ወላጆች ራሳችሁንና ልጆቻችሁን ለመጠበቅና ሀገራችሁን የመዳን ኃላፊነታችሁን ለመወጣት
በመደበኛ ትምህርት ፍልፍናና ይዘት ላይ ትኩረት በማድረግ መወያየት ይኖርባችኃል፡፡
ይህንን ለመገንዘብ በግንቦት 2009 በፈረንጆች አቆጣጠር የኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግሥት ለቅድመ መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል ልጆቻችሁን ለማስተማር ያዘጋጀውን
የሥርዓተ-ትምህርት ማኅቀፍ በአጭሩ በመዳሰስ እዚህ ላይ ለጥፌላችኃለሁ፡፡ አሁን በመዘጋጀት ላይ የሚገኘውን ፍኖተ ካርታም ከዚህ
አንጻር በመመልከት ምሁራንና የባህልና የእምነት ሊቃውንት ድምጽ ማሰማት፣ ግብአት መስጠት የጠበቅባችኃል፡፡
በሥራ
ላይ የሚገኘውን የትምህርት ሥርዓት ኢትዮጵያዊ እሴቶችን ዋጋ ቢስ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ምልክቱ እንዳይገኝ ተግቶ የሚሠራ የሚያስመስለው
ይዘት ለማሳየት የሥርዓተ-ትምህርት እሴት ተብሎ በኢትዮያ ፌደራላዊ ሩፑብሊክ የትምህርት ሚኒስቴር ከ(KG – Grade 12) በMay 2009 በተዘጋጀው ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ የተመዘገበውን
መመልከት ይበቃል፡-
²Through
their learning experiences students should (ተማሪዎች በትምህርት ሂደት ውስጥ የሚከተለውን መሆን/ማወቅ
አለባቸው):-
ü develop
and refer their own set of beneficial values
(የራሳቸው የሆነ ጠቃሚ መድብለ እሴት ያዳብራሉ)
ü understand
the value of their culture and their heritage (የራሳቸውን ባህል እሴትና ውርስ ይረዳሉ)
ü respect
the values of other people and other cultures (የሌሎች ሕዝቦችን እሴቶችና ባህሎች ማክበር)
ü understand
the value of education as a means of progressing both as an individual and as a
country.² (ትምህርት ለግልና ለሀገራዊ እድግት
(ተራምዶት) ያለውን ጠቀሜታ ይረዳሉ) ይላል፡፡
ከላይ
የተመለከቱት የሥርዓተ ትምህርቱን ግብ የሚገለጥጡ ዐረፍተ-ነገሮች በጥንቃቄ በኢትዮጵያዊ ዓይን በመመልከትና በመሥፈር ጥያቄና ትችን እያስቀመጥንበት ለውይይት እናቅርበው፡-
(1) develop
and refer their own set of beneficial values
(የራሳቸው የሆነ ጠቃሚ መድብለ- እሴት ያዳብራሉ) ለሚለው
የሚከተሉትን ጥያቄዎችና ትችቶች ማንሳት ይቻላል፡-
·
ልጆቻችን በማን እምነት፣ በማን ባህል፣ በማን ታሪክ፣ በማን ፍልስፍና ላይ
የሚመሠረት እሴት እንዲያዳብሩ ተፍልጎ ነው ²የራሳቸው
እሴት² የተባለው? የመልካምና ጠቃሚ እሴት
መሥፍርት ምንጭ ማነው? የሚበየነው በማን ፍልስፍና ነው?
·
ይህን ሥርዓተ
ትምህርት የሚያዘጋጁ ምሁራን ራሳቸውም የተገኙት ኢትዮጵያዊነት ካገለለው ትምህርት ቤት ሲሆን፣ አማካሪዎችና በጀቱን የሚረዱት የዩኔስኮን ፍልስፍና
በመላው ዓለም ለመተግበር የሚሠሩ አካላት በመሆናቸው ይህ ተማሪዎች አንዲያዳብሩት የተፈለገው የግል እሴት ኢትዮጵያዊ ያልሆነ መሆኑን
ያስረዳል፡፡
(2)
understand the value of their culture and their heritage (የራሳቸውን ባህልና ውርስ ዋጋ ይረዳሉ)
ለሚለው ዐረፍተነገር የሚከተሉትን ትችቶች ማንሳት ያስፈልጋል፡-
·
²የራሳቸውን ባህልና ውርስ ዋጋ ይረዳሉ² የሚለው
ዐፍተ ነገር በተግባር ምንም አይናገርም፡፡
ምክኒያቱም የራሱን እሴት ከሴኩላር ውጭ-ገብ ፍልስፍና እንዲያዳብር የተፈረደበትና ከሀገራዊ ማንነቱ በሚማረው ትምህርት ውስጥ እንዳይመለከት በጥንቃቄ የሚሠራበት ሕጻንና ወጣት ባህልና ውርስን የሚረዳው በቱሪስት መስህብነትና በባዶ ድምጽ
ወይንም ቅርጽነት ካልሆነ በስተቀር ከታሪክ፣ ከእምነት፣ ከሀገራዊ ፍልስፍናዊ መሠረት ጋር ሊያስተሳሰርና ሊገገነነዘብ አይችልም፡፡
ጥቅሙም በበዓላት ላይ ራስን ከሌሎች ለይቶ ለማሳየት ብቻ የሚጠቅም፣ ለልማትም ለጥፋትም የማይጠቅም መዝናኛ አድርጎ ይመለከተዋል፡፡
·
የራስ ባህልና ውርስ ዋጋ የሚያገኘው በታወቀ፣ አንድን ማኅበረሰብ ልዩ የሚያደርግና ራስን ለመቻል፣ እንዲሁም በራስ
ማንነት ጸንቶ ከቆሙ በኃላ ሌላው የዓለም ማኅበረሰብ አስተዋጽኦ ለማድረግ
የፍልሰፍና፣ የእሴት፣ የእምነት ትርጉም ኖሮት ለሥነ-ምግባር፣ ለሥራ፣ ለፈጠራና ለመልካምነት መሪ ሲሆን ከታየ ብቻ ነው፡፡ ይህ
በሌለበት ይህ የትምህርት ሚኒስቴር ዓረፍተ ነገር ምን ትርጉም ይሰጣል?
(3)
respect the values of other people and other cultures (የሌሎች ሕዝቦችን እሴቶችና ባህሎች ማክበር)
ለሚለው 㙀ረፍተ ነገር ለሚከተሉትን መከራከሪዎች ምላሽ የሚሰጥ አንዳች ሀጋራዊ አረዳድ የለም፡-
·
²የሌሎችን ሕዝቦችን እሴቶችና ባህሎች
ማክበር² ሲባል የሀገሩን እሴት የማያውቅ
ትውልድ የሌሎቸን እንዴት ይረዳል? በምን መሥፍርት ተጠቅሞ መከበር የሚገባውንና የማይገባውንመረዳት ይችላሉ?
·
የሀገሩንና የወላጆቹን እሴት ጥሎ በዘመናዊ ትምህርት ቤት በሚማረው ትምህረት ብቻ እሴት እንዲያዳብር
የሚሠራበት ትውልድ ²የሌሎችን
እሴቶችና ባህሎች ማክበር² ሰለምን ይጠበቅበታል?
·
የራሱን እሴት እንዲጥልና ሴኩላር የሆነ እሴት እንዲያዳብር የተፈረደበት
ተውልድ በምን መንገድ የሚከበርና የማይከበር እሴትንና ባህልን ሊለይ እንደሚችል ምንም ፍልስፍናዊም ሆነ እምነታዊ መነሻ እንደሚያገኝ አይታወቅም፡፡
(4)
Understand the value of education as a means of progressing both as an
individual and as a country.²(ትምህርት ለግልና ለሀገራዊ እድገት
(ተራምዶት) ያለውን ጠቀሜታ ይረዳሉ) ለሚለው ዐረፍተ ነገር ኢትዮጵየዊየን ሊቃውንት የሚስማሙበት ትርጉም የለም፤ ስለዚህ የኢትዮጵያን የትምህርት አቅጣጫ ለመበየን የሚከተሉትን መከራከሪያዎች ምላሽ
በመስጠት መጀመር ይኖርበታል፡-
·
²ትምህርት ለግልና ለሀገራዊ እድገት
(ተራምዶት) ያለውን ጠቀሜታ ይረዳሉ² የሚለው ዐረፍተ-ነገር ²የትኛው
ትምህርት?² የሚለውን ጥያቄ በግልጽ ባይናገርም፣
በሰውርና በመጀመሪያ ዐረፍተ-ነገር እንደሚያሳየው ሀገራዊ እውቀት፣ እምነት፣ ታሪክ፣ ትውፊት፣ እሴትና ፍልስፍናዎችን በማስወገድ ውጭ-ገብና ሴኩላር ብቻ የሆነውን ማለቱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
·
በሌላ በኩል
የግልና ሀገራዊ እድገት ማለት ምን ማለት እንደሆነ በትክክል አልተገለጸም፡፡ በመጀመሪያው የግብ ዝርዝር ውስጥ ²የራሳቸው
የሆነ ጠቃሚ መድብለ እሴት ያዳብራሉ² የሚለው ትውልድ ²እድገት² የሚለውን
ትርጉም የሚፈጥረው ራሱ ከሚያዳብረው እሴት፣ እርሱም ዩኔስኮ የሚተረጉመው እድገት መሆኑን ያመለክታል፡፡ በዚህ መሠረት የትውልድ
የእድገት ትርጉም፣ ርእይ፣ ህልም ሙሉ በሙሉ የተውሶ ስለሚሆን ኢትዮጵያዊ ማንነት የሌለው ይሆናል፡፡
አሁን
በሥራ ላይ የሚገኘው ሥርዓተ ትምህርት ይዘት ሲጠቃለል፤ ኢትዮጵያዊነት የሌለው፤ ሁላችን ራሳችንን ትተን አዲስ እና አቅጣጫው ወዳልታወቀ እድገት ፍለጋ በቅዠት እየተመራን እንድንኖር የሚያደርገን
ነው፡፡ አድርጎናልም፡፡
በዚህ
ትምህርት ውስጥ ያለፈው ትውልድ ምንም እንኳ ለዕለት ጉረሱ ገቢ፣ ለሀገሩ ልማት የሚቻለውን ለማድረግ እየሞከረ ቢገኘም ውጤቱና የወደፊት
ተስፋውም አሉታዊ ሆኖ ይገኛል፡፡ አሉታዊ ጠባይ
በሚከተሉት ነጥቦች ይገለጣል፡-
1. በሁሉም የሕይወት ዘርፍ (ማኅበራዊ መስተጋብር፣ ትዳር፣ የምግብ ሉዓላዊነት (በምግብ ዋስትና
ስም ጥገኝነት ማስፋፋት ቀርቶ)፣ በኢዱስተሪ ምርት፣ በግብርና ዝማኔ፣ በጤና ጥበቃ፣ ወዘተ ግራ መጋባት ላይ መገኘት፤ ሁሉም ለኖር አስፈላጊ የሆኑ ምርቶች በባዕዳን ግብአት ብቻ እንዲለሙ
የተደረገበት ሰተራትጂና ፖሊሲን በመተግበራችን፡፡
2. የተውሶ ፍልስፍና ላይ የተመሠረተና ሀገራዊ መሠረት የሌለው የፍትህ፣ የፖለቲካና የአስተዳደር ውጥንቅጥ
3. ሁለገብ ሀገራዊ የፍልስፍፈና ድህነት ያስከተለና ሀገራዊውን እውቀት ያገለለ ዘመናዊ ትምህርት ያስከተለው የወላጆችና የልጆች አለመናበብ
4. ኢአማኒነት (ኤቴይዘም)፣ በመንፈስና በአካል ከሀገር መሰደድ
5. እድሜያቸው 18 ዓመት
ሳይሞላ፣ በጋብቻ ሳይጣመሩ በዝሙት የሚጠመዱ ወጣቶች ቁጥር መጨምር (ከ50 በመቶ በላይ መድረስ)
6. ከፍተኛ የውርጃና ከጋብቻ ውጭ መጽነስ
7. ከፍተኛ
ሥነ ምግባበር ብልሽት
(ሱሰኝነት፣ ሌብነት፣ ስንፍና፣ ግብረ ሶዶማዊነት፣ ጥላቻ፣ ዘረኝነት፣ ግለኝነትና ሽሚያ፣ የጌምና የጨዋታ ሱስ)
8. የፍቺ መጨመር፣ ወንጀለኝነት፣
ሕግ አለማክበር
9. መገናኛ ብዙሀን መልዕክት፣ የኪነ ጥበብ ውጤቶች፣ የንግድ ማስታወቂያዎች ፈጂነትን
(ኮንሲዩመርዝም)፣ ዝሙት፣ ጊዜአዊ ስሜት ማርኪያዎችን የሚያራግቡና ዘለቄታዊ ጥቅምን የሚያዘናጉ
10.
ሀገራዊ እሴት፣ ርእይና ፍልስፍና
የሌለውና ስደትን የሚናፍቅ ተውልድ መፍጠር ሀገራዊ የትምህርት አመራር በዩኔስኮና እርዳታ ሰጭ ሀገራት ፍላጎት ሥር መውደቅ
አስተያየቶች