የዐመሓራነት የህወሃትና የኦነግ አይነት “ብሔርተኝነት” እይደለም!
ዐመሓራነት ሰብአዊነትና ፍትሕ፥ እኩልነትና እውነት ነው!!
ተጻፈ ከፋንታሁን ዋቄ መስከረም ፫ ቀን ፳፻፲፯
ዓለም ዐቀፍ ዝና የነበረው የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት በወራዳ ድንክ አእምሮዎች፥ አገርና ሕዝብን
ከሆድና ከሕጻን ቅዠታቸው አሳንሰው በገዛ ወገኑ ላይ አዘመቱት። እንደዚህ አድርገው አዋረዱት። ላም እሣት ወደለች አንዳትልሰው እሣት ሆነባት፥ እንዳት ተወዉ ልጅ ሆነባት
እንዲሉ የዐመሓራ ሕዝብ ራሱን ከታወጀበት የ50 ዓመታት የዘር ማጥፋት
ሁለገብ ጥቃት በኋላ በሕወሃትና ኦነግ ሕገ አራዊት መሠረት የተወለደው
ብልጽግና በይፋ በተመሠረተው የኦነግ-ኦሮሙማ የብልጽግና አመራር ቀጥተኛ ፍጅት ተካሄደበት፤ ማፈናቀል፥ እያደኑ መግደል፥ ማደኸየት፥
በበሽታ ማስጠቃት፥ ከትምህርትና ከፖለቲካ ተሳትፎ ማራቅ ወዘተ እየተፈጸመበት ታገሰ፤ በመጨረሻም ለመታገስ የማይመች በጦእ ሠራዊት
ቀጥታ ፍጅት ተከፈተበት። ፍጅቱን የሚፈጽመው በአብይ አህመድ የጠቅላይ
ጦር አዛዥነት የሚመራው ይከበር የነበረው የአገር መከላከያ ጦር ሠራዊት ነው። እናም ለዐመሓራ የቀረበለት አማራጭ ራሱን መከላከል፥ እያለቀሰ በራሱነ ወገን
ላይ መተኮስና እያዘነ መማረክ ነው።
እነርሱ የቆሎ ተማሪ ከጎጆ እየጎተቱ ሲረሽኑ፥ መነኩሴና ሕጻን ሲደፍሩ፥ ሰብል ሶያቃጥሉና
ከተማ ሲያፈርሱ ሰውነቱን ዛሬም አስከብሮ የኖረው በዓለ ሕሊና ዐመሓራ (ባንዳ፥ ዘረኛ፥ ስስታምና ሸቃጭ አማራን አይመለከትም) ግን የማረከውን በጠላትነት ያሰለፉበትን "ጠላት" ወገኑን
እየደባበሰ እና እያጽናና፥ ጫማ ሳያስወልቀው፥ ግፍ ሳይፈጽምበት ወንደሜ "ጥላችን ከሥርዓት ጋር፥ ከክፉ አስተሳሰብና አስተዳደር ጋር
እንጂ ከማንም የሰው ልጅ ጋር አይደለም" እያለ በኃዘን ይንከባከበዋል። ይኼው በዘረኝነትና በጥላቻ ሕወሃትና ኦነግ መርዘው
ያሳደጉት የመንግሥት ሠራዊትና የጠቅላይ ጦር አዛዡን የአብይ አህመድ አሊን ድንቁርናና ጭካኔ የወረሰው ሠራዊት ግን የማረከውን ብቻ
ሳይሆን ቤቷ የተኛችን በሽተኛ ሴትና ተማሪ ወደ ካምፕ ወስዶ እንስሳት ስንኳ የማይፈጽሙትን የቡድን ዝሙት እየፈጸመ ይደፍራል፥ በመጨረሻም
ረሽኖ አስክሬኑን ሜዳ ላይ ያሰጣል።
በአንድ አገር ተወልደው የቅዱስ
መልአክና የርኩስ ሰይጣን ያህል የመለያየታቸው ምሥጢር ደምና አጥንት አይደለም፤ ሁሉም አንድ የአዳም ልጆች ናቸው፤ የሁሉም በሥጋ
የዚህች ታሪካዊ አገር ልጆች ናቸው፤ ዋነው ልዩነቱ ሁሉም ሰው መሆናቸው ላይ አይደለም፥ ቋንቋቸው አይደለም፥ የሠፈሩበት ቦታም አይደለም።
የልዩነቱ ምሥጢር ያለው እና ሰው ሆኖ ተወልዶ ሰው ሆኖ በማደግ እና ሰው ሆኖ ተወልዶ ዘር ሆኖ መሠራቱ ላይ ነው። ሰው ሆነው በሰውነት የቀጠሉት ነጻ ሕዝቦች ናቸው፥ ዘረኞች (ስማቸውን አሳምረው
‘ብሔርተኞች’ ይሉታል) ግን ከሰውነት የወረዱ፥ ሰብአዊ ሕሊናቸውን ለቡድናቸው በባርነት አሳልፈው የሰጡ፥ ሕሊናቸው በሆዳቸው መቃብርነት
የተደፈነ እና ከተፈጥሮ ሕግ የወጡ ናቸው።
እነዚህ የቡድን ዕሳቤ ባሮች ናቸው ላለፉት ፸ ዓመታት የሐሰት ትርክት ሲቀዱና ሲፈበርኩ፥
ሲያሰራጩና ትውልዱን ከሰውነቱ ሲያስወጡ ኖረው፥ ባለፉት ፴፮ ዓመታት
እንደ አራዊት ሰው በማፈናቀል፥ በመግደል፥ በመድፈር፥ በመቀማት፥ በማፈን የቀየሉት። እነዚህ ናቸው ቤተ መንግሥት ገብተው አረዊትነታቸውን
ሕግና ፖሊሲ፥ አሠራርና መዋቅእረ ያደረጉት። አንዚህ ናቸው መለስ ዜናዊን፥ ስበሐት ነጋን፥ አብይ አህምድ አሊን፥ አባ ዱላ ገመዳን፥
ሽመልስ አብዲሳን፥ ሌንጮ ለታን፥ ጃራ አባ ገዳን የመሳሰሉ ማጥፋትና መቀማት፥ መከፋፈልና ማጋጨት እንጂ ዕድሜአቸውን ሙሉ አንድም
አለዎንታዊ አስተዋጽኦ ለመላው አገር ቀርቶ “ነጻ አውጭህ” ነን ላሉትና በመንጋነት አስከትለው ለሚጫወቱበት ማኅበረሰብ ስንኳ ማበርከት
ያልቻሉት።
በቡድን ዕሳቤና በዘረኝነት መንፈስ ራሳቸውን ከሰውነት በታች ያወረዱትን እነዚህ የክፋት
መተርጎሚያ ቡድኖች ታግሶ መኖር የከበደው የዐመሓራ ሕዝብ ንቅናቄ ፋኖ በሰውነቱ መጽናቱን በሚያሳየው መልካም ስነ-ምግባር አስመስክሯል።
ይህንን በዐመሓራና በመሳዮቹ ላይ የሚታይ የሰው ልጅ ልዕልና፥ የተጠበቀ ሰብአዊ ሕሊና አይተው ስንኳ አሁን ስለ ሚፈጸመው
ሁለገብ አገራዊ ጥፋትን ለሞመራው ለአብይ አህመድ አሊና ለሥርዓቱ፥
ለሕወሃትና ለክፋቱ አንታዘዘም የሚል ማኅበረሰብ ለምን “ኦሮሞ ነን”፥ “ትግራዋይ ነን” በሚሉ ወገኖቻችን አለመታየቱ የሚገርም አይደለም።
የማሰብና እንደ ሰው በነጻነት የማሰብ፥ የመናገርና የማድረግ ልዕልናቸውና ክሂሎታቸው፥ መንፈስና እምነት ሁሉ ተጠቃሎ ተውሰዶባቸዋል፤
ሃይማኖታቸው፥ ፖለቲካቸው፥ ትእረክታቸው ባህላቸው ሁሉ ከሰውነት ተፋትቶ ‘የየነጻ አውጭዎቻቸው’ ጠቅላይና ብቸኛ ገንዘብ ሆኗል። ኦሮሞ ሆኖ እንደሰው፥ ትግሬ ሆኖ እንደሰው ማሰብ ሳይሆን እንደ ኦነግና ሕወሃት ማሰብ ሰብእናን ወደ ቡድን አውርዶታል።
ኢትዮጵያ ነጻ የምተወጣው፥ ዐመሓራና ነጻ ሕዝቦችም ሆኑ የነጻ አውጭዎች ባርያ የሆኑት ወገኖቻችን እረፍት የሚያገኙት ከጎሣ ፖለቲካ
ፍጡርነት ወደ እግዚአብሔር ነጻ ሕዝብነት ለመሸጋገር ወስነው ዘረኛ ሥርዓትና ድርጅቶችን ጠራርገው ከአገራችን ሲያስወግዱ ብቻ ነው።
አንደግዲያውን ይህ ከታወቀ ዐመሓራን ‘ጠላት’ ብለው
የሚያጠቁትን ሕሊና ቢሶች በጠመንጃ ብቻ ሳይሆን በሰብአዊ ልዕልናው፥ በሞራል ቅድስናው የማሸነፍ አቅሙን መቼውንም ከመቼውም በላይ
ከፍ አድርጎ መጠበቅ አለበት። ከዚህ ከፍታ ዝቅ የሚያደርግና በጠላትነት ከፈረጁት እኩል ዐመሓራን ሊያዋርዱት የሚችሉ አንዳንድ ምልክቶች
“ልሂቃን” በተባሉ እና በጭፍን ከውጭ ከመገልበጥ ውጭ በገራቸው መሠረታዊ ነባር እሤቶች፥ መንፈሳዊና ባህላዊ ፍልስፍና፥ የታሪክ
አብሪ ትምህርቶች ላይ መቆም የማይችሉ ሰዎች "የዐማራ ብሔርተኝነት ይለምልም"፥ “ኢትዮጵዑኣኒስተ ኃይልና
አማራዊነት” በማለት ከሰውነት ካር የተስማማውን ዐማሓራነት በኦነግነትና ሕወሐትነት ልኬታ "ፋሽት" ሊያደርጉት ይሞክራሉ። ለምን ብሔርተኛ አልሆንከም ማለት ልምን ሕሃትንና ኦነግን መስለህ ፋሽታዊ
ተግባር አትፈጽምም፥ ለምን ሐሰት አትተርክም፥ ለምን ሁሉም የእኔ ነው አትልም፥ ለምን አዲስ የአማራ አገር የሚባል ካርታ ስለህ
ኢትዮጵያን አትረሳትም፥ ለምን ሌላ ማኅበረሰ ሰብእ አታፈናቀልም አትጨፈጭፍም፥ ለምን ሴት አትደፍርም፥ ለምን ካህናትና አረጋውያንን
አታዋርድም፥ ለምን ጎረቤት ጨፍጭፈን ርስት አታሰፋም፥ ለምን ለባእዳን ጋር ተላልከህ ጎረቤት አውራጃዎችን በመውጋት ታሪክ አትቀይርም
እያሉት እንደሆነ ወደው አያስተውሉም።
የሚያውቁት ያንኑ የሰሙትንና ያዩትን ብቻ ነው፥ ለዚያውም የሚቀዱት ከዐመሓራና የኢትዮጵያዊነት
ጠላቶች ነው።
እነዚሁ ምሁራን ናቸው የዛሬ 50 ዓመት ንጉሣችንና ፓትሪያርካችንን ገድለው፥ ነባር ዕውቀቶቻችን፥
የስነ-መንግሥትና ስነ-ሕዝብ አስተምህሮዎቻችንን ደምሰሰውና ተዋግተው ግራ ስነጋባና መሄደጃ ሲጠፋን “ነጻ እናውጣችሁ” ብለውን ከፋፍለው
ያፋጁን፥ ቀጥሎም የፍጅት ሕገ መንግሥት ጽፈው፥ ሰውን ከሰብአዊ ልዕልናው አውርደው የቡድን ባርያ አደርገው ከፋፍለው ያፋጁንን፥
ዛሬም ስንኳ ከጥፋታቸው የማይማሩትን "ምሁራን" ተብዬ የባዕዳን ዕሳቤ ማኅደሮች ሰምተህና ተሳስተህ በብሔርተኝነት
ስም የምትዋጋቸውን ከሰውነት የወረዱ "ዘረኛ" ጠላቶችህን እንዳትመስል ተጠንቀቅ።
ዐማሣራ ሆይ! "የተጠቃኸው 'ኢትዮጵያ' ስላልክ"፥ አሁን ግን “ዐመሓራ
ብቻ ነኝ” በል፤ "አማራነት ደማዊ ነው" እንጂ ሌላ ትርጉም የለዉም፤ "ዐመሓራነት በክልል የተወሰነ ማኅበረሰን ነው”፥ “ዐመሓራነት አማርኛ ቋንቋ መናገር ነው”፥ "በዘር
ያልተሰበሰበ ድል አያገኝም” ወዘተ የሚል እጅግ ጎስቋላ ዕሳቤ የሚያራምዱትን አትስማ። ዐመሓራነት ጤናማ ሕሊና ያለው ሰው ሁሉ ገንዘብ እንጂ አሁን የሚዋጋቸውን ወደ አራዊትነት የሚያወርድህና ለ50 ዓመታት በጠላትነት
ፈርጀው የሚያጠቁህን ቡድኖች አይነት "ብሔርተኛ" የተባለ ስም የተሰጠው ሰይጣናዊ ፋሽስት አትሁን።
ዐመሓራ አሁን ባለህበት ሰውነት ልክ ቀጥል!! “ብሔርተኛ” የተባለውን የጠላቶችን መንፈስ
ከወረስካ ግን የሰብእና ጠላት ሆነህ “ዐመሓራነትን” እንደሌሎቹ ብሔርተኞች ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ቡድን ሆኖ ከመሞትና ከመግደል ራሳችሁን
ጠብቁ!!
እዚህ ውስጥ እስካላችሁ ድረስ ሰብእናው የተጠበቀ ትግሬ፥ ኦሮሞ፥ ጉራጌ፥ ወላይታ፥ ሲዳማ፥
አፋር፥ ሱማሌ ሁሉ “ብሔርተኛ” ያልሆነ ሰው ነውና አማራ ነው።
ብሔርተኝነት ከዐመሓራነት ጋር እንዴት እንደማይስማማ ላመልክት፦
የዐመሓራነት/ሰዋዊነት መለያዎች |
በዐመሓራነትና በኢትዮጵያ ያለው
ብሔርተኝነት መካከል የሚገኝ የጋራ እሤት |
ብሔርተኝነት/ዘረኝነት መለያዎች |
||
1.
ሰብአዊነት |
× |
1. ቡድነኝነት |
||
2.
ፍትሓዊነት |
× |
2. አድሎአዊነት |
||
3.
እውነተኝነት |
× |
3. የሐሰት ትርክት |
||
4.
የሰው ልጅ እኩልነት |
× |
4. የቡድን የበላይነት |
||
5.
የዜጎች እኩል ባለርስትነት |
× |
5. የቡድን ልዩ መብትና ጥቅም |
||
6.
ቋንቋ፥ እምነትና ባህል ከሰብአዊነት በታች መደረግ |
× |
6. የቡድን ማንነት ከሰብአዊነት በላይ የሚገንንበት |
||
7.
አቃፊነት እስከ መዋሐድ |
× |
7. አግላይነት እስከ ዘር ማጽዳት |
||
8.
የአገር ሉዓላዊነትና የሕዝብ ውኸደት |
× |
8. የጎሣ ሉዓላዊነትና የጎሣ ሀገር መፍጠር |
||
9.
አገራዊ የዜጎች መንግሥታዊና ማኅበራዊ መዋቅር |
× |
9. የጎሣ አግላይ መዋቅር፥ አግላይ ኢኮኖሚ፥ አግላይ
መንፈሳዊና ማኅበራዊ አደረጃጀት |
||
10.
የባህል፥ ቋንቋ፥ ውርርስ፥ ቅልቅል ጋብቻ፥ በሄዱበት መልመድ |
× |
10.
የባህል ጽዳት፥ አለመጋባት ወይንም ሙሉ በሙሉ ሌላውን ወደ ራስ በመቀየር መሠረቱን ማጥፋት |
||
11.
ሁላችንም የአንድ ሰው ልጆች እኩል ሰዎች ነን |
× |
11.
እኛ ከሌሎች እንበልጣለን፥ የተለየ ዝርያ ነን |
||
12.
ፍትሐዊ ባለርስትነት |
× |
12.
መቀማት የቻልነው ሁሉ የእኛ ነው |
||
“የዐመሓራ ብሔርተኝነት
ይለምልም” የሚሉና ኢትዮጵያዊነት ለዐመሓራ መጠቃት ምክንያት ነው የሚሉ ወንድም እኅቶቻችን ዐመሓራን ብሔርተኛ በማድረግ አሁን ሊያጠፉት
ለ50 ዓመታት ካጠቁት የሕወሃትና የኦነግ ብሔርተኝነት ጋር እኩል ኢሰብአዊ ውራጅ አስተሳብ ልታደርጉት ነው?
ወይስ የዐመሓራ ብሔርተኝነት
አሁን በአገራችን ከሚገኘው ኢትዮጵያ-ጠል፥ ጸረ-ሰብእ፥ ጸረ-ውህደትና አንድነት፥ የአውነት ጠላት ሐሰተኛ፥ ገዳይና አሳዳሥ ያልሆነ
ሌላ አይነት “አዲስ ብሔርተኝነት” ልትፈጥሩ ነው?
“አዲሱ” የዐመሓራ ብሔርተኝነት
አሁን ከምናውቀው ዐመሓራነት በምን ይለያል?
የጎሣ ልሂቃን “የብሔር
ፖለቲካ” ትግል ውስጥ የገቡት በአእምሮ ሕጻንነት፥ በበታችንት ስሜት፥ በተውሶ የባእዳን ትምህርት አእምሮ መታጠብ ላይ በተመሠረተ
ጭፍን ግልበጣ (mindless copying) ተመርተው መሆኑ ይታወቃል።
የዚህ አይነት ፖለቲካ ሕይወት የሚኖረው ጠላት ሲያገኝ ነው። በዚህ መሠረት የኦነግና የሕወሃት ጠላት ዐመሓራነት፥ ኢትዮጵያዊነትና
ኦርቶዶክሳዊነት ናቸው። ጠላት ያሉትን በሚያስከትሉት መንጋዎቻቸው
አእምሮ ለመቅረጽ የሐሰት ትርክት ማምረትና ጠላት ከጠፋ በኋላ ለየጎሣቸው የሚገኘውን ወተትና ማር የሚያዘንብ መንግሥታዊ ሥርዓትና
የለማ አገር፥ ፍጹም ሰላምና ነጻነት በምናብ ስሎ ማሳየት ነው። ይህ ሁሉ ድካም የአእምሮ ድህነት፥ እውነትኛ፥ ፍትሕና ሰብአዊነትን፥
ሁሉ አቀፍነትና ፍቅርን ያገናዘበ ፖለቲካዊ ርእዮተዓለም የመፍጠር አቅም ማጣት፥ የበታችንት ስነ ልቦና፥ የባእዳን አሽከርነትና በቡድን-ዕሳቤ
እሥረኝነት የመያዝ እዳዎች ናቸው።
ስምንት “የአማራ ብሔርተኝነት ይለምልም” ለሚሉ ለዐመሓራዎች የማቀርበው ጥያቄ፦
1.
የብሔረ-ሰብ ጠላት አበጅተሃል?
ካበጀኽ ኢትዮጵያ ውስጥ ጠላቶችህ የትኞቹ ማኅበረሰቦች ናቸው?
2.
ኢትዮጵያን ጠላትህ አድርገኻታል?
ኢትዮጵያን ካልጠላህ ከኢትዮጵያ ያነሰ በቦታና በቋንቋ ክልል የሚወሰን የብሔር ማንነትና ቦታህ ምንድ ነው?
3.
ግፍን፥ ኢፍትሐዊነትን፥ ህልውናህን፥
ሰብአዊ ክብርህን በመከላከል ራስህንና አገርህን ለማዳን የፖለቲካ ፍልስፍና ድህነት አጥቅቶሃል?
4.
የበታችነት ስነ-ልቦና ሰለባ ያደረገህ
ታሪካዊ ጠባሳና ሌሎችን በመጥላት፥ በመቀማትና ሐሰት በመተረክ የምትታከመው በሽታ አለብህ?
5.
ከኦነግ/ብልጽግና እና ከሕወሃት
የአፓርታይድ ሕገ-ምንግሥት ፥ አስተሳሰብ፥ የብሔርተኝነት ትርጓሜ ውጭ አገርን፥ ማኅበረሰብእን፥ ሰብአዊነትን፥ መብትና ነጻነት መተርጎም
የሚያስችል ታሪካዊ፥ ባህላዊ፥ እምነታዊ መሠረት የለህም?
6.
ዐሓራነት እሤት ነው ወይስ የደምና
የአጥንት ጉዳይ ነው? ደምና አጥንት ከሆነ ከፋሽዝም በምን ይለያል? በፋሽዝም ውስጥ ነጻነት፥ ሰብአዊነት፥ ፍትሕ፥ እኩልነት እንዴት
ይረጋገጣል?
7.
“ኢትዮጵያኒሰት ኃይሎች” የሚለው
በአሉታዊነት የሚነገረው ንግግር ከዐመሓራ፥ ከኢትዮጵያና ከኦርቶዶክሳዊነት ጠላቶች የመነጨ ነው ወይስ ከዐመሓራ ወዳጆች?
8.
የዐመሓራ ብሔርተኝንት (ያለ ጠላት የማይፈጠር ፖለቲካ ሠራሽ ማንነት) ለዐመሓራ ህለውና
አደጋን ለማስወገድ አሁን ማኅበረሰቡን ለማጥፋት ተደራጅተው የሚሠሩ አካላትን በትጥቅ ማሸነፍ ብቻ ከሆነ፥ የህለውናውን ዘለቄታዊነት
ዋስተና ባለው መዋቅራዊና ሥርዓታዊ አውድ ለማስቀጠል ሁሉም የሚሳተፍበትን አገራዊ ሥርዓት፥ ቀጠናዊ ሰላም ታሳቢ ማድረግ ይኖርበታል፥
ይህ ግድ ከሆነ “ብሔርተኛ” ከሆነ እንዴት ከሌሎች ጋር የሚስማማበት
ፖለቲካዊና መንግሥታዊ ሥርዓት ይፈጥራል?
አስተያየቶች