቲያኑና ምእመናን ቤት አንዲገኝ አድርጋለች፥
ü የስማዕታቱን ተጋድሎና ተያያዥ ትምህርት የሚሰጥ መጽሐፍ አሳትማለች፥
ü በእያንዳንዱ በግብጽ ውስጥ የሚፈጠር የጽንፈኞች ፍናዳታና ግድያ በክርስቲያን ላይ የሚደርሰውን
አደጋ ዓለም አቀፍ ዜናና እውቅና ታሰጣለች፥
የእኛ ቤተ ክህነትና የእኛ የምንለው ግን የእኛ ጠላት መሆኑ በተግባር ለመግለጽ “እኔ ሚሊሺያ አይደለሁምና የሚገደሉ
ልጆቻችሁን አልጠብቅም፥ ገዳማቱ የነፍሰ ገዳይ ማሠልጠኛ ስለሆኑ ‘እርምጃ ውስዳለሁ’፥ ገና ሰው ይሞታል፥ ቤተ ክርስቲያንም ይቃጠላል
---፥” በሚል ንግግር እና በተግባር ገዳማትን በመድፍና ቦምብ በአንድ ሳምንት ከ570 በላይ ገዳማውያን በመግደል፥ ቤተክርስቲያኖችን
የወታደሮች ምሽግ በማድረግ፥ ካህናትን በድንጋይ አስድብድሞ በማስገደል፥ ወጣቶችን በጥይት በታቦት ፊት በመረሸን፥ ምእመናን ከአሮሚያ
በማጽዳትና ማንንም ለሕግ ባለማቅረብ ያሳየ መሪ ነው።
ከግብጽ ጋር በንጽጽር አስቤ እንደቀና ያደረገኝ ቤተክህነታችን ነገር፦
ü
ከዚህ መንግሥት ጋር እየተመካከርን ችግር እንፈታለን በሚል ቧልት ሕዝብን እያዘናጉ እልቂትን ለ፮
ዓመታት አስቀጥለዋል፥
ü
ምእመናን በሐሰተኛ የህግ ማስከበር
ሽፋን ለ70 ዓመታት የተደበቀውን ኦርቶዶክሳዊውን ማኅበረሰብእ የማጥፋት ትግበራ በድሮን መግደል፥ ምእመን ጨፍጭፎ በቡልዶዘር መቅበርና
“ደስ ይበላችሁ! በልጽግናል ደስ ይበላችሁ!” እያሉ የሚቀልድ ቤተ መንግሥትን ሕፋን በመስጠት፦ (ሀ) “ቤተ ክርስቲያን በፈተና ውስጥ እያለፈች ነው፤ (ለ) ቤተ ክርስቲያን ከመስቀል
አትወርድም፥ (ሐ) በዓላችን የደመቀና ትውፊታችንን የጠበቀ ነው ብሎ መፎከር፥ (መ ) ሕነጻችን ተመረቀ፥ የመሠረት ድንጋይ አኖርን፥
ዜና ማሠራጨት፥
ü
እርዳታ ሰጠን፥ መቶ ሰው ተጠመቀ
--- ደስ ይበላችሁ፥ አጨብጭቡ፥ እልል በሉ ---“ ወዘተ በሚል
ሰማዕታቶቻችን እንዳይዘገቡ፥ እንዳይገለጹ፥ በቀኖና እውቅና እንዳየስጥ
በማድረግ ከእረኛ የማይጠበቅ ተቃራኒ አቋም ላይ መገኘት፥
ü
ምዝበራና የዘመድ አዝማድ ተቋምና
ከክርስትና አርአያነት አንፃር ምእመን ሰሚ አጥቶ ሲኖዶስን እንደ መንግሥት በሰላማዊ ሰልፍ ደጅ የሚጠናበትና ከምንግሥት የበለጠ
በበደሉ የሚከሰስ አስተዳዳሪዎችና ሊቃና ጳጳሳት የበዙበት፥
ü
ኦርቶዶክሶች በጎሣ ተከፋፍለው እየተፋጁና
ፍጅቱን ሕጋዊና ሃይማኖታዊ ተቀባይነት እንዲያገኝ የጎሣ ጳጳሳት አንዲፈጠሩ ቀኖናውን በማዳከምና ለኤጲስቆጶስንት የማይበቁ ጎጠኛ
የፖለቲካ ሠራተኞችን የፈለፈለ ቤተ ሲኖዶስ፥ --- ወዘተ መኖሩ፥
----- አለመቅናት፥ አለመናደድ፥ አለመናገር አይቻልም። ይህን ለመቻል “ስለ ቤተ ክርስቲያን አያገባኝም፥ የሚያልቀው
ክርስቲያን አይመለከተኝም፥ እኔ ብቻ ይድላኝ” የሚል የእነዚህን የሐሰት እረኞች ስነ-ልቡና መላበስ ያስፈልጋል።
እሰቲ አስቡት ---- እውነቱ ይኽ ነው፦
v ሊቢያ ያረደን ያ ደም ጠጭ የሰይጣን እዚሁ አገራችን እየለማ ይመስላል። ከወለጋ ጀምሮ እስከ
ቡራዩ ሥራውን የሚሠራው ከቤተ መንግሥትና ጫካ ከተቀመጡት እና በብሔር
ፖለቲካ ሥር በተሸሸጉት በኩል በዚህ በ6 ዓመት የስንት ኢትዮጵያውያን ደም ጠጣ? ብሎ የሚጠይቅና ለመፍትሄው የሚሠራ የሃይመኖት
አባት ሲጠፋ፥
v ከዛሬ ዓመታት አስቀድሞ “ኢትዮጵያዊነታችሁን ላጣራ” ያለው
መንግሥታችን ባለፉት 6 አመታት እምነታችንና የቋንቋ ዘውጋችንን እያጣር
ከአይሲስ በከፋ መንገድ ሚሊዮቹን ፈጅቶ ሲያበቃ ዛሬ ከሊቢያው በከፋ
ደረጃ በደም ሲያፈስስ የሐዘን መግለጫ ስንኳ የነፈገ ሲኖዶስ፥
v የግብጽ ቤተክርስቲያን ለሞቱባት ፳፩ ሰማዕታት የቅድስና
ማዕረግ ሰጥታ ቤተክርስቲያን በስማቸው ገንብታ፥ መጽሐፍ አሳትማለች።
የእኛ ቤተ ክህነት ከሚያጠፋን መንግሥት ትዕዛዝ እየተቀበለ ቆኖና ሓርያትን ደምስሶ የጎሣ ጳጳስ ይሾማል፥ ባለፉት 6
ዓመታት በእየለቱ የሚሰዉትን ምእመናን እንኳ ትቶ ካህናትን ስንኳ መዝግቦ አላከበራቸውም።
v በተቃራኒው እንደ ሩፋኤል፥ ሲዊሮስ፥ ዜና ማርቆስ፥ በቅርብ ግዜ ከክርስቶሳዊነቱ መሥፍርት ውጭ ንጹሕ ኦሮሞ ተብሎ የተሾመው፥ ሲⶄም ኬክ ቆርሶ ፎቶ
ሲነሳ የነበረውና “አልተመቸኝም ቀይሩኝ” ብሎ ለመሾም ምክንያት ያደረገውን የቋንቋ መደበቂያ በመቃረን ወደ ማያውቀው የቋንቋ ሰፈር
የተቀየረው ሁሉ አጀንዳቸው ክርስቲያን ሰውን መጠበቅ፥ አሕዛብን መማረክና ወደ በረቱ መጨመር አይደለም። አጀንዳቸው ሆዳቸውና ኪሳቸው
ነው።
v የቤተ መንግሥቱ ግብ ኦርቶዶክሳዊነትና ኦርቶዶክስን ማጥፋትና አገሪቷን ለጎሣ ከፋፍሎ ታላቋን ኦሮሚያና ታላቋን ትግራይ
ጎን ለመጎን መመሥረት ነው። ይህ ደግሞ ባህር ተሻግረው፥ ብር አበድረው፥ አማካሪ ልከው፥ ሲጣሉ አስታርቀው የሚመሯቸውና ዘላለም
የዓለምን አገራት (በተለይ ኦርቶዶክሳዊያን አገራትን) እየከፋፈሉና እያጋጩ በባርነት የመግዛት የዳርዊን ሰይጣን የሰፈረባቸው በሽተኞች
የውጭ አካላት ድጋፍ አሏቸው።
ይህን እውነታ አይቶ ዝም ማለት
የሚቻለው ምን አይነት ክርስቲያን ነው? ክርስትናው ቢቀር ምን አይነት ሰብአዊ ሕሊና አለው?
ይህን እውነተኛ ትችት ለመቃወም
የሚችል አንድም ጳጳስ የለም! አውነት ነዋ!
ይህን ትችት ለመቃወም የሚከተሉትን
ትናንሽ የአባትነት ሥራ ሠርቶ ማሳየት ያስፈልጋል፦
፩) ባለፉት 6 ዓመታት በሥርዓቱና
ሥርዓቱ ጫካ ባስቀመጣቸው ጨፍጫፊዎች የተገደሉ ካህናት እና መእመናን ዝርዝር፥ በሀገረ ስበከት፥ በወረዳና በአጥቢያ
፪) ባለፉት 6 ዓመታት የፈረሱና
የተቃጠሉ አቢያተ ክርስቲያናት ዝርዝር፥ በሀገረ ስበከት፥ በወረዳና በአጥቢያ
፫) ባለፉት 6 ዓመታት የእርሻ
መሬታቸውን፥ የንግድ ድርጅታቸውን፥ የባንክ ገንዘባቸውን የቀሙ ኦርቶዶክሳውያን ዝርዝር፥ በሀገረ ስበከት፥ በወረዳና በአጥቢያ
፬) ባለፉት 6 ዓመታት ከቀያቸው፥
ከከተማ ቦታቸው የተፈናቀሉ ካህናትና ምእመናን ዝርዝር፥ በሀገረ ስበከት፥
በወረዳና በአጥቢያ
፭) ባለፉት ፴፮ ዓመታት በፖለቲካ
ጫናና ለሌሎች እምነቶችና ፍልስፍናዎች በሚደረግ መንግሥታዊ ድጋፍ
ከእምነት የወጡ ምእመናን ብዛት ዝርዝር በሀገረ ስበከት፥
በወረዳና በአጥቢያ
፮) ባለፉት ባለፉት ፴፮ ዓመታት
በተለያዩ የጎሣ ፖለቲካ ድርጅቶች፥ በመንግሥት፥ መንግሥት በሚደግፋቸው ሌሎች እምነቶችና አምላክ የለሽ ድርጅቶች ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን
የሚያጠቁ መጽሐፍት፥ ንግግሮች፥ የመደበኛና መደበኛ ባልሆኑ የማሠልጠኛ ሰነዶች በመሰብሰብ አደራጅቶ ማቅረብ
፯) ለሰማዕታት ቤተክርስቲያን
መሰየምና ታቦት መቅረጽ፥ ስንክሣር አንዲጻፍ ማድረግ
፰) በጎሣ የተሾሙትን ዘረኞች
መሻር፥ የተጣሱ ቀኖናትን ቆጥሮ ወደ ቦታው መመለስና ውጉዛን ወደ መሥመር ማስገባት
፱) የምዝበራና የሌብነት ሰንሰለቱን
ለመበጣጠስ አሁን በየደረጃው በሀብት፥ ሰው በመቅጠርና በማዛወር፥ ገንዘብ በማስተዳደር ላይ የሚገኙትን ሁሉንም አገልጋዮች በማንሳት
አዲስ ሰው ከምእመናን ጋር እያቀናጁ መመደብ
፲) መነኮሳትን ከከተማ ወደ
ጋዳማት መመለስ
፲፩) ለሁሉም ጥፋቶች ተጠያቂ
የሆነው ዋናው መንግሥት መሆኑን በማወጅና ክርስቲያኖችን በማስተባበር ለመፍትሔ ሥራ ማስጀመር፥ ለዓለም ተቋማት፥ ልፍርድ ቤቶች ማቅረብ
ከእነዚህ ተግባራዊ ከእረኞች
የሚጠበቅ አንዱን ስንኳ ያለማድረግ፥ በበዓላት ድምቀት፥ በሕንጻ መርቃና ፍሬ ቢስ ብቻ ሳይሆን አፍራሽና አዘናጊ ጉባኤ እያደረጉ
መቀጠል ከሆነ --- “እረኛው ከተኩላው የከፋ ነው” የሚለውን ብያኔ ይዞ መእመናንና ሊቃውንት
ቤተክርስቲያንና፥ ክርስቲያኖችን እስከነ ተፈጠሮአዊ የመኖር ሀብታቶቻቸው የማትረፍ ንቅናቄ መጀመር ይኖርበታል።
እሰቲ ምእመናን በተቻላችሁ መንግድ
ሁሉ አባቶችን ይህን እንዲያደርጉ ጠይቋቸውን እነርሱ ያድርጉትና እኔ
ሐሰተኛ ልሁን!!! በሐሰተኝነቴ አፍሬ ይቅርታ ልጠይቅ፥ ምእመናኑም ከጥፋት ይትረፉ፥
እነዚህን መገናኛዎቼን ሱበሰክራይብ፥ ማጋራት፥ አባል በመሆን፥ እንደየ አመለካከታችሁ የመወያያ ጉዳዮችን በገጾቼ ላይ በመጻፍ ለአገራችንና ለቤተክርስቲያናችን ሰላምና አንደነት አስተዋጽ እናድርግ
Telegram: https://t.me/+io2m-XA1OBE2NmM0
YOUTUBE:- https://www.youtube.com/@Orthodox_Secular_FantahunWakie/videos
ትዊተር፦ @fwakie
FB:- https://www.facebook.com/fwakie
Blog:- https://ethiopiaorthodoxchristian.blogspot.com
እግዚአብሔር ያክብርልኝ፤
ታናሽ ወነድማችሁ ፋንታሁን ዋቄ
አስተያየቶች